ህዳር 13
ቀን 2000 ዓ.ም
ፕሬስ ሪሊዝ
ማስታወቂያ
ሚኒስቴር
በሶማሌ ክልል
የእርዳታ አቅርቦቱ
ተጠናክሮ እየተካሄደ
ነው
የኢትዮጵያ መንግሥት
በሶማሌ ክልል የምግብ
እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው
ተረጂዎች የተለየ
ትኩረት በመስጠት
የዕርዳታ አቅርቦቱን
በተጠናከረ ሁኔታ
እያካሄደ ነው፡፡
በክልሉ በ5 ዞኖች
ውስጥ 640 ሺህ ለሚሆኑ
የሰብአዊ ዕርዳታ
ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል
ተብሎ ከመንግሥታቱ
ድርጅት/ተመድ/ በቀረበው
ሪፖርት መሰረት
በመንግሥት በኩል
እርዳታው በአፋጣኝና
በተቀላጠፈ መልኩ
የሚደርስበት ሁኔታ
በመመቻቸቱ በአሁኑ
ወቅት ሥርጭቱ እየተካሄደ ነው፡፡
ከአደጋ
መከላከልና ዝግጁነት
ኤጀንሲ በተገኘ
መረጃ
መሰረት ካለፉት 3
ሳምንታት ጀምሮ እስከ
ህዳር 10 ቀን 2000 ዓ.ም ወደ
91ሺህ 532 ኩንታል የምግብ
ዕርዳታ
ፊቅ፣ጎዴ፣ቆራሄ፣ደገሃቡርና
ዋርዴር ዞኖች ለሚገኙ
ተጎጂዎች ተልኳል፡፡
ከዚህም ውስጥ 65 ሺህ 480
ኩንታል እህል፣ 7ሺህ 185
ኩንታል ጥራጥሬ፣ 7407
ኩንታል አልሚ ምግብ እንዲሁም
2ሺህ 65 ኩንታል የምግብ
ዘይት ነው፡፡
ቀደም ባሉት
ጊዚያት ተመሳሳይ
መጠን ያለውን ዕርዳታ
ወደ ክልሉ ለማጓጓዝ
ከ2 እስከ 3 ወራት ይፈጅ
የነበረ ሲሆን በአሁኑ
ወቅት በአካባቢው
አስተማማኝ ሰላም
ከመኖሩ ጋር የተቀናጀ
አሰራር መዘርጋቱ የምግብና
ተጓዳኝ ዕርዳታዎችን
በአፋጣኝ ለማቅረብ
ያስቻለ ብቻ ሳይሆን
አፈጻጸሙንም
በሚገባ
ለመከታተል አመቺ
ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
የሰብዓዊ ዕርዳታ
አቅርቦቱን
የተቀላጠፈ
ለማድረግም ተመድ
ባቀረበው ጥያቄ
መሰረት በቀብሪደሀርና
ደገሀቡር
ከመንግሥትና ከተመድ
አካላት የተውጣጡ
ድጋፍ ሰጪ ማዕከላት
ተከፍተው የዕርዳታ
አቅርቦቱ ለታለመለት
ዓላማ መዋሉን የቅርብ
ክትትል እየተደረገ
ነው፡፡ በተጨማሪም በዞኖች
ያለው ሁኔታ ተጠንቶ 18
መንግሥታዊ ያልሆኑ
ድርጅቶች በሰብአዊ ዕርዳታ
እንቅስቃሴ
እንዲሳተፉ
ተፈቅዶላቸዋል፡፡
በክልሉ አሁን
ያለውን እንቅስቃሴ
የበለጠ ለማጠናከርና
የተቀላጠፈ
ለማድረግም የዕርዳታ ማሰራጫ
ጣቢያዎችን ወደ 186
ለማሳደግ ኤጀንሲውና
የዓለም ምግብ
ፕሮግራም በአፈጻጸሙ
ዙሪያ ወደተግባር
ስለሚሸጋገርበት
ሁኔታ ጥናት እየተደረገ
ነው፡፡
በአካባቢው
ያለውም የሰዎችና የእንሰሳት
ጤና ሁኔታ የቅርብ
ክትትል የተደረገበት
ሲሆን በሰዎች ጤና
ረገድ የፌዴራል ጤና
ጥበቃ ሚኒስቴር ከክልሉ
ጤና ቢሮ ጋር የቅድመ
ክትትል እያደረገ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅትም
የመድሀኒት፣
የሕክምና
መሣሪያዎችና
ቁሳቁሶች እንዲሁም
የጤና ባለሙያዎች
ችግር አለመኖሩ
ተረጋግጧል፡፡
የግብርናና ገጠር
ልማት ሚኒስቴርም
የእንሰሳት ጤና
በተመለከተ ከክልሉ
ቢሮዎች ጋር እየሰራ
በመሆኑ በአቅርቦቱ
ረገድ እስካሁን የታየ
ችግር የለም፡፡
በተጨማሪም የጤና ጥበቃ
ሚኒስቴር 3 ክሊኒካል
ነርሶችን በፊቅ ዞን
መድቦ ክትትል
እያደረገ ነው፡፡
በክልሉ የዕርዳታ
ቁሳቁሶችን በተቀናጀ
ሁኔታ ለማጓጓዝም
በመንገድ
ትራንስፖርት
ባለሥልጣን
ሰብሳቢነት የሚመራ
የትራንስፖርት
ስምሪት
የሚያስተባብር
ከአደጋ መከላከልና
ዝግጁነት ኤጀንሲና ከአጓጓዥ
ድርጅቶች የተወከሉ
አባላትን ያካተተ
ብሔራዊ
የትራንስፓርት
አስተባባሪ ኮሚቴ
ተሰይሞ ሥራውን
በመጀመሩ ባለፉት 3
ሳምንታት በ301 ተሽከርካሪዎች
አማካይነት የዕርዳታ
ቁሳቁሶችን የማጓጓዙ
ተግባር ተከናውኗል፡፡
ለአካባቢው
ከተመደበው የስብአዊ
ዕርዳታ ውስጥ
እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ
የተጓጓዘ ሲሆን ይህም
ቅድሚያ ለሚሰጣቸው
ወረዳዎች ትኩረት
በመስጠት በአፋጣኝ
እንዲደርስ
ተደርጓል፡፡ በተለይም
የዝናብ ወቅት ደርሶ
መንገዶች ሊቋረጡ
የሚችሉባቸውን
አካባቢዎች ታሳቢ
በማድረግ
የማጓጓዙ ሥራ
ቅድሚያ ትኩረት
ተሰጥቶት
እንዲከናወን ተደርጓል፡፡
# #
# #