የግንቦት 20 የድል በዓል ምክንያት በማድረግ በኤርትራ ኩናማ  ዲሞክራስያዊ አርነት ንቅናቄ የወጣ የድጋፍ መግለጫ

 

ብሄሔሮች፡ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለናጻነታቸው ታግሎ ድል ሲቀዳጁ፡ የድሉ ውጤት ተጠቃሚዎች የታገሉት ብቻ ሳይሆን ላልታገሉና ለወዳጅ ጎረቤትም የሚዳረስ ሆኖ ደስም ያሰኛል፡፡ ምክንያቱም የአንድ ጎረቤትና ወዳጅ አገር የውስጥ ችግር ለሌላው ሸከም ስለሚሆን፡፡ በዚ ረገድ ስታይ ዛሬ ለ16 ተኛው የድል በዓል በማክበር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብና ባለፈው ግንቦት 24 (በፈረንጆች ኣቆጣጠር) ካከበረው የኤርትራ ህዝብ የትግል አጋርነታቸው በተግባር ያስመሰከሩ ታላቅ ህዝቦች ናቸው፡፡  እነዚህ ሁለት ታላቅ ህዝቦች በመሪ ድርጅታቸው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራስያዊ ግምባር (ኢህኣዴግ) እና ህዝባዊ ግንባር ሐርነት ኤርትራ (ህግሓኤ) መሪነት ለድል በቅተዋል፡፡ አለመታደል ሆኖ የኤርትራ ህዝቦች ላለፉት 16 የናጻነት አመታት ከባርነት ወደ ባርነት ሲማቀቁና የልማት አቅጣጫ ስጠፋባቸው የታደለው  የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃና ጎደና በመገኘታቸው እንኳን ለዚህ አበቃችሁ ብባል የሚበዛባቸው አይደለም፡፡ በኢኮኖሚ መስክ እየታየ ያለው መሻሻልና እመርታ እንኳንስ ለወዳጅ ለጠላትም የሚስብ ሆኖ በመገኘቱም ሊኮሩበት የሚገባ ጸጋ ነው፡፡

 

የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝቦች በማናቸው ረገድ ልዩነት የማይታይባቸው ከማናቸውም የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ብቋንቋ፣ በባህል በተዋልዶና አስተሳሰብ በእጅጉ የተቀራረቡ ናቸው፡፡ በመቀራረባችና የአንድነታችን ተጠቃሚዎች እኛንና እኛ ብቻ ነን፡፡ በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋትና ጸጥታ የበኩላችን የጋራ ድርሻ እንዳለን ሳንገነዘብ ቀርተን አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ወንድም የሆነውን የሶማሊ ህዝብ ጉዳይ እንደ ግል ጉዳይ ተቐብሎ ክቡር መስዋእት በመክፈል ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን መብቃቱ የተላቅነት ምልክት ነው፡፡ ላለፉት 16 አመታት በመንግስት አልባነት ስትጠቀስ የኖረችውን ለሶማሊ ህዝቢ የተስፋ ጭላንጭል እንድታይ መብቃቱ ከአንድ ሃላፍነት ካለው ህዝብና መንግስት የሚጠበቅ ጸጋ ነው፡፡

 

የተከበራችው የግንቦት 20 በዓል ተሳታፊ የኢትዮጵያ ህዝቦች በሙሉ

 

ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ጠንቁ በፕረዝደንት ኢሰያስ አፍወርቂ የተመራውና በመመራት ላይ ያለው ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን በሶማሊያ የተገኘው የሰላም ጭላንጭል ጨርሶ እንዲደበዝዝ ካለው ፍላጎት ተነስቶ ከኤርትራ ህዝብ ፍቃድና ፍላጎት ውጪ በመሄድ ከአሸባሪ ኃይሎች ጋር በመተባበር የአከባቢያችን ሰላም በማወክ ላይ ይገኛል፡፡ ከኤርትራዊ መንግስት አመራር ፍላጎትና እውቅና ውጪ ወንድም የሆነው የሶማሊያ ህዝብ የተወሰነ እፎይታ አግኝተዋል በማግኘትም ላይ ነው፡፡ የሶማሊያ ህዝብና አገር ላለፉት 16 ዓመታት በመንግስት-አልቦነት ተጠቅቶ እርስበርስ ሲጋደል፣ ሲታመስና ስሰቓይ ከነበረውና  በአሁኑ ጊዜ የተከፈለው መስዋእትነትና ያገኘው ሰላም መረጋጋት ሲነጻጸር በእጅጉ ከሚጠቀው በላይ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ይሁንና በሶማሊያና በኢትዮጵያ ሰላም መገኘት  ብቻ ለአከባቢያችን ዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ በአፍሪካ ቀንድ አንድ የጋራ ጠላት አለ፡፡ ይህንን የጋራ ጠላትና  ሽግር በጋራ  የማስወገድ ጉዳይ ለኛ ለኤርትራዊያን ብቻ ሊተው አይገባም፡፡ የኤርትራ ኩናማ ዲሞክራስያዊ አርነት ንቅናቄ ለዚህ አመከላ የማስወገድ መድረክ እና አጀንዳ ላይ የኤርትራ ሉኡላዊነትና ነጻነት ከሚቀበሉና ከሚያከብሩ ህዝብና መንግስት ጋር የመተባበርና አብሮ የመታገል ጉዳይ እንደ አንድ አገራዊ ሃላፍነት ይቀበለዋል፡፡ የኢሰያስ መንግስትና በሉኡላዊነት ስርቻ ውስጥ የተወሸቁ ሃይሎች የፈለጉትን ያህል ብጮሁና ብመጻዳቁ በጋራ ክንዳችን የመደቆሳቸው ጉዳይ የማይታበል ሓቅና የተጨቆኑ ህዝቦች የትግል ምስክር ስለ ሆነ፡ ከሶማሊያ መረጋጋት በኃላ ወደ ኤርትራ ወዳለው እብርተኛው መንግስት ፍታችን ማዞር እንዳለብን ይታየናል፡፡ ይህ ዓቢ ዓላማ ሲሳካ ብቻ ነው በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ የሁለቱ አገሮች ህዝቦች ስለ ልማትና ዲሞክራሲ ማሰብ የሚችሉ፡፡

 

 

ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ሰላምና ልማት ጠንቅ የሆነውን መንግስት ስገረሰስ ብቻ ነው በመሪ ድርጅታችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራስያዊ ግምባር (ኢህአዴግ) የተገኙ ድሎች ሲሰፉና ሲጎለበቱ ነው ዜጎቻችሁ እኩል ተጠቃሚዎች የሚሆኑት፡፡ ይህ ስርዓት ስወገድ ብቻ ነው የሁለቱ አገር ህዝቦች ለጋራ ዓላማና ልማት የሚነሱ፡፡ ይህንን ቁዱስ ተግባር ዳር ለማድረስ በሚያገናኙን መድረኮች ኢጅ ለኢጅ ተያይዘን እንዲንነሳ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡ 17ኛው የድል በአሎቻችን የአፍሪካ ቀንድ አመኬላውን በማስወገድ በጋራ የሚናከብርበት እንዲሆን ከኛ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማበርከት ዝግጁነታችን እንገልጻለን፡፡ ደግመን እንኳን ለዚ አበቃችሁ እንላለን፡፡

 

 

የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝቦች ትስስር በጋራ ትግላችን ያብባል !!

የኤኩዲኣን የትግል መርሆች ለዘልኣለም ያብባሉ !!

 

የኤርትራ ኩናማ ዲሞክራስያዊ አርነት ንቅናቄ

ግንቦት 27/2007