Back to Front Page


Share This Article!
Share
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አስተሳሰብ ከሀገራችን ዘላቂ የእድገት ግብ (Sustainable Development Goal) አንፃር

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አስተሳሰብ ከሀገራችን ዘላቂ የእድገት ግብ (Sustainable Development Goal) አንፃር

ከባሕረ-ነጋሽ 10-08-18

በቅርብ ግዜ የተመሰረተ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የተባለ ፓርቲ የሚያራምዳቸው አንዳንድ የፖሊቲካ አስተሳሰቦቹ እጅግ አሳሰቢ እንዲሁም ከሀገራችን ዘላቂ የእድገት ግብ (Sustainable Development Goal) የሚቃረኑ ናቸው፡፡፡ ስለፓርቲው አስተሳሰቦች ከአሁኑ ቀደም ብዙ ስለተፃፈ ስለእያንዳንዱ አስተሳሰቦቹ በዚችው አጭር ፅሁፌ መዳሰስ የአንባቢ ግዜ ላለማባከን ከላይ በአርእስቱ ከተጠቀሰው ብቻ የሚስማማ ይዘት ለማተኮር እፈልጋለሁኝ፡፡ በተለይ የድርጅቱ ሊቀ-መንበር ዶር. ደሳለኝ ጫኔ ከኤል ቲቪ ጋዜጤኟ ቤተልሄም ታፈሰ ጋር በነበራችው ቃለ-መጠይቅ የድርጅቱን አመለካከት መሰረት በማድረግ የሰጡት መልስ በበርካታ መመዘኛዎች ድርጅቱ ከዘላቂ የእድገት ግብ መርሆች የሚጣጣም አይደለም፡፡

የአማራ ብሄር ቁጥሩ ለመቀነስ ባለፉት 27 ዓመታት በብሄሩ(ክልሉ) ሴቶች በከፍተኛ ደረጃ የወሊድ መቆጣጣርያ እንዲጠቀሙ በማድረግ ቁጥሩ እንዲቀንስ ብሎም ሴቶቻችን እንዲመክኑ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ለማምከን ተሞክሯል የሚል ውንጀላ ለእኔ ተራ አሉባልታ ከመሆን አልፎ የሚሰጠኝ ስሜት አይኖርም፡፡ የቤተ-ሰብ ምጣኔ ወሊድ መቆጣጣርያ በተመለከተ ግን እንደተፈለገው ስፋት ባይኖሮውም በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ተግባራዊ ይሆን እንደነበር አውቃለሁኝ፡፡

የህዝብ ብዛት መቆጣጣር ለዘላቂ የእድገት ግብ ወሳኝ መሳርያ በመሆኑ የሀብት እጥረት ያላቸው አብዛኛዎቹ የአለማችን ሀራት እንደ ፖሊሲ በማስቀመጥ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ በማንኛውም መመዘኛ የህዝብ ብዛት ከዘላቂ የእድገት ግብ አንፃር ማጣጣም ብልህነት ነው፡፡ በሀገራችንም እንደተፈለገው ባይሄድም የህዝብ ብዛት ለመቆጣጣር የተለያዩ እርምጃዎች ተወስዷል፡፡ ሁሉም ክልሎችም የህዝብ ብዛት ምጣኔ ተግባራዊ ለማድረግ ሞክሯል፡፡ በክልሎች መሀከል የአፈፃፀም ክፍተቶችና ደካማነት ልዩነት ቢኖርም መንግስት ብቻ ሳይሆን የዘርፉ ምሁራኖችም በሰጡት ምክረ-ሀሳብ ሁሉም ክልሎች የህዝብ ቁጥራቸውን ከዘላቂ የእድገት ግብ ለማጣጣም የተለያዩ ተግባራት አከናውኗል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም የሁሉም ክልሎች ህዝብ ቁጥር ያለ ምንም ልዩነት በመጨመር ላይ ነው፡፡ በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እክል በመፍጠር ለዘላቂ የእድገት ግብም እንቅፋት የሚሆንበት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

Videos From Around The World

ለምሳሌ የሀገራችን ማእካላዊ ስታቴስቲክስ ኤጀንሲ እ.ኤ.አ በነሓሴ 2013 Population Projection of Ethiopia for All Regions፡ At Wereda Level from 2014-2017 በሚል ባወጣው ሪፖርት ባስቀመጠው የህዝብ ቁጥር ትንበያ ከ2006 ዓ.ም እስከ 2009 ዓ.ም በሀገር፣ በክልል፣ ዞንና ወረደ ደረጃ የሚኖር ህዝብ ብዛት ቁጥር አስቀምጧል፡፡ በክልልና ሀገር ደረጃ እንደሚከተለው ይተነብያል፡-

ታ.ቁ

ክልል

2006 ዓ.ም

2006 ዓ.ም

2008 ዓ.ም

2009 ዓ.ም

1

ትግራይ

4,960,003

5,055,999

5,151,998

5,247,005

2

ዓፋር

1,678,000

1,723,007

1,769,002

1,812,002

3

አማራ

20,018,988

20,399,004

20,769,985

21,134,988

4

ኦሮምያ

32,815,995

33,691,991

34,575,008

35,467,001

5

ሶማሊ

5,307,002

5,452,994

5,598,002

5,748,998

6

ቤንሸንጉል ጉሙዝ

975,998

1,005,001

1,033,999

1,066,001

7

ደ/ብ/ብ/ህ/ክልል

17,837,005

18,276,012

18,719,008

19,170,007

8

ጋምቤላ

396,000

409,002

422,002

435,999

9

ሀረር

226,000

232,000

240,000

246,000

10

አዲስ አባባ

3,194,999

3,273,001

3,352,000

3,433,999

11

ድሬ ዳዋ

427,000

440,000

453,000

466,000

12

በሀገር አቀፍ ደረጃ

87,952,991

90,076,012

92,206,005

94,351,001

 

በትንበያው መሰረት አማራ ክልል ከሌሎች ክልሎች እጅጉን ባነሰ እያደገ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ የህዝብ ቁጥሩ በተመሳሳይ ሬሾ (ፐርሰንት) በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ግዜ በሁሉም ክልሎች እየታየ ባለው የህዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት የሀገራችን ህዝብ በ1983 ዓ.ም ከነበረበት በእጥፍ ጨምሮ በኡሁኑ ግዜ ከ100 ሚልዮን በላይ ደርሷል፡፡ እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ጭማሬ የሚባል በመሆኑ ጭማሬው አስጊ ነው፡፡

በአሁኑ ግዜ አብዛኛዎቹ የአለማችን ሀገራት የህዝባቸውን ቁጥር በመቆጣጣር ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማስመዘገብ በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ ናቸው፡፡፡፡ ለምሳሌ እንደ ቻይና የመሰሉ ሀገራት የህዝብ ቁጥራቸውን ለመቆጣጣር የone child policy በህግ ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ ሌሎች ሀገራትም የህዝባቸውን ብዛት ለመቆጣጣር የተለያዩ ፖሊሲዎች በመቅረጽ ተግባራዊ አድርገዋል፡፡

ወደ ሀገራችን ስንመጣም መንግስት ዘላቂ የእድገት ግብ ለማረጋገጥ የተመጠነ የህዝብ በዛት በሀገሪቱ እንዲኖር የቤተ-ሰብ ምጣኔ ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ ተገዷል፡፡ ምሁራኖችም፣ ሰብአዊ መብት ተሟጓቾች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም ሀገራችን የህዝቧን ብዛት እንድትቆጣጣር በማሳሳብ ላይ ናቸው፡፡ በሚፈለገው ተግባራዊ ባለመሆኑም በአሁኑ ግዜ በሀገራችን የህዝብ ብዛት ዘላቂ የእድገት ግብ ለማረጋገጥ እንቅፋት የሚሆንበት ደረጃ ላይ ነው፡፡ ክልሎች የቤተሰብ ምጣኔ በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የህዝባቸውን ቁጥር መቆጣጣር ባለመቻላቸው በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ወጣቶች የሚታረስ መሬት ለማግኘት ይቅርና ጎጆ ለመቀለስ እንኳን ክንድ የምታክል መሬት ማግኘት አልቻሉም፡፡ በተጨባጭም በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የህዝብ ብዛት በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ጫና በመፍጠር ዘላቂ የእድገት ግብ ለማሳካት ተግዳሮት በመሆን ላይ ነው፡፡

በአማራ ክልልም በተግባር የህዝብ ብዛት ባስከተለው ጫና ምክንያት ወጣቶች በገጠር መሬት እጥረት ምክንያት ኑሯቸውን መግፋት አቅቷቸው ከተሞች እያጨናነቁ ይገኛሉ፡፡ የክልሉ ቴሌቪዥን ጣብያ (አማራ ቲቪ) በክልሉ ወጣቶች የሚታረስ፣ ጎጆ መቀለሻና እና ለስራ ፈጠራ የመሬት እጥረት ችግር እንደሚያጋጥማቸው ሲያስተጋባ በተደጋጋሚ እሰማለሁኝ፡፡ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ያለው ሀቅ ከላይ የተጠቀሰ ሆኖ ሳለ የአማራ ህዝብ ቁጥር በወሊድ መቆጣጣርያ ምክንያት እንዲቀንስ ተደርጓል እንዲሁም የአማራ ሴቶች የአማራ ብሄር እንዳይባዛ እንዲመክኑ ተደርጓል የሚለው የሊቀ-መንበሩ ንግግር መሰረተ-ቢስ ነው፡፡ የማእከላዊ ስታቴስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ ማመን ካልቻሉ የPHD አካዳሚክ ማአርግ ስልላቸው በክልላቸው ያለው ሁኔታ እራሳቸው መሬት ላይ ወርደው በቀላሉ በጥናት ይደርሱታል ብዬ አስባለሁኝ፡፡

ዘላቂ የእድገት ግብ የሚጪው ትውልድ ጥቅም ጭምር ያገናዘበ በመሆኑ እንዲህ አይነት አሉባልታዎች በህይወት ባለው ትውል ብቻ ሳይሆን በመጪው ትውልድም ሀላፊነት የጎደለው ቀልድ በመሆኑ በጥንቃቄ ማጤን ያስፈልጋል፡፡ የሀገራችን የቤተ-ሰብ ምጣኔ ጉዳይ ከፖሊቲካ መነፅር ወጥተን ማየት ያስፈልጋል፡፡ የቤተ-ሰብ ምጣኔ ወሊድ መቆጣጠርያ የህዝባችን ቁጥር እንዲቀንስ፣ ሴቶችን እንዲመክኑ አድርጓል፣ ገለ መሌ የሚል መሰረተ-ቢስ ንግግር እጅግ ኋላ-ቀርነትና ነባራዊው ሁኔታ ያላገናዘበ ነው፡፡ በትውልድ መቀለድ ነው፡፡

 

Back to Front Page