Back to Front Page


Share This Article!
Share
ራሴን:አልገድልም

 

ራሴን:አልገድልም...

ለምን:ብዬ?
ለማን:ብዬ?
አደራ:አለብኝ:
ህዝብ:የሰጠኝ:
ያልከዳሁት:ያልዋሸሁት:
ሃቁን:ልነግር:የቀጠርኩት::

Videos From Around The World

እናንተ:ግን:የፈራችሁ:
እውነት:መስማት:ያሰጋችሁ:
እንደ:ፕላናችሁ:
በመጀመር:ፕሮጀክቱን:አጥላልታችሁ:
ሲቀጥልም:እኔን:አጠፋችሁ::

ከዚያም:ማሳመኛ:
ላይ:ታች:ምክንያት:ፍለጋ:
ግራና:ቀኝ:አጣብቃችሁ:
ሰፋፍታችሁ:ደርታችሁ:
አይናችሁን:በጨው:አጥባችሁ:
ደግሞ: ይኸው:ብቅ:አላችሁ::

ውጥናችሁ:እንዲሳካ:
ትዕዛዝንም:ሰጣችሁ:
ህዝብ:ወዶና:ፈቅዶ:
የሚያዋጠውን:መዋጮ:
ባልጠየቀበት:እንዲያቋርጥ:
የግድቡን:ሰራተኛ:
እንዲወጣ:በአመት:ፈቃድ:
እንዲህ:ነው:እንጂ:ደግነት:
በተቻለ:አቅም:
ህዳሴውን:ማቆም:
ከግብፅ:ጋር:ድርድሩስ:
ከእንግዲህ:ምን:ሊፈይድ:
ለነገሩ:እንደሆነ:አያስፈልግ::

ይባስ:ብላችሁ:
በድጋሚ:ልትገድሉኝ:
በራስ:ማጥፋት:ደግሞ:ወንጅሉኝ:
አቤት:ክፋት:የአደባባይ:ውሸት:
እኔ:አልጠብቅ:ከናንተ:እውነት::
ፍትህ:ካለ:በወዲያኛው:
የእጃችሁን:እሱ:ይክፈለው:
አገር:ብቻ:ትሁን:ደህና:
ፅኑ:ዜጎቿን:ይዛ:
ሰላም:ለህዝብ:እንደገና::

 

ሰላም:ከሀገረ:ንግስት:

10/09/2018

 

 

Back to Front Page