Back to Front Page


Share This Article!
Share
የተቋውሞ/የድጋፍ ሰልፍኛ ብዛት ስንት ነው?

የተቋውሞ/የድጋፍ ሰልፍኛ ብዛት ስንት ነው?

 

(ድጋፍ ለ ሰኔ 30/10/2010 ከህዳሴ ኢትዮጵያ የተሰራጨው ፅሑፍ)

 

ክቡራን የሰው ልጆች: ቀላል የቁጥር ስሌት የምታውቁ ሁሉ: ኣንዳንድ ግዜ ሆን ብለን ወይም ሳናውቅ የኣንድን ክስተት ሒሳባዊ ቀመር ስናዛንፍ ይስተዋላል:: በቀጥታ ወደ ዋና ኣስተያየቴን ለመግባት : በኢትዮጵያ የሚደረጉ የድጋፍ ይሁን የተቋውሞ ሰልፎች ወይም ትእይንቶች የሚሳተፈው የህዝብ ብዛት በጣም በሚያሳፍር ደረጃ ኣብዞቶ ወይም ኣሳንሶ መናገር ነው:: የሚያሳዝነው ግን ሆን ብለው ቁጥሩን የሚያዛቡት ጥቂቶች ሲሆኑ (ያሰቡትን ግብ ለማጠናከር ብለው) ኣብዛኛው ግን ተባለ እኮ ብሎ ወይም ደግሞ ካለው ድባብ ተነስቶ የሚሰራው ስሜታዊ የሒሳብ ስሌት ነው::

 

በቅርቡ(ሰኔ 16/10/2010) ለጠቅላይ ሚንስትራችን የተከበሩ Dr. አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ የወጣው የሰልፈኛው ብዛት በተመለከተ ከዛን ቀን ጀምሮ ሲያነጋግር ነበር:: በዛን ቀን ቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ እያለ የተወሰኑ ኣስተያየት ሰጪዎች ኣጭር የሂሳብ ስሌት እየሰሩ(ህዳሴ ኢትዮጵያ ባስነበበን ሰፋ ና ጠለቅ ባለ መልኩ ባይሆንም) የሰልፈኛው ብዛት ከ600ሺ እንደማይበልጥ ተደጋጋሚ መልእክት ያስተላልፉ ነበር:: ከዚህ የተነሳም ETV ሳይቀር ከ4-5ሚልዮን ይገመታል ብለው መናገር ጀምረውት የበረ ውሸት ገታ እንዲያረጉት አርጎዋቸዋል:: የኔ ኣስታየት ስለ ሰኔ 16/10/2010 የተደረገ የድጋፍ ሰልፍ የህዝብ ብዛት ጉዳይ ብቻ ኣይደለም: ከዛ በፊት የተደረጉም ይጨምራል ብቻ ሳይሆን ስለቁጥር ማጋነን ና ማሳነስ የኔ ምልከታ መናገር የጀመርኩት ከ1997 ዓ.ም ለኢህአዴግ ና ለቅንጅት የምርጫ ድጋፍ ከነበረው የቁጥር ውሸት ጀምሮ ነው:: በዚህ ኣጋጣሚ መናገር የምፈልገው ማንንም መሪ ወይም ፓርቲ በመደገፍ ወይም በመቋወም ኣይደለም ይሄን ትዝብቴን እየፃፍኩት ያለሁኝ: በተራ ቁጥር ለመከራከርም ኣይደለም: ሳይንሳዊ እውነታዎች ሆን ብለን ወይም በኣግባቡ ሳናሰላው ብናዛባው ፓለቲካዊ ይሁን ሌሎች ተያያዥ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ስላለኝ ነው::

Videos From Around The World

ለምሳሌ በ1997 የፓርቲዎች የምርጫ ውድድር ግዜ ቅዳሜ ዕለት ኢህአዴግን ለመደገፍ የወጣው ህዝብ ብዛት ከ 1-2 ሚልዮን ይደርሳል ተብሎ እነ የተከበሩ አምባሰደር ስዩም መስፍን ሳይቀር በሰልፉ የህዝቡ ብዛት በማየት ይሄ የህዝብ ብዛት የሚያሳየን ህዝቡ ኢህኣዴግን እንደመረጠ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም ብለው ነበር::

በነጋታው እሁድ እለት ቅንጅትን ደግፎ የወጣው ሰልፈኛ ደግሞ እነ የተከበሩ ኣቶ ልደቱ ኣያሌው የመሩት ከ 3 ሚልዮን በላይ የአ.አ ህዝብ ደግፎናል ብለው በማሰብ የኢትዮጵያ ህዝብ ቅንጅትን ነው የመረጠው ብለው በመደምደም ወደ የእልህ ፓለቲካ ውሳኔ ገቡ::

እርግጥ ነው ለኢህኣዴግና ለቅንጅት ደግፈው የወጡ የህዝብ ብዛት ሲነፃፀር ቅንጅትን ደግፎ የወጣ በእጅጉ ይበልጥ ነበር:: እኔ በዚያን ግዜ ሁለቱም ኣልደግፍም ነበር(ኢህኣዴግ ቅድሚያ ምርጫዮ ቢኖርም) : ሆኖም እስኪ የቅንጅት ድጋፍ: ስሜትና: ብዛት ምን እንደሚመስል በአካል ለማያት ብየ ሰልፉ ተቀላቅየ ነበር(ለኢህኣዴጉ ድጋፍ አልተሳተፍኩም):: በዚያ ለቅንጅት የድጋፍ ስልፍ የታዘብኩት ከልብ ለመደገፍ ብዛት ያለው ሰው መምጣቱ ና በተጨማሪ ሁኔታውን ለማየት የመጡ(እኔን የመሰሉ) መኖራቸው ነው:: እንግዲህ በዛን ግዜ የአ.አ ህዝብ ብዛት እስከ 3 ሚልዮን ይገመት ነበር:: እናስብ እንግዲህ: ተቋዋሚ/ደጋፊ እስካልን ድረስ ቁጥሩ እኩል ባይሆንም 3 ለሁለት መከፈሉ ኣይቀርም: ልጆች:ሽማግሌዎች: ኣብዛኛዎቹ የቤትእመቤቶች(ከሃይማኖት ወይም ባህል ኣንፃር) ሰልፍ የማይገኙ መሆኑ: ደጋፊም ሆኖ በተለያየ ምክንያት ሰልፍ የማይገኝ ብዙ መሆኑ: በተጨማሪ ከዛም ከዚያም የለሁበትም የሚል ብዙ ህዝብ ያለ መሆኑ ስናስብ እና በግርድፉ ብናሰላው ኣንድ ፓርቲ ደግፎ ሊወጣ የሚችለው የሰው ብዛት ከኣንድ ሦስተኛ በላይ ኣይሄድም:: በሳይንሳዊ እና ሒሳባዊ ዘዴ ብናሰላው ደግሞ የተከበሩ ህዳሴ ኢትዮጵያ የሰሩት ቅመራ ተቀባይነት ኣለው::

መስቀል አደባባይ የክብ ግማሽ(half of circle) ወይም የእንቁላል ግማሽ(half of ellipse) ቅርፅ ነው ያለው::

 

ለማሳጠር ከሥእሉ እንደምንመለከተው: ዘና ባለ የርዝመት ስሌት 510ሜትር ዲያሜትር(255m ረዴስ) የሆነ ክብ ቦታ: ግማሹ በሰዎች ተጨናንቆ ይሞላ ብለን ብንወስደው እና መካከለኛ ና ቀጫጭን ጉልበት ያላቸው ሰዎች ናቸው ብለን ብንወስድ: እንዲሁም እጃቸውን ወደ ታች ዘርግተው ቀጥ ብለው የቆሙና ምንም እቃ (የመፈክር ቦርድ ወይም ተሽከርካሪ ነገር) ሳይዙ እና ሳይጨፍሩና ሳይወራጩ ይቁሙ ብለን ብናስብ: በ 1 ካ.ሜ ስኬር ሊቆሙ የሚችሉ የሰው ብዛት ከ6-8 ሰው ነው(እንደታሰረ እንጨት ሆነው ማለት ነው):: ስሊዚ የክብ ቦታ ስፋት 3.14159x(255x255)= 204281.88975 msq ግማሹ 102,141 msq ወስደን : ከ 102,141x6=612,846 ሰዎች እስከ 102,141x8=817,128 ሰዎች ነው ሊይዝ የሚችለው:: መስቀል አደባባይ bird view ሲታይ የተመልካች ስቴጅ የሚቀመጠው ሰው ኣብዛኛው ግዜ በመስመር ቁጭ ብሎ ሲሆን: በመስመሮቹ መሃል ከ30ሴንት ሜትር በላይ ክፍተት ስላለው የሰው ብዛት ሳሳ ብሎ ይታያል:: ከሜዳው ሆነን ወደስቴጁ ስንመለከት ደግሞ ግጥም ብሎ የሞላ መስሎ ይታየንና ስሜታዊ ቁጥር እንደምራለን::

ስለዚ ከስሜታዊነት ነፃ ሆነን በ 1ሜ.ስ ከ3-5 ሰዎች ይቁሙ ብንል : በስእሉ የምናየው መስቀል አደባባይ ሊይዝ የሚችለው ከ 102,141x3=30642 ሰዎች እስከ 102,141x5=510,705 ሰዎች ነው::

ታድያ ላይ የጠቀስኳቸው ሰዎች ወደ ሰልፍ መምጣት የማይችሉበት ምክንያትና የአ. የህዝብ ብዛት ወደ ጎን ትተን የቦታውን ስፋት ብቻ ታሳቢ በማድረግ: በ1997 ኢህኣዴግን ደገፈ የተባለው ከ 1million በላይ የት ላይ ቆሞ ነው? ቅንጅትን የደገፈ ከ3ሚልዮን በላይ ነው የተባለውስ ? የኣሁኑ የሰኔ 16/10/2010 ETV ሳይቀር ወደ 4 ሚልዮንና ከዛ በላይ ተገኝቷል ተብሎ ይገመታል ብሎ ያስተላለፈውስ ? በጣም ያስተዛዝባል:: ያን ያክል ህዝብ በአ.አ ና ዙሪያው ይኑርና ሁሉም ሳይቀር ወደ ሰልፉ ተሳተፈ ብንልስ የት ላይ ይቁም?

እዚህ ላይ ተጨማሪ ምክንያት ማንሳት ያለብን ከአ.አ ዙሪያና ከሌላ ኣከባቢ የመጡ ሰዎች በብዛት ተሳትፏል የሚል ምክንያት ነው:: ይሄም ቢሆን የተሳሰተ ስሌት ኣለው: እንዴት ብንል የሰኔ 16/2010 እንውሰድና : ቦታውም ከ4-5million ይያዝ እንበልና: ግማሹ (2million በላይ) የመጣው ከአ.አ ዙርያና ከሌላ ሩቅ ቦታ ነው ብንል: ኣሁን ባለን ተጨባጭ የትራንስፓርት ኣቅም: ወደ አ.አ በቀን ስንት ሰው ሊጓዝ ይችላል? ቀደም ብሎ ና ከዋዜማ ጀምሮ ይምጣ ብለን ብናስብስ 2million ህዝብ ሊያስተናግዱ የሚችሉ ሆቴሎች አ.አ አሉን ? ወይስ ጎዳና ላይ ነው የተስተናገዱት(የተኙት)? ስሊዚህ ከአ.አ ዙርያና ሌላ ቦታ ሊሳተፍ የሚችለው ህዝብ በዛ ቢባል ከ50,000 በላይ አይዘልም::

ለማጠቃለል ያክል: ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ እንደተከታተልኩትና በሳይንሳዊ መንገድ እንዳሰላሁት መስቀል አደባባይና ዝርያው ያሉ ወጣ-ገባ ያሉ መንገዶቹን ጨምሮ መያዝ የሚችለው የህዝብ ብዛት እስከ 550,000 ነው::

በዚህ መሰረት ከፍተኛ የህዝብ ብዛት የታየበት የተኛው ነው ብለን ብንጠይቅ : የ 1997 የቅንጅት ሰልፍ ነው:: ምክንያቱም እንደ ኣሁኑ በባቡር መንገድ ያልተጣበበና : ለፀጥታና ለመሪዎች ጥበቃ ተብሎ ህዝቡ ወደ መሪዎች(እንግዶች) እንዳይጠጋ የሚከለክለው ነገር ኣልነበረም: ሜዳውና መንገዱ እስከ እስታድዮም ድረስ ግጥም ብሎ መልቶ ነበር: እስከ 360,000 ይጠጋል:: በሁለተኛ ደረጃ የሰልፍ ተሳታፊ የህዝብ ብዛት የማስቀምጠው የሰኔ 16/10/2010 ሲሆን ካለው የባቡር መንገድ ሁኔታ ና የፀጥታ ጉዳይ የግድ ኣስፈላጊ በመሆኑ ህዝቡ የተፈቀደለት ቦታ ብቻ ነበር የቆመው(በስተመጨረሻ ኣከባቢ ወደ ናፈቀው መሪው ኣከባቢ ፓሊሶቹን ገፍቶ ቢጠጋም): ወደ ስታድዮም ኣከባቢ የመስቀል አደባባይ ሰፊ ቦታ ክፍት ወይም ሳሳ ያለ ነበር: ከ340,000 እስከ 350,000 ቢሆን ነው:: በስተመጨረሻ በ1997 ኢህኣዴግ ደግፎ የወጣ የህዝብ ብዛት እስከ 300,000 ቢደርስ ነው::

በዚህ ኣጋጣሚ ለኣዲሱ ጠቅላይ ሚንስትራችን የተቃና የስልጣን ዘመን ይሆንለዎት ዘንድ እየተመኘሁ: በሰኔ 16/10/2010 በአሸባሪ ድርጊት የተጎዱ ዜጎች ፈጣሪ ብርታትና ፅናት ይስጣቸው እያልኩኝ: ያ አስነዋሪ የሽብር ጥቃት ያደረሱ ሰዎች በአስኳይ ተጣርቶ ለህዝቡ ይፋ ይደረግ ዘንድ እንፈልጋለን:: አጥፊዎቹም ተገቢው ቅጣት ይሰጣቸው::

 

ከእንግዲህ መስቀል አደባባይ million ሰልፈኛ ወጣ የሚል የውሸት ስሌት ይቁም!

 

መልካም ክረምት

Awot tegbr

ሓምሌ 1/11/2010

Back to Front Page