Back to Front Page


Share This Article!
Share
ፋኖ ማለት ምን ማለት ነው?

ፋኖ ማለት ምን ማለት ነው? ፋኖ የሚለው ቃል ኣማርኛም ፣ ትግርኛም ፣ ግዕዝም ኣይደለም :: ታድያ ፋኖ ማለት ምንድ ነው? ቃሉስ ክየት የመጣ ነው? የኣማራው ወጣት ፋኖ የሚለው ቃል ኢትዮዽያዊ ቃል ያልሆነ መሆኑንስ ይገነዘባል?

ሃይላይ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ 09-22-18

ቀደም ሲል ፋኖ የሚለው ቃል በዘፈን እንዲሁም በግጥሞች ስንስማው ከቆየን ዓሰርት ዓመታት ተቆጥረዋል:: በተለይ ኣሁን ደግሞ በኣገራችን በተለይ በኣማራ ክልል እየተደረገ ያለው ዓመጽ ፣ ያለመረጋጋት ፣ ዘረፋ፣ ወዘተ እንደ መሪዎችና ኣንቀሳቃሽ ሃይል ታስበው በኣማራ ክልል ያሉትን ወጣቶች ለመግለፅ የተለያዩ ኣካላት ፋኖ የሚለው ቃል በተደጋጋሚ ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ ::

Videos From Around The World

ፋኖ ማለት ምን ማለት ነው? ፋኖ የሚለው ቃል ኣማርኛም ፣ ትግርኛም ፣ ግእዝም ኣይደለም :: ታድያ ፋኖ ማለት ምንድ ነው? ቃሉስ ከየት የመጣ ነው? የኣማራው ወጣት ፋኖ የሚለው ቃል ኢትዮዽያዊ ቃል ያልሆነ መሆኑስ ይገነዘባል? ወዘተ የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሰመመለስ የተወሰነ ዳሰሳ በማድረግ ምላሽ ይሆን ዘንድ እንደሚከተለው ለመግለጽ ያክል እንደሚከተለው ኣቅርቤዋለሁ ::

በመሰረቱ ፋኖ የሚለው ቃል ኣመጣጡ ከቅኝ ገዢዎችና የባሪያ ስርዓት ጋር የተያያዘ ስለሆነ እነዚህ ቅኝ ገዢዎች ሲያደርጉት የነበረ ድርጊቶችና ክሰተቶች በጥቂቱ መቃኘት የግድ ይላል :: ቅኝ ገዢዎች ከፍተኛ የሆነ ሃብት የማካበት ፍላጎታቸውንና ይላቸውን ለማጠናከር የሚል ቅጥ ያጣ ፍለጎት ለማርካት በዓለም ላይ ያሉ ሰፋፊ ለእርሻ ሊውሉ የሚችሉ መሬቶች በማልማት ብሎም ወደውጭ በመላክ ክፍተኛ የሆነ ሃብት ማካበት ይቻላል በሚል ኣስተሳሰብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በኣንድ ወቅት ዓለማችን ኣስተናግዳለች :: እነዚህ ለእርሻ ሊውሉ የሚችሉ መሬቶች ለማልማት ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃብት ማሰማራት ይጠይቃል:: ከነዚህ የእርሻ ኣይነቶች የ ሱኳር ፣ ቡናና የመሳሰሉ ምርቶች ተጠቃሽ ናቸው :: ይህንን ፍላጎት ለሟሟላት የባርያ ጉልበት ሁነኛ መሳሪያ እንደሆነ በማሰብ ይህንን ጉልበት ለመሰብሰብ ከፍተኛ ዘመቻ በኣፍሪካ ላይ ተካሄደ :: በዚህ ጊዜ በተለይ ከምዕራብ ኣፍሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኣፍሪካውያን በቅኝ ገዢዎች ተወስደው በተለያዩ ደሴቶች በማኖር ጉልበታቸውን በመበዝበዝ ሰፋፊ እርሻዎችን እንዲያለሙ ይገደዱ ነበር ::

ታድያ ከነዚህ ደሴቶች ኣንዷ በፈረንሳይ ስትገዛ የነበረችው ማርቲኒክ ደሴት ናት (Martinique Island):: ማርቲኒክ ደሴት በምስራቃዊ ካሪቢያን ባህር የምትገኝ 1,128 ስኬር ኪሎሜትር ስፋት ያላት ከ500,000 የማይበልጥ የህዝብ ብዛት ያላት በኣሁን ጊዜም እነደ ኣንድ የባህር ማዶ የፈረንሳይ ግዛት የሆነች ኣገር ናት ::

በ 17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመርያ የስኳር ንግድ በጣም የተስፋፋበትና ብዙ ትርፍ የሚያስገኝ የንግድ ዘርፍ ስለነበረ በ 1685 ንጉስ ሉቃስ 15ኛ (Louis XIV) ኣፍሪካውያንን ከመኖሪያ ቤታቸው እየተወገዱ ወደ ፈረንሳይ የስኳር እርሻዎች ማጓጓዝና እንደ ባርያ ማሰራት እንደ ህግ ሆኖ እንዲተገበር በኣዋጅ የጥቁር ዓንቀጽ (Code Noire) ተብሎ በሚገለጽ ህግ ኣወጣ :: ከዚህ ግዜ ጀምሮ በእንደዚህ ኣይነት የገዢና ተገዢ የኣፍሪካውያንና ፈረንሳይ ውህደት ተጀመረ ::

በ 1693 እንግሊዞች ፈረንሳይን በማጥቃት ማርቲኒክ ደሴትን በስኬት ተቆጣጠሩ :: ማርቲኒክ ደሴት በስኳር በተለይ ካላት ከፍተኛ ምርት ፈረንሳይ ከ እንግሊዝ ጋር ማርቲኒክ ደሴትን መልሳ ለመያዝ ለ7 ዓመት በጦርነት ኣሳልፋለች :: በ7ኛው ዓመት 1763 በፓሪስ በተደረገው ስምምነት (የፓሪስ ስምምነት ተብሎ የሚታወቅ) ፈረንሳይ በካናዳ የነበራት ይዞታ ለእንግሊዝ እንድትሰጥና እንግሊዝ ደግሞ ማርቲኒክንና ኣጎራባቿ ጓዴሎፔን ለፈረንሳይ እንድትሰጥ ተደረገ :: ማርቲኒክ ደሴት ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በመሬት መንቀጥቀጥና ከውቅያኖስ በሚመጣው ማእበል ብዙ ጊዜ ጉዳት ደርሶባታል :: በ April 04, 1792 የፈረንሳይ ህግ ኣውጪ ኣካል ለሁሉም ኣይነት የሰው ቀለም ዜግነት እነዲሰጥ ኣድርጎ የባርያው ኣገዛዝ ግን ባለበት እነዲቀጥል የሚደነግግ ነበር :: በ 1794 የፈረንሳዩ ስምምነት ተብሎ የሚታወቀው የባሪያ ኣገዛዝ እንዲፈርስ ቢደረግም እንግሊዞች በዚህ ወቅት በ 30 March 1794 የነበረው የኣገዛዝ ስርዓት ተሽሮ በነበረው እንዲተካና ባርያዎቹም ወደየጌታቸው ተመልሰው በባርነት እንዲያገለግሉ ፣ በባሪያዎች ላይ የመሰብሰብ ፣ የመወያየትና ሌሎች መብቶችን ክልከላ ተደረገ ::

በ 1913 ፈረንሳይ ከጀርመን ጋር ወደ ጦርነት የመግባት ድባብ ባጠላበት ወቅት ፈረንሳይ በምትገዛቸው ሪጅኖች የግዴታ የውትድርና ኣገልግሎት እነዲካሄድ ኣወጀች :: በዚሁም መሰረት በየኣመቱ 1,100 ሰዎች ከማርቲኒክ ደሴት ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ፈረንሳይ ይላኩ ነበር :: በመጨረሻም በተደረገው የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ላይ 18,000 ማርቲኒካውያን ተሳትፈው ለፈረንሳይ ሲሉ 1,306 የሂወት መስዋዕትነት ከፍለዋል :: በ 1946 የፈረንሳይ ቢሄራዊ ሸንጎ ማርቲኒክ ደሴት ከቅኝ ግዛትነት ወደ ኣንድ ክፍለ-ፈረንሳይ ሆና እንድተዳደር ውሳኔ ኣሳለፈ ::

 

ፋኖ በካሪብያን ደሴት ከሆነችው ማርቲኒክ ደሴት በባሪያነት ከኣፍሪካና ህንድ ከሄዱት የትውልድ ዘር ከሆነው ከኣባቱ ፈሊክስ ካስሚር ፋኖ ና (Felix Casmir Fanon) የጥቁር ማርቲኔካዊና የነጭ ኣላስትያን ዘር ከሆነችው ከእናቱ ኢልያኖር መደሊሴ (Eleanore Medelice) በ July 20, 1925 የተወለደ ነው :: የፋኖ ቤተሰብ መካካለኛ ገቢ ያላቸው የነበሩ ሲሆን ፋኖ 18 ዓመት ሲሞላው ወደ የፈረንሳይ ሃይሎች ተቀላቀለ:: ፋኖ በሂወት ዘመኑ ሳይኪያትሪስት ፣ ፈላስፋ ፣ ኣብዮተኛና ደራሲ ነበር : : ፋኖ የጻፋቸውና ስራዎቹ በድህረ ቅኝ ኣገዛዝ ጥናት ፣ ሁነኛ ቲዎሪዎችና በማርከሲዝም ተጽኖ ፈጣሪ ነበር : : ፋኖ እንደ የህክምና ዶክተርና ሳይኪያትሪስት እንደ የፈረንሳይ ተቀጣሪ ሰራተኛ በፈረንሳይ ወታደሮችና ኦፊሰሮች ፣ በነጻነት ታጋዮች ኣካላዊና ስነኣእምሮኣዊ ጉዳት ለደረሰባቸው የስነልቦናዊ ኣገልግሎት በመስጠት ፣ ለኣልጀራዊያን ዜጎች የኣካል ድብደባ ለደረሰባቸው የስነልቦናዊ ኣገልግሎት በሆስፒታል ተቀጥሮ ያገለግል ነበር : : ፋኖ በዚህ ኣይነት ተግባር ለብዙ ጊዜ ፈረንሳይን ለማገዝ ስላልፈለገ በ 1956 በራሱ ፍላጎት ከሆስፒታሉ ለቀቀ : :

 

ፋኖ ፍራንትስ እንደ የህክምና ዶከተርና ሳይኪያትሪስት ኣልጀሪያን ከፈረንሳይ ቅኝ ኣገዛዝ ነጻ ለማውጣት ይካሄድ ወደነበረው እንቅስቃሴ በመደገፍ የኣልጀሪያ ቢሄራዊ ነጻነት ግንባር ኣባል ነበር : : ከዚህ ጊዜ በኋላ የኣልጀሪያን የነጻነት እንቅስቃሴ ሲታገል ከቆየ በኋላ በደረሰበት ህመም በ December 06, 1961 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ : : ፋኖ ፍራንትስ በሂወት ዘመኑ ከፈረንሳይዋ ባለቤቱ ጆሲ ወንድ ልጅ ኦሊቨር ፋኖና ከጆሲ በፊት ፋኖ በነበረው ግንኙነት የተወለደችው ሴት ልጁ ሚሬይለ ፋኖ መንደስ ፍራንስ ወልዷል : : ጆሲ በ 1989 በኣልጀርስ ሂይወትዋን ራሰዋ ያጠፋች ስትሆን ሚሬይለ ደግሞ በፓሪስ ዴስካርተስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ነች : : በኣሁኑ ጊዜም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የፋኖ ቤተሰቦች እየተጋበዙ ለህዝባዊ ውይይት ሲጠሩ ይታያል : :

 

የፋኖ ፍራንትስ ፎቶግራፍ ከዚህ ቤታች የተመለከተው ነው : :

 

Image result for fanon

 

 

ቸር እንሰንብት

 

 

 

Back to Front Page