Back to Front Page


Share This Article!
Share
የስልጣን ጥመኛ ጥሙን ለማርካት ሃገርንና ህዝብን ከማጥፋት ኣይመለስም

የስልጣን ጥመኛ ጥሙን ለማርካት ሃገርንና ህዝብን ከማጥፋት ኣይመለስም

ከኣሉላ ዮውሃንስ 15 መስከረም 2011

መቐለ

የበርካታ ሃገራት ተመክሮ እንደሚያሳየው ስልጣን የተጠናወታቸው ግለሰቦችና ብድኖች ከቻሉ በሰላም፣ ካልሆነ ከብጥብጥ እስከ ሃገርና ህዝብ መቃጠል፣ መበታተንና እልቂት እንዲፈጠር ማድረግ ለሰኮንድም ቢሆን ኣይተኙም፡፡ እነሱ ስልጣን ላይ ካልወጡ ኣገር ብትበታተን፣ ህዝቡም ቢገዳደልና ቢበታተን ደስታቸው ወደር የለውም፡፡ ምክንያቱም አኣስተሳሰበቸው ከኣህያ የተሻለ ስላይደለ፡፡

Videos From Around The World

ባሳለፍናቸው ስድስት ወራት ብዙ ኣሳዛኝና ይበል የሚያስብሉ የተደበላለቁ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ ከበጎ ጎኑ ብንጀምር በፖለቲካዊ ኣመለካከታቸው ብቻና ብቻ ታስረው የነበሩትን እንዲፈተቱ ማድረግ፣ የፖለቲካ ምህዳሩ ለማስፋት በኢህኣዴግ በኩል ይደረግባቸው የነበረውን ጫና መቋቋም ባለመቻላቸው በውጭ ይኖሩ የነበሩትን በሰላማዊ መንገድ ለመታገል እንዲገቡ መፍቀድ፣ ከኤርትራ ጋር የነበረው ውጥረት ማርገብ መቻሉና በሁቱ መንግስታት እገዳ ተጥሎባቸው የነበረው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መጀመሩ፣ ወዘተ

በሌላ በኩል ሲታይ ደግሞ ኣገሪትዋን የወጉ፣ያደሙ፣ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ውድመት ያደረሱና ብሎም በዘረኝነት ሰዎች በማንነታቸው በጅምላ እንዲገደሉ ያደረጉና የስደረጉ ወንጀለኞችን በስመ ይቅርታ ከእስር መፍታት፣ እኛ ስልጣን ላይ ካልወጣን ሁሉንም ነገር መጥፋት ኣለበት ብለው በፕሮፓጋንዳና በትጥቅም ጭምር ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለመበታተን ከሚያሴሩ ሃይሎች ግንባር ፈጥረው ከዚያም ከዚህም ከህዝብ ገንዘብ እያሰባሰቡ የግል ንሮኣቸውን ሲያደላድሉ የነበሩ የፖለቲካ ነጋዴዎች በስመ ምህዳር ማስፋት ወደኣገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ፣ ከባንዴራ ጀምሮ በተለያዩ እርምጃዎች ህገመንግስቱን መጣስ፣ በዚሁም የመደመር እሳቤን ካልተቀበላችሁ በሚል በእያንዳንዱ ክልል ጣልቃ በመግበት፣ ነውጠኞች ከማደራጀት እስከ ቀጥታዊ ወተሃደራዊ ጣልቃ ገብነት በመጠቀም ከመርህ ውጭ ኣሻንጉሊት የክልል መንግስታት መፍጠር፣ በታሪክዋ ኣይታው እማታውቀው ዘርን መሰረት ያደረገ ጋርዮሻዊ ግድያና መፈናቀሎችን መከሰት፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች እንቅስቃሴኣቸው ማቆምና በነዚህ ፕሮጄክቶች ኣመራር ይሰጡ የነበሩ ስለግል ጥቅማቸው ኣስበው የማያውቁትን ስምና ስራቸውን ከማጥፋት እስከ ማግለልና መግደል የደረሰ እርምጃ መውሰድ የደረሰ ኣሳፋሪ ድርጊቶችን ተከናውነዋል፡፡

ለዘህ ሁሉ እልቂትና መፈናቀል ዋናዎቹ በስመ ይቅርታ የተፈቱት ወንጀለኞችና ኣሸባሪዎች መሆናቸው ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ህግ እንዲከበር የሚያስችል ተጨባጭ እርምጃ በግዜው መወሰድ ባለመቻሉ መሆኑኑም እንዲሁ፡፡ በኦሮምያና በኣምሓራ በተቀናጀ ኣኳሃን ኣካባብያቸውን ከሌላ ብሄር የማፅዳት ዘመቻ በሰፊው እየተሰራበት ይገኛል፣ ከትግራይ ወደ ኣዲስኣበባና ከኣዲስኣበባ ወደትግራይ የሚያስኬደው ኣውራጎዳና የፌደራል መሆኑ ቢታወቅም እጅግ የብሄር ጥላቻ የተጠናወታቸውና በስልጣን ጥማት በሰከሩ የክልሉ ኣመራሮች ገፋፊነትና ኣይዞህ ባይነት እስከኣሁን ዝግ መሆኑና በዚሁ መንገድ ለመንቀሳቀስ ሙከራ ያደረጉ ከንብረት መዘረፍ እስከነመኪናው ማቃጠል የሚሄድ እርምጃ ሲወሰድ ሃይ የሚል የለም፡፡ በጎንደር ሑመራ በኩልም በተመሳሳይ፡፡

እኔ እስከማውቀው ድረስ በዚሁ ስድስት ወራት ካለተቀየረ በስተቀር ኣገራችን ባለሁለት ኣገር ዜግነት ኣታስተናግድም፡፡ በዚሁ በስመ ምህዳሩን ማስፋት የገቡት የፖለቲካ ፓርቲ ነን ባዮች በኣብዛኛዎቹ የሌላ ኣገር ዜግነት ያላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ሃይሎች ዓላማቸው ኣንድና ኣንድ ነው፡፡ እሱም ስልጣንን መያዝ ካልሆነ ግን ቀድሞውንም በሪሞት ያደርጉት እንደነበረ ማበጣበጥና እልቂት እንዲፈጠር በማድረግ ኣገሪቷን መበታተን ኣልያም የተዳከመችና ተንበርካኪ ሃገር እንድትፈጠር ማድረግ ነው፡፡ ታድያ ይህ ህጋዊ ያልሆነ የሌላ ሃገር ዜጎች በሃገራችን ፖለቲካ ጉዳይ እጃቸውን እያስገቡ ሰላማችንን ሲያደፈርሱ፣ መሰረተልማታችን ሲያስተጓጉሉና ሲያደፈርሱ ይታያሉ፡፡ ለሌላ ሃገር ዜግነት ላላቸው ሰዎች በሃገራችን የውስጥ ጉዳይ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተላላኪ በመሆን ገብተው እንዲፈተፍቱ መፍቀድ ኣሳፋሪ ተግባር ኣይሆንም ትላላችሁ?

ስለዚህ እውን ኢህኣዴግ ካለ የኢህኣዴግ ጉባኤ ትኩረት ሰጥቶ ሊያያቸው ከሚገቡ ወሳኝ ጉዳዮች ኣንዱ የሌላ ኣገር ዜግነት ያላቸው ሰዎች ኣርፈው በሰላማዊ መንገድ እንዲኖሩ ከመፍቀድ ባሻገር በውስጥ ፖለቲካ ጉዳያችን ኣይደለም ሊፈተፍቱ በሰላማዊ መንገድም ቢሆን ሊንቀሳቀሱ ህጉ የማይፈቅድ ስለሆነ በኣስቸኳይ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲገቱ ማድረግ የሚያስችል ኣስቸኳይ እርምጃ መውሰድ ይሆናል፡፡ እንድያ ካልሆነ ግን እነዚህ የሌላ ሃገር ዜግነት ያላቸው ሰዎች የስልጣን ጥማታቸው ከልክ የያለፈ ስለሆነ እነሱ በፈለጉት መንገድ ስልጣን ካልያዙ ሃገሪቷን ከማፈራረስና ህዝቦቿን እንዲተላለቁ ከማድረግ ወደውሃላ ኣይሉም ብቻ ሳይሆን ወላጆቻቸውንና ልጆቻቸውንም ከመግደል የሚመለሱ ኣይሆኑም፣ የስልጣን ጥመኝነት ከሃሽሽ የበለጠ ኣደንዛዥ ነውና፡፡   

 

Back to Front Page