Back to Front Page


Share This Article!
Share
አዲሱ የመደመር ቀመር በአስተዉሎት ማየቱ አይከፋም!!!

አዲሱ የመደመር ቀመር በአስተዉሎት ማየቱ አይከፋም!!!

ከኖህ ሙሴ

ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓ.ም

መቸስ በየግዜዉ ብቅ የሚል መፈክር አይጠፉም፡፡ እንሆ ዛሬም መደመር የሚባል መፈክር እንደ መፅሃፍ ቁዱስ ቃል ጥዋትና ማታ ከጋዜጤኛዉ እሰከ ባልስልጣኑ ከነጋዴዉ እሰከ ታክሲ ረዳቱ ባጠቃላይ አለ የተባለ የህ/ሰቡ ክፍል በቀልድም በቁምነገርም ቃሉ ስልችት እሰኪል ድረስ እየተሰማ ነዉ፡፡

ነገር ግን ይህ ቃል በብዙ ሰዉ ሲነገር ቢሰማም እዉነተኛዉ ትርጉሙ ገብቶት የሚናገረዉ እምብዛም ነዉ ፡፡ አብዛኛዉ ግን መፈክሩ ፋሸን ሆኖበት ወይም ይህ ባይል ከሚደርስበት መገለል ራሱን ለማዳን አለያም እኔም አለሁ በማለት ምናልባት ሊገኝ ከሚችል የሆነ ጥቅም እንዳይቀር ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ይህንን ቃል የሚያስተጋባ ሰዉ ለመሆኑ መደመር ሲባል ምን ማለት ነዉ ተብሎ ቢጠየቅ በተናጋሪዉ ቁጥር ልክ ትርጉሙም እጅጉን ሰለሚለያይ፡፡

በመሰረቱ መደመር ሲባል በአስተሳሰብና በተግባር ተዋህዶ ለአንድ አላማ ስኬት መስራት ማለት ነዉ እዉነተኛዉ ሰሜቱ፡፡ አንዲህ ያለ ነገር የሚመጣዉ ደግሞ ከመደመሩ የሚገኝ ዘርፈ-ብዙ የጋራ ጥቅም መኖሩን ተቀብለዉ ሰዎች ያለማንም ጉትጎታና ግፊ በራሳቸዉ ነፃ ህሊናና ፍለጎት መርጠዉ ሲደመሩ እንጂ ዋ!! አትደመርና ዋጋህን ታገኛለህ በሚሉ አሰፈሪ ቃላቶች እየተገፉ ሲገቡበት አይደለም፡፡

ስለሆነም መደመር የራሱ የሆነ በጎም ክፉም ዓላማ አለዉ፡፡ ለዚህም ነዉ ሰዎች አዉቆዉ እና ተረድተዉ መደመር ያለባቸዉ፡፡ አለበለዝያ 20 በጎችና 10 ጅቦችን በአንድ ተደምረዉ በአንድ በረት ቢያድሩ በማግሰቱ ዉጤቱ 10 ጅቦችና 20 የተቦጫጨቁ ስጋዎችና ቆዳዎች ማግኘት ይሆናል፡፡

ሌላዉ መታወቅ ያለበት ጉዳይ መደመርና መጨፍለቅ እጅግ የተለያዩ ነገሮች መሆናቸዉ ነዉ፡፡ መደመር የሚቻለዉ መደመር የሚችሉ ሁለት የተለያዩ ነገሮች የየራሳቸዉ አፈጣጠርና ሰብእና እንደያዙ ለጋራ ዓላማና ለጋራ ተጠቃሚነት የሚፈጥሩት ግንኙነት ሲሆን ይህም በምርጫና በምርጫ ብቻ የሚከወን ይሆናል፡፡ መጨፍለቅ በአንፃሩ የጥቅም ግጭት ያላቸዉና ፈፅሞ በጎ ዉጤት በማያስገኝ ለዛዉም ከምርጫቸዉ ዉጭ በኃይል ወይም በሆነ ግፊት በአንድ ላይ በማመጣት የቁጥር እንጂ የአይነት ግዝፈት የሌለዉ የጭፈለቃ ዉህደት ነዉ፡፡

Videos From Around The World

እኛ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ በጋራ ብንሆን የሚኖረዉን ጥቅም በማወቅ እንዲሁም በመከባበርና በመቻቻል ሁላችንም በእኩል የምንጠቀምባት ሀገር ትኖረን ዘንድ በነፃ ምርጫችን ከተደመርን እንሆ 27 ዓመታት አልፎናል፡፡ ይህ መደመራችንንም የሚያመጣዉ ጥቅምና ጉዳት በስፋት ከጫፍ እሰከጫፍ መክረንን ዘክርን ከዚህ በሚከተለዉ ቃል በማስማምያዉ ሰነዳችን (በህገ-መንግሰታችን) በዚህ መልኩ አስፍረነዋል፡፡

እኛ የኢትዮጵያ ብሔር በሔረሰ ቦችና ህዝቦች በሃገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘሊቂ ሰሊም ፤ ዋስትና ያለዉ ዳሞክራሲ እንዱሰፍን ፡ ኦኮኖምያዊና ማህበራዊ እዴገታችን እንዱፊጠን ፤ የራሳችን እድል በራሳችን የመወሰን መብታችንን ተጠቅመን በነፃ ፌሊጎታችን ፡ በሕግ የበሊይነት እና በራሳችን ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንዴ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት ቆርጠን በመነሳት ፡ ይህን ዓላማ ከግብ ለማዴረስ የህብረተሰቡና የብሔር / ብሔረሰብ መሰረታዊ መብቶች መከበራቸዉ ፡ የፆታ እኩልነት መረጋገጡ ፡ ባሕልችና ኃይማኖቶች ካለአንዲች ሌዩነት እንዱራመደ የማዴረጉ አሰፈሊጊነት ፅኑ እምነታችን በመሆ ኑ፤ በማለት፡፡

በዘሁ መልክ ደግመን እንደንሰማማ ያሰፈለገን ምክንያትም ከዛ በፊት አንድ ላይ ስላልነበርን ሳይሆን በፊት አንድ ላይ እንድንሆን የተደረግንበት መንገድ በመደመር ሳይሆን በመጨፍለቅ ስለነበር ነዉ፡፡ ይህም ማለት ከ80 በላይ ባህሎች ፤ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ፤ እምነቶች ፤ እና የአኗኗር ዜብየዎች የነበረን ቢሆንም ይህንኑ ተጨፍልቆ በአንድ ባህል ፤ በአንድ ቋንቋ እንድንኖር ተደርጎ ለመቶ አመታት የቁም ስቃይ በማየታችንና ይህንኑ ለመቀየር ወደር የለሽ መስዋእትነት ከፈለን ጨቋኙን ስርዓት ለመገርስስ በመቻላችን ነበር፡፡

ታድያ በዚህ መልኩ በነፃ ፈቃዳችን ተደምረን አንድ ላይ የፖለቲካ ፤ የኦኮኖሚ እና የማህበራዊ እድገት እያስመዘገብን ባለንበት ሁኔታ ዳግም ተደመሩ ማለትን ምን አመጣዉ ብለን ግራ ብንጋባ ሊገርም አይገባም፡፡ ቃሉም እንደየራስችን ፍላጎትና እዉቀት ብንተረጉመዉና በነገሩ እጅጉን ብንጠራጠር የሚገርም አይሆንም፡፡ ምክንያቱም በምን ዓይነት አዲስ ስሌት ዳግም ልንደመር እንደተፈለገ ስላልገባን፡፡ ደግሞስ በበጎ መልኩ ለመቀበል ብንከጅልም መደመር እያሉ በአፍ እየሰበኩ መቀነስን የሚያመጡ እርምጃዎችና አካሄዶች የሚያቀነቅኑ ንግግሮች (የቀን ጅቦች ፣ ፀጉረ-ለወጦች) ከተመሳሳይ አፍ እየሰማን እንዴት አንጠራጠር?

ሌላዉ ከዚህ ጋር ተዳብሎ የሚቀነቀነዉ ደግሞ ፍቅር ሁልንም ያሸንፋል የሚባለዉ ነዉ፡፡ ስንት የጥቅም ግጭትና ክፋት ባለበት አለም ሆነን ፍቅር ያሸንፋል በሚል ብቻ ህግና ስርዓት ፍርሶ አገር ሰላም ይሆናል ብሎ ማሰብ እንኳን በቤተ-መንግሰት በቤተ-እምነትም አይሰራም፡፡ ፍቅር እኮ ከሁለት ወገን ሲመጣ ነዉ የሚሳካዉ፡፡ ለዘሁ ማሳያ ደግሞ በተደጋጋሚ ለኤርትራ ይቀርብ የነበረዉ የሰላም ጥሪ በኤርትራ ወገን ተቀባይነት በማጣቱ ያልተሳካ ሲሆን አሁን ግን የኤርትራዉ ፕሬዝዴንት ከራሳቸዉ ችግር ተነሰተዉም ይሁን በሌላ ምክንየት ዛሬ በመቀበላቸዉ ሊሳካ የቻለዉ፡፡ ነገር ግን አለም በአፍቃርያን የተሞላች አይደለችምና አፍቃሪም ተፈቀሪን አስተዉሎ መምረጥ ካልቻለና ተፈቃሪዉም የአፍቃሪዉን በጎ ፍላጎት ተረድቶ አፀፋዉን ካልሰጠ ሁሌም የሚሳካ አይደለም፡፡

ነገር ግን ማንም ሰዉ ማፍቀር ቢችል እንኳን መርጦ እንጂ ሁሉንም ነገር ማፍቀር አይችልም ያፈቀረዉንም ቢሆን ሁሉንም በእኩል ማፍቀር አይቻለዉም፡፡ ይህ ተፈጥራዊም ነዉ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ፍቅር የዉሰጥና እዉነተኛ ስሜት ስለሆነ በፈለግነዉ መጠንና አይነት ልናሰፋዉና ልናጠበዉ የምንችል ሰዉ ሰራሽ ቁስ አይደለምና፡፡ ለዚህ ነዉ አንድ ወንድ እንድን ሴት ብቻ አፍቅሮ ለትዳር የሚበቃዉ፡፡ አለበለዝያማ ሁሉም ላፍቀር ቢልና ማፍቀር ቢችል በአለም ያሉ ሴቶች ሁሉ የአንድ ወንድ ሚሰቶች ይሆኑና ሌሎች ወንዶች ባደ በቀሩ ነበር፡፡ በፖለቲካዉ ስንመጣ ደግሞ እጅግ የተወሳሰበ ፍላጎትና ጥቅም ስላለ ዝም ብሎ ፍቅር ሰለተሰበከ ብቻ ችግሮች መፍትሄ አይገኝባቸዉም፡፡ ምክንያቱም የሰዉ ልጅ ባህሪ በግለኝነትና በስግብግብነት እንዲሁም በእኩይ መንፈስ ጭምርም የተሞላ ስለሆነ የፈለገዉ ፍቅር ብታሳየዉ የአንተን ፍቅር ለመጋራት ብሎ ጥቅሙን አይተዉም፡፡ ለዚሀም ነዉ ይህንን በአግባቡና በህግ ለማስተዳድር እንዲቻል መንግሰት ማሰፈለጉ፡፡

ወደ ተጨባጭ የአሁኑ የአገራችን ሁኔታ ስንመጣም መደመርና ፍቅር ለአገር የሚበጅ መሆኑ ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለዉ ሰዉ የሚስተዉ ባይሆንም በተግባር እየታየ ያለ ነገር ግን እየተደመርን ሳይሆን በፊት ተደመረንበት የነበረዉን ምሰሶ እየተናደ መሆኑን ነዉ፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወደዉና ተፈቃቅደዉ የሚኖርባትን አዲሰትዋን ኢትዮጵያ ለመመሰረት ባፀደቁት ህገ-መንግሰት የአንድነታቸዉ ተምሳሌት አርማ የሆነችዉን ባለኮኮብዋ ሰንደቅ ዓላማ ባደባባይ መቅደድና መርገጥ ለዛዉም በእንደመር ባይ ኃይሎች ሲደረግ በሚታይበት ሁኔታ ፣ ዜጎች በየትኛዉም ቦታ ተንቀሳቅሶ የመኖርና ኃብት የማፍራት እንቅስቃሴ በሰመ-መጤ በሰመ-ፀጉረ ለወጥ በግላጭ ተጥሶ ሲገደሉና ንብረታቸዉ ሲዘረፍና ሲቃጠል እያየን ፣ በስንት ህዝቦች መስዋእትነት የተገነባዉ ፌዴራላዊ ስርዓት ለማፍረስ በሰመ-እንደመር ሰልፈኛች በሽግግር መንግሰት እንተካዉ እየተባለ በአደባባይ መነገር በተጀመረበት ፣ ህዝብ የመረጣቸዉ የክልል ባለስልጣናት ከፌዴራል መንግሰት በሚሰጥ ትእዛዝና ጣልቃ-ገብነት ከስልጣን ሲባረሩ እያየን ፣ ማንም የመንደር ጎረምሳ ተሰባስቦ መንገድ ሲዘጋና ያሻዉን ገንዘብ አምጡ እያለ ሲዘርፍ፤ ባጠቃላይ በሰመ-እንደመር ስርዓተ-አልበኝነት ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፋ ሲሄድና ህገ-መንግሰቱ በግላጭ እየተጣሰ እያየን የመደመር ቀመሩ በትክክል መደመር ነዉ ወይስ መጨፍለቅ ብለን ግራ ብንጋባ ምኑ ነዉ የሚገርመዉ፡፡

ዛሬ ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት የአንድ ብሄር የበላይነት አለ በሚልና የእኩል ተጠቃሚነት ችግር አለ ተብሎ በተለያየ የአገሪቱ ክልል በተነሳዉ አመፅና ህዉከት ግፊት ለስልጣን የበቃ ኃይል የመጣበት መንገድ በማየት ሊላዉም ኃይል እንደአቋራጭና ጥሩ ስልት ወስዶ በየቦታዉ በድንበር ሰበብና የትናንት ማንነታችን እንመልሳልን በሚል ትርከት የመደመር ኃይል እንደሆነ እየሰበክ በተግባር ግን ተደምሮ የነበረዉን ህዘብ ወደ ግጭትና አጠቃላይ ትርምስ በማስገባት በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ እንቅልፍ ሳይወሰደዉ እየሰራና ብዙ ችግሮችን እየፈጠረ ባለበት ሁኔታ የመደመር ትርጉሙ ቢጠፋን መደመር ለምን ብለን ብንጠየቅ ከጥፋት ሊቆጠርብን አይገባም፡፡ ይልቁንም ይህ መጥፎ አዝማምያ በግዜ ካልተገታና ካልታረመ በቀር ባጠቃላይ አገራችን መንግሰት-አልባ ከመሆንና የእርስበርስ ጦርነት (ሲቪል ዋር) ዉስጥ ከመግባት የሚያስቀራት ነገር አይኖርም፡፡

መፍትሄዉስ ?

መፍትሄዉ አጠቃላይ ወደ ወቅቱ አመራር በተለይም ወደ አዲሱ ጠ/ሚ/ር ያተኮረ ነዉ፡፡ ባጭሩ መፍteሄ ይሆናል ያልኩትን እንደሚከተለዉ አስቀምጣለሁኝ፡፡፡-

1ኛ. ጠ/ሚ/ር ደ/ር አብይ አህመድ ከዚህ በፊት በሚያዝያ 2 ቀን 2010 ዓ.ም ኢ.ህ.አ.ደ.ግ ደ/ር ዓብይን አምኖ እንደመረጣቸዉ እሳቸዉም ለድርጅቱ እዉነተኛ ዓላማ ቁርጠኛና ታማኝ መሆን ይጠበቅባቸዋል እንዳልኩት አሁንም ጠ/ሚ/ሩ በተናጠል የሚሄዱበትንና ከድርጅቱ መስመር የወጣ አሰራርን ትተዉ ተመካክረዉና ነገሮችን በጥሞና አይተዉ ዉሳኔዎችን ማስተላለፍ ይገባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ዘላቂነት የሌላቸዉ የዉጭም ይሁን የዉስጥ ኃይሎች የተሳሳተ የአይዞህ ግፋበት አሳሳች ድጋፍ በጥንቃቄ በማየት ከነዚህ ኃይሎች ራሳቸዉን ማቀብ ይገባቸዋል፡፡ አለበለዝያ ዉጤቱ እሳቸዉ ካሰቡት በተቃራኒ ሊሆንባቸዉ ይችላል፡፡

ሌላዉ ማስተዋል ያለባቸዉ ጉዳይ በስመ ምህረትና ይቅርታ ከባድ ወንጀል የፈፀመዉን ጭምር ያለአንዳች ልዮነት መፍታት ኃላ ላይ ችግር ማምጣቱ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም መፈታት የሌለበትን ሰዉ መፍትት ቀይቶ መታሰር የሌለበትን ወደ ማሰርም ሊያመራ ይችላልና፡፡ አሁን እንደምንያዉ በይቅረታ የተፈቱት ሰዎች የተሰጣቸዉን ምህረት አመሰግነዉ ሰለማዊ ኑራቸዉ እንደማጣጣም በቀላቸዉን ህዝብን ከህዝብ በሚያጋጭ መንገድ ለማሰኬድ እየሰሩ ስላሉ፡፡ ይሀ ሁኔታ ሲቀጥል ደግሞ መንግሰት ትእግሰቱ ተሟጦ ወደ እርምጃ ሲገባ መታሰር የሌለበትን ሰዉ ጭምር ማሰርን ሊያመጣ ይችላልና በዚህ ላይ ትልቅ ጥንቃቄ ቢያደርጉ ለማለት ነዉ፡፡

የኢትየ-ኤርትራ የሰላም ጉዳይም ዓላማዉ እጅግ የሚደገፍ ቢሆንም አካሄዱ ላይ ግን ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ በድንበር ያሉ ህዘቦችን በስፋት ማሳተፍ ፣ የሚደረጉ ዉሎችና ሰምምነቶች ኃላ ላይ ከሚያስከትሉት ዉጤት ጋር መመዘን የመሳሰሉት በግልፅ ሊመከርባቸዉ ይገባል፡፡ አለበለዝያ ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፋታል እንዳይሆን ነገሩ፡፡

2ኛ. ህዝቡም በሆያ ሆየ ብቻ አገር እንደማይበለፅግን ሰላምን ማሰጠበቅ እንደማይቻል አዉቆ ዛሬ በእጁ ያለዉን ሰላም በዋዛ እናዳያስመልጥና ቁጭት ላይ እንዳይወድቅ ነገሮች በምን መንገድ እየሄዱ እንደሆነና ሊያስከትሉት የሚችሉትን ጥፋት በሰከነ መንገድ በማየት አዲሱን አመራር መምከርና ማስተካከል እንዲሁም መደገፍ ይኖርበታል፡፡

3ኛ. ድርጅቱም (ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ) ነገሮች ከቁጥጥር ስር እሲኪወጡና አጠቃላይ ቀዉስ እሲኪፈጠር ዝም ብሎ ከማየት ተቀራርቦ ለዉጡን ህዝቡን በተሻለ መንገድ ወደሚጠቅም አካሄድ እንዲያመራ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

4ኛ. በስመ-መደመር ዉሃዉን ከመርዙ ፣ እህሉን ከእንክርዳዱ ከማዋሃድ ይልቅ ጠቃሚዉን ሓይል ብቻ እንዲሰባሰብ በማድረግ የተሻለችና ሁሉንም ህዝቦችዋ እኩል የምታስተናገድ ጠንካራ ኢትዮጵያን መገንባት ላይ ሁልም በየፊናዉ መረባረብ ይኖርበታል፡፡

5ኛ. አሁን አገራችን ያለችበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና ግዜ የማይሰጥ መሆኑ ህዝቡ አዉቆ በመፍትሄዉ ላይ በግዜ የለንም መንፈስ መረባረብ ይኖርበታል፡፡

ቸር እንሰንብት

ሰላም ለአገራችንና ለህዝቦችዋ!!!

 

Back to Front Page