Back to Front Page


Share This Article!
Share
የኣማራ ሊህቃኖች ውዥንብር

 

የኣማራ ሊህቃኖች ውዥንብር

ኢትዮዽያ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ኣገር ነች፡፡ ይህን ሃቅ ማንም ሰው ሊክደው ኣይችልም፡፡ ይሁን እንጂ ይህ እውነታ በሃገራችን ለብዙ መቶ ዓመታት ተዳፍኖ ኖሯል፡፡ ከሃያ ሰባት ዓመት በፊት ኢህወደግ የደርግን ስርዓት ከገረሰሰ በኋላ የኣገራችን ስነ ምህዳር በኣብዮታዊ ዲሞክራስያዊ ስርዓት ማስተዳደር ሲጀመር ሁሉም ህዝቦችና ክልሎች በየፊናቸው የልማቱ ተሳታፊ በመሆን የክልላቸውን ልማትና እድገት ለማፋጠን ዋነኛ መንገድ ከፍቶላቸው በማሕበረ ኢኮኖሚ ኣመርቂ ስራዎች ተሰርቷል፡፡ በመቶ ዓመት ውስጥ ያልተሰራውን ልማት በሩብ ክፍለ ዘመን ሁሉም ሊመሰክርለት የሚችል ውጤት ተገኝቷል፡፡

መኖራቸውን ተዘንግተውና ተረስተው የነበሩት ህዝቦች ህልውናቸው ተረጋግጦ በልማቱ ላይ በመሳተፍ ክልላቸውን ጠቅመው ራሳቸውን እንዲጠቅሙ እድል ገጥመዋቸው በልማቱ ሂደት የራሳቸውን ኣስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ የህዝብ ጥቅምና የሃገር ልማት የማይታያቸው የኣማራ ሊህቃኖችና ትምክህተኞች በክልላቸው ህዝባቸውን ኣሰባስበው ወደ ልማት ማሰማራትና ህዝቡ በልማት ኣድጎና በልፅጎ እንዳይታይ የሚፈፅሙት እኩይ ተግባር ጭቁኑ የኣማራ ህዝብ ሊረዳው ኣልቻለም፡፡

በሃገራችን በተጀመረው የኣብዮታዊ ዲሞክራስያዊ ስርዓት ሁሉም ክልሎች በየክልላቸው የተጠናከረ የልማት ስራዎች በመሰራት ኣመርቂ የሚባል ልማት ለማስመዝገብ ችሏል፡፡ ይህ በየክልሎቹና በየኣከባቢው በተገኘው የልማት ሂደት በአጠቃላይ ለኣገሪቱ ገፅታ ትልቅ ኣስተዋፅኦ ኣበርክቷል፡፡ ሃገራችን ለተወሰኑ ዓመታት ሁለት ኣሃዝ ያለዉ የኢኮኖሚ እድገት እናስመዘገበች ኖራለች፡፡ በዚህም በብዙ ወገኖች እንደ ኣብነት ስትገለፅ ቆይታለች፡፡ ባደረገችው ኣበረታች ውጤት በተለያዩ ሃገራት ትኩረት እንድታገኝ ኣስችሏታል፡፡

Videos From Around The World

በመሆኑም እስከ ቅርብ ዓመታት ኢትዮዽያ ሃገራችን የሰላምና የልማት ተምሳሌት እየተባለች ስትመካከሽ ነበር፡፡ ካለፉት ሁለት ወይም ሶስት ዓመታት ግን እድሜ ለትምክህተኛችና ለሆዳቸው ለሚኖሩቱ ከታሪካዊ ጠላቶችዋ በማበር ሰላምዋ እንዲደፈርስ በር ከፍተውላቸው የነበራት የሰላም ኣየር ተበላሽቶ፣ ሰዎች በየመንገዱ የሚገዱሉበት እስከ መሆን ደርሷል፡፡ ኣማርኛ ካልተናገርክና ኣማራነትህ ካላረጋገጥክ ሌላ ብሄር ሁነህ መኖር ኣትችልም ለማለት ደርሷል፡፡ ኢትዮዽያ የምትኖረው እኛ ስንመራና ስናስተዳድር ነዉ ሊሉን ምንም ኣልቀራቸውም፡፡ ይህችን ኣገር እስካሁን ያቆዩዋት እነሱ ተከላክለውና ጠብቀው እንደሆነ ኣድርገው ምንም ሳይሸማቀቁና ሰያመናቱ ሊነግሩን ይፈልጋሉ፡፡ የኢትዮዽያ ታሪክ ለሚያውቅ ግን በምንም መልኩ ሊያታልሉት ኣይችሉም፡፡

ኣሁን በኣጋጣሚ የመጣው መሪ ደግሞ ኣካሄዱ ምን እንደሆነ ሊታወቅ ኣልቻለም፡፡ እንደ ፍየል እረኛ እንዳመጣለት ነው ተነስቶ የሚበረው፡፡ እግረ መንገዱ ያገኘውን ነገር ነው እየሰራ የሚመጣው እንደ እንጨት ለቃሚ፡፡ በተለያየ ኣከባቢ ሲሄት ሳያስበው የተለያየ መልእክት እየዘበራረቀ ያስተላልፋል፡፡ ኣንዳንዴ የክልል ኣስተዳዳሪ ነው ወይስ የፌዴራል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስተር ብለህ ልትጠይቅ ትገዳዳለህ፡፡ እንደ ጠቅላይ ሚኒስተር በምን ተጠያቂነት እየሰራ እንዳለ ራሱም ቢሆን ኣያውቀውም፡፡

ይህ ሰውየ ለመንግስትነት ሳይሆን ለመናፍቃን ስብከት ነው የሚመቸው፡፡ ለራሱ ሃይማኖት ሳይኖረው ስለ ሃይማኖት እየሰበከ ያለ ስራው እየሰራ ነው፡፡ የኢትዮዽያ የህዝብ ተወካዮች ፌዴሬሽን ምን እየሰራ እንደሆነ ሊገባኝ ኣልቻለም፡፡ ፌዴሬሽኑ ስልጣኑና ሓላፊነቱ በውን የሚያውቀው ኣልመሰለኝም፡፡ ይህ ሰው ኢትዮዽያን ለማጥፋት ከጠላቶችዋ በገንዘብ ተደልሎ የመጣ ይመስለኛል፡፡ ወደ ስልጣን ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከኣሁን ስለ ህገመንግስቱና ስለ ድርጅቱ የኢትዮዽያ ህዝቦች ኣብዮታዊ ዲሞክራስያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እንዲሁም ስለ ትልቁ ሕዳሴ ግድብ ትንፍሽ ያለበት ሰዓት ኣልሰማሁም፡፡

ይህ ሁሉ ሳስብ በኣእምሮየ ላይ ብዙ ጥያቄዎች ይመላለሱብኛል፡፡ የአገራችን ታሪክና ቅርስ ለሱ ምኑም ኣይደለም፡፡ እኛ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የብዙ ቅርሶች ባለቤት ነን፡፡ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ግን እነኚህ ቅርሶች ምኑም አይደሉም፡፡ በማይመለከተዉ ጉዳይ እየገባ በህዝቦቹ መካከል ጥላቻና ግጭት እንዲነሳ ነዳጅ እያርከፈከፈ ነዉ፡፡ የኢትዮዽያ ህዝብ በተለየ ደግሞ የትግራይ ህዝብ አካሄዱን በሚገባ ትኩረት ሊያደርግበት ይገባል፡፡ በየመድረኩ የሚያወራቸው ዓረፍተ ነገሮች ወይም ትግራይን ያገለሉ ናቸው ወይም በትግራይ ህዝቦች ላይ ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ ናቸው፡፡

ሰውየው ይዞት የተነሳ መርህ ኣለዉ ብዙ ጥያቄ ሊያስነሳ የሚችል፡፡ ሰውየው ክርስትያንም ኣይደለም እስላምም ኣይደለም ግን ሃይማኖትን ለማስታረቅ ይዳዳል፡፡ የኢትዮዽያ ሲነዶስ ለሁለት ተከፍሎ ነበር ብሎ ሲለን በጣም ይገርማል፡፡ እንዴት ለሁለት ተከፈለ ብሎ የሚጠይቀው አካል አላገኘም፡፡ በኢትዮዽያ ያሉ እስላሞች በኤርትራ ካሉ እስላሞች ሊፀልዩ ይችላሉ፣ ኦርቶዶክሶች፣ ካቶሊኮችም እንዲሁ ስል በአደባባይ ነግሮናል፡፡ የኢትዮዽያ ሲነዶስ ደግሞ በአመሪካና እዚሁ ለሁለት ተከፍሏል ብሎናል፡፡ ወደ አመሪካ የሄደው እኮ የነብስ ልጃቸው ወደ

ዙምባቤ ሲሄድ የኢትዮዽያ ህዝብን ትተው ወደ አመሪካ ስለሄዱ ነዉ፡፡ መንግስት አመሪካ ድረስ ሄዶ ኑ ተመለሱ ማለት ነበረበት ወይ? የኢትዮዽያ መንግስት እስላም ኣይደለም፣ ክርስትያን ኣይደለም ዋቀፈታም ኣይደለም መንግስታዊ ስራ ነዉ የሚተገብረው፡፡ ያሁኑ መሪ ግን ሃይማኖታዊ ነዉ ወይስ መንግሰታዊ? ተግባሩና ሃላፍነቱ በውል አልያዘውም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ አሁን ቆይታው ሕገ መንግስቱ መሰረት ኣድርጎ የሰራው አንድም ስራ የለም፡፡ ሕገ መንግስቱ የሰጠው ተግባርና ሃላፍነት በቁጥር 13 የስራ መደቦች አሉት፣ ከነዚያ መደቦች አንድም ኣልተገበረም፡፡ በሰላም ስም የሚነግድበት ስራ ግን ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የሰራው ኣይደለም፡፡ አሰራሩም የአባቱ የአፄ ምኒልክ ኣካሄድ ነዉ የተከተለዉ፡፡ አፄ ምኒልክ ለክብራቸው ነበር የሚሰሩት ይህ ሰውየም ህልሙ የአገሪቱ መሪ ለመሆን ብቻ ነው፡፡ የኢትዮዽያ ጠላቶችን ባለሟል በመሆን ከግብፆችና ከአረቦች እየተመሳጠረ አገሪቷን ለማፍረስ ይዳደዋል፣ አመሪካንም በአገራችን ውስጥ ጣልቃ እንድትገባ ኣድርገዋል፡፡ አመሪካ የገባችበትን አገር ደግሞ ሰላም ሲሆን አላየንም ለሰላም አልታደሉምና፡፡

በየ መድረኩ እየሄደ የሚናገራቸው ቃላት ለሰሚዉ የሚገርሙ ናቸው፡፡ የጥላቻ ግንብ ኣፍርሰን ድልድይ እንገነባለን እያለ ሁሌ እንሰማለን፡፡ የሚያስብ አእምሮ ያለዉ ከሆነ የጥላቻ ግንብ የሚፈልግ ማንም ሰው የለም፡፡ ሌላው እንደመር የሚለዉ ብሂል ነዉ፡፡ አብረን ተደምረን አይደለም እንዴ የፌደራል ስርዓት የመሰረትነዉና በልማት ስንጓዝ የነበርነዉ? አሁን በምን ስሌት ነው እንደመር የሚባለው፡፡

ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በሃገሪቱ ችግር ሲፈጥር የነበረው የአማራና የኦሮሞ አስተዳዳሪዎች የብጥብጡ መሪዎች አልነበሩም ወይ? የማን የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ነዉ? የሰረቁትን ለመደበቅና ወንጀልነታቸውን ለመሸፈን እነሱ የፈጠሩት ሁከት ነው፡፡ እዉነት የህወሓት ባለስልጣናት ኣልሰረቁም ብየ ባልከራከርም ከአማራና ከኦሮሚያ ክልሎች እንዳልሰረቁ ግን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ እንደመርስ ሲባል እንዴት ብለን ነው የምንደመረው? ስንዴውና እንክርዳዱ እንዴት ባንድ ጎራ ውስጥ እንደምራለን? ሰውየው በምን መርህ ሊመራን እንደተነሳ ፈፅሞ ሊገባኝ አልቻለም፡፡

የአማራ ሊህቃኖች ሆዳቸው በሆዳቸው የኢትዮዽያ ኣንድነት ሲሰብኩ ኣንድነት የሚሉት ኣንድ ቋንቋ መናገርና ኣንድ ኣይነት እምነት መያዝ ነው፡፡ የአማራ ኣካሄድ ከብዙ ዓመታት በፊት በሃገራችን እንደማያስኬድ ቢነገራቸውም ሊያዳምጡና በሰከነ መንፈስ ሊያስቡበት ኣልቻሉም፡፡

በመሆኑም ይህች አገር ለብዙ መቶ ዓመታት የልማትና የእድገት ኣየር ሳትተነፍስ በድህነት ተጠፍራ ቆይታለች፡፡ ሊሂቃኖቹ ሆዳቸው የሚመሉበት ካገኙ የህዝባቸው ችግር አይታያቸውም፡፡

እስኪ እውነት እንነጋገር ለአማራ ህዝብ የሚጠቅመው ሁሉም ህዝቦች የእኩልነት መብት ተሰጥቷቸው ክልላቸው በፍትሃውነት ሲያለሙት ነዉ ወይስ እንደለመዱት በተማከለ መስተዳደር እየተማከልን የተወሰኑት አማሮች በተለያዩ የአስተዳደር ደረጃ ተመድበው በሁሉም አካባቢ እየተዘዋወሩ ስሰሩ ነዉን? ይህ ኣካሄድ ለተወሰኑት ሆዳሞች ሊጠቅማቸው ይችላል ለሰፊው ህዝብ ግን ከዚህ የሚጠቀመዉ ነገር ኣይኖርም፡፡ የአማራ ሊህቃኖች ለህዝቡ ከማሰብ ይልቅ ለክብራቸውና ለሆዳቸው በማሰብ በሌሎች ብሄሮች እንዲጠላ እያደረጉት ነው፡፡ በአማራ ሆነ በኦሮሞ ክልል የሌላ ክልል ሰዉ በሕገ መንግስቱ መሰረት መኖር እንደማይቻል የሁሌ ትዝብታችን ሆኗል፡፡ በእነዛ ሁለቱ ክልሎች ያሉ ኣስተዳዳሪዎችና የፀጥታ አስከባሪዎች ችግሮች እንዲባባሱ እንጂ መፍትሄ እንዲያገኙ ሲሰሩ ኣይታዩም፡፡

በዚህ ምክንያት በነ ገዱ ኣንዳርጋቸውና በነ ለማ መገርሳ የስልጣን ዘመን ሕይወታቸውና ንብረታቸው ያጡት ወገኖች ብዙ ናቸው፡፡ የነዚያ ክልል ፖሊሶች ተበዳዮችን ሊታደጉ ኣይችሉም ኣይፈልጉምም፡፡ ለትምህርት የሄዱ ወጣቶችና በስራ ምክንያት በእነዚህ ክልሎች የተሰማሩ ሰዎች መከራና ችግር ሲያጋጥማቸው የሚከላከልላቸው ኣካል ኣላገኙም፡፡ ፍቅር! ፍቅር! እያሉ ይዘምራሉ እንጂ በፍፁም የህዝብ ፍቅር የላቸውም፡፡ የህዝብ ፍቅር ማለት የብሄርህ ሰዎች እየወደድክ የሌሎች ብሄር ህዝቦች መጥላት መገለጫው አይደለም፡፡ ህዝብ ያለ ማዳላት ብእኩል ዓይን ነዉ መታየት ያለበት፡፡

ከዚህ መረዳት የሚቻለው እነዚህ ሰዎች ለችግርና ለመከራ ወቅት እንደማይሆኑ ነዉ፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎቹ ምን ያህል የዘቀጠ ስብእና እንዳላቸው መገመት ያስችላል፡፡ የትግራይ ተወላጆች በእነዚህ ክልሎች የሚገደሉት ለምንድ ነው? የህወሓት መሪዎች በድለዋቸውም ቢሆን ለምን በማይመለከታቸው ሰዎች ላይ ይበቀላሉ? እስቲ የቢኣደን ኣመራሮች ስለበደሉ የአማራ ህዝብ በሌላ ክልል መገደል አለበት? ኦነግ ወይም አህዴድ ባጠፋው የኦሮሞ ህዝብ መጨፍጨፍ አለበት ማለት ነው? እውነት እናውራ ከተባለ የትግራይ ህዝብ የደርግን ስርዓት ለመጣል ከማንም የኢትዮዽያ ህዝብ እላፊ መስዋእትነት ከፍሏል እንጂ እላፊ ጥቅም ኣላገኘም አይጠይቅምም፡፡ ለህዝቦች እኩልነት በመታገሉና የፌደራል ስርዓት በመትከሉ መጠላት ይገበዋል ወይ?

እስኪ ለማወዳደር እንዲ ጠቅማችሁ ብዙ የደርግ ሰራዊት የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ነበሩ፡፡ እነዛ ወታደሮች የደርግን መንግስት ለማስቀጠል ሲባል ብዙ ኢሰብአዊ ድርጊቶች ሲፈፅሙ ነበር፡፡

ደርግ ከተደመሰሰ በኋላ ግን የትግራይ ህዝብ ከደርግ ጋር ሆናችሁ ስትበድሉን ነበር ብሎ ቂም አልያዘም፡፡ ስርአቱ ነዉ ያጣላን በማለት ቀን ሲፈርስባቸው ተንከባክቦ በየኣውራጃው ማቆያ ቦታ ኣዘጋጅቶ እያረፉና እየተመገቡ እንዲሄዱ ኣድርጓል፡፡ በነበረው ሃብተ ገነትም ያለውን እያካፈለና እየመገበ ወደየ ትውልድ አገራቸው ሸኝቶዋቸዋል፡፡ ይህ የፈጠራ ድርሰት ኣይደለም በዛን ወቅት የደርግ ሰራዊት አባላት የነበሩትን መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአሁኑ ወጣቶች ላያውቁት ይችላሉ በእነሱም አልፈርድም በእነ ገዱና በእነ ደመቀ መኮንን ግና በጣም አፍራለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች በምንም መልኩ የአማራን ጨዋ ህዝብ መሪዎች ሊሆኑ አይገባቸውም፡፡ ቁጭ ብለዉ የቀረፁትን ሕገ መንግስት እየጣሱ ህዝቦችን ሲያጨፋጭፉ ያሳፍራል፡፡ ይገርማችኋል ሌላ ሰው ቢናገርና ቢያማርር ምንም አይመስለኝም ራሱ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ሲያበቃ በኣደባባይ ለሃያ ሰባት ዓመት አንገታችን ደፍተን ኑረናል! ሲል ተናግሯል፡፡ እሱ አንገቱ ከደፋ ሌላዉ ሰው ምን ይበል? ይህ ኣባባል ህዝቡ ይቀበለናል ብለዉ ይሆናል ግን ውለው ኣድረው በህዝባቸው መናቃቸው ኣይቀርም፣ እዩኝ! እዩኝ! እንዳሉ ደብቁኝ! ደብቁኝ! ማለታቸው ኣይቀርም፡፡ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ሁኖ አንገቱ ከደፋ አንገቱ ያስደፉት ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስለሆኑ እሳቸውን ነዉ መጠየቅ ያለበት፡፡

እዚህ ላይ ብዙ መናገር ይቻል ነበር ግን . ከታሪክ እንደምናውቀዉ ከኣያታቸው ሆነ አባቶቻቸዉ የወረሱት ነዉ፡፡ ለራሳቸዉ ክብር እንጂ ለሃገራቸውና ለህዝባቸው ጥቅም ሲከራከሩ ኣላየንም፡፡ ለሃገራቸውና ለህዝባቸው ጥቅም የሚታገሉቱማ በሆዳሞች እየተጎነተሉ እንዲባረሩ ይደረጋሉ፡፡ በስም ህዝባችን እያሉ በተግባር ግን ህዝቡን የሚጠላበትና እንዳይታመን የሚያደርግ ስራ ይሰራሉ፡፡ እነሱን የሚጠቅማቸው ስራ ከሆነ አገሪቷ ብትሸጥ ምንም ማለት ኣይደለም፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኢትዮዽያዊ በተለይ የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች የመሪዎቻቸውን አካሄድ ማጤን ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሰላም ለአገራችን!

 

ምሕረት በአምላክ

26-11-2010 ዓ.ም.

Back to Front Page