Back to Front Page


Share This Article!
Share
አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ፤ ተረቱ አሁን ሲታይ

አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ፤ ተረቱ አሁን ሲታይ

ክበደ ጣሰው


ነሃሴ 14 2011


ታሪኩ እንዲህ ነው። ደጃዝማች አያሌው ብሩ የታወቁ ጀግና ጎንደሬ ነበሩ፡፡ በዚያ ጊዜ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ የጎንደርን መሳፍንትና ባላባቶች ለማስገበር እየታገሉ ቢሆንም ጎንደሬዎች አየሉባቸው፡፡ እንዲያውም አብዛኛዎቹ የንጉሱን አማራነትና የሰለሞናዊ ዝርያነት አጠያያቂ ነው እያሉ ሀሜት በማሰራጨት ለንጉሱና ለሽዋ ባላባቶች ትልቅ ስጋት ፈጥረው ነበር ይባላል፡፡ ታዲያ ንጉሱ ጎንደሪዎቹን በቀጥታ መውጋት የማያዋጣቸው መሆኑን አውቀው፤ ደጃዝማች አያሌውን ቀርበው፤ እነዚያን መሳፍንቶችንና ባላባቶች ወግተህ ካስገባሃቸው አንተን የበጌምድርና ሰሜን ገዢ አድርጌ እሾምሃለሁ፤ ብለው ጠየቆዋቸው፡፡ ደጃዝማችም በዚያ ተስማምተው፤ በተለይም በሰሜን የነበሩትን ሃይለኛ ራስ (ስማቸውን ረሳሁ) ወግተው፤ ሁሉንም አስገበረው ክች አሉ፡፡ በጎን ግን ንጉሱ የራሳቸውን ሰው እየመለመሉ ቆይተው ያን ሰው የበጌ ምድርና ሰሜን ገዢ አድርገው ሾሙ። አያሌው ብሩ ጉድ ተሰሩ። በዚህም የተነሳ ያገሬ ዘፋኝ አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ ሰው አማኙ እያለ ገጠመ። እስከ ዛሬ ድረስ ይህ ግጥም በጎንደርና በሌላ አማራ ክልል አካባቢዎች ይዘፈንበታል፡፡


ይህ ታሪክ አሁን እዚህ ላይ ለምን አስፈለገ? እያላችሁ ነው። 


ጸጋዬ ሃጎስ የሚባል ሰው ኦሮምያ ቱዩብ (Oromia Tube) በተባለ ሚዲያ ላይ የአማራ ጠላት ማን ነው? በሚል ርእስ፤ የአማራ ጠላቱ የራሱ ድንቁርና ነው፤ አማራ ማለት የሰማውን የሚያምን፤ በጎውንና ከክፉ የማይለይ፤ ሞኝ ተላላ ህዝብ ነው፤ ብሎ ጻፎ ነበር። ጥሩ ወዳጅ ግንባር ይናገራል እንጂ ዞሮ አያማም እንደሚባለው፤ አቶ ጸጋዬም የሰጡት ሃሳብ ገንቢና ትምህርታዊም ነው ቢባል መጥፎ አይደለም። 

Videos From Around The World

ቁም ነገሩ የአማራ ህዝብ በተፈጥሮው የዋህ እንጂ ደንቆሮ አይደለም፡፡ አማራ የሰለጠነ ህዝብ ለመሆኑ የታሪክ መረጃዎች ብዙ ናቸው፤ ለዚህም ዋናው መረጃው አማርኛን አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በቀላሉ ተምሮታል። በተጨማሪም አማራ ሃይማኖተኛ እንጂ ላጤ አጭበርባሪ አይደለም። ሰው ያምናል እንጂ አይጠረጥርም፡፡ ችግሩ ያለው ክአማራ የዋህነት አይደለም፤ መጻሁፍ ቅዱስ እኮ እግዚአብሄር የሚወዳችሁ የዋህ ስትሆኑ ነው ብሎ ያስተምረናል። ችግሩ አጭበርባሪውና የዋሁ አንድ ላይ ሲገናኙ፤ አንዱ ይበለጣል፤ ሌላው ይበደላል። ደጃዝማች አያሌው ብሩም ምኝ አልነበሩም። ሃይለስላሴ ብልህ ፖለቲከኛ ስለነበሩ የራሳቸውን ሰው መሾምን መረጡ። ለዚህም ያገሬ ዘፋኝ፤ አያል ተባባል ስሙ ባል ስሙ ባል እያለ ይዘፍናል። የግጥሙም ትርጉም፤ አያሌው ብሩ የዋህ ቢሆኑም ስማቸው የተከበረ ሆኖ ይቀራል ነው። ይህም ስለሆነ ነው ታሪካቸው አሁን እዚህ ላይ ምሳሌ ሆኖ የቀረበው። 


ጥያቄው፤ አሁን አጭበርባሪዎች በበዙበት ዘመን፤ አደጋ ለመከላከል ምን መደረግ አለበት? ትግስትና አስተዋይነት ካልተጨመረበት የዋህነት እኮ በራስ ላይ ጉዳት ያመጣል። በተለይም በማህረሰባዊ ሚዲያዎች በሚሰራጨው ወሬ የአማራው ወጣት አእምሮውና አስተሳሰቡ ተበክሎ የተለያሉ ሃይሎች በፈለጉት መንገድ እያሰማሩት ይገኛሉ፡፡ የአንዳንድ አማራ ድርጀቶችን ኦን ላይን ፕላትፍርም (Online platform) ሳይቀር እየተጠቀሙ የጥላቻና የክፍፍል ፖለቲካ አጀንዳ ሲያራምዱ ዝም ተብለው ይታያሉ። 


እንጂነር ስመኜውን የገደሉት ትግሬዎች ይሆናሉ ተብሎ ቢወራ፤ ድሃ ሰርቶ አደር ትግሬዎች በአማራዎች ተገደሉ። በስራ ባልደረቦቻቸው ተደብድበው እንደተገደሉ ይነገራል። 


ዳሸን ቢራ የትግሬዎች ነው፤ ይህን ቢራ አትጠጡ(boycott) ተብሎ ፕሮፓጋንዳ ተሰራጨ። በዚህ የተነሳ በአንዳንድ አማራ ክልል ከተማዎች ዳሽን ቢራ አይሽጥም። ይህ ቢራ ፋብሪካ አንደኛ የአማራዎች (ብአዴን) ነው፤ ህለተኛ ጎንደር ውስጥ ስራ ፈጣሪ ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ ነው። ቢራው ካልተሸጠ ኪሳራ ይመጣል፤ብዙ ወጣቶችም ከስራ ይባረራሉ። 


ወጣቶች በስሜት ተነሳስተው የህዝብንና የግለሰቦችን ንብረቶች ያወድማሉ። ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸውም ስራቸውን ያጣሉ። ማን ተጎዳ? 

አባቶቻችን ክትግሬዎች ጋር ብዙ የደስታና የክፉ ዘመን አብረው አሳልፈዋል። ታሪካቸውና ባህላቸው አንድ ነው ብለው ያምናሉ። መንግስትን የሚቃወም እኮ መቃወም ይችል ነበር። በክልሉ የሚኖሩትን ሰርቶ በሌ የትግራይ ሰዎች፤ አሀዱ ብለው ክርስትና ያጠመቁንን ካህናት ሳይቀር፤ ዳርንጎት/ጉርሻ ሰጥተው ያሳደጉንን እናቶች ሳይቀር፤ ከአገር ማስወጣት አሳፋሪ ስህተት ነው።


በአሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት ብአዴን እና በኦሮሞው ድርጅት ኦህዴድ መካከል ተፈጥሮ ያለው አፍላ ፍቅር ብዙዎቻችን አያስገረመነ ቀጥሎአል። ይህ ፍቅር ህዋሃትን ለማዳከም እና የኦሮሞን የስልጣን የበላይነት ለማረጋገጥ ኦህዴድ ሆነ ብሎ ያቀደው የፖለቲካ ስትራቴጂ ነው እንጅ ዘላቄታ ላይኖረው ይችላል ብሎ መናገር ብልሃት እንጅ ጸረ ኦሮሞ መሆን አይደለም። ህዋሃት ይጠቃል ወይስ አይጠቃም ለሚለው ጊዜ ያሳዬናል። የራስ አስተዳድርና ስልጣን ለሰጣቸው ለትግሬዎቹ ያልሆኑ የኦሮሞ ብሄርተኞች፤ ነፍጠኛ አማራ እያሉ ለሚጻርሩት ህዝብ ታማኝ ወዳጅ ይሆናሉ ወይ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ግልጽ ነው። በአጠቃላይ የብአዴን ክኦዴድ መለጠፍ በሆዋላ ራቁት መቅረትን የሚያስከትልና ለአማራ ህዝብ ክስረት የሚያመጣ ፖለቲካ ከሆነ፤ አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ እየተባለ የሚነገረው ተረት በኛ ትውልድ ሊደርስም ይችላል። 


አማራ ብቻውን መኖር አይችልም። የክልሉ ኢኮኖሚው ብዙም እያደግ ስላልሆና ብዞዎቹ ወጣቶች ያላቸው አማራጭ ወደ ሌላው ክልል ሄዶ መስራት ነው። ታዲያ የአማራ ክልል ወጣቶች ክክልላቸው የሚኖሩትን ንጹህ ዜጋዎች ያባራሉ ይገድላሉ እየተባለ፤ እንዴት ሆኖ ነው የአማራ አገር ወጣት ወደ ሌላ ክልል ሄዶ መስራት የሚችለው? እስኪ አስቡበት! በአሁኑ ሰዐት የአማራ ክልል መሪዎች ክሌላ ከልል ተፈናቅለው የመጡ አማራዎችን ጉዳይ ለማንሳት ይክብዳቸዋል፤ ምክኒያቱም በራሳቸው ክልል የሌላ አካባቢ ሰዎች ሲፈናቀሉና ሲገደሉ አላስቆሙም። እነዚያ ወንጀለኛ የወጣት ቡድኖች ይህን ተረድተው በትግራይ ተወላጆችም ሆነ በሌላው ንጹህ ዜጋ ላይ ጥቃት ከማድረስ ይቆጠቡ። 

በለውጥ ጊዜ ብዙ ያልታሰቡና የልተጠበቁ ሁኔታዎች ሊከሰቱ ይችላሉ። ደርግ እንደወደቀ አነግ የዘር ማጥፍት ዘመቻ በአማራዎች ላይ አቀናጅቶ ብዙ አማሮችን ገደለ። በእስራት ላይ የነበሩትን በህዋላ የሞቱት ዶክተር አስራት ወልደየስና ሌሎች በጣም ጥቂት የቁርጥ ቀን የአማራ ልጆች ተነስተው ጮኽው ግድያው አቆሙ። ሊላው አማራ ተብየው፤ ሙሁሩ አብዮተኛው ተራኪው፤ ወዘተ፤ ከእያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት ተሰጦ ይተራመስ ነበር እንጂ ለወገኖቹ አልደረሰም። ለወደፊቱ ክፉ ጊዜ ክመጣ ይህ እንዳይደገም። ብልሃት ያስፈልጋል። የዋህነት በልኩ ተመጥኖ የአማራ ህብረተሰብ ህልውና መጠበቅ አለበት። ይህ ደግሞ ብልሃት እንጂ ሌላውን የሚጎዳ ተንኮል አይደለም። ዋናው የእኔ መልእክት ይህ ነው።


በመጨረሻም፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የጥምር መንግስት ለመምራት ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል። ብአዴን ህዋሃት ኦህዴድ ሌሎችንም አባል ድርጅቶችን ጨምሮ እንደ ድሮው ምርጫ ሰረገላ ላይ ተቆፍጥጠውንና ተዝናንተው በቀላሉ ማለፍ አይኖርም። የአሁኑ ሁኔታ ክታየ በሚቀጥለው ምርጫ የተቃዋሚ ፖለቲካ ሃይሎች በብዛት እንደሚመረጡ መገመት አያዳግትም። 


ወጣቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማንጨብጨብ፤ መዝፈን፤ መዘመር፤ መጨፈሩን ትቶ እርሳቸው የያዙትን አቅጣጫ ቢያራምድ ይመረጣል። ጠ/ሚሊስትሩን የሚረዳው ወጣቶቹ ነብስ አውቀው ክፉና በጎውን ሲለዩ፤ ሰላምና ፍቅር ሲያስፋፉ፤ በመደራጀት ለስራ ፈጠራ ሲሰማሩ፤ ኢኮኖሚው ሲያድግ ነው። ሽብርተኛ ሃይሎችም፤ በተለይም አልሸባብ እና አልቃይዳ፤ የወጣቱን አለመረጋጋት አይተው አገሪቱ ውስጥ መረብ እንዳይዘረጉ፤ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

 

ከአክብሮት ጋር

 

Back to Front Page