Back to Front Page


Share This Article!
Share
ትምክህት ይሉኝታ አያውቅም፤ ማንንም አይምርም

ትምክህት ይሉኝታ አያውቅም፤ ማንንም አይምርም

ሄኖስ አቤል

መስከረም ፪ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም

ምዕራፍ ፩

ክፍል ፪

ደቂቀ እስጢፋኖስ (የአማራ ልሂቃን) እምየ ምንሊኮች በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት ካወጁ በርካታ ወራት ሆኖዋቸዋል፡፡ በእርግጥ በትግራይ ላይ ጦርነት ከማወጅ ቦዝነው አያውቁም፡፡ በኦሮሞ ላይም እንደዛው፡፡ የበግ ለምድ ለብሰው ከአማራ ማህፀን የመጡ ተኩላዎች ከኦሮሞ ጋር ውግንና ያላቸው መስለው በትግራዩም በኦሮሞውም ላይ አደጋ እየፈጸሙ ቆይተዋል፡፡ አሁን የሚጋለጡበት ሰዓት የደረሰ ይመስላል፡፡ የአማራ ልሂቃን በአስራ አንደናው ሰዓት ላይ ናቸው፡፡ ፊንፊኔ የነውጥ ቀጠና ለማድረግ ፋኖ ብለው እያዘመቱ ያሉት እነ ገዱ አንዳርጋቸው እና ደመቀ መኮንን ናቸው፡፡

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የትምክህት ጠርዝ የሆኑት ታማኝ በየነ እና ግንቦት 7 ወደ አገር ሲመጡ ደቂቀ ምንሊክ ምንነቱ ያልታወቀ ጨርቅ፣ የግንቦት 7 አርማ በፊንፊኔ ጎዳናዎች ሲያውለበልቡ ቆይተው አሁን የኦሮሞ ወጣቶች መስከረም ፭ ቀን ዓ.ም ለሚመጣው የኦሮሞ ነፃ-አውጭ ግንባር (ኦነግ) አመራርና አባላት አቀባበል ለማድረግ ፊንፊኔን በኦነግ ባንዴራ ለማሸብረቅ ሲንቀሳቀሱ ችግር ሲፈጥሩባቸው እየታዘብን ነው፡፡ ትምክህት ይሉኝታ አያውቅም፤ መከባበርን አይቀበልም፡፡ ልዩነትን አያስተናግድም፤ አንድ አይነትትን ይሰብካል፡፡ ትምክህት (Chauvinism) የፀረ-ዲሞክራሲያዊነት የመጨረሻ ጫፍ መጀመሪያ ነው፡፡ ይህ ባህሪው የነበረ፣ ያለና የሚኖር ነው፡፡ አሁን በዚህ ትምክህት ሳቢያ በፊንፊኔ ከተማ የምንንም ሰው ህይወት ሊያልፍ አይገባም፡፡ ደም ሊፈስም አይገባም፡፡ ትምክህተኞቹ በፊንፊኔ አደባባዮች የፈለጉትን ጨርቅ እንደሰቀሉ የኦሮሞ ወጣት በግብረ ገብነት ነበረ ታግሶዋቸው ያለፈው፡፡ እነሱ ግን የኦሮሞ ወታትና የኦሮሞ ህዝብ የሚኮራበት ኦነግ ባንዴራ ወይም አርማ በተራቸው ፊንፊኔን አቆነጃታለሁ ካለ መታገስ የግድ ይላል፡፡ ነገር ግን ትምክህት ትዕግስት የሚባለውን ነገር አያውቅም፡፡

Videos From Around The World

ታዲያ አሁንስ ምን ይሉን ይሆን? ያለ ኪሳራ አገር አትመሰረትም! በዓለም ያሉ አገሮች አገር የሆኑት መስዋእት ከፍለው ነው በማለት አፍሪካዊ ሂትለር ምንሊክ የፈጸማቸውን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ሲያመካኙ ነበር፤ ምንሊክ በኦሮሞ ላይ የፈጸመው ግፍ እንደ አንድ ገድል ቆጥረው አንድ አገር ለመመስረት የሚጠይቀውን ነው ያደረጉት ብለው ለማመካኘት ይሞክሩ እንደነበር አሁንስ ምን ይሉን ይሆን! አቤት የትምክህት ቅጥፈት፡፡ ሲያውለበልቡት የነበሩትን ምንነቱ የማይታወቅ ጨርቅ የኢትዮጵያ ለማድረግ መስዋእት ያስፈልጋል ይሉን ይሆን? ሁኔታው እንመልከት፡፡ የትምክህቱ መንደር ችግር እየፈጠረ ቆይቷል አሁንም ሊፈጥር ነው፡፡

ትምክህት ከአፍንጫው ራቅ ብሎ አይመለከትም፡፡ ከትናንት በደሉ፣ ከትናንትናው ሴራው ተምሮ ነገን ለደህና ነገር ለመጠቀም ዝግጁነት የለውም፡፡ በይቅርታ ምክንያት በደሉን ትውት ሲያደርጉለትም ያገረሽበታል፡፡ የአማራ ልሂቅ የማነኛውም ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ ጠላት ነው የምለው ለማለት ብቻ አይደለም፡፡ ትምክህት ማንንም አይተውም፤ ትግራዋይ አይል፣ ኦሮሞ አይል ሌላ አይል፡፡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ትምክህተኛ ሌላ ህዝብ ጠልቶ እወክለዋለው የሚለው ህዝብ አይወድም፡፡ የባሰ የጭካኔ አረሜናዊ ተግባሩ የሚፈፅመው የእኔ በሚለው ህዝብ ላይ ነው፡፡ በአማራ ላይ ነው መዓቱን የሚያወርደው፡፡

ትምክህትና የአማራ ልሂቃን አንድና የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፀር ነው የምንለው ከአባቶቻችን የሰማነው ታሪክ ተንተርሰን ሳሆን አሁን በእኛ ዕድሜ፣ ባለንበት ዘመን በ፳፩ኛው ክ/ዘመን በዓይናችን ስለምንመለከታቸው ነው፡፡ አሁንም ግን እንደከዚህ ቀደም ይቅር እንልላቸዋለን፡፡ ነገር ግን ትዕግስትም የራሱ የሆነ ወሰን አለው፡፡

ብላታ ሃ/ማሪያም ረዳ ለአዲሱ ትውልድ ትምህርት ሲያስተላልፉ የአባቶቻችሁ ታሪክ የምተርክላችሁ ስላልተፃፈ እንዲፃፍና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ በዚሁም ለወደፊት ልክ እንደ አባቶቻችሁ በአምላክ አምሳል ከተፈጠረው የሰው ልጅ ሁሉ እንደ ህዝብ ተከባብራችሁ እንድትኖሩ በማሰብ ነው እንጂ ለካ እንደዚህ ነበር፣ እንደዚህም አድርገውናል ብላችሁ ቂም እንድትቋጥሩ አይደለም፡፡ ብለው ነበር፡፡

ጀግናው የአንደኛው ወያነ መሪ ብላታ ሃ/ማርያም ረዳ አክለውም አባቶቻችሁ ቂመኞች አልነበርንም፤ አይደለንምም፡፡ ልጆቻችንም ልክ እንደአባቶቻችሁ ቂመኞች እንዳልሆናችሁ አምናለሁ፡፡ ጀግንነት መሰነቅ እንችልበታለን፤ ቂም የምንቋጥርበት ግን የለንም፡፡ እንዲህ ስለሆንም ነው ውሎ ሲያድር ልጆቻችን ጠላቶቻችንን ያሸነፉት፡፡ አባቶቻችን እንዳስተማሩን እውነትም ቂም የምንቋጥርበት አካል የለንም፡፡ ይሁን እንጂ ከትምክህት ኃይል በየጊዜው የሚታወጅብን ጦርነት አልተቋጨም፡፡ መከራ፣ ግፍ፣ ውድመት፣ ስቃይና ግድያ በትግራይ ህዝብ ላይ አቅደው እየተገበሩት ይገኛሉ፡፡

የአዲስቷ ኢትዮጵያ መሀንዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ መቼም የማይረሳ አንድ ነገር ተናግሮ ነበር፡፡ ደርግ ሁሌም ይኖራል ብሎ ነበር፡፡ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ዓብይ አሕመድም በበኩላቸው በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ በነበራቸው መድረክ ደርግ አላሸነፍነውም ያሸነፍነው ጣልያንን ነው አሉ፡፡ ጣልያን አሸነፈን ወይስ አሸነፍነው? አዋረደን ወይስ አዋረድነው? ጣልያን የሚፈልገውንና የሚበቃውን ከለከልነው ወይስ የሚበቃው መንጥቆን የሚፈልገውን ከለከልነው? የሚለው ለወደፊቱ ተመራማሪዎች የሚዳስሱት ሆናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ዓብይ አህመድ ግን አንድ ነገር ስተዋል፡፡ ጭቆና፣ ጭፍጨፋ፣ ግድያና ግፍ በነጭ ተፈጸመ በጥቁር ልዩነት አለው ወይ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም፡፡ የአገሬ ሆነ የሌላ አገር ጅብ ያው ጅብ ነው ከሚል አንደበት ምንሊክ ከሂትለር፣ መንግስቱና ደርግ ከጣሊያን ነጥሎ መመልከት የሀሳበ ፅኑነት (consistency) ዝንፈት የሚያሳይ ቢሆንም ደርግ አለመሸነፉ ላይ ግን ይስማማሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ዓብይ አሕመድ ይህንን ያሉት በአንድ በኩል የደርግ ቅሪቶችን (እንደነ አንዳርጋቸው ፅጌና ጆሌዎቹ) ለማስደሰት (ህዝበኛነትን) በሌላ በኩል ግን ቅኔ መዝረፋቸው ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ዶር. ዓብይ አሕመድ ደርግ አለመሸነፉን ነግረውናል፡፡ እውነትም ከመንግስታዊ ሥልጣን ከገባሪ አድራጊነትን ነው የተጠረገው እንጂ ከቡቹሎቹ፣ ከሙርኮኞቹና ከደቂቀ እስጢፋኖስ ተመንግሎ አልተጣለም፡፡ መለስ ዜናዊ እውነት ታይቶት ነበር፡፡ ደርግ ከመቃብሩ አመድ ልሶ ሊያንሰራራ እንደሚችል ታይቶት ነበር፡፡

አሁን አሁን ግን ህወሓቶች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ፀረ-ትግራዋይ አስተሳሰብ፣ አመለካከትና ተግባር ላይ የነበራቸውን ትዕግስት የተሟጠጠ ይመስላል፡፡ በአንድ ዓነትነታዊያን የሚቀነቀነው ፀረ-ብሄር፣ ብሄረሰብና ህዝብ አስተሳሰብና ድርጊት ያንገሸገሻቸው ይመስላል፡፡ ይሁን እንጂ ህወሓቶች አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ ተስፋ አልቆረጡም፡፡ ኢትዮጵያን ለማዳን መስዋእት ከጠየቀን የትግራይ ህዝብ ተጨማሪ መስዋእት ሊከፍል እንደሚገባ በመስበክ ላይ ይገኛሉ፡፡ እውነቱን ለማስቀመጥ ከሆነ ከእንግዲህ የሚከፈል መስዋእት ከንቱ መስዋእት ነው፡፡

ከዚህ በፊት የተከፈለው መስዋእት መልሱ ክህደት በሆነበት አገር፤ ያ ክቡር ዕድሜያቸው ኢትዮጵያን ለመታደግ ያባከኑት ጀግኖች አስተዋጽኦ ጥላሸት በሚቀባበት አገር፤ ክቡር ህይወታቸውን የከፈሉበት መራራ ትግል በአደባባይ ለማራከስ በሚሞከርባት ኢትዮጵያ የትግራይ ህዝብ ዳግም መስዋእት ሊከፍል? ለምን? የማን ልጅ የትኛው ወጣት ነው ለዚህ የአብርሃም በግ ሆኖ የሚቀርበው? አይሆንም፡፡ የትግራይ ህዝብ መስዋእት መክፈል ካለበት በአምላክ አምሳል የተፈጠረውን የሰው ልጅ አክብሮ፣ ሌሎች ብሔር፣ ብሔሮችንና ህዝቦች ልጆች ከራሱ ጋር እቅፍ አድርጎ በመያዝ ለሰው ልጅ የሚሰጥ ክብር ሁሉ ሰጥቶ በትግራይ ህዝብ ላይ የታቀደውና ያጠላ አደጋ ለማምከን በሚደረግ መስዋእት ላይ ነው መክፈል የሚገባው፡፡ ትርጉም አልባ መስዋእት የሞት ሞት ነው፡፡ ይህንን ዓይነት ሞት ደግሞ ከአባቶቻችን አልተማርነውም፡፡ ትግራይ ውስጥ ትርጉም ያለው መስዋእት ለመክፈል ልክ እነደከዚህ ቀደሙ ማንነታችና ክብራችንን ለመጠበቅ ማንኛውም ዓይነት መስዋእት ለመክፈል ዝግጁ ነን የሚል ወጣት በአስተማማኝ ደረጃ ተገንብቷል፡፡ ታጋሽና አስተዋይ ወጣት ባለቤት መሆን ተችሏል፡፡

አሁን ከውስጥም ከውጭም በተደራጀም ባለተደራጀም መንገድ የትግራይ ህዝብ ለማዳከም፣ የትግራይ ህዝብ ለማሸማቀቅ፣ የትግራይ ህዝብ ቀና ብሎ እንዳይሄድ ለማድረግ በርካታ ሴራዎች እየተካሄዱ ነው፡፡ እነዚህ የማንነት ክብር መገለጫዎች በማንም ተሰቱ ሳይሆኑ የትግራ ህዝብ በክንዱ የራሱ ያደረጋቸው ናቸው፡፡ ማንም ሊወስድበት አይችልም፡፡ በፍፁም፡፡ ትምክህተኞች በድብቅ፣ በሚስጥርና በግላጭ ጦርነት እያወጁ ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ ጠላትን እንዴት ማምከንና ማጥፋት እንዳለበት ለትግራይ ህዝብ መምከር ልጅ እናትን ምጥ የማስተማር ያህል ነው፡፡ ህወሓቶች ለሰላም፣ ለፍቅርና ለአንድነት ብለው ካልሆነ በስተቀር በግልፅም ሆነ በድብቅ የሚሸረብ ሴራ መንግሎ በማውጣት፣ በማጋለጥ እና አስፈላጊው እርምጃ በመውሰድ ረገድ የማንንም ልምድ አያስፈልጋቸውም፡፡ የአርባ ሦስት ዓመታት ልምድ በቂያቸው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከአባቶቻቸው፣ ከአያቶቻቸውና ቅድመ አያቶቻቸው የወረሱዋቸው ፖለቲካዊና ወታሃደራዊ ጥበቦችም ባለቤቶች ናቸው፡፡

በአገራችን ያለው ድብቅና ግልፅ ፀረ-ህዝብ እና ፀረ-ህወሓት እንቅስቃሴ ለህወሓት የተደበቀ አይደለም፡፡ አንድ ነገር ግን ማስተዋል ይቻላል፡፡ ህወሓቶች ነገሮችን ዝቅ አድርጎ የማየት፤ ነገሮችን ንፋስ አድርጎ መመልከትና አውሎ ነፋስ አንዳንድ ጊዜ ጠራርጎ የሚወስድበት አጋጣሚዎች እንዳሉ በውል ተረድቶ አለመዘጋጀት፤ ምን ያመጣሉ፣ ሥራዎቻችን ይመስክሩ የሚሉ ሩቅ የማያስጉዙ የተሳሳቱ የደካሞች ግምቶች አባዜ ያሉባቸው ይመስላሉ፡፡ ይህ የህወሓት መገለጫ ያልሆኑ አሁን አሁን የራሳቸው እያደረጉዋቸው ያሉ ባህሪዎች ናቸው፡፡ የሰላምና የግጭት (Peace and Conflict) ምሁራን በሰላም ጊዜ ለጦርነት ተዘጋጅ፤ በጦርነት ጊዜ ለሰላም ተዘጋጅ የሚለውን ሜለኛ አባባል ይስቱታል፡፡

የትግራይ ህዝብ የሰው ትርፍ የለውም፡፡ እያንዳንዱ ትግራዋይ ትርጉም ያለው የብዙ ሰዎች ልክ ነው፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በጣና በለስ፣ በወልዲያ ትግራዎት በመሆናቸው ብቻ፣ በማንነታቸው ብቻ የግድያ ሰለባ ሲሆኑ፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲዘረፉና ሲባረሩ ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ ረገድ አሁንም ድረስ ክፈተቶች ይስተዋላሉ፡፡ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የሚመጡ የትግራይ ተወላጆችም አስፈላጊውን እንክብካቤ ሲደረግላቸው አይታይም፡፡ እቺ አገር ለትግራዎት ሲኦል ሆናባቸዋለች፡፡ በኢትዮጵያ ላለፉት አንድ መቶ ዓመታት የነበሩ ነገስታትም ሆነ መንግስታት በትግራይ ህዝብ ላያ ያደረሱዋቸው ጥቃቶች የትግራይ ህዝብን ለማጥፋት፣ ለመከፋፈልና ለማዳከም የሸረቡዋቸው ተንኮሎችና ሴራዎች ናቸው፡፡ ይህንን እየታወቀ መዘናጋት አያስፈልግም፡፡

የሸዋ ደቂቀ እስጢፋኖስ አጼ ምንሊክን እንሂድ ትግራይ ተዳክሟል፤ እንግባ እናስገብራቸው ሲሉዋቸው እምየ ምንሊክ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ትግሬና እሳት አንድ ነው፤ እሳትም ነዶ ካላለቀ፣ ትግሬም እርስ በእርሱ ተዋግቶ ካልተላለቀ አይገባም፡፡ ደቂቀ እስጢፋኖስ/ሸዋውያን/ምንሊካውያን ሁሌም ቢሆን የትግራይ መዳከም፤ የትግራ ህዝብ መከፋፈልና መጠፋፋት እንደተመኙ ነው፡፡ የአማራ ልሂቃን/ደቂቀ እስጢፋኖስ አሁንም እየቀጠሉበት ይገኛሉ፡፡

የእምየ ምንሊክ የመንፈስ ልጆችና የልጅ ልጆች ደቂቀ እስቲፋኖስ የትግራይ ህዝብ አንድነት ለመበታተን በርካታ ሙከራዎች፣ በርካታ ሴራዎች ሸርበዋል፤ በርካታ ተንኮሎች እየቀየሱ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ጎንደር የመሸገው የወልቃይት አስመላሽ ኮሚቴ የትግራይ ህዝብ ትዕግስቱን ፈትኖታል፤ የወልቃይት ህዝብም የማያወላዳ መልስ ሰጥቶዋቸዋል፡፡ እኛ የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ የሌለን ትግራዎት ነን አርፋችሁ ተቀመጡ ብሎዋቸው እንዲመለሱ አድርጎዋቿል፡፡

አሁን ቀጠሉና ራያ የአማራ ነው ብለው መጮህ ጀመሩ፤ ይህ ጨሆት ሳይሳካ ቀረ፡፡ የራያ ህዝብ አያም በል ከማለት ውጭ ጆሮ ሳይሰጣቸው በዝምታ ሲያልፋቸው በሌላ በኩል መጡ፡፡ የመጀመሪው ሙከራ ሲመክን የትግራይ ልዩ ኃይል በራያ ህዝቦች የሚያደርሰውን በደል ያቁም የሚል መፈክር ይዘው የእምየ ምንሊክ የልጅ ልጆች ፊንፊኔ ላይ መሽገው በተልእኮ የትግራይ ህዝብ ትዕግስት ሲፈትኑ ህወሓቶች ትዕግስታቸውን ወደ መጨረሻው ደረሰና ፈጣን ምላሽ መስጠትን መረጡ፡፡

አሁን ስለ ራያ ጉዳይ የትግራይ ብሄራዊ ክላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም ለሁሉም የጥፋት ተባባሪና አስተባባሪ (ETv, የአማራ መገናኛ ብዙሀን፣ ሌሎች በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሀን) የማያዳግም ምላሽ ሰጥተዋቸዋል፡፡ የዒስባ የህዝብ ልጅ፡፡ አድቡ ብለዋቸዋል፡፡ ቤቶቻችሁን አጽዱ ብለዋቸዋል፡፡ የመገናኛ ብዙሀኖችም ህዝባዊ ኃላፊነቶቻችሁን ተወጡ፡፡ ከነፈሰው ጋር አትንፈሱ ብለዋቸዋል፡፡

አቶ ረዳኢ ሓለፎም የትምክህተኞች ድብቅ ዓላማ ላይ ብዙም ማለት አልፈለጉም፤ ግልጽና ተጨባጭ ዓላማቸው እያወቁም ድብቁን ዓላማ ላይ ትንታኔ መስጠትም አይጠበቅባቸውም፡፡ ጊዜ እንደማባከንም ይቆጠራል፡፡ ግሩም ምላሽና ማብራሪያ! የሚገርመው ግን እንደ እሳቸው ያለ አስተዋይ ወጣት ፖለቲከኛ እየተደመረ ሳይሆን እየተባዛ መሄድ ይጠበቅበታል፡፡ ህወሓትም እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ለማፍራት የ፳፬/፯ የቤት ሥራዋ አድርጋ ከሰራች ከትግራይ አልፈው አሁን በመፍረስ አፋፍ ላይ ላለቺው አገርም ይተርፋሉ፡፡ ከፍተኛ ተስፋ ተሰምቶኛል፡፡ ክልላዊ፣ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ሁኔታ በአግባቡ የሚተነትን፣ የነገው የኃይል አሰላለፍ ምን ሊሆን እንደሚችል የሚገምት፣ የአሁኑ የኃይል አሰላለፍ በውል የሚረዳና የሚተነትን ፖለቲከኛ ያስፈልጋታል ትግራይ፡፡ ዕድሉ ማስፋት ከተቻለ ህወሓቶች ቆርጠው ከተነሱ መንገዳቸው ህዝባዊና ህዝባዊ ብቻ፣ መስመርና መስመር ብቻ በማድረግ ዥዋዥዌ ከመጫወት እራሳቸውን ከታደጉ የትግራይ ወላድ ለራሷ ቀርቶ ለሌላም ትተርፋለች፡፡

ከፊንፊኔ የነቆጠው ተላላኪ ራያን በተመለከተ የትግራይ ቴሌቪዥን ባዘጋጀው የምሁራን መድረክ በርካታ ነጥቦች ተነስተዋል፡፡ በበኩሌ ረክቼባቸዋለሁ፡፡ ነገር ግን አንድ ሁለት ነጥብ ልጨምር፡፡

አንደኛው በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ልዩነቶች አሉ ሲባል በርካታ ብሔሮች፣ በርካታ ቋንቋዎች፣ በርካታ ባህሎች፣ በርካታ እምነቶች አሉ ማለት ነው፡፡ እነዚህ የማንነት መገለጫዎች ታፍነው ኖረዋል፡፡ ታፍነው መኖራቸው ሳይበቃ እነዚህ ማንነቶች የራሳቸውን ክደው የሌላ ማንነት ተገደው እንዲለብሱት ይደረግ ነበር፡፡ ይህ የብሔር ጭቆና ካላልነው ሌላ ምንም ልንለው እንችላለን? ታሪክ በመካድ አንድነት አይመጣም፡፡ ልዩነቶች በመድፈቅም አንድነት አይሳካም፡፡ የብሔር ጭቆና ስለመኖሩ የሚያረጋግጡ በርካታ በሺዎች የሚቆጠሩ አሳማኝ ማስረጃዎች ቢኖሩም አንድ ነትብ ላንሳና ክፍል ፫ በቀጣይ፡፡

1.      የአማራ መገናኛ ብዙሀን ባዘጋጀው የምሆራን የምክክር መድረክ አንድ አዛውንት እንዲህ አሉ፤ አማራነት በጂኦግራፊ ሚታጠር ሳሆን ይቅርታ አድርጉልኝና አማራነት መንፈስ ነው፡፡ ትዝ ይላችሁ እንደሆን ምናልባት ወያኔ እንደገባ ሰሙን በደቡብ ያለ አንድ ህፃን ልጅ ለምንድን ነው የምትማረው ተብሎ ሲጠየቅ አማራ ለመሆን ነው መልሱ የነበረው፡፡..ከዛላምበሳ ጀምሮ እስከ ደቡብ መቸረሻ ድረስ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ አማራ ነን የማይል፣ አማራ ለመሆን የማይፈልግ የለም ብለው እርፍ፡፡ ታዲያ የሰው ልጅ ወዶና ፈቅዶ ማንነቱን ይክዳል እንዴ ጎበዝ? ስለሆነም የመጀመሪያው ነጥብ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አማራ እንዲሆኑ የማድረግ ቅዠት ነው የሚያልሙት፡፡ አንድ በልሉኝ፡፡

ሁለተኛው ነጥብ የአማራ ልሂቃን/ ሸዋውያን/ ደቂቀ እስጢፋኖስ/ ምንሊካውያን በታሪካቸው የሰው ፍቅር የላቸውም፡፡ እነሱ ከመሬትና ከነዋይ ነው ፍቅራቸው፡፡ የአርትራ ጉዳይ ሲነሳ ዓሰብና ምፅዋዕ እንጂ የኤርትራ ህዝቦች ጉዳያቸው አይደለም፡፡ ራያ ሲሉም መሬቱን እንጂ ህዝቡ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ ወልቃይት ሲሉም መሬቱን አንጂ ህዝቦቹ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ መተከል ሲሉም መሬቱን አንጂ አንድ ቀን ህዝቡን ሲሉ አይደመጡም፡፡ ሸዋ ሲሉም መሬቱን እንጂ ኦሮሞዎቹን ጉዳያቸው አይደለም፡፡ እነዚህ አካላት ሰዎች አይደሉም እንዴ? ስለዚህ የራያ ህዝብ ብለው ሲያነሱ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ስለሆኑ ወይም ድርጊቱ ስለተፈጸመ አይደለም፡፡ የትግራ ህዝብ የምንከፋፍልበት እናገን እንደሆነና መሬቱን እንዴት እንመንትፍ ነው፡፡ አይሆንም፤ በጭራሽ፡፡

ትምክህት የማንንም ህልውና አይቀበልም፡፡ አያከብርምም፡፡ በዛሬው ቀን (፳፻፲፩ ዓ.ም) ፊንፊኔ ላይ እየሆነ ያለው በትምክህት ምክንያት ነው፡፡ የአማራ ልሂቃን እራሳቸው ያሴሩት እራሳቸውን ይበላቸዋል፡፡

Back to Front Page