Back to Front Page


Share This Article!
Share
በበጀት ዓመቱ ወደ ዓለም ገበያ የተላኩ ቡናዎች በመጠን የ5.67 በመቶ ጭማሪ ማሳየታቸው ተገለጸ፡፡ አጠቃላይ ከቡና ቅመማ ቅመምና ሻይ 854.28 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ ወደ ዓለም ገበያ የተላኩ ቡናዎች በመጠን የ5.67 በመቶ ጭማሪ ማሳየታቸው ተገለጸ፡፡ አጠቃላይ ከቡና ቅመማ ቅመምና ሻይ 854.28 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

 

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በዘንድሮ 2010 በጀት ዓመት በመጠን 238,465.55 ቶን ጥሬ ቡና ወደ ውጪ ተልኮ 838.15 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን ገልጿል፡፡ ይህም በባለፈው ዓመት ወደ ውጭ አገር ገበያ ከተላከው ቡና የ5.67 በመቶ ጭማሪ ያለው ሲሆን በአጠቃላይ አፈፃፀሙ ከእቅዱ ጋር ሲነፃፀር በመጠን የ88.19% እና በገቢ የ72.44% አፈፃፀም እንደሆነ ታውቋል፡፡

 

የቡና ኤክስፖርት አፈፃፀም ከተመሳሳይ 2009 ከሐምሌ እስከ ሰኔ ወር ያለው ሲነፃፀር በመጠን 12,797.89 ቶን (5.67%) ጭማሪ ቢኖረውም በገቢ ግን የ44.31 (5.02%)ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ እንዳለው የባለስልጣን መ/ቤቱ ሪፖርት ያሳያል፡፡ ለዚህ ከሚጠቀሱት ምክንያቶች ውስጥ በሲዳማ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ እና ሀረር አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው የተመጣጠነ ዝናብ እጥረት፣ አጠቃላይ በአለም የቡና ዋጋ ላይ ቅናሽ መታየቱ፣ የቡናችን ጥራት በሚፈለገው ያህል የተጠበቀ ባለመሆኑ እና በአገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ነው፡፡

 

የባለስልጣን መ/ቤቱ መረጃ እንደሚያመለክተው ከእቅዱ አንፃር በአሥራ ሁለት ወራት ውስጥ በመጠን ከፍተኛ የሆነ አፈጻጸም የተመዘገበው በህዳር ወር ውስጥ ሲሆን የ115 በመቶ አፈጻጸም አለው፡፡ በአንጻሩ ዝቅተኛ አፈጻጸም የታየው በመጋቢት ወር (69%) መሆኑ ታውቋል፡፡ በገቢ ደግሞ በነሐሴና በመስከረም ወራት ከፍተኛ (92%) አፈጻጸም ሲኖረው ዝቅተኛው ደግሞ በመጋቢት ወር (56%) በአፈፃፀምነት ተመዝግቧል፡፡

 

የባለስልጣን መ/ቤቱ አያይዞ እንደገለጸው ከሐምሌ-ሰኔ ወር 2010 በጀት ዓመት የተላከዉ ቡና በመዳረሻ ሀገራት ሲታይ ጀርመን በመጠን 51,634.44 ቶን (22%) ድርሻ እና በገቢ 145.10 (17%) ድርሻ ሚሊዮን  የአሜሪካን ዶላር፣ አሜሪካ በመጣን 26,656.66 ቶን (11%) ድርሻ እና በገቢ 140.90 (17%) ድርሻ ሚሊዮን  የአሜሪካን ዶላር እና ሳውዲ አረቢያ በመጠን 37,405.5ቶን (16%) ድርሻ እና በገቢ 120.99 (14%) ድርሻ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አፈፃፀም በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን በገቢ ይዘዋል፡፡ የተቀሩት በ2010 ገቢ ቅደም ተከተል 4ኛ ጃፓን፣ 5ኛ ቤልጅየም፣ 6ኛ ደ.ኮሪያ  ፣ 7ኛ ጣሊያን፣ 8ኛ ሱዳን፣ 9ኛ ፈረንሳይ እና 10ኛ እንግሊዝ ሲሆኑ ከ1 እስከ 10 ያሉት በአጠቃላይ በመጠን 86.2% እና በገቢ 84.39% ይሸፍናሉ፡፡ በጥቅሉ የእነዚህ ዋና 10 መዳረሻ ሀገራት ከ2009 አፈፃፀም ጋር ሲወዳደር 5.78% ጭማሪ በመጠን  እና -5.32% ቅናሽ በገቢ አሳይተዋል፡፡

 

በሌላ በኩል በዘንድሮ ከሐምሌ እስከ ሰኔ ወር 2010 በጀት አመት የቅመማ ቅመም ወጪ ንግድ ክንዉን በመጠን 10257.31 ቶን ቅመማ ቅመም  ወደ ውጪ ተልኮ 12.81ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል፡፡ ይህ አፈፃፀም ከእቅዱጋር ሲነፃፀር በመጠን የ55.84% እና በገቢ የ40.92% አፈፃፀም በመሆን ተመዝግቧል፡፡ ይህ ማለት ከዕቅዱ አንፃር በመጠን የ44.16% ቅናሽና በገቢ የ59.08% ቅናሽ አሳይቷል፡፡ የ2010 በጀት አመት አፈፃፀም ከተመሳሳይ 2009ዓ.ም ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመጠን 238.73 ቶን እና በገቢ 5.08 ሚልዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የሻይ ወጪ ንግድ ክንዉንም በመጠን 1745.96 ቶን ሻይ ወደ ውጪ ተልኮ 3.32 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል፡፡ ይህ አፈፃፀም ከእቅዱ ጋር ሲነፃፀር በመጠን የ70.74% እና በገቢ የ76.49% አፈፃፀም በመሆንተመዝግቧል፡፡ይህ ማለት ከዕቅዱ አንፃር በመጠን የ29.26% እና በገቢ የ23.51% ቅናሽ አሳይቷል፡፡ የ2010 በጀት አመት  አስራ ሁለት ወራት አፈፃፀም ከተመሳሳይ 2009 ዓ.ም አስራ ሁለትወራት ጋር ሲነፃፀር በመጠን 152.53 ቶን ቅናሽ ሲያሳይ በገቢ 0.11 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በ2011 በጀት ዓመት የቡና ምርታማነት በአማካይ ከ6.19 ወደ 10.2 ኩንታል በሄክታር ለማድረስ እቅድ የተያዘ ሲሆን 457.5 ቶን ቡና በመላክ 1.83 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት እቅድ ተይዟል፡፡

 

ለበለጠ መረጃ

ስንታየሁ ግርማ

Sintayehugirma76@gmail.com

0947763765

 

Videos From Around The World

 

Back to Front Page