Back to Front Page


Share This Article!
Share
ዶክተር ዐቢይ እና የአራት ወራት ቆይታቸው ስኬት

ዶክተር ዐቢይ እና የአራት ወራት ቆይታቸው ስኬት

(በእቴጌ ዳጊ) 08-09-18

ባለፉት አራት ወራት ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ቀንና ሰአት ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ስኬታማ የሆኑ ክሰተቶችና ነገሮች ተከናውነዋል::ዶ/ር አብይ አህመድ ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅርና ክብር በንግግራቸው ስለመደምር ስለአንድነት፣ ስለዴሞክራሲ ስለኢትዮጵያዊነት ስለ እርቅ ይቅርታና ፍቅርን በመስበክና በተግባርም ይቅር በማለት አዲስ የሆነ መንገድ ቀይሰዋል ::

ባለፉት ጊዜያት ችግር ውስጥ የነበሩ አካባቢዎችን ቅድሚያ በመስጠት እረፍት የለሽ ጉዞዎችን አድርገው ለነበሩትም ችግሮች እልባት ሰጥተዋል። እንዲሁም ባለፉት ጊዜያት ውስጥ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ድንቅ የተባሉና ተደማጭነትን ያስገኙ ውጤታማ የሚሰኙ ንግግሮችን በማድረግና ህዝቡን በማወያየት የየአካባቢውን ቋንቋ በመቀላቀል፣ የየአካባቢውን ባህል በማንጸባረቅ፣ የህዝቡን የልብ ትርታ ከልብ በማድመጥና የሚያረካ ምላሽ በመስጠት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ተስፋ እንዲያጭርበትና ለለውጡ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆንና ድጋፉን በተግባር እንዲያሳይ አድርገዋል።

Videos From Around The World

ባለፉት አራት ወራት በአዲሰ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በቻግኒ፣ ሃዋሳ፣ አዳማ፣ ቦንጋ ፣አምቦ ና ሌሎች የሀገሪቷ አካባቢዎች ተደርገው በነበሩት የድጋፍ ሰልፎች ህዝቡ ምን ያህል ከዶ/ር አብይ አህመድ ላማ ጋር በሙሉ ልቡ እንዳለ የሚያሳይ ጉዳይ ነው:: ይሄን ደግሞ ዶ/ር አብይ አህመድና አመራሮቻቸው ከህዝቡ ዘንድ እንደተላከ ማበረታቻ እና ሀላፊነትን ለመወጣት እንደ ተሰጠ አደራ ማየት መቻል አለባቸው::

በፖለቲካው ዘርፍከዚህ ቀደም ተቃዋሚ ፓርቲ በሚል ስያሜ ሲጠሩ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተፎካካሪ ፓርቲ የሚል መጠሪያን ሰጥተው ከመጥራት ጀምሮ አብረው እንዲሠሩ ጥሪ በማቅረብ ፣ሀገር ውስጥ ያሉ ሚዲያዎችም ካለማንም ጣልቃ ገብነት በነጻነት እንዲዘግቡ፣ በሽብርተኝነት ተፈርጀው የነበሩ የሀገር ውስጥ ድርጅቶችን ከሽብርተኝነት መዝገብ ላይ በህጋዊ መንገድ በመሰረዝ ፣የፖለቲካ አመራር እስረኞችን በመፍታት፣ ውጪ ሀገር የነበሩ ተቃዋሚ ሚዲያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ ጥሪ በማቅረብና የወዳጅነትን ሰሜትን ለመፍጠር መሠረት በመጣል ላይ ይገኛሉ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በውጭ ግንኙነት አመርቂ ሊባል የሚችል ውጤት አስመዝገበዋል:: በተለይም በደምና በአጥንት ከተሳሰርናት ከጎረቤት ሀገር ኤርትራ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን ሞት አልባ ጦርነት በማፍረስና በሁለቱ ወንድማማች ሀገራት ህዝቦች መሀል ጥሩ የሆነ ግንኙነት መፍጠር ተችሏል :: ከዚህ በፊት የነበረው የቂምና ቁርሾ ግንኙት አሁን ወደ ሰላማዊ ግንኙነት በመቀየር ተዘግቶ የነበረውን የኤርትራን ኤምባሲ በመክፈት ቀጥታ የአውሮፕላን በረራና የስልክ አገልግሎት መጀመሩ በሁለቱ ሀገራት ለሁለት አስርት መታት ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች መገናኘት የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል:: የሁለቱ ሀገራት እርቅም ያለ ሦስተኛ ወገን በመካሄዱ ከአህጉራችን አፍሪካ ተርፎ ለዓለም ሀገራት ምሳሌ መሆን ችሏል::

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የደቡብ ሱዳንን ፕሬዝዳንትና ተቃዋሚም በአዲስ አበባ አግኝተው አወያይተዋል። ከጂቡቲ ጋርም በተደረገው ውይይት የወደብ ድርሻ የመግዛትና በኢትዮጵያ ከሚገኙ ውጤታማ ድርጅቶች መሃል የአየር መንገድና የኤሌክትሪክሲቲ ድርጅቶችን ድርሻ ለመሸጥ ሀሳብ ቀርቦ ስምምነት ላይ ተደርሷል::

በኢኮኖሚ ረገድ በሀገራችን ላለፉት ጊዜያት ባለሁለት አሀዝ ያደገ ኢኮኖሚ እድገት የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በተለያየ ምክንያት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እነደነበር ይታወሳል:: በተጨማሪ በቁጥጥር መላላትና በባንክ ምንዛሪና በጥቁር ገበያ ምንዛሪ መካከል ሰፊ ልዩነት በመፈጠሩ የውጭ ምንዛሪው ዝውውር በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች እጀ ለመውደቅ ጫፍ ደርሶ ነበር።

ይህን እጥረት ተከትሎ በተለይ በኮንስትራክሽን ዘርፍ እና በአጠቃላይም በሌሎች ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ በመፈጠሩ ሥራዎች ተቀዛቅዘው፣ የኑሮ ውድነቱም ግሽበት ይታይበት ነበር። የውጭ ኢንቨስትመንት የመሳብ አቅማችን በመቀዛቀዙ ምክንያት የሥራ አጥ ቁጥርም ከፍ ብሎ ነበር። አሁን እየተወሰደ ባለው እርምጃ ተስፋ ሰ, ሁነታዎች እታ ነው:: በ ጥቁር ገበያ ዶላር ምንዛሪ ከብረው የነበሩ ሀገር ወዳድ ዜጎች ተቀባይነት እያጡና እየከሰሩ ይገኛሉ:: ባንኮችም ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በዶላር ምንዛሬ ብዙ ሰዎችን እያሰተናገዱ ነው::

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በነበራቸው የአሜሪካ ጉብኝት በሶስት ከተሞች ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር መክረው ነበር ይህም ውጪ በሚኖሩ ዜጎች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተቀባይነትንና ተወዳጅነትን አትርፎላቸዋል:: በውጤቱም የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች በየቀኑ ለማኪያቶ ከሚያወጡት ወጪ በቀን ከአንድ ዶላር ጀምሮ ለእናት ሃገራቸው ኢትዮጵያ ለመለገስ ቃል አንዲገቡና ያንን ገንዘብ መላኪያ ይሆናቸው ዘንድም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መላኪያ አካውንት ሊያስከፍቷቸው ችለዋል::

Back to Front Page