Back to Front Page


Share This Article!
Share
እልል በይ ግብፅ

*** እልል በይ ግብፅ ***  
መሪዎቻችን ምለዋል 
አባይ ቀስ ብሎ 
እንዲያዘግም
እንዳይቸኩል
እንዳይፈጥን።

ሰውረዋል 
ቀንሰዋል 
አለቃውን
ጠበቃውን
የኩራት ካባውን። 


አብረዋል...
ወሬው እንዲሆን 
የውሀ ሽታ
እንዲርቀን 
እንዲጠፋ 
ከቲቪ ከሬድዮ 
ብሎም ከጋዜጣ።

እድምዋል
ስራ አቁመዋል
ወርፈዋል 
    ብለው...
መሪዬ ካለ 
አባይ ለምኔ። 

  እልል በይ ግብፅ
  ስራሽ ፍሬ አፍርቷል።


ኢዮብ ከባህር ማዶ

08-30-18

Back to Front Page