Back to Front Page


Share This Article!
Share
የኢትዮጵያ ተሰሚነት ያንሰራራ ይሆን?

የኢትዮጵያ ተሰሚነት ያንሰራራ ይሆን?

በስንታየሁ ግርማ sintayehugirma76@gmail.com

07-20-18

“ጂኦፖለቲካል ፊቸር” ጆርጅ ፍሪድ ማን በተባሉ አሜሪካዊ የጂኦ ፖለቲካል ተንታኝ እና የአለም አቀፍ ጉዳዮች ስትራቴጂስት በ1949 እ.ኤ.አ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ በተለያዩ ድረ ገፆች አለም አቀፍ ሁኔታዎችን ይተነትናል፡፡ ይኸው ድህረ-,ገፅ “ኢትዮጵያ በቀጠናው ሀያል እየሆነች ነውን?” በሚል ርዕሰ-አንቀፅ ባወጣው መጣጥፍ በአፍሪካ ቀንድ ያሉት ተዋናዮች በዋናነት አሜሪካ፣ ኢራን፣ ቻይና፣ ሩስያ፣ ቱርክና ሌሎች የአውሮፓ ሀያላን ናቸው፡፡  በዝርዝሩ የሌለ ሀገር ቢኖር ከቀጠናው  ውስጥ ነው፡፡  ይህ ግን አሁን አሁን እየተለወጠ ያለ ይመስላል፡፡  ኢትዮጵያ በቅርቡ ብዙ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለውጦች እያደረገች ነው፡፡  አላማው ደግሞ በውስጥም ሆነ በውጭ ኢትዮጵያን እንደገና መገንባት ነው፡፡  እነዚህ እቅስቃሴዎች ደግሞ ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላትን ተፅእኖ የማሣደግ እና በቀጠናው መሪ የመሆን ፍላጎቷን ያሣያል፡፡

ኢትዮጵያ በቀጠናው መሪ ለመሆን ልዩ ቦታ አላት፡፡  ለብዙ ዘመናት ከቅኝ ገዥዎች ነፃ ሆና ቆይታች፡፡  የአፍሪካ ቀንድ በአሁኑ ወቅት ብዙ ተዋናዮች አሉበት፡፡  ኢትዮጵያም ተፅእኖ የማሣረፍ ፍላጎት አላት፡፡  ይሁንና ኢትዮጵያ በውስጧ ብዙ  ተግዳሮቶች አሉባት፡፡  በመጀመሪያ ደረጃ ከሌሎች ተዋናዮች ጋር ስትነጻጸር ደካማ መስላ ትገኛች፡፡  ይሁንና ከታሪክ ስንረዳ ከሌሎች ተዋናዮች የበለጠ ሀይል እንዳላት እንረዳለን፡፡  የአክሱማይት ዘመን እንኳን ብንወስድ(1270-1974) በአፍሪካ ቀንድ ተጽእኖ ለማሣደር አቅም እንደነበራት ማሣያ ነው፡፡  በአክሱማይት ጊዜ ኢትዮጵያ 1.25 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎ ሜትር ያለው ግዛት ትቆጣጠር ነበር፡፡  ግዛቷም ሰሜን ኢትዮጵያን፣ ኤርትራን ፣ ሰሜን ሱዳን ፣ ደቡባዊ ግብጽን ጅቡቲን እና ምዕራባዊ የመንን ያጠቃልል ነበር፡፡

Videos From Around The World

የአክሱማይት ግዛት በአፍሪካ፣ በአረብ እና በግሪክ ሮማን ክፍለ አለም መገናኛ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ኢትዮጵያ የበለፀገች ነበረች፡፡  ጠንካራ ባህር ሀይል  የነበራት በመሆኑ የባህር እንቅስቃሴውን ለመቆጣር አስችሏት ነበር፡፡  ልክ እንደአሁኑ ኢትዮጵያ የአክሱማይት ግዛት ብዝሀነት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የያዘ ነበር፡፡  እንደታሪክ ፀሀፊዎች ከሆነ ንጉሶቹ ግዛቶቹን በመከፋፈል ለአካባቢው አስተዳደር በመስጠት ያስተዳድሩ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ የግዛት ሃያልነቷን የውጭ ወረራ በመመከት አሣይታለች፡፡  የአቶማን ግዛት በማስፋፋት እና የግብጽን ወራሪ በመቋቋም፡፡ 

ይሄ ደግሞ ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ነፃነቷን እና ባህሏን ጠብቃ ለማቆየት አስችሏታል፡፡  ይህ ታሪክ ለአሁኑ ጊዜም ትርጉም አለው፡፡  ኢትዮጵያ 100 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ስትሆን  ክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖቶች በብዙዎች የሚመለኩ ናቸው፡፡  ከ80 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች ይኖሩባታል፡፡  ከነዚህ ውስጥ ኦሮሞ 32% አማራ 28% ይሸፍናሉ፡፡  ትግራይ እና ሶማሊያ እያንዳንዳቸዉ 6.5% ሲሸፍኑ ከ9 በላይ ብሄሮች ከ1 ሚሊዮን በላይ ህዝቦች አሏቸዉ፡፡  የአክሱም እና ሌሎች መንግስታት ሥልጣንን ባማከለ መልኩ ኢትዮጵያን አስተዳድረዋል፡፡  እ.ኤ.አ. በ1974 የኢትዮጵያ ግዛት በወታደራዊ መንግስት ተተካ፡፡ ወታደሩ ሃይልን በመጠቀሙ አመፅ አስከትሏል፡፡ በ1991 አ.ኤ.አ. በብሔር ላይ የተመሠረተ ፌደራዊ ስርአት መከተል ጀመረች፡፡

ይሁንና እ.ኤ.አ. ከ2016 ጀምሮ በኦሮሞ ማህበረሰብ በኩል በፌደራል መንግስት ላይ ተገቢዉ   ቦታ ይሰጥን በማለት አመጾች ተቀሠቀሡ፡፡ እንደ አንዳንድ ተንታኞች የፌደራል ሥርአቱ መገንጠልን የሚበረታታ በመሆኑ ዉጤታማ አይደለም ይላሉ፡፡

ይሁንና የፌደራል ስርዓቱ ደጋፊዎች ስርአቱ ምርጥ አማራጭ ነው ይላሉ፡፡  ትልቁ ችግር በውሳኔ አሠጣጥ ያለው የተዛባ ሁኔታ ነው ይላሉ፡፡  በተለይም በክልሎችና በማዕከላዊ መንግሥትም ቢሆን ብዛት ያላቸው ብሔሮች በበቂ ሁኔታ አልተወከሉም፡፡  የተወሠኑ ቡድኖች ሥልጣን ጠቅልለው ይዘው ነበር፡፡  የ2016 አመፅ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርን በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣን እንዲለቁ በማድረግ በጣም ጠንካራ እና አካታች ማዕከላዊ መንግስት የመመስረት ጥረት እንዲጀመር ፈር ቀዷል፡፡

በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው አዲሱ መንግስት ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወሳኝ ውሳኔዎች እና እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነዉ፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ወሳኝ ጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ አለው፡፡ የንግድ መተላለፊያ ነው፡፡  ተግዳሮቶችም አሉበት፡፡  የፅንፈኞች ትኩረት ቦታ ነው፡፡  የዉጭ ሀይሎች በጅቡቲ፣ በሱዳን፣ በሶማሊያ እየተርመሠመሠ ነው፡፡  ኢትዮጵያ ሁልጊዜ የውጭ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት ያሳስባታል፡፡ የ2016 አመጽ ጀምሮ ደግሞ ለውጭ ጣልቃ ገብነት የበለጠ ተጋላጭ አድርጓት ነበር፡፡  አሁን በአንፃራዊነት እየተረጋጋች ነዉ፡፡  አሁን ባለው ሁኔታ እራሷን ነጻ በማውጣት በቀጠናው መሪ የመሆን እድል አላት፡፡  የኢትዮጵያ መንግስት የቅርብ ጊዜያት እንቅስቃሴዎች እና የዶክተር አብይ ንግግር ማለትም ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ክብሯ ትመልሳለች የሚለው እና በአዲስ አበባ የተካሄደው የድጋፍ ሠልፍ ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ክብሯ የመመለስ ፍላጎቷን ያሣያል፡፡

ይሁንና ይላል ጂኦፖለቲካ ፊዉቸር፤ ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ክብሯ ለመመለስ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው ይላል፡፡  በመጀመሪያ ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ እና ሁለተኛ የድንበር ላይ ግጭቶችን ማስወገድ ይኖርባታል፡፡  ሦስተኛ የወደብ አማራጮችን ማስፋት ይኖርበታል፡፡  የአክሱም ስልጣኔም፣ የተመሠረተዉ እነዚህ ሦስቱን በማሟለት ነበር፡፡

ውስጣዊ መረጋጋት

ውጤታማ የውጭ ፖሊሲ አውጥቶ ከመተግበር በፊት የውስጥ ጉዳዮችን በአግባቡ ማስተናገድን ይጠይቃል፡፡  ይህ ደግሞ ሰላምንና መረጋጋትን በውስጥ አስተማማኝ ማድረግን ይጠይቃል፡፡  በመጀመሪያ በፖለቲካው መስክ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል፡፡  ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ከፍተኛ ለውጥ ካለው ከኦሮሞ ብሄር የተገኙ በመሆናቸውእና ድርጊታቸውም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ያካተቱ ከበፊቱ የተሻለ ውክልና ያለው የብሄር ፌዴራሊዝም በመገንባት ላይ ናቸዉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴርም የእስልምናና ክርስትና መሠረት ያላቸው በመሆኑ ተቀባይነታቸው ከፍ ያለ ነው፡፡  የመከላከያና የደህንነት ሀይሉን አመራሮች ቀይረዋል፡፡  የጸጥታ ሀይሏን ከመጠን በላይ ሀይል የመጠቀም ድርጊቶችን አውግዘዋል፡፡  እንደ ግንቦት 7 እና ሌሎች በስደት ላይ የነበሩ ተቃዋሚዎችን ወደሀገር ቤት እንዲገቡ ጥሪ አድርገዋል፡፡  ግጭቶችም በተፈጠሩ አካባቢዎች ላይ ያሉ የአካባቢው አመራሮች ስልጣን እንዲለቁ ጥሪ አድርገዋል፡፡  እስከ አሁን አዎንታዊ ምላሽ አግኝተዋል፡፡  ብዛት ያላቸው ተቃዋሚዎች የጦርነት አዋጃቸውን አንስተዋል፡፡  በደቡብ የአካባቢ አመራሮች ስልጠናቸውን ለቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዘረኝነትን በማውገዝ አንድትንና የጋራ ማንነትን በማጎልበት ኢትዮያዊነትን ለመገንባት እንቅስቃሴ ላይ ነች፡፡  ይህ ደግሞ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቀነስ እና ለጋራ ግብ ህዝቦቿን ለማሰለፍ ይረዳታል፡፡

ይህ በተራው ደግሞ የማዕከላዊ መንግስት አለምአቀፍ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ብሔሮች እና ሀይማኖቶች በጎን በማሠለፍ ከውጭ ተጽእኖዎች ነጻ የሆነ ውሳኔ እንዲያሣልፍ ያግዘዋል፡፡ መንግስት ኢትዮጵያዊ በታሪኩ እንዴት የግብጽና የጣሊያን ወረራን በጋራ እንደመከተ በመስበክ ዜጎች ኩራት እንዲሠማቸው በማድረግ አንድ ለማድረግ በመጣር ላይ ነው፡፡  መንግስት ይህንን የጋራ ታሪክ በማውጣት ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞ ክብር ለመመለስ እና ቢያንስ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመከላል እንደ ሁነኛ መንገድ እየተጠቀመበት ነው፡፡

በኢኮኖሚው  መስክ ያጋጠመውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመፍታት እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስቀጠል በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው፡፡

የድንበር ጸጥታ ማረጋገጥ

ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር ያላትን የፀጥታ ችግር ለማሻሻል እየሰራች ነው፡፡  ከኤርትራ ጋር የነበረባትን ችግር ለመፍታት የአልጀርሱን ስምምነት በመቀበል ለመተግበር ቁርጠኝነቷን አሳውቃለች፡፡ የድንበሩ ችግር መቃለል የወታደራዊ ወጪን በመቀነስ ሀብትን ለልማት እንዲውል ያስችላል፡፡  በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የኢንቨስተሮችን በራስ የመተማመን ስሜት ያሣድጋል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ኢትዮጵያ የአሠብ ወደብን ለመጠቀም ያስችላታል፡፡

ሶማሊያ አሁንም የበለጠ የጸጥታ ድጋፍ ከኢትዮጵያ ትፈልጋች፡፡  ኢትዮጵያ ይህንኑ ማስቀጠል ይኖርበታል፡፡

በሡማሌያዉ ድንበር በኦጋዴን የተገኘው የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ በመዘርጋት ሁለቱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚ በማድረግ የድንበር ውጥረቱን ማርገብ ያስፈልጋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ግጭትን መፍታት ለኢትዮጵያ ወሳኝ ነው፡፡ በግምት ከ400000-500000 የደቡብ ሱዳን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲሠደዱ አድርጓቸዋል፡፡

የወደብ አገልግሎት

በአለም ንግድ ለመሣተፍ ከፈለገች ኢትዮጵያ የወደብ አማራጮቿን ማስፋት ይገባታል፡፡ እ. ኤ.አ. ከ1991 ጀምሮ ኢትዮጵያ ወደብ አጥታለች፡፡  ይህ ከጂኦፖለቲክስ አኳያ ከፍተኛ ኪሣራ ነው፡፡  ወደብ በማጣቷ ለአለም ገበያ ምርቶቿን ለማቅረብ በሌሎች ሀገሮች ጥገኛ እንደትሆን አድርጓታል፡፡  ኢትዮጵያ በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ ሰላጤ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ ከፈለገች የባህር በር ወሳኝ ነው፡፡  ከዚህ በመነሣት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የወደፊት የባህር ሃይል መኖር አስፈላጊ ነው ያሉት ሚዛን የሚደፋ ሀሣብ ነው፡፡  በእርግጥ የአክሡማይት መንግስት የራሱ ባህር ሃይል መኖር ለብልጽግናው እና ለተሰሚነቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው፡፡ ለጊዜው የኢትዮጵያ ትኩረት ግን የራሷን ኢኮኖሚ ማሳደግ ነው፡፡  ከ90-95 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ኤክስፖርት በባህር ላይም በዋነኝነት በጅቡቲ ወደብ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡  በዚች ትንሽ ሀገር ላይ ከፍተኛ ሁኔታ ጥገኛ መሆን ከፍተኛ ስጋት እና አደጋ አለው፡፡  አዲስ አበባ በአካባቢው ያለው  የውጭ ሀይሎች የባህር ላይ ጦር እጅግ ያሣስባታል፡፡ አንዳንዶች ሦስተኛው የአለም ጦርነት የሚነሣ ከሆነ የሚነሣው ጅቡቲ ላይ ነው ይላሉ፡፡  ምክንያቱም በጅቡቲ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ኢራን፣ ቱርክ ፣ ሳዉዲ፣ ሩስያ ወዘተ. ወታደራዊ ሃይል አላቸው ወይንም ለማቋቋም በእቅድ ላይ ናቸው፡፡  በዚህ ዘመን ደግሞ ከተጽእኖው ማንም ነጻ ሊሆን አይችልም፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት ግሎባላይዜሽን እንደ እሳት ነው፡፡  እሳት በራሱ ጠቃሚም ጎጂም አይደለም፡፡  ጎጂነቱም ሆነ ጠቃሚነቱ የሚወሠነው እንደአጠቃቀሙ ነው፡፡  ስለዚህ ኢትዮጵያ የተለያዩ ሀገራት በጅቡቲ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በንቃት በመከታተል እና በመተንተን የራሷን ስትራቴጂ መተግበር ይገባታል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያ በተለያዩ ወደቦች የምታደርገውን የአክሲዮን ግዥዎች አጠናክራ መቀጠል ይኖርባታል፡፡ 19 በመቶ የበርበር ወደብ የአክሲዮን ግዥ የበለጠ ማሳደግ ይኖርበታል፡፡  ከቶጎጫሌ እስከ በርበር ወደብ የሚገነባዉ የ740 ኪሎሜትር መንገድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ቁርጠኝነቷን አሣይታለች፡፡  ከኬንያ ጋርም ከለቡ ወደብ ጋር የሚገናኝ የመንገድ ፕሮጀክቶች አሏት፡፡  ይሁንና ኢትዮጵያ የወደብ አገልግሎት በቀጣይነት ለማግኘት መተማመኛ ማግኘት አለበት፡፡

እነዚህ ከላይ የተገለጹት የኢትዮጵያ ማለትም በሀገር ውስጥ ሰላምን አስተማማኝ ማድረግ፣ የድንበር ችግሮችን መፍታት እና የወደብ አገልግሎት ዋስትናን የማረጋገጥ ሙከራዎች ኢትዮጵያ በቀጠናው መሪ የመሆን ፍላጎትዋን የሚያሣይ በኢኮኖሚ የመበልጸግ ፍላጎቷን ነው፡፡  ይሁንና በአፍሪካ ቀንድና በልዕለ ሀያላን አገራት መካከል እያደገ የመጣውን ፉክክር በማየትና ኢትዮጵያ ራስን ለመግለጽ እና ከሌሎች ሀገሮች ጋር ለመፎካከር ያላትን ምኞት የሚያሳዩ ናቸው፡፡  ይህን ለማሣካት ብዙ አመታትን ሊፈጅ ይችላል፡፡  ያውም የሚሣካ ከሆነ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ቀጠናው መሪ የለውም፡፡  የውጭ ተፅእኖን የሚቀንስላት ከአፍሪካ ቀንድ የወጣ ሀገርም የለም፡፡  ይሁንና ከታሪክ እንደምንረዳው እና በቅርቡ ኢትዮጵያ እያደረገች ካለው እንቅስቃሴዎች ይህንን የማድረግ አቅም ያላት ይመስላል፡፡

ምንጭ፤

Ethiopia:  A regional power in the making?—Geopolitical Futures.

 

Back to Front Page