Back to Front Page


Share This Article!
Share
ማንነትን ግሃድ ያወጡ ድርጊቶች

 

ማንነትን ግሃድ ያወጡ ድርጊቶች

ከኣሉላ የወሃንስ መቐለ 08-06-18

ደማሪው መደመር ከሚለው ስም ባሻገር ሌላ ኣያውቅም ብቻ ሳይሆን መደመርም በቅጡ የሚያውቅ ሆኖ ኣላገኘሁትም፡፡ ሰውየው ሸምድዶ የመትፋት ችሎታ ከፓስተርነቱ ልምድ የቀሰመ እንደሆነ በግልፅ የሚያሳይ ተግባር የእንደመር፣ እንፋቀር፣ ይቅር እንባባል፣ ያለፈውን ነገር ሁሉ ትተን በይቅርታ ተደምረን ኣንድ እንሁን ይላል ደማሪው፡፡

ቦድማስ ለማለት እንኳን ቦዲማስ ብሎ ሊያስተምረን ሞከረ፡፡ ቦድማስም የሚያስፈልገው ኣራቱም የሂሳብ ስሌቶች ኣንድ ላይ ሲሰሩ ተደበላልቀው ከስሌት ውጭ የሆነ ውጤት እንዳይሰጥ በጥንቃቄ በመለየትና ቅደም ተከተል ይዞ ወደ ትክክለኛ ውጤት ለመድረስ የሚያስችል እንጂ የሚፈርስ ብራኬት የለም፡፡ ብራኬት ከፈረሰ ኣንዱን ከሌላው ይደበላለቅና ያልተፈለገ ውጤት ይሰጣል፡፡ ይህ ነው ሰውየው ሂሳብ በኣግባቡ የተማሩ ለመሆናቸው የሚያጠራጥረኝ፡፡

እንግዲህ ደማሪው እንደሚለው ኣንድ ለይ እማይደመረውን ለመደመር በመመኮሩ ምክንያት በኣራቱም የሃገሪቷ ኮርነሮች ከ27 ዓመታት በተለይ ደግሞ ደማሪው በለስላሳ መፈንቅለመንግስት ስልጣን ላይ ከወጣ በሃላ ለመጀመርያ ግዜ በስፋትና በጥልቀት ዘርን የለየ ጥቃትና ትርምስ እንዲሁም መፈናቀል በስፋትም ሆነ በመmጠን እያየለ የመጣበት ሁኔታ እያየን ነው፡፡

ኦሮማራ በሚል የግዜኣዊ ሽርክና ማህበር በመመስረት ህወሓትንና የትግራይ ህዝብ ኣንገት ለማስደፋት እየተካሄደ ያለው ኣገር ሰላም ብሎ ከትግራይ ውጭ የሚኖረው ህዝባችን እያሳደዱ እንደ እባብ በድንጋይና በቆመጥ ሲገድሉት፣ ንብረቱ ሲዘርፉትና ሲያባሩሩት ተውረግራጊው ትንፍሽ ኣላለም፡፡ ኣሁንም በጣና በለስ ይሰሩ የነበሩ ዘራቸው ከትግራይ በመሆናቸው ብቻ ተቀጥቅጠው ተገድዋል ኣስቃባጩ ግና ኣሁንም ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎት ቀረ፡፡ ታድያ መደመርና ይቅርታ የሚሰራው ለተለየ ህዝብና ግለሰቦች ብቻ ነው? እንደዛ ባይሆን ከሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳደሮች በተለየ ሁኔታ የኣማራና የኦሮሞ ባለስልጣናት ተይዞ ኣገር እየተቃጠለች በኣፍሪካና በኣመሪካ ሽርሽር ባልተመረጠ ነበር፡፡ ይባስ ብሎ የነውጠኛው ኣለቃ ለሆነውና እድሜልኩ ልደት እሚባል ኣክብሮ የማያውቀው ለማ መገርሳ በሰማይ፣ በቦይንግ ላይ ልደቱን ለማክበር ያን ሁሉ ወጪ ማውጣ የማናለብኝነትና የሀገርን ሃብት ለግል ጥቅም የማዋል ኣስቃባጭ ተግባር ነው፡፡ በኣሁኑ ወቅት ግን ኣገሪቷ ለነዳጅ መግዣ ኣጥታ በብድር ከሳውዲኣረብያ በመለመን ላይ ባለበት ሁኔታ በኣገር ውስጥና ከሃገር ውጭ የቆየውን ትንሽ ሃብት ለተለያዩ ድግሶች እየዋለ መሆኑ ደግሞ እጅግ ኣሳፋሪ ያደርገዋል፡፡ የደማሪው ኣፍና ተግባር በተቃርኖ የተሞላ መሆኑ ፍንትው ኣድርጎ ያሰየ ተግባር ነው፡፡

Videos From Around The World

ህዝብን የናቀና ግለሰቦችን ያመለከ ደማሪው ኣለቃው የክልል ኣስተዳዳሪ፣ የህዝብ ለህዝብ ውይይት የመንደር ሽምግልና ብሎ መወረፍ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ኦነግነቱን በተግባር ያስመሰከረ

በሚኒሶታ ግዛት ኦሮሞ ወሳኝና ተከታይ ኣምሓራ መሆኑ በግላጭ መናገሩ ተጨባጭ ምስክር ነው፡፡ ኦነግም እስከነ ታጣቂዎቹ ወደ ሃገር እንዲገቡ በመፍቀድ የሽብር ተግባራቱን በማካሄድ የራሱን ግዛት ሙሉ በወለጋና በተለያዩ ኣካባቢዎች ግዛቱንእያስፋፋ ባለበት ወቅት መልካም ፍቃደኝነቱን ባርኮለታል፡፡ ታድያ የኣይጥ ምስክር ድንቢጥ እንዲሉ ዋሪ ኣባፊጣ የተባለው ሰው በዓይጋ ፎሩም እንደፃፈው አንድነትና ኢትጵያዊነት እየተዘመረ ባለባት ሀገር ውስጥ የብሔርም ይሁን የሃይማኖት ግጭት ሊኖር እንደማይችል መገንዘብ ተገቢ ይመስለኛል ይለናል።ስለጥቅም የእነዚህ ድብቅ ሴራዎችና ከንቱ ጥረቶች ተዋንያን ጥቅማቸው የተነካባቸው አንዳንድ አካላት መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰነባብቷል ይለናል።ስልጣን ለማግኘት የሚደረግ መሯሯጥ ወይንስ ሁኔታውን ያላገናዘበ የተዛባ ኣስተያየት፡፡

በመቀጠል ዋሪ ኣባፊጣ አገሪቱ የምትመራባቸው መሠረታዊ መርሆዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች የሚመነጩት የኢትዮጵያ ህዝቦች ፍላጎቶች ለማሟላት በመሆኑ እያንዳንዱ የመንግስት እንቅስቃሴ ከዚህ አኳያ የሚታይ ነው። የመንግሥት ሥልጣን፣ መንግሥት የሚያራምዳቸው እምነቶች፣ የሚከተላቸው መርሆዎችና ፖሊሲዎች ምንጭ የኢትዮጵያ ህዝቦች ናቸው። መንግሥት በተለይ ካለፉት አራት ወራት ወዲህ ይህን እውነታ ለማሳካት ተንቀሳቅሷል ይለናል ከህገመንግስት በተፃራሪና ያለምንም የህዝብ ምክክር የተለያዩ ፖሊሲዎችና የህግ ሽረቶች እያካሄደ በለበት ወቅት። በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ውስጥ የእምነት ነፃነትና የሃይማኖት እኩልነት ተረጋግጧል። መንግስትና ሃይማኖትም ተለያይተዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግለሰቦች የራሳቸውን የእምነት ነፃነት ለማስከበር በማሰብ የእኔ እምነት ትክክል ስለሆነ እኔን ብቻ ተከተለኝ በማለት ማስገደድ እይችሉም። ምክንያቱም ሌላውም ዜጋ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ያሻውን እምነት መያዝ ስለሚችል ነው ይለናል ዋሪ ይህንን ነገር በዚሁ ኣራት ወራት ብቻ እንደተፈጠረ ለማሳየት በመጣር ላለፉት 27 ዓመታተ ሰፍኖ የኖረው ሃቅ፡፡ እንድያውም በኣሁኑ ወቅት መንግስት ተብየው በሃይማኖት እጁ እየስገባና እያስፈራራ እኔ በምፈልገው ሂዱ እያለ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ተደርጎ የማያውቀውን የኣንድ ብቻ የኦርቶደክስ ፓትርያክ ሁለታችሁም ታስተዳድራላችሁ ካልሆነ በገዛሃገሩ በሲኖደስ የተመረጠውን ፓትርያርክ ወርዶ በኣሜሪካን ሃገር ኣለሙን እያየ የነበረውና የደርግ ካድረ በመሆኑ ብቻ ደርግ ሲወድቅ ሸሽቶ ወደኣሜሪካን የገባው ራሱን በውጭ ሃገር የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብሎ የሾመ ይሆናል በማለት ኣሳፋሪ ታሪክ የፈጠረው ሰባኪው መሆኑን የኣደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ።

ከዚህ ባሻገር በተለያዩ የኣሜሪካ ግዛቶች ከኢትዮጵያውያን ጋር ለመወያየት ብሎ ኣገሪቷ ያላትን ሃብት ኣሟጥጦ ሲበትንና ሲያጠፋ ለዚሁ ሰብሰባ የሚቀርቡና መልስምM የሚሰጣቸው በብሄራቸው መሆኑ ያሳየ ለመሆኑ ኣሉላ መጀመርያ እንዳይገባ ለመከልከል መመኮሩ፣ በስንት ጉድ ከገባ በሁዋላም ኣንድን እድል እንዳያገኝ በየፈደርጉ የኢሰፓ ካድረ ክብረት መነፈጉ፣ ሳይታወቁ እድል ኣግኝተው ጥያቄ ላቀረቡትም ይህ ጥያቄ የማን እንደሆነ ኣውቀዋሎህ፣ ሌላ ግዜ በስፋት እመልሰዋሎህና ኣሁን ልዝለለው፣ ኣሁን ያለው የመንግስት ስርዓት ምን ይባላል ዲሞክራሲያዊ ስርኣት ኣሁን ኣለ ወይ ተብሎ ለተጠየቀው ሲመልስ ጋዳ ከማንም ዓትነት ዲሞክራሲያዊ ስርዓቶች የላቀ እንደሆነ በግላጭ ነገረን ጋዳ ግን የጋርዮሽና በዛን ግዜ ለነበረው የኣስተዳደር ዘይቤ የሚመጥን እንጂ ኣይደለም ሊበልጥ

ከዘመናዊው ስርኣት ጋር ለውድድር የሚቀርብ ኣይደለም፡፡ ይም ሆነ ይህ ኣሁን እያየን ያለነው የታላቅዋን ኢትዮጵያ ሳይሆን የታላቅዋ ኦሮምያ ምስረታና መስፋፋት፣ በሁም የኦኖግ ሚድያዎች፣ የኦኖግ ኣቀንቃኞችና የኦነግ ባንዴራ ከኦሮምያ ክልለሎች ኣልፎ እስከሚለንየም ኣዳራሽ መውለብለቡ ብቻ ሳይሆን ኣሁንም በከፍተኛ የዘር መርዝ በመርጨት ላይ ለነበረው ጁሃርም በዚች ምስኪን ሃገር ገንዘብ ከፍተኛ ገንዘብ የፈሰሰበት ድግስ በቀጥታ ስርጭት የቴሌቪዥን ሽፋን ተሰጥቶት በኦነጋውያን ለማና ደማሪው ከፍተኛ ኣቀባበልና ምጎሳ ተደርጎለታል፡፡ ታድያ መደመር ለኦነጋውያን ወይንስ ለኢትዮጵያ ህዝብ

ታድያ በዚህና በዝያ እየተንሸራሸሩና ኣሸሼው ገዳሜ ማለታቸው ሳያንስ የፍቅርና ይቅርታ ሰባኪው ለሃገሩ እድገትና ብልፅግና ለ7 ዓመታት በሃሩር የተጠበሰና ከቤተሰቡ ተለይቶ የኖረውን የቁርጥ ቀን ልጅ ለሆነው እንጅነር ስመኘው ለመግደል ከግብፅ ለተሰጠው ግዳጅ በሚገባ ያሳካ፣ ባለቤቱም እስከኣሁን የት እንዳጠፋት በማይታወቅ የጀግናው ልጆችን ጎዳና ላይ ያስቀረ፣ በቀብሩ እለት በጠራራ ፀሃይ ቤቱ እንዲቦረቦርና እንዲዘረፍ ያደረገ ዲያብሎስ ከመሆን ኣልፎ በየተኛው መመዘኛ ነው ነብዪ የሚያደርገው፡፡ ረጋና ሰከን ብሎ ማሰብና ያለበትን ሁኔታ ኣመዛዝኖ ተገቢ መንገድ መያዝ እጅጉ የሚያዋጣ ይመስለኛል፡፡ ነገሮችን በሆይሆይ ኣልፈነው ከሄድን ግና ከደርጉ የባሰ መበላላት ይመጣና ወይኔ ብሎ መመለስ ወደማይቻልበት ሁኔታ መግባታችን ኣይቀሬ ነውና ደማሪው እየደመረ ሳይሆን በታሪካዊ ጠላቶቻችን የተሰጠውን ሃገሪቷን የማፈራረስ ዳጅ እየፈፀመ ስለሆነ ኣደብ ግዛ ሊባል ይገባል፡፡

Back to Front Page