Back to Front Page


Share This Article!
Share
ለውጡን ቀጣይነት ያለው ለማድረግ

ለውጡን ቀጣይነት ያለው ለማድረግ

በስንታየሁ ግርማ 07-31-18

በዶ/ር አብይ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚመራው የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደቶች ሀገራዊና አለም አቀፋዊ እውቅና እየተቸራቸው ነው፡፡ አንዳንዶች እንደውም ኢትዮጵያ በአክሱም ዘመን ያላትን ተሰሚነት የመመለስ እድል አላት እያሉ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማለትም በሀገር ውስጥ እየታዩ ያሉ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች ከጎረቤት አገራት ጋር ያሉ የድንበር ግጭቶችን መፍታት እና የወደብ አማራጮችን ማስፋት፤ የኢትዮጵያን ተሰሚነት የሚመልሱ እንደሆኑ እንደማረጋገጫዎችን እየቀረቡ ነው፡፡

እንደውም ወርልድ ፖለቲክስ ሪቪው የጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ የአሜሪካ ጉብኝት እስካሁን ወደ ዳር የተዋትን አፍሪካ ፕሬዝደንት ትራምፕ ትርጉም ያለው ትርጉም ያለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመጀመር ያስችላታል ይላል፡፡ በአጠቃላይ ለውጡ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ከፍተኛ ተስፋ የሰነቀ ቢሆንም ለቀጣይነቱና በሚከተሉት ላይ ትኩረት ቢሰጥ ጥሩ ነው፡፡

የለውጡ ዋነኛ ሀይሎች ወጣቶች ናቸው፡፡ ወጣቶች በለውጡ ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ ዘ ኢኮኖሚስት እንደሚለው ከሆነ የአፍሪካ ወጣቶች ሦስት ነገሮችን ይፈልጋሉ፡፡ ነጻነት፣ ትምህርት እና የስራ እድል፡፡ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ አለም አቀፍ እውቅና የተቸረውን እድገት ብታስመዘግብም አሁን 20 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት ወለል ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ አብዛኛው ወጣት ነው፡፡ ይህንን ወጣት የስራ እድል እንዲፈጠርለት ማድረግ እና ሌላውም ነገ ስራ እንዲያገኝ ተስፋው የለመለመ እንዲሆን ማስቻል ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ስራ የለውጡ ደጋፊ የሆነ ሀይል ከአመት በኋላ የለውጡ ተቃዋሚ መሆኑ አይቀርም፡፡ በተለይም በአሁኑ ሰኣት ጫት በመቃም የሚያሳልፈው ወጣት ነገ ወደ አደንዛዥ እጽ ከዚያም ወደ ተደራጀ የወንጀል ቡድን በመግባት የሀገሪቱን እጣፈንታ እንዳያጨልም መስራት ይገባል፡፡ ከስራ እድል በተጨማሪ በጫትና በመሳሰሉት ላይ ከፍተኛ ታክስ (Sin Tax) መጣል ይገባል፡፡ ጫት የሚሸጥባቸውም ሆነ የሚቃምባቸው ቦታዎች ተለይተው መከለል አለባቸው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለው የዛሬ ወጣቶችህን መዋያ ንገረኝና የነገን የሀገሪቱን እጣ ፈንታ ልንገርህ ይላል፡፡

Videos From Around The World

በሁለተኛ ደረጃ ለውጡን በተመለከተ ከግሎባላይዜሽን (ሉዓላዊነት) ጋር አስተሳስሮ ማየት እና መምራትን ይጠይቃል፡፡ አሁን ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን በኢትዮጵያ የሚካሄደው ለውጥ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ የሚነካቸው አገራት ይኖራሉ፡፡ አሁንም አለም በምርትና ገበያ በጥብቅ ተሳሰረች በመሆኗ የአሜሪካ ገበያ ምርት የሚባል ነገር የለም፡፡ የአለም ገበያ የአለም ምርት ነው ይላሉ፡፡ አባባሉ ከግሎባላይዜሽን ውጪ መሆን አይቻልም ማለት ነው፡፡ ቦይንግ 777ን በመጥቀስ ያስረዳሉ፡፡ ቦይንግ 777 ከ132ሺህ500 በላይ ክፍሎች ያሉት ሲሆን በ7 አገራት ከ500 በላይ አቅራቢዎች ይመረታል፡፡ እያንዳንዱ አገር እንደ አንጻራዊ ምርጫ /Comparative Advantage/ በማምረትና በመሸጥ የራሱን ድርሻ ይወስዳል፡፡

ስለዚህ ቦይንግ ብራንዱ የአሜሪካ ቢሆንም የአሜሪካ ምርት ሳይሆን የአለም ምርት መባል አለበት ብለው ይሞግታሉ፡፡ በአጠቃላይ ቴሌ (ኢንተርኔት) ግሎባል ገበያና ግሎባል አድማጭ ተመልካችን ሲፈጥር ትራንስፖርት ግሎባል መንደርን ፈጥሯል ይላሉ፡፡

ይህም በግሎባላይዜሽን ሁሌም በተዋሃዱት መጠን ተጠቃሚ ቢሆንም ግሎባላይዜሽን ሽኩቻንና ግጭቶችን አላስቀረም፡፡ አሁን አለም ከአንድ ዋልታ ወደ ብዙ ዋልታዎች እየተቀየረች ነው፡፡ በዚህ ባለብዙ ዋልታዎች ደግሞ አሰላለፋችሁ ከኔ ጋር ይሁን የሚለው ብዙ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ይህንን በጥበብ ማየትና ማስተናገድ ይገባታል፡፡ ሳሙኤል ሀንግቲንግተን እንደሚለው ከሆነ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ በአለም ላይ የሚነሳው ግጭት በዋነኝነት በአይዲኦሎጂ ሳይሆን በስልጣኔ ላይ የተመሰረተ ነው ይላል፡፡ በአለም ላይ የነበሩ ሰባት ወይም ስምንት ስልጣኔዎች እርስ በርሳቸው ፉክክርና ሸኩቻ ያደርጋሉ ይላል፤ እነሱም፤

  የቻይና ስልጣኔ ቪየትናምንና ኮሪያን ጨምሮ

  ከሌሎቹ ኤስያ የሚለየው የቻይና ስልጣኔ

  የህንድ የሂንዱ ስልጣኔ

  እስልምና ስልጣኔ (የአረብ ቬንዙላ ሰሜን አፍሪካ፣ አረብ ቬንሱላ እና መካከለኛውን ኤሲያን ይይዛል፡፡ የአረብ ቱርክ ፐርሺያንና እና ማሌዢያን ይጨምራል)

  የምዕራብ ስልጣኔ ( አውሮፓንና ሰሜን አሜሪካን ይይዛል)

  የሩሲያ ኦርቶዶክስ ስልጣኔ

  የላቲን አሜሪካ

የአፍሪካ ስልጣኔ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ስልጣኔ ሀንቲንግተን እንደሚለው በእነዚህ ስልጣኔዎች መካከል ያለ ግጭትና ፍጭት በአግባቡ ካልተስተናገደ ከፍተኛ ውድመትን ያስከትላሉ፡፡ አንዱ የሌላኛውን ስልጣኔ ለማጥፋት የሚያደርገው ድርጊት ከባድ ውድመትን ያስከትላል፡፡ ምክንያቱም ከስልጣኔ ጋር የሚደረጉ ግጭቶች ከማንነት ጋር የሚያያዙ በመሆናቸው በቀላሉ ሊታረቁ አይችሉም፡፡ አሁን ባለብዙ ዋልታዎች ኢትዮጵያ ከእያንዳንዱ ጋር በመወገን ሌላውን እንዲያገሉ የመፈለግ ሁኔታ ይታያል፡፡ ከኤርትራ ጋር ያደረግነውን ስምምነት እንኳን አንዳንዶች ጅቡቲን አንዳንዶች ኬንያን ይጎዳል የሚሉ አሉ፡፡ Middle Monitor የተባለ ድረ ገጽ "Ethiopian prime minister to UAEs crown prince" "you have lost them" በሚል ርዕስ ባወጣው መጣጥፍ ኢትዮጵያ በ2017 ኳታርን ከአለም ለማግለል አልተባበረችም፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ዱባይ የተጫወተችውን ሚና እውቅና አልሰጠችም እና ሌሎች ወቀሳዎችም የያዘ ዘገባ አቅርቧል፡፡ ቀጠናው የአለም መፋለሚያ ሆኗል፡፡ አንዳንዶች 3ኛው የአለም ጦርነት የሚነሳ ከሆነ በጅቡቲ ላይ ነው ይላሉ፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ዋነኛው አላማ ብሄራዊ ጥቅሟን ማስጠበቅ እንጂ ማንንም ማስደሰት ማስከፋ አለመሆኑን በአግባቡ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ አለም አቀፍ ልምድ እና ሰፊ መረብ ያላቸው አለም አቀፍ የህዝብ ግንኙነት በአማካሪነት መጠቀም የሚለው ይመስላል፡፡

ከረጅም ጊዜ አኳያ ማህበራዊ ካፒታል /Social Capital/ መገንባትና ማበልጸግ ወሳኝ ነው፡፡ ሮበርት ፑትማን እንደሚለው ዴሞክራሲ ሊበለጽግ የሚችለው በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ አደረጃጀቶች ማለትም ክለቦች፣ ማህበራት፣ የነጻ አገልግሎቶችና ሀይማኖታዊ ቁርኝቶች ወዘተ. መሳሰሉት ግለሰቦችን የሚያስተሳስሩ መተማመንን የሚፈጥሩ ሰጥቶ መቀበል የመሳሰሉት ማህበራዊ እሴቶች ለሀገር ብልጽግና ወሳኝ ናቸው፡፡ ሀገርን የሚያበለጽጉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ለምሳሌ እንደ ህዳሴው ግድብ የመሳሰሉ ፕሮጀክቶች በራሳቸው ደግሞ ማህበራዊ ካፒታልን ያፋፋሉ፡፡ ኢትዮጵያም የሚጠቅማትን ማህበራዊ ካፒታል ያሳድጋል፡፡

ፀሀፊው ከአ/አ ዪኒቨርሲቲ በማስተርስ የህዝብ ግንኙነት እና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ተመራቂ ሲሆን በ1986ከአ/አ ዪኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡

 

Back to Front Page