Back to Front Page


Share This Article!
Share
በጠራራ ፀሐይ በአደባባይ ሰው ቁልቁል ስቅሎ የሚገድሉ ቄሮዎች፣መኪና አቁም የሚዘርፉ ፣የንግድ ተቋም የሚያቃጥሉ ፍኖዎች፣እንዴት ለውጥ ያመጣሉ፣ ስላም ያስፍናሉ፣ አገር ይገነባሉ?

በጠራራ ፀሐይ በአደባባይ ሰው ቁልቁል ስቅሎ የሚገድሉ ቄሮዎች፣መኪና አቁም የሚዘርፉ ፣የንግድ ተቋም የሚያቃጥሉ ፍኖዎች፣እንዴት ለውጥ ያመጣሉ፣ ስላም ያስፍናሉ፣ አገር ይገነባሉ?

ጸሐፊ፣ ልኡል ገብረመድህን (ከአሜሪካ)

ነሐሴ 16/2010።

የስው አብይ ጠላቱ አስተሳሰቡ ነው።በሚያስበው ልክም ያድጋል፣ይለወጣል፣ይወድቃል፣ይነሳል፣ይኖራል፣በመጨረሻም ይሞታል ።ከዚህ ሂደት ውጭ ሰው ሌላ ታሪክ የለውም።የአንድ አገር የማህበረ-ኢኮኖሚ እድገት መሰረቱ ሌላ ሳይሆን የአስተሳሰብ ለውጥ ነው።አስተሳሰብ ስው ይጎዳል፣አገር ያጠፋል።አስተሳሰብዜጋ ይገነባል፣አገር ያሳድጋል። በአጭሩ የሀሳብ አጠቃቀም ስበት( Utilization of ideological philosophy)እንደየአጥቃቀማችን ይወስናል።ሰው ለመግደል ከፈጣሪ ወይም ከመንግስት ፍቃድ አያስፈልግም።ፍቃድ ስጪና ከልካይ  ለመግደል ባቀደ ሰው እዕምሮ ላይ ነው። የአስተዳደር በደል ለመፈፀም ህዝብ ማስትአይልቁም፣አይበልጡም።ማህበረስብ የስዎች ስብስብ በመሆኑ ማህበራዊ ጥቅሞችና ጉዳቶች በጋራ የመጋራት ባህልና አመክንዮ ያዳብራል።በጊዜ ርቀት ላካበታቸው እሴቶች (Norms)ልዩ ትኩረት ይስጣል፣ከትውልድ ትውልድ እንዲሻጋገሩም ልዩ ልዩ አስተምህሮዎች ይጠቀማል።በእብሮነት መኖር እሳቤ ውስጥ ፍትሀዊነት ይኖራል ።አስፈላጊነቱም አንዱን ሌላውን ያለአግባብ እንዳይጫነው ለመከላከል ነው። ሁሉም እንደየእኗኗሩና ባህሉ በነፃነት እንዲኖር ለመኖር የሚያገለግሉት የፍላጎት ማሳኪያ መርሆች መካከልነፃነትንና ፍትህን ከሚኖርበት የኑሮ ዘይቤ ጋር አዋድዶና አቀናጅቶ ለመኖር በጋራ መሪውን (አስተዳዳሪውን) ይስይማል። የማህበረስቡ(የማህበራዊ)መሪውም የማህበረስቡ አገልጋይ (public servant)ተብሎ ይስየማል። የማህበረስቡ መሪ(መሪዎች) ማህበረስቡ በጋራ የተስማማበት መርህ ያስፈፅማል(ያስፈፅማሉ)።መሪ የማህበረስቡ በህግጋት ሲጥስ ማህበራዊ ቀውስ (Social discomfort& discontent)ይፈጠራል ።ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች መነሻቸው ማህበረስብ አይደለም። የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መነሻ የፍትሀዊነትና ነፃነት መጓደል ነው።ስለዚህ መሪዎች የማህብፕራዊ ቀውስ ምክንያት ናቸው።

Videos From Around The World

     በአለም ላይ የማህበራዊ ትስስር ከዳበሩባቸው አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ ናት። የበርካታብርቅዬ ብሄረሰቦች ባለቤት የሆነች ኢትዮጵያ ያላትን ውስጣዊ ማህበራዊ ፅጋ በአግባቡ ሳትጠቀምበት ጊዜ እየመሽባት፣ዘመን እየናጣትትገኛለች ።ፓለቲካ ቀንደኛ ችግሯ ነው።ይህ ችግር ሲንከባለል የመጣ ችግር ነው።ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም ያልነበረ አዲስ ማህበራዊ ባህል በኢትዮጵያ እየታየ ነው።የዳበረ ማህበራዊ ትስስር የነበረው ህዝብ በመቃቃር ላይ ነው። እኔ በግሌ ማህብረስብ ከማህበረስብ ወይም ህዝብ ከህዝብ የሚያጋጭና የሚያነቋቁር፣ የሚያቀጣጥል ወላፈን ከየት መጣ እያልኩኝ እራሴን ዘውትር እጠይቃለሁ። የአንድ ዘር ወይም ብሄር በአንድ ሌላ ማህበረሰብ ክልል ወይምከተማ ዝቅ ሲልም መንደር ለዘመናት ባዳበረው ማህበራዊ የባህል አምዱ ጠብቆ መኖር እየተሳነው፣አዲሱ ትውልድም ግራ በመጋባት ላይ ይገኛል።በተለይ ባለፉት 30 አመታት የመጣኢትዮጵያዊ ትውልድ የምህበራዊ መቀዛቀዝ ዋዜማ ላይ ይገኛል። የጥላቻ መርዝ አየተጋቱ ያደገ ትውልድ ማህበረስበአዊ ትስስር ለማጎልበት ጊዜ ያስፈልገዋል።የዛ ዘርና ብሄር ሲገዛህ ነበር ተብሎ እንደታሪ ለትውልድ አይተለፍም። ሲቀጥል ደግሞ ሲጨቁንህ ነበር የሚለው ሲታከልበት ጉዳዩ  በደንባራ ፈረስ ቃጭል ተጨምሮበት ይሆናል።ብዙ የሚበጅ የትውልድ ሽግግር ፀጋ እያለን የማይረባ ትውልድ የሚጎዳ ዲቃላ አስተሳሰብ እየስበክን ቁልቁል የሚመትር ትውልድ በኢትዮጵያ እየተፈጠረ ነው። የአንዱ ዘር ወይም ብሄር ጥቃት የሌላው ዘር ጉዳት መሆኑ መታስብ ነበረበት።የሱማሌ ማህበረሰብ ከኦሮሞ ማህበረስብ ምን ያጋጨዋል? የሲዳማ ህብረተስብ ከወንድሙ የወላይታ ህዝብ ጋር ለምን ችግር ውስጥ ይገባል? የአማራ ህዝብ ለምን ከወንድሙ የትግራይ ህዝብ ጋር ይላተማል?። በአንድ ክልል የተለያዩ ብሄረስቦች ቢኖሩና ቢስፍሩ የሚጎዳው ማን ነው የሚጠቀመውስ?። የኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ትስስሮች የሚያላሉ ችግር የፓለቲካ አስተሳስባችን ድክመት የፈጠራቸው ደንቃራ ምክንያቶች ናቸው።

በኢትዮጵያ አንድ የፓለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረስብ ለመገንባት እንሰራለን የሚሉን የኢትዮጵያ መሪዎች አስራራቸው ከአነጋገራቸው ጋር ሲመዛዘን ጉዳዩ ውስጠ ወይራ ነው።ዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት እየስበክን እንዴት አንድ የፓለቲካ ማህበረሰብ መስራት ይቻላል።የአገር መገለጫ ክብር በሆነው ሰንደቅዓላማ (ባንዴራ)የጋራ መግባባትና ተቀባይነት በሌላበት አገር እንዴት አንድ የፓለቲካ ማህበረስብ ማስብ ይቻላል? ። የዝር ፓለቲካ በተስፋፋበት አገር እንዴት አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ እንዲኖር ማቀድ ይቻላል? ።በስብአዊ መብት አያያዝና በዲሞክራሲ ያልዳበረበት አገር ላይ እንዴት የፓለቲካ መስከን ሊስፍን ይችላል? ። ባለፉት 27 አመታት የተመዘገበ የኢኮኖሚ እድገት ቢኖርም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖር ማህበረሰብ የጠቀመ እድገት አልነበረም። በዚህ ላይ የመንግስት ብልሹ አስራር ተጨምሮበት ህዝብ በመንግስት ላይ ማመፅ ጀመረ። ከምርጫ 97 ጀምሮ መንግስት የከረሩ ህጎችና ደንቦች በማፀደቁ የህዝቡን መሬትና ቁጣ ቢጨምር እንጂ አልቀነሰም። በኦሮሚያ ክልል የቀስቀስ ህዝባዊ አመፅ መነሻ የኢኮኖሚ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነበር። መንግስትም ለተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች በአግባቡ ፈትሾ ተገቢው መልስ ከመስስጠት ይልቅ ድርጅታዊ ጥልቅ ተሀድሶ ላይ ነኝ በማለት ሳይጠልቅ፣ሳይታደስ የኦሮሞ ወጣቶች (ቄሮዎች) እንዲሁም የአማራ ወጣቶች (ፋኖዎች) ተቀራራቢ የአመፅ እቅድ በመንደፍ ለለውጥ ተነሱ። ህዝባዊ አመፁም መንገዶች በመዝጋት ፣ንፁሀን ሰዎች በመግደል፣የመንግስትና የግለሰብ ንብረት በማቃጠል፣ እንዲሁም የተለያዩ አሻጥሮች በመጠቀም መንግስት ማዳከሙን ቀጠለ ። የቄሮና የፋኖ የለውጥ ጥያቄዎች ህዝቡ በመልካምነቱ የተቀበለው ሳለ ህግ አልባ ተግባሮች እየተፈፀሙ በመሆናቸው ህዝብ ቁጣውን በማስተጋባት ላይ ይገኛል ።ቄሮዎችበመንጋ ተስባስቦ ሰውን የሚያህል ክቡር በሻሽመኔ በቀን አደባባይ ላይ ስቅሎ በመግደላቸው የአለም ህዝብ ያስደመመ አሳፋሪና አስደንጋጭ ክስተት ሆነዋል ።ይህ አስደንጋጭ የቆሮዎች ተግባር በኢትዮጵያውያን ተኮንነዋል።በመንጋ እየተመሩ፣ሰው በአደባባይ እየገደሉ፣የህዝብና የአገር ሀብትና ንብረት እያወደሙ እንዴት ለውጥ ይመጣል? ።ፋኖዎችም ምንም እንኳን እንደ ቄሮዎች በጠራራ ፀሀይ ሰው በአደባባይ ስቅሎ ባይገድሉም የግለስብ ሆቴል በቃጠሎ አውድመዋል።ይህ ተግባር ከለውጥ ፈላጊ ሀይል የሚጠበቅ አልነበረም።ሰው ጥሮ ግሮ ያፈራው ንብረት በማን አለብኝነት በእሳት ማጋየት ምን የሚሉት ለውጥ ነው።ለውጥና መብት ማስከበር እንዴት ሰው ከመግደል ጋር ይገናኛል?። ለውጥ መፈለግ ስርአት አልባ ተግባሮች መፈፀም ማለት አልነበረም፣አይሆንምም።የለውጥ ጥያቄ መነሻ ያደረጉ ህግ አልባ ወንጀሎች መቆም ይኖርባቸዋል ።ለውጥ ስንሻ የሌላውም መብት ሳንረግጥ መሆን አለበት።በለውጥ ሰበብ ሰው መግደል፣ዘር ቆጥሮ ህዝብ ማፈናቀል፣ የግለሰብ ንብረት መዝረፍና ማውደም የለውጥ መስረትና እሳቤ የሌላቸው ንፁህ የውንብድና ተግባሮች በመሆናቸው መንግስት በቄሮና ፋኖ ስም ተደራጅቶ ወንጀል የሚፈፅሙ መንጋዎች ለፍርድ ማቅረብ አለበት።መንግስት ከተለያዩ ክልሎች ከመኖሪያቸውና ስራቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ነበሩበት ቦታና ሰፍራ እንዲመለሱ መንግስታዊ ድጋፍ ማድረግ ይኖርበታል ።በመንጋ ሰውን መግደል ወንጀል ብቻ ሳይሆን የኋላ ቀርነት (ያለመስልጠን) ምልክት ጭምር ነው።በዚህ ክፍለ ዘመን ሰውን በአደባባይ ስቅሎ አስቃይቶ መግደል በስው ፉጡራን ይፈፀማል ተብሎ የሚታስብ አልነበረም። ቄሮዎችና ፋኖዎች የሚፈፅሙት አሳፋሪና አስቃቂ ተግባራት በኢትዮጵያ አየታየ ያለው ለውጥ በጥርጣሬ እንድናየው አድርጎናል።መንግስትም በቄሮዎችና ፋኖዎች ለሚፈፀሙ ከፍተኛ የወንጀል ጥሰቶች ተገቢ ትኩረትና የእርምት እርምጃዎች አልወስደም።ነፃነት ማለት በመንጋ ተሰባስቦ የስው ህይወት መቅጠፍ፣ የግለሰብ ሀብትና ንብረት ማጥፋት ከሆነ ነፃነት ሳይሆን ባርነትና ጠባብነት ነው። በዚህ መንገድና ሁኔታም ተፈላጊው ሰላማዊ ለውጥ ፈፅሞ አይመጣም፣አይሳካም።

 

 

 

 

 

Back to Front Page