Back to Front Page


Share This Article!
Share
ኢትዮጵያ በመበተን ኣፋፍ ላይ?

ኢትዮጵያ በመበተን ኣፋፍ ላይ?

ገብረ ሥላሴ ኣርኣያ

ሰኔ 2010 ዓ/ም

 

ኢትዮጵያን ካልበተናት ለኤርትራ ህልውናም ሆነ ዘላቂ ሰላም ትልቅ ፈተና ሆና ትቀጥላለች የሚለውን የኢሳያስ ኣፈወርቂ መንግስት ህልም እየተሳካ ይመስላል። ያውም ኢትዮጵያውያንን ተጠቅሞ። በቅርቡ ኣዲስ ኣበባ ኣቀባበል የተደረገለት እና ቤተ ኢስራኤሎችን (ፈላሻ) በገንዘብ በመሸጥ የሚታወቀው የደርጉ ሚኒስትር ካሣ ከበደ እንደሚለው ኢሳያስ ኣፈወርቂ በኢትዮጵያ ኣንድነት የማይደራደር ሰው ሳይሆን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያንን ኣባልቶ ሳይበትነን ተኝቶ እንደማያድር በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ኣሁን እያሳየ ያለውን ሰላምን በክፊል የመቀብል ሁኔታ የኣጭር ጊዜ ስልቱን ለማስፈጸም እንዲጠቅመው ከሚል እሳቤ ነው። ከገባበት የኢኮኖሚ ኣጣብቂኝ ለመውጣት ሲል ትግራይን ዘሎ ከኣዲስ ኣበባ ጋር ግንኙነት ማድረግ ኣዋጪ ሆኖ ኣግኝቶታል። እሱም ቢሆን ግን የኢትዮጵያ ሁኔታ እስኪለይለት ድረስ የሰላም ድርድሩ ትንሽ ያዝ ማድረግ እንደመረጠ ኣንዳንድ ታማኝ ምንጮች እየገለጹ ነው። የረጅም ጊዜ እቅዱ ግን ከላይ እንደተጠቀሰው ኢትዮጵያን ኣፍርሶ በኤርትራ ትእዛዝ የሚነዱ እና የሚበዘበዙ ብዙ ትንንሽ ኣገሮችን በኣፍሪካው ቀንድ መፈጠር ነው።

Videos From Around The World

ነገር ግን እሱ ምን ያድርግ?! ስለ ኣገር ኣንድነት እየዘመሩ ኣገርን የሚሸጡ የውስጥ ደላሎች እንደ ኣሸን በፈሉበት ሁኔታ ከድሮውም ቢሆን ጠላትነቱ ያወጅበንን ኢሳያስን መውቀስ ተገቢ ላይሆን ይችላል። ልብ ብሎ ለተመለከተ ጉዳዩ ግልፅ ነው። የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ፈሊጥ እየተከሄዳ ያለው የፖለቲካ ሽርሙጥና እና በቀል ለማንም ኣይበጅም ብቻ ሳይሆን ኣገሪቱን ወደ ታሪክ ኣመድ ሊቀይራት እንደሚችል መገንዘብ ኣስፈላጊ ነው። ህወሓትም ሆነ በጠላትነት የፈረጁት የትግራይ ህዝብ የሰራው ሃጢያት ካለ ኣንድ ብቻ ነው። መቶ ኣመት ኢትዮጵያን የብሄረሰቦች እስርቤት ኣድርጎ፣ ዘርፎ፣ ጨፍጭፎ፣ ኣስርቦ፣ የህዝቦች ስብእና ክዶ ኣገሪቱን እና ህዝቦችዋ በኣለም ፊት ኣዋርዶ ኣንገታችንን ያስደፋው ደም መጣጩ የኣማራው ገዢ መደብን ላይመለስ ጠራርጎ ወደ ታሪክ ቆሻሻ ለመጣል በተደርገው የህዝቦች መራራ ትግል (ጭቁኑ የኣማራ ገበሬም ጭምር) የትግራይ ህዝብና ህወሓት የኣንበሳ ድርሻ እንደ ነበራቸው የሚያከራክር ኣይደለም። በዚህ ምክንያት የትግራይን ህዝብ ሆነ ህወሓትን ከምድረ ገፅ ሳይጠፉ እንቅልፍ ሊወስዳቸው ኣይችልም።

እነዚህ ራሳቸው በዳይ ግን ቂም ቋጣሪ ሃይሎች ብኣ... ከለላ ኣድርገው ኢህኣዴግ ውስጥ በመግባትና ራሳቸውን ደብቀው የቆዩ ሲሆኑ ኣሁን በግልጽ ወደ ኣደባባይ ወጥተዋል። በቅርቡ በባህርዳር የተመሰረተው የኣማራ ብሄር ንቅናቄ (ኣ.ብ.ን) ባለፉት ኣመታት ብኣዴን ሰርስሮ በመግባት ድርጅቱን በቁጥጥሩ ያደርገ የነገዱ ኣንዳርጋቸው ቡዱን እንደሆነ ለማንም ሰው ግልፅ ነው። እነዚህ ዘረኞችና ጸረ ህዝብ ባለፉት ጥቂት ኣመታት በትግራይ ተወላጆች እና ህገ መንግስታዊ መብቱን በጠየቀው የቅማንት ህዝብ ላይ ጥይት ሲያዘንቡ የነበሩ እና ብዙ ሂወት ያስቀጠፉ የዘመኑ ኣዲስ ፋሺሽቶች እንደሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ሰሞኑ በሚታየው ግርግር ሰክረው ድል ያደረጉ መስሎዋቸው ራሳቸውን በኣደባባይ ማጋለጣቸው ግን መልካም ኣጋጣሚ ተደርጎ መታየት ኣለበት።

ይህ በነገዱ እየተመራ ያለው ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን በመላ ኣገሪቱ ያሉትን ብሄር ብሄረ ሰቦች (የኣማራ ህዝብ ጭምር) ኣምነውና ፈቅደው ያጸደቁትን ህገመንግስት እና ባንዴራ ኣሸቀንጥሮ የደርጉና ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚያሳይ ባንዴራ ሲጎትቱ ታይተዋል። ይህ ቡድን ብኣዴንነቱን ሰርዞ ኣ.ብ.ን መቀላቀሉን ይፋ ኣድርገዋል። ባህርዳር ሰልፍ ላይ እንደታየው የብ... ነባር ኣመራሮችን (ኣንዳንዶቹም የእነ ገዱ የጥፋት መንገድ ያልተቀብሉ) ሲያወግዙ መታየት ብቻ ሳይሆን ብኣዴን ይዞት የመጣውን የክልሉ ባንዴራም ጭምር እንዳይሰቀል የከለከሉ ይመስላሉ። ይህ ኣማራን ወደ ድሮ ቦታውን እመልሳለሁ፣ መተከል፣ ግማሽ ትግራይ፣ ሸዋ ሙሉውን፣ ኣዲስ ኣበባ፣ ኣስበን ጨምሮ ግማሽ ኣፋር ግዛቴ ነው እያለ ያለው ኣስፋፊ ቡድን ክተለያዩ ክልሎች ጋር ብቻ ሳይሆን በኣማራ ክልል የሚገኙ ሌሎች ብሄሮችም ጭምር ለመጋጨት ዝግጁነቱን ግልፅ ኣድርገዋል። ምንም እንኳን ለስሜት መቀስቀሻ ሲባል ህወሓትን በጠላትነት የፈረጀ ቢሆንም ብኣዴንን ትቶ በተግባር ኣ.ብ.ን መቀላቀሉ ይፋ ያደርገው ከሁለት ተጨባጭ ስጋቶች የመነጨ እንደሆነ መታወቅ ይኖርበታል።

ኣንድኛው ስጋት፣- ... እንደሚታወቀው ኢህኣዴግን ከመሰረቱ እና በትጥቅ ትግሉም፣ በተለይም በመጨርሻ ኣካባቢ የራሱ መጠነኛ ኣስተዋፅኦ ያደርገና ከደርግ ውድቀት በኃላም ኣዲሱን ህገመንግስታዊ ስርኣት በመመስረት ሂደት የማይናቅ ኣስተዋጽኦ ኣድርገዋል። ሆኖም ግን በወደቁትና በተሸናፊ ሃይሎች በደረሰበት የማያቋርጥ ስም ማጥፋትና ኣሉታዊ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት በኣማራው ህዝብ፣ በተለይም ሙህሩና ከተሜው ዘንድ ተቀባይነት ኣጥቶ መቆየቱን ይታወቃል። በሂደትም ድርጅቱ በእነ ገዱ ኣንዳርጋቸው ኣይነት ጥገኛ ሃይሎች እየተሰረሰረ ከመሄድ ኣልፎ ደርግን በመፈለምና ኣገሪቱ ዛሬ ላመጣችው ኣዎንታዊ ለውጥ የማይናቅ ሚና የተጫወቱ ነባር ታጋዮችን ጥግ በማስያዝ በድርጅቱ ውስጥ የበላይነታቸውን ኣረጋግጠዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ የጠ/ሚንስትር ኣብዪ ዋሳኔን ተከትሎ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎች ወደ ኣገርቤት እየገቡ በመሆኑ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይም ...ንን በፕሮፓጋንዳ ጦርነት የገጠሙ የኣማራ ቡድኖች ሲገቡ ህዝቡ ፊቱን እንዳይዞርባቸው በመስጋት ዛሬ ህወሓትን በኣደባባይ በጠላትነት በመፈረጅ እና ስሜት ቀስቃሽ ንግ ግሮችን በማድረግና ህዝቡን ስሜት በማስጮህ ጎራቸው የለዩ መሆናቸውን ማረጋገጥ የፈለጉበት ሁኔታ ነው ያለው። ከዚህ የባሰ ኣስቀያሚ የፖለቲካ ኣክሮባት ደግሞ ያለፈው 27 ኣመታት የነበረውን መንግስት ያልነበሩበት ይመስል እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ እና ክህደት ኣይናቸውን በጨው ታጥበው በስርኣቱ ከእነሱ ያነሰ የሚኒስትርነት ቦታ፣ የደህንነት ሰራተኛ፣ የመከላከያ ሰራዊት የነበረውን ኣካል ሲከሱና ሲያወግዙ ተሰምተዋል። እንግዲያውስ የጠቅላይ ሚንስትር ኣብይ ድጋፍ ሰልፍ ብለው የወጡት ዋና ምክንያት ይሄንን ቅጥፈታቸው ለህዝብ በይፋ ለመንገር እንጂ ኣብይ ስለወደዱ እንዳልሆነ መገንዘብ ኣስፈላጊ ነው።

ሁለተኛው ስጋት፣- ይህ ከባድ የሚባል ስጋት ነው። በኣግሪቱ እየታየ ያለውን የጎራ መደበላለቅ ተክትሎ እና ጠ/ሚንስትር ኣብይ ባድረጉት ጥሪ ብዙ የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች በተለይም የተለያዩ የኦ.. ቡድኖች ኣገር ቤት እየገቡ መሆኑን ይታወቃል። በዚህ የሰጉት የኣማራ የፖለቲካ ሃይሎች በመሰባሰብ እና ህዝቡን በስሜት በመቀስቀስ የኣማራ ብሄርተኝነት እንዲጦዝና ሃይል ያላቸው መሆኑን ለማሳየት የሚደረግ ጥረት ነው። እነዚህ የኦሮሞ ሃይሎች በኦ.... ኣቀባበል እየተደረገላቸው በመሆኑ በኣማራው ዘንድ ከፍተኛ ስጋት ከመፍጠሩ የተነሳ እነሱም የደርግ ባለስልጣናት ሳይቀሩ ቤተመንግስት ድረስ እየተቀበሉ ይገኛሉ። ከዚህ በፊት ደጋግመን እንደ ገለጽነው የኦሮማራ ፕሮከት ህወሓትን ከጨዋታ ውጭ ከማድረግ የዘለለ ሌላ ኣላማና ይዘት የለውም። የፈለጉትን ያክል ቢወራጩ ግን ከክልላቸው ኣልፈው ሌላውን መግዛት እንደማይችሉ እስኪገነዘቡት ድረስ ተደጋግሞ ሊነገራቸው ይገባል።

በተረፈ በጥቅላይ ሚኒስትሩ እየተቀነቀነ ያለው ክልሎችን የማፍረስ ከይሲ ሃሳብ ሁሉም ብሄር እና ብሄረ ሰቦች በጥሞና ሊከታተሉት እና በኣንድ ኢትዮጵያ እና በመደመር ስም ለጠቅላይ ኣግላይ ኣገዛዝ ራሳቸውን ኣሳልፈው እንዳይሰጡ መታገል ይኖርባቸዋል። ሲጀምር የፌደራል ስርኣቱ የስልጣን ምንጭ ክልሎች እንጂ በተቃራኒው እንዳልሆነ ማስገንዘብ ያስፈልጋል።

በመጨረሻም ኣ.ብ.ን የሚያስተዳድራት ኣማራ ክልልና ኦ.ነ.ግ የሚቆጣጠራት ኦሮሚያ የኣገሪቷ እጣ ፈንታ ይወስን ይሆን? የከፋው ደግሞ ኣማካሪቸውና የስራ እቅድ የሚያቀብላቸው ኢሳያስ ኣፈወርቂ መሆኑ ነው። የፈረንጆችም እንደተጠበቀ ሆኖ። ለማነኛውም በኣገርቤቱ የፖለቲካ ሜዳ ተዋናዩ እየበዛ ስለሆነ በሚቀጥሉ ወራቶች የሚኖሩትን ተከታታይ ፊልሞች ኣስተውለን እንመልከት።

ቸር ያሰማን

Back to Front Page