Back to Front Page


Share This Article!
Share
መንግስት የለም

*** መንግስት የለም ***

Videos From Around The World

ስርዐተ  አልበኝነት

ነግሷል  በክልል

የፍቅር  አርበኞች

ሆነዋል   ዘረኞች

ጭካኔነት   ተቆጥሯል

እንደ  ጀግንነት

ወጣቶች   ሆነዋል

ፈላጭ  ቆራጮች

ዜጎች   ተባረዋል  ከቀያቸው

ስደተኛ  ሆነዋል ባገራቸው

 

የመንጋ  ዳኞቹ

ሰቅለዋል   በሻሸመኔ

የባህር  ዳሮቹ

ሆነዋል  ፖሊሶች

የጅግጅጋዎቹ

ሆነዋል  ወታደሮች

 

እነዚህ  ወጣቶች...

የፖለቲካ  መሳሪያዎች

ህይወትን  ሲቀጥፉ

ሲያርዱ  ሲያቃጥሉ

በድንጋይ  ሲወግሩ

         የታለ...

አዲሱ  ስርዐቱ

አዲሱ  መንግስቱ

አዲሱ  ለውጡ

አዲሱ  ቲሙ

አዲሱ  መዋቅሩ።

 

                          ኢዮብ ባህር ማዶ

 

Back to Front Page