Back to Front Page


Share This Article!
Share
የመቀለው ህዝባዊ ሰልፍ፤የፊስቡክ አድምተኞት ቁጣ እና የሰሞኑ ዶክዩመንታሪ

                            የመቀለው ህዝባዊ ሰልፍ፤የፊስቡክ አድምተኞት ቁጣ እና የሰሞኑ ዶክዩመንታሪ

አሃዱ ሰላሙ 12-15-18

የመቀለውን ሰልፍ የተመለከቱ የፈስቡክ እድምተኞት በሰልፈኞቱ ተበሳጭተው ብዙ ብዙ ተናግረዋል።.የሰልፉን አላማ አስመልክተውም እነሱ ሌቦች ያሉዋቸውን "የህወህት አመራር አባላትን ደግፈው ነው፣ የጌታቸው አሰፋን እጅ አንሰጥም ብለው ነው፣ ህወሀት መሸሸጊያ ሊያደርጋቸው አስገድዷቸው ነው፣" የሚሉትን የመሳሰሉ ትርጉዋሜዎችንና ብይኖችንም ሰጥተዋል። እነዚህን ሁሉ የመሰለኝ ትርጉዋሜዎችና ብይኖች አይቼና አንብቤ ተገርሜ ባልፍም አንዲት ጥያቄያቸው ግን ጭንቅላቴ ውስጥ ቆየች፤፤ ጥያቄዋም " ለአመታት ህወሃትን አውግዘን ሰልፍ ስንወጣ አንድም ቀን አብረውን ሰልፍ ሳይወጡ ዛሬ እንዴት ህገ መንግስቱ ይከበር! ብሄር ተኮር ጥቃት ይቁም!" ብለው  ሰልፍ ይወጣሉ?" የምትል ነበረች፤፤ጥያቄዋ ለእኔ ትምክህተኛው አህዳዊ ሀይል ለትግራይ ህዝብ ያለውን ንቀት ቁልጭ አርጋ ያሳየች ነበረች፤፤

Videos From Around The World

ይህች ጥያቄ ለኔ በአሃዳዊት ኢትዮጲያ አባዜ ተለክፎ ለሃያ ሰባት አመታት ሲጮህና ሲናከስ የኖረው ትምክህተኛ ህይል እብደት መቼም ቢሆን የማይድን የእድሜ ዘመን ልክፍት እንደሆነ ያሳየች ነበረች፤፤ በትምክህት ላበዱት ሳይሆን በዚህ ፅንፈኛ ሀይል ፕሮፓጋንዳ ለተወናበዱና ብዥታ ውስጥ ለወደቁ ቁጥራቸው ቀላል ለማይባል የማሀበራዊ ገፅ እድምተኞች እኔ እንደግለሰብ የራሴን አስተያየት ልስጥ አልስጥ እያልኩ ከራሴው ጋር ስምዋገት የሰሞኑ ዶክዩመንታሪ ተብዬ ተለቀቀና ቀድሞኝ መልሱን ሰጣቸው፤፤ ሰሞኑን የተለቀቀው ዶክዩመንታሪ በንጹህ ልብም ሆነ ለይስሙላ ለምትጠይቁ ሁሉ የማያሻማ መልስ ሰጥትዋችሁዋል፤፤

የትግራይ ህዝብ አብርዋችሁ ሳይጮህ የቆየው፡ በርግጥም ጩኸቱ ለዲሞክራሲ፤ለፍትህ፤ለሰባአዊ መብት መጠበቅና፣ የመጻፍና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲከበር ሳይሆን፡ፌዴራላዊው ስርአትእንዲፈርስ፤አልፎ ተርፎም የትግራይ ህዝብ ተነጥሎ የጥቃት ኢላማ እንዲሆን እየተሰራ እንደሆነ ስለገባው ነበር፤፤ ይኽውና አሁን እንዳይሆን ይፈልገው የነበር ብሔር ተኮር ጥቃት በፌዴራል መንግስቱ ይሁንታና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማበረታቻ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ተከፍቶበታል፤፤ የትግራይ ህዝብ አብሮን ለምን አልጮኽም ለምትሉ ሁሉ ዶክመንታሪው ግልጽ መልስ ስጥትዋችሁዋል፤፤ አክራሪውን አሃዳዊ ሃይል "ተው! ይሄ ነገር ደግ አይደለም!" ማለት ጉንጭ ማልፋት ነው የሚሆነው፤፤

 በትምክሀት ሃይሉ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ የሆናችሁ፤ አገር ከመውደድ ያልዘለለ ድብቅ አጀንዳ የሌላችሁ ኢትዮጲያውያን በተለይም ወጣቶች ሰከን ብትሉና ብታስትውሉ ግን ምኞቴ ነው፤፤ የትግራይ ህዝብ ሁሉም የኔ የሚላት ኢትዮጲያ እንድትፈጠር የታገለና የሞተ ህዝብ እንጂ ኢትዮጲያን ሊያፈርስ የተነሳ ህዝብ አይደለም፤፤ ሌባም አይደለም። አገሩን ወዳድ፤ባህሉን ጠባቂና ህይማኖቱን አጥባቂ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ከደርግ ጋር በተደረገው የትጥቅ ትግል ከከፈለው አካላዊና ቁሳዊ ዋጋ ባላነሰ ሁኔታ፤ ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ባልሰራው እየተወቀሰ፤ባልበላው እየተከሰሰ፤ኢሃዲግ እንደ መንግስትና ፓርቲ ለሰራውም ሆነ ላልሰራው ጥፋቶች ሁሉ የትግራይ ህዝብ ተነጥሎ እንደ ህዝብ እየተረገመ፤እየተወቀሰና እየተዘለፈ ስለ ኢትዮጲያዊነት ሲል፤ ስለ አብሮ መኖር ሲል አይችሉትን እየቻለ ኖርዋል፤፤

 ኣሁን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አበረታችነትና በመገናኛ ብዙሃኑ አዝማችነት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ታውጆበታል፤፤ ዶክመንታሪው ታይቶና፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጽህፈት ቤታቸው ድህረ ገጽ የ"ገና እንቀጥላለን!" የሚመስል መግለጫቸውን ሰጥተው ውሎ ሳያድር ጎንደር ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ይማሩ የነበሩ ሁለት የትግራይ ተወላጆች ተገድለዋል፤፤ በርካቶችም ቆስለዋል፤፤ ከትግራይ ውጪ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ዛቻና ማስፈራርያ እየደረሰባቸውም ይገኛል፤፤ የትግራይ ህዝብ በገዛ አገሩ እየተቀጠቀጠና እየተሳቀቀ፤እየተሰደበና እየተዘለፈ ይቀጥላል ማለት ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው፤፤ አንድን ህዝብ ነጥሎ፤ፈርጆና የአውሬ ምስል ሰጥቶ መንቀሳቀስ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንጂ ሌላ አይደለም፤፤ ይህ አካሄድ አገርን ወደ እርስ በርስ ጦርነት መግፋት እንጅ ሌላ አይደለም፤፤ የርስ በርስ ጦርነት ደግሞ ለአገርም ለህዝብም አይበጅም፤፤ እዚህም እዚያም እየተቀስቀሱ ያሉ ትናንሸ ግጭቶች እንክዋን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን እያፈናቀሉ እንደሆነ እያየን ነው፤፤

 ይህ " ጃሎ በል!" ከወዲሁ ትልቅ አደጋ ከፊትዋ እንደተደቀነባት ምልክቱ እየታየባት ላለች አገር የርስ በርስ ጦርነት ጥሪ ነው፤፤ የርሰ በርስ ጦርነት ደግሞ አገሪቱን ወደ መበታተን እንደሚመራት ለመገመት የፖልቲካ ሳይንስ ሊቅ መሆን አይጠይቅም፤፤የትግራይን ህዝብ አንበርክኮና አንገቱን አስደፍቶ የመቀጠል አጀንዳ ካለም አጀንዳው የትግራይን ህዝብ ስነልቦና ካለመረዳት የመነጨ ነው የሚሆነው፤፤ የትግራይ ህዝብ ጭቆናን የሚሸከምበት ጫንቃ የለውም፤፤ ህዝብን ለህዝብ የማለያየት ተንኮል በአብዛኛው ስሜት ላይ ብሚሰራ ፕሮፓጋንዳና እነሱ እና እኛ የሚለውን ትርክት በማሾር ነው የሚከወነው፤፤ ይህንን የሸር ፕሮፓጋንዳ ደግሞ በተለይ ጽንፈኛው የአሃዳዊት ኢትዮጲያው ሃይል በማህበራዊ ገጾች ለአመታት ተክኖበት ነው የኖረው፤፤

 ይህ አሃዳዊው ሀይል በሃገር ውስጥ የቀድሞው ብኣዴን ውስጥ ተሰግስጎ መግባቱን የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች አሉ። ትምክህተኛው ሀይል በአማራ ክልል በድንበር ጥያቄ ስም በትግራይና በአማራ ህዝብ መሀል የህዝብ ለህዝብ ግጭት እንዲኖር ተግቶ እየሰራ እንደሆነ እየተስተዋለ ነው። ይህ ደግሞ በዋነኛነት የሚሰራው በማህበራዊው ሚድያ ነው። የማህበራዊ ሚዲያው ዋነኛ ተጠቃሚ ደግሞ ወጣቱ ነው። ወጣቱ እንደዜጋ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁትን በሬ ወለደ ወሬ ሳያላምጥ ባይውጥ ምኞቴ ነው።በተለይ የትግራይ ወጣቶች ስሜትን በሚነኩ ዘለፋዎችና ትንኮሳዎች ትምከህተኛው ሃይል መረብ ውስጥ እንዳይወድቁ ከመቼውም በላይ መጠንቀቅ ይገባቸዋል። የትምክተኛው ከፍተኛ ትኩረት ልዩነቶችን ወደ ህዝብ ማውረድና ህዝብ ለህዝብ ግጭት መፍጠር ነው።

 የትግራይ ህዝብን ወደ ፈተና እየገፋው ያለው ሃይል የማንም ህዝብ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ከማንም ህዝብ ጠብ የለውም። አሃዳዊው የትምክህት ሀይልና ከአሃዳዊው ሀይል ጋር ጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጋብቻ ከፈጸመ በሁዋላ ፌዴራላዊውን ስርአት የማስጠበቅ ግዴታውና አሃዳዊውን የትምክህት ሃይል የማስደሰት ሚናው ተደባልቆበት ብዥታ ውስጥ የገባው ሀይል ነው። የትግራይ ወጣቶች እንዲሁም በመላው አለም ያሉ ተጋሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ በማህበራዊው ሚዲያ ላይ መሳተፍ ግድ የሆነብን ሳአት መጥትዋል። በህዝባችን ላይ የሚነዛውን ውሸት እግር በግር እየተከተሉ ማጋለጥ፤ እውነቱን ማሳወቅ፤ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጲያ ውስጥ እየሆነ ያለውን ነገር ማሳወቅ ግድ ይለናል።

የማህበራዊ ሚዲያው የትምክህት ሰራዊት ሆን ብሎ በስድ ቁዋንቁዋና ሃሳብ የሚያደርገውን የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ፤ በሰከነ የአባቶቻችሁ ጭዋነት ጭብጣችሁን እያስረዳችሁ ማምከን ይጠበቅባችሁዋል።የተጋሩን ማንነት በፌዴራል መንግስት መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር የሚታገዘው የትምክህት ሀይል ሳይሆን እናንተው ራሳችሁ ከአባቶቻችሁ በወረሳችሁት፤ ጭዋነት ማንንም ሳትዘልፉ ማንነታችሁን ትገልጣላችሁ። እናንተን የተመለከተውን ትርክት ከትምክቱ ሃይል ካፉ ትነጥቁታላችሁ። የሚሼል ኦባማን አባባል ልዋስና"እነሱ ሲዘቅጡ፤እናንተ ከፍ እያላችሁ"ሃሰቱን ያለርህራሄ ታጋልጣላችሁ። አዮኹም ናይና!!

 

Back to Front Page