Share This Article!
Share

Back to Front Page

ልጆቼ አይኖቼ

ልጆቼ አይኖቼ

ሠላሳ ሶስቶቹ 
ከኔ የወጡቱ 
ፌዴራሊዝምን 
የመረጡቱ 
በአዲሷ ኮሚሽን 
ያልተታለሉቱ
እጃቸውን አውጥተው 
የተቃወሙቱ 

ልጆቼ አይኖቼ 
የኔ አንበሶቼ 

ደህና ሁኚ በሏት
በደምና ህይወት 
ለገነባችኋት

ለተፈራረከችው
ልክ እንደጀበናዋ 
ለተበታተነችው
ለድሮዊቷ 
በስሟ ብቻ 
ለቀረችዋ
ለፌደራሊዝሟ 
ለተተካችው 
በኮሚሽኗ  

በሉ አንበሶቼ 
እንዳትሉ 
አናሳ አናሳ 
ኮሚሽኗ 
አትወደውምና

ኢዬብ ከጮማ እምኒ

12-29-18

 

Videos From Around The World


Back to Front Page