Back to Front Page


Share This Article!
Share
በተውኔት የምትመራ ሃገር ሰለም፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ማስፈን ኣይቻላትም

በተውኔት የምትመራ ሃገር ሰለም፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ማስፈን ኣይቻላትም

ከ ኣሉላ ዮሃንስ 09-12-18

መቐለ

ኣንድ ግዜ ጅብ በሬ ቀበሮ ደግሞ ላም ኣገኙና በየተራ እንዲጠብቁዋቸው ተስማሙ፡፡ ላሚቱ ትከብድና በኣጋጣሚ የመውለጃዋ ቀን ተረኛ ጠበቂ ጅብ ነበረና የተወለደችውን ጥጃ ይዞ ከላሚቷ የወጣውን እትብት ወደ በሬው ቂጥ ወትፎ ወደ ማደርያቸው ሲደርስ ቀበሮዋ ደህና ዋልክ ኣያ ጅቦ ትለዋለች ጅብም ደህና ነኝ በሬየ እኮ ወለደ ይኸውና ምን የመሰለ ጥጃ ወለደ ይላታል፡፡ ቆበርየም ምን እያልክ ነው ከመቸ ወዲህ ነው በሬ እሚወልደው የወለደችውማ የኔዋ ላም ናት ብላ ትከራከራለች፡፡ ጡንቻ ራስ እሚተማመነውና እሚያስበው በጡንቻው ነውና ባክሽ የኔ በሬ ነው የወለደው ስትፈልጊ ሌሎች እንስሳት ጋር እንሂድና ይመስክሩብን ኣላት፡፡ ቀበሮዋም በዚሁ ተስማምታ ለምስክርነት ያገኙዋቸው እንስሳት ኣያ ጅበ እያስፈራራ እስቲ መስክሩ በሬ ነው ወይስ ላም እምትወልድ ይላቸዋል፡፡ በሬው የጅቡ መሆኑን ያውቁ ስለነበር በፍርሃት ኣይ በሬ ነው የሚወልደው ይላሉ፡፡ በስተመጨረሻም ጦጣ ያገኙትና ኣያ ጅቦ ኣንተ ጮጫ በሬ ነው የሚወልደው ወይንስ ላም ይለዋል በሃይለቃል፡፡ እሱም እንደሌሎቹ በፍርሃት ድሮ ድሮ ላም ዛሬ ግን በሬ ነው የሚወልደው ይለዋል፡፡ ይህንን ያልተtገባ ምስክርነት የሰጠው ማምለጫ ስላልነበረው ነበርና ቀድሞ ሄዶ ቆይቶ ወደቤታቸው ሲመለሱ መንገድ ላይ ጦጣው ኣለት ይደበድባል፡፡ ይህንን የተመለከተ ጅብ ኣንተ ጦጣ ለምንድነው ኣለቱን የምትደበድበው ይለዋል፡፡ ጦጣዉም ተቀብሎ ኣይ ልጥ ማውጣት ፈልጌ ነው ይለዋል፡፡ ጅብም በተራው ኣለት ይላጣል እንዴ ብሎ ሲጠይቀው በፊተኛው ተናዶ  ግን በፍርሃት ያልሆነ ምስክርነት ሰጥቶ የነበረው ጦጠጣ ታድያ በሬስ ይወልዳል እንዴ ብሎእውነቱን ተናግሮ ሸሽቶ ኣመለጠ ይባላል፡፡  

Videos From Around The World

እንግድያው ሃገራችን በታሪክዋ ለመጀመርያ ግዜ በፖለቲከኛ ሳይሆን በደራሲና በተውኔት ባለሞያ መመራት ከጀመረች እነሆ ኣምስት ወራትን ኣስቆጥራለች፡፡ በነዚህ ወራት የተሰሩ ተውኔቶች እንካችሁ፡

ሲጀምር ፋኖና ቄሮዎች ተብለው የተስፋ እንጀራ ቃል ተገብቶላቸው ባደራጁዋቸው ወጣቶች ኣገሪትዋ እንድትናወጥ፣ ሰላምዋ እንዲደፈርስ፣ ኢንቨስትመንቶችና የህዝብ መሰረተ ልማቶች እንዲወድሙ፣ ሰዎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ፣ ንብታቸው እንዲዘረፍና እንዲቃጠል ንሎም በኣሰቃቂ ሁናቴ ሂወታቸውን እንዲያልፍ እንዲሁም መንገዶችን በመዝጋት መኪኖችን በማቃጠል የሰውና የንብረት ዝውውር እንዲገታ በማድረግ በለስላሳ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን ላይ ወጡ ይህ የመጀመርያ ውጤታማ ተውኔታቸው ነው፡፡

በመቀጠ-ል እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራትT ሰላመዊ በሆነ መንገድ ለመምራት የስልጣን ክፍፍፍል የሚደረገው ኣዲስ ሽግግር ሲኖር ካልሆነ በስተቀር በብቃት እንጂ በህዝብ ብዛት፣ በብዛትም ሲታይ ፍፁም በማያንፀባርቅ ሁናቴ ኣልተከፋፈለም፡፡ ከኣንድ ፅንፍ ወደሌላው ፅንፍ የተንገላወደና ከህወሓት የበላይነት ወደሌላኛው ጫፍ መውሰድም ሌላኛው በስኬተ የተካሄደ ተውኔተ ነው፡፡

በሶስተኛ ደረጃ በስመ ምህረት ለሚገባውም ለማይገባውም፣ ለሚስክኑም ለወንጀለኛም በጅምላ እንዲፈቱ በማድረግ ቀደም ሲል የነበረው በኣንድ ብሄር ያነጣጠረ ጥቃት እንዲያፋፍሙት ማድረግና በህዝበኝነት ኣaሄድ ኣይደለም በሳምንታት እስከኣሀሁን እንኳን የነበረውን ከማጥፋትና ከማውደብ በስተቀር ጠብ እሚል ስራ ሳይሰሩ በከእስር የወጡ ወንጀለኞች ኣስተባባሪነት ደራሲውን ለማመስገን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲጠራ መፍቀድ፣ ከዚያም ከእግዚኣብሄር የወረደ ሰው የመግደል ሙከራ ተደረገበት ለማስባል ከትሪቡኑ በጣም በርቀት ቦምብ እንዲፈነዳ በማድረግ ቦምቡም ኣቅም የነበረው ኣልነበረም በድንጋጤ ግን ሰው ሞተ ብዙዎቹ ለኣካላዊ ጥቃት ተዳረጉ፡፡ በደቂቃዎችም በደራሲው ኣንደበት የፀጥታን ጉዳይ እንደማረጋጋት ቤንዚን ለመጨመር ሆን ብሎና ታቅዶ በሞያው ብስለት ባላቸው የቀን ጅቦች የተካሄደ ጥቃት እንደሆነ ደመደሙ በዚሁም የኣዲስ ኣበባ ህዝብ በትግረይ ተወላጆች የማሸማቀቅ ስራ ተሰራ በተለይ ሸጊቱ መሆንዋን ዘንግቶ እስኪነገር ድረስ፣፡ የዚህ ሰልፍ ኣዘጋጆች ለጠፋው ሂወትና ኣካል መጉደል ተጠያቂዎች ኣልተደረጉም ብቻ ሳይሆን የትግራይ ህዝብ በደምብ በሌላው እንዲiላ በብርቱና በማያባራ ሁናa መርዛቸውን መርጨት ቀጠሉበት ኣሁንም እየረጩ ይገኛሉ፡፡ መደመር፣ ይቅር መባባልና መፋቀር ማለት እንዲህ መሆኑን በሚገባ የዳበረ የተውኔት ችሎታ ኣዳብረዋል፡፡

በኣራተኛ ደረጃ ሰለጠኑ በሚባሉ ሃገራትም ጭምር ኣስተዳዳሪዎች ሁሉንም ሰው ያስደስታሉ፣ ምንም ኣይነት ጥሰት ኣያካሂዱም ተብሎ እማይወሰድ እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም ለመደመር ያመች ዘንድ የስራ እድል የተፈጠረላቸውና በገንዘብ የተገዙ ዋልጌዎችን በማደራጀት በደቡብ ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ የመደመር ፋሽን የማይቀበሉትን በማውረድ ይህንን ፋሽን በሚከተሉት መተካት፡፡ ቀጥሎም ተመሳሳይ ሁኔታ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብጥብጡ እንዲካሄድ በማድረግ ተሞክሮ ቢከሽፍም ብጥብጥ ስላስነሳችሁ ከስልጠጣናችሁ በራሳችሁ ግዜ ልቀቁ ብሎ ማለትተውኔቱ የጀማሪም ኣይመስልም፡፡ ለጥቆም ተመሳሳይ ብዱኖች በሶማሌ ኢትዮጵያ በማካሄድ፣ ኣብያተ ክርስትያን እንዲቃጠሉና ሰዎች እንደሞቱ በማድረግ ቅጥረኞቹ ግዳጃቸው ሲወጡ በሰላም መደፍረስ ስም መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ያለ ክልሉ ይሁንታና እውቅና እንዲገቡ በማድረግ ኢህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ ያለምንም የክልሉ ፓርላማ እውቅናና ተሳትፎ መንግስት እንደመንግስት ከክልል እስከወረዳ እንዲለወጥና እንዲደመር በእውቀት የተመራ ተውኔት ኣካሄዱ፡፡ ይህንን ተሞክሮ ወደትግራይም በማስፋት መጀመርያ ኮማንዶ በድብቅ በመስደድ ቀጥሎም የወwልቃይት ዘፈን ሲሰለቻቸው በራያ ስም መጥተው በዚህ ተግበር እንዲሰማሩ የሚሹ ሰዎች በማጣታአው ለካሜራ ይመች ዘንድ ከስተድዮም ኣካባቢ ጎደና ኣደሮችን በማሰባሰብ በኢቲቪ በር ኣጠገብ ሆነው ፍትህ ለራያ፣ ራያ ኣማራነው እናም በብሄሩ ጥቃት እየደረሰበት ነው የሚል የበሬ ወለደ ወሬ ቢቲቪ እንዲተላለፍ በማድረግ በሰላም ላይ የምትገኘን ትግራይ ለመበጥበት ያስእለናል ያሉትን ጉርም ኣድርገው ተውነውታል፡፡

ሌላ ብዙ ብዙ ነገር ኣለና ኣንዱን ብቻ ልጨምር፡፡ እንጂነር ስመኘው ለሃገሩ እድገትና ፍቅር ሰባት ዓመታትን ከኣርባ ዲግሪ ሰንቲግሬድ በነ ቦታ እየተቃጠለ በጀግንነት የግድቡን ስራ ሲመራ የነበረ ሪክ ምንግዜም ሰዘክረው የሚኖር ባለውለታ ሆኖ እንጂ በነግብፅ ኣሻጥር ግድቡን ለቆ ቢወጣ ከኣምስት እጥፍ በላይ ምቾትና ጥቅም ማግኘት ይችል እንደነበረ ብቻ ሳይሆን ለማማለል እንደተሞከረም ይነገራል፡፡ ታደያ ነገ ዛሬ ይህንን ግድብ ኣልቆ ታሪክ ሰርቸ ኣርፋሎህ ይል የነበረው ሰው በኣዲስ ኣበባ እምብርት ቦታ ላይ ተገድሎ መኪና ውስጥ ተጥሎ የመገኘቱ ጉዳይ ይፋ ከሆነበት ግዜ ጀምሮ በእለተቀብረ ከተረጨው የየቀን ጅቦች ገደሉት ወሬ ኣጣረተን ይፋ እናደርጋለን የተበለውን በኤፍ ቢ ኣይ ታግዞ ምርመራ ሲደረግ ቆይቶ በሁለቱ ወሩ ራሱ ነው የገደለ የሚል ተውኔት እንደ ኣፄ ቴድሮስ መሆኑ ነው ተነገረን፡፡ በመጀመርያ ደረrጃ መስተዋቱ በጥይት ኣልተበሳም፣ ቀጥሎም እመኪናው ውስጥ እንኳን ተገድሎ ቢሆን የተረጨ ደም ፍንጣሪ ይኖር ነበር፣ በጀሮ ግንድ የሽጉጥ ምላጭ ለመሳብ እንኳን እንደማይመች መሰርያ የማያውቅም የሚገነዘበው ሆኖ ሳለ የራሱን ገደለ የምርመራ ውጤት የተዋጣለት ትወና ነው፡፡ እሺ እሱስ ራሱu ይግደል ሚስቱስ ራሷ ገድላ ትሆን ዱከዋ  የጠፋው?

በኣምሓራ ክልል በትግራይ ተወላጆች ስንት ግፍ እየተሰራ፣ በባቲ ስንት ግፍ እየተሰራ ኣሁንም በቅማንትና በኣገው ስንት ግፍ እየተሰራና ፓርቲ ለምን ትመሰርታላችሁ በሚል በየቀኑ እየተለቀሙ በየእስርቤቱ እየተወረወሩ ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ እያለፈው ያለው ኢቲቪ ተውኔታዊ የራያ ማንነት ለማስተላለፍ ግዜ ኣልፈጀበትም ብቻ ሳይሆን ቀጥታ ስርጭት ነበር ማለት ይቀላል፡፡ እስከኣሁን እየታዩ ያሉ ተውኔቶች በጀማሪዎች በመሆኑ ግድፈት ቢኖራቸውም የዘመናችን ምርጥ ተውኔቶች ተብለው በኢትዮጵያ ታሪክ እንደሚመዘገቡ ጥርጥር የለኝም፡፡ ይህ ኣካሄድ በእንጭጨጩ ካልተገታና በመርህ መመራት ካልቻልን ግን እንደሃገር ብዙ መጓዝ ኣንችልም፡፡ የኛ ጉዳይ በዘዴ ካልተያዘ ከምናያቸውና ከምንሰማቸው የኣፍሪካ ሃገራት የባሰና መመለስ ወደማይቻልበት ሁኔታ ይወስደናል፡፡ ከግብፅ፣ ከኤርትራከኣረብ ሃገሮችና ከኣሜሪካ ጋር እየተካሄዱ ያሉ ለህዝቡ የተደበቁ መርህ ኣልባ ስምምነቶች ተመልሰው ሃጊቱን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ፈራሚዎችም ጭምር የሚያቃጥል እንዳይሆን ረጋ ተብሎና ታስቦበት እንዲሁም የህዝቡን ይሀንታ ንሮት ቢተገበር ሁላችንም ኣራፊዎች እንሆናaን ኣገራችንም ወደ እድገት ማማ ትመለሳለች፡፡ ስለዚህ ተውኔቱ በመተላለፉ ለያስከትለው ከሚችል ጉዳት ኣንፃር ሳንሱር እየተደረገ ቢለቀቅና ቢተወን ከጥፋት ሊያድን እንደሚችል መገንዘብ በሳልነት ነው፡፡ ፍቅር፣ ይቅር መባባል፣ ሰለኢትዮጵያዊነት ማሰብና ማስተግበር የሚቻለው በተግባር እንጂ በከንቱ ስብከት ኣይደለም፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡ ኣገራችን ከስብከትና ተውኔት ተላቃ በሳል ፖለቲካ እንድትመራ መጪው ዓመት ከስሜታዊና ግብታዊ ኣስተሳሰቦች ወጥተን የኣገራችን ህዝቦች ያለፈውን ክፉ ነገር በነበር እሚያወሩበት ያድርግልን ኣሜን፡፡

Back to Front Page