Back to Front Page


Share This Article!
Share
ግልጽ ደብዳቤ

ግልጽ ደብዳቤ

በቀለ ብርሃኑ ጷግሜ 2010

 

 

ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድ

የእትዮጲያ መንግስት ጠ/ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ እትዮጵያ

 

ክቡር ሆይ፤

ሁለት ዋና ዋና የሚምስሉኝን ጉዳዮች ለእይታዎ ማቅረብ እችል ዘንድ ይፍቀዱልኝ።

አስቀድሜ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ስልጣን ላይ በመገኘትዎ ባገሪቱ ሰላምን ለማስፈን የሚያደርጉት ጥረት ይሳካልዎ ዘንድ ምኞቴና ጸሎቴ ነው።

በዕድሜዎ ጎልማሳ ነዎት፤ ለስልጣን የሚያበቃ ዕድሜ።በዕድሜዬ አባተዎ ስለምሆንና በብዙ ተመክሮዎች ውስጥ ስላለፍኩኝ አንዳንድ የሚመስሉኝን ነገሮች ለማካፈል ደፈርኩ። እርሰዎም ባይሆኑ አማካሪዎችዎ ጆሯቸዉን እንደሚሰጡኝና መልእክቴን እንደሚያስተላልፉልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

ቅን አሳቢነትዎንና ፈጣን ለዉጥ ለማምጣት ያለዎትዎን ጉጉት እጅጉን አደንቃለሁ፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የማያቸው መሻሻሎች ተስፋ እንድሰንቅ ረድተውኛል። ባለፉት ሁለት ወራት ያሳዩዋቸው ያመራር መሻሻሎች የ ኢትዮጵያ የደበዘዘ የሚመስልው ተስፋዋ ብሩህነት እየታየበት ነው የሚል አስተሳሰብ እያመዘነብኝ መጥቷል።

ሕዝብኝነት (ፖፒዩሊዝም- populism) ያመጣዉንና እያመጣ ያለዉን እልቂት በከፍትኛ ደረጃ ስለምገነዘብ ወደ ሥልጣን የመጡ ጊዜ ያየኋቸው ሆያ-ሆየዎች በጣም አሳስበዉኝ ነበር። አሁን ግን በቅርቡ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ (ፕሬስ ኮንፈረንስ) ሳዳምጥ መንፈሳዊ መረጋጋትን እየፈጠረብኝ ነው። አገሪቱ በግለ-ሰብ ብቻ ሳይሆን መርህ ባለው በለውጥ ዉስጥ በሚገኝ ድርጅት እንደምትመራ አመላካች ሆኖኛል።

በዚህ መስመር መቀጠለዎ ለኢትዮጵያ አንድነት፤ እኩልነትና እድገት ወሳኝነት እንዳለው በመገንዘብ አንዳንድ የሃሳብ መስተካከሎች ያስፈልጋሉ የምላቸውን ቁም-ነገሮች ለማቅረብ እፈልጋለሁ።

እግረ-መንገዴን አንድ ነገር ላንሳ። በሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ለወጣቱ ያልንበረ ሚና እየተሰጠው ነው። በርግጥ ወጣት ትኩስ ነው። ጉልበታም ነው፤ ሃገር ወራሽ ነው። ግን ያገራችን ታሪክ እንደሚያሳየን ከሃገር ሽማግሌው፤ ከ-አባ ገዳው እንዲሁም በተለያዩ ብሄረ ሰቦች እንምንገነዘበው ወጣቱ ሚናዉን እንድያውቅ ቢደረግ መልካም ነው። ወጣት የሚፈልገዉን ይጠይቃል፤ መመርያ ዪሻል፤ መልካም አመራርን ይፈልጋል። ለህግ ይገዛል። አገርን ግን አይመራም። ወጣቱ ካለፈው ወጣት ታሪክ ብዙ ነገር መማር ዪገባዋል ።የወላጆቻችን እባካችሁ ሰከን በሉ መልእክት እንደ ቧልት በመቁጠር ከፊሎቻችን የሳት እራት ሆነን፤ ብዙዎቻችን ስደትኞች ሆነን የተቀሩት ደግሞ እድሜያቸው እየገፋ፤ ከስተታቸው እየተማሩ እዚህ ላይ ደርሰናል። ላገሩ የሚያስብ ወጣት መልእክቴን እንደሚገነዘበው እርግጠኛ ነኝ።

Videos From Around The World

ወደምጣሁበት ጉዳይ ልመለስና ቁም-ነገሮቹን በሁለት ልክፈላቸው፦ አገራዊና ዓለም-ዓለም አቀፋዊ

1.   አገራዊ

(ህ) የክልላዊት አደጋ

ከልልና ክልላዊነት የተለያዩ ምልከታዎችን ይሰጣሉ; የመጀመርያው አስተዳደራዊ ሲሆን ከልልነት ደግሞ አስተሳሰባዊ ነው። የመጀመርያው ፈደራላዊ አስተዳደርን ሲያመልላክት ሁለተኛው ደግሞ ጎጠኝነትን፤ ማን አህሎኝነትን፤ ጠባብነትን አደገኝነት አመላካች ነው።

(ለ) የብሄረተኝነት አደጋ

ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ግንዛቤዎች በብሄርና ብሄረተኝነት ያሉትን እሳቤዎች ያንፀባርቃሉ። ብሄር የሀዝብን ማንነት (የተለያዩ መስፈርቶች ቢኖሩትም) ሲገልጽ ብሄርተኝነት ደግሞ አመለካከትን።

ብሄርትኝነት- ፈረንጆች ናሺናሊዝም ይሉታል - (እንደ ሃይማኖት አክራሪነት) አደገኛ የሆነ መንጋነትን የሚያስነሳ ማዕብል ነው። በፍልስፍና ደረጃ የብሄር አክራሪነት (አልትራ ናቲኦናሊስም) ፋሺታዊና ናዚያዊ አገዛዝን የሚጋብዝ አደገኛ አስተሳሰብ ነው። የኛ አገር ሰው ፖለቲከኛ ዲሞክራሲያዊ የሚል ማሻሻያ አስቀምጦበት አደገኛ ዝንባሌውን ሊያሳንሰው ቢሞክርም የብሄርተኝነት እሳቤ በ-እኔ በልጥነት፤ የቋንቋ በላይነት፤ አርብኝነት (ፓትርዮቲዝም) የታጀለ ስለሆነ ዉሎ-አድሮ በአደገኛ ዝንባሌው ይረታል። የኛ ሰዎች ሆን ብለው አደገኛነቱን ተገንዝበው ያደረጉት ነገር እንዳልሆነ ዪገባኛል። ስለዚህም እንድያ ስል ከቁጥጥር ዉጭ ሊሆን እንደሚችል በመገንዘብ ሁነታዉን እንዲረዱ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ለመጠቆም ነው። ባንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚታየው አስጊ የበሄርትኝነት ዘንባሌ አንድ ምሳሌ ነው፤ እናም ሳይውል ሳያድር ባጭሩ ማስተካከል ተገቢ ዪሆናል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር፡

ስለዚህም ብሄርትኝነት ዲሞክራሲያዊ ሊሆን እንደማይቸል መረዳት ያስፈልጋል። አክራሪ ብሄርትኝነት (Ultra Nationalism) ፋሺስታዊ ስርዓትን የማነጽ መንደርደርያ መንገድ ነው።ያለፉት የ ዓለም የጦርነት ታሪኮች መሰረት ፋሺዝም- ናዚዝም ፤ ከናሺናሊዝም ጉያ የተፈለፈሉ አስተሳሰቦች መሆናቸውን ተገንዝቦ እነዚህን ዝንባሌዎች ለማዳክም ትልቅ ስራ ይጠበቀዎታል።

ብሄረተኝነት ከብሄር ማንነት ማክበርና መከባበር ጋር መደባለቅ የለበትም።ይህንን እዉነታ ለወጣቱ ማስረጽ እጂግ አስፈላጊ ዪሆናል።

2.   ዓለም- አቀፋዊ - ሚናችንና የስትራተጂክ ፖሊሲያችን

የኢትዮጵያ የዉጭ ፖሊሲ በገለልተኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። በንጉሠ-ነገሥቱም ሆነ በናንተ ኢሀአደግ ዘመን ያገራችንን ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችል አማራጭ የሌለው ስትራተጂ በመሆኑ ነው የተመረጠው።

አካሄድን በጥሞና መገንዘብ ያስፈልጋል። የምዕራቡ ዓለም ገለልተኝነትን አይወድም። ጎራዉን ያልለየ ሁሉ በጠላትነት ዪመደባል - ቢያንስ በቁራኛ ዓይን ቀለበት ዉስጥ ዪታጠራል። ምእራቡ አለም የጋራ ተጠቃሚነትን አያጎለብትም፤ድሃ -ተኮር እድገትን አያበረታታም። ባጭሩ የምእራቡ ዓለም ዝምድና በግል ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዝምድና ነው። ለምን የሚል ጥያቄ ከተነሳ አጭሩ መልስ ታዳጊ አገሮች ዉስጥ የሚገኙት የባንክና ፋይናንስ፤ ተሌኮሙኒከሺን፤ የሃይል ማመንጫ ተቋሞች እጂግ ትርፋማ በመሆናቸው የትሩፋቱ ብቸኛ ተጠቃሚ መሆን ስለሚሹ ነው።

ኢትዮጵያ - አፍሪካ ባጠቃላይ- ከማንም ጋር የምታደርገው ፖለቲካዊም ሆነ ኤኮኖምያዊ ግኑኝነት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ዪገባል። ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ጥንቃቄ ትፈልጋለች። ከ አረቡ አለምና ከም እራባውያን ጋር የሚኖራት ግንኙነት በጋራ ጥቅምና በረዥም ስትራተጂክ እቅድ ላይ የተመሰረተ ሊሆን ዪገባል።

ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን በገለልተኛነትና በነጻነት እንዲሆን የርሰዎ ፍላጎት እንደሆነ እገምታለሁ። ይህ ትክክለኛ አካሄደዎ በጉዙዎ ላይ ፈተና እንደሚፈጥርበዎ የተገነዘቡትም ይመስለኛል። ለዚህ ነው ምዕራባውያንና የተወሰኑ አረባውያን ደንበኞቻቸው ከመሰረታዊ መስመርዎ ልያሰናክልዎ ደፋ ቀና የሚሉት፡ የስለላ መረቦቻቸዉን በመዘርጋት ላይ የሚገኙት። በዚህም የተነሳ ባሁኑ ጊዜ የዉጭ ፖሊሲያችን አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ የሚገኝ ይመስለኛል።

የውጭ ሃይሎች ከቻይናና መሰል የ ኢኮኖሚ መርህ ከሚከተሉ አገሮች ኢትዮጵያን ለመነጠል በጣም እየተውተረተሩ ዪገኛሉ። ቻይና ከሁሉም ያፍሪካ አገሮች በሚባል ደረጃ ጥብቅ የሆነ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግኑኝነት አዳብራለች። ፈረንጆቹ በተለይም አሜሪካ ኢትዮጵያን ከቻይና ካለያዩ ሌላውም የአፍሪካ ሃገር ዪከተል ዪሆናል በሚል መላምት አገራችንን ለማነሁለል አድርገዉት የማያዉቁትን ቢያደርጉ ብዙም አይደንቀኝም። ከዚህ ወጥመድ መራቅ ገን ቀድመን ልናስብበት ዪገባል። የቻይና መንግስትም ይህን የተረዳ ዪመስለኛል።

የኢትዮጵያ መንግስት ዉስጣዊ አንድነቱን ካላጠናከረ የውጭ ተጋላጭነቱ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ አስጊ ደረጃ ላይ ዪገኛል።

የተወሰኑ የአረብ አገሮች የኢትዮጵያ ማደግና መፈርጠም እንቅልፍ ይነሳቸዋል። ግብጽ የራሷ የሆነ ምዕተ ዓመታትን ያስቆጠረ የ አባይ ጉዳይ ስላለና ምንም ተደጋግሞ ቢነገራትም እምነት ስለሌላት ሁሌም ባይነ-ቁራኛ ታየናለች። ለዚህ መፍትሄአችን ታላቁን የህዳሴ ግድብ ለመጨረስ ባዲስ ሃይል መነሣሣት ነው።

ሃብታሞቹ አረቦች - በተላይ ኤሜረቶችና ሳውዲ ምስራቅ አፍሪካን ለመቆጣጠር ባላቸው ጉጉት ወዳጅ መስለው ቀርበዋል። ወዳጅነታቸው መልካም ቢሆንም ከቅርብና ተፈጥሯዊ ግንኙነት ካሉን ወዳጆቻችን ጋር እንዳያራርቁን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል። ከተፈጥሯዊ ወንድሞቻችን ከ ኤርትራውያን ጋር የምናደርገው ወዳጅነትም በአረቦች ይሁንታ ላይ መሰረት ያደረገ እንዳይሆን እንጠንቀቅ።

ብዙ ኢትዮጵያውያን ከዉጭ በተለይ ከ አሜሪካ ያገራቸዉን ጥሪ ተቀብለው መግባታቸውና ለመግባት መዘጋጀታቸው እጅግ የሚያስድስት ነው፡ ያስገባሉ ተብሎ ከሚጠበቀው እውቀት/ክህሎትና የዉጭ ምንዛሪ በበለጠ በሞራል ላገር ባንድነት መቆሙ የሚያመጣው ጠቀሜታ ለኔ ዪበልጥ ያጓጓኛል፤ ይህ በጎነት እንዳለ ሆኖ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጉድፎችን ደግሞ አበጥሮ ማውጣት ውይም ጉዳታቸው የሚቀነስብትን መንገድ ማሰላሰል ያስፈልጋል። ሁለት ነገሮችን ልጥቀስ፦ አንድ በብዛት በ ሲ.አይ.ኤ የተመለመሉ ትውልደ- እትዮጵያውያንና ፈረንጆች መግባታችው፤ ሁለተኛው ደግሞ ያገራችንን ነባራዊ ሁኔታ የማይገነዘቡ፤ ሁሉም አውሮፓዊ አመለካከት ስልጡንነት የሚመስላቸው ምሁራን ድያስፖራዎችን ሚዛናዊ ያልሆነ ጆሮ መስጠቱ ነው። የነዚህ ወገኖች ተልእኮ ሁሉንም መንገድ በመጠቀም የውጭ ሃይሎችን ፍላጎት ማሟላት ነው።

የኔ ዕይታ

አንዳንዴ ችግሮቹ ምን እንደሆኑ ሳይለዩ ወደ መፍትኄ የመሮጥ መጣደፎችን አያለሁ። ረጋ ብሎ ማሰብ የግድ አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው።

አሁን ያለው ያገሪቱ ዝብርቅርቅ ያለ ክስተት በፊት የነበረዉን ስትራተጂክ አካሄድ ሊያደናቅፈው አዪገባም። አንዳንዴ ችግሮቹ በውል ሳይለዩ ወደ መፍትሄ የመግባት መጣደፎችን አያለሁ። ቆም ብሎ ማየት የግድ አስፈላጊ ነው።

ፓርቲዎ ኢህአደግ ዲሞክራሲ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው፤ ሙሰኞችን ኪራይ ሰብሳቢዎችን ፈርጣማ ለህግ የማይንበረከኩ ሃብታሞችን፤ አገር ያስመረረዉን ቢሮክራሲን ማጥፋትን እንደ ቀዳሚ አጀንዳው ከያዘው ዓመታት ተቆጥረዋል።

ሆኖም ግን እስካሁን ድረስ ዋናዉን አገር ያስመረረ ማነቆ ላይ የሚወሰድ እርምጃ አይታዪም። እናም ትኩረት ተሰጥቶት ስራ መጀመር ያለበት ነገር ነው። እስካሁን ድረስ በተለይም አኩርፎ የነበረዉን ውጭ ያለዉን ህዝባችንን ለመደመር የሚደርጉት እንቅስቃሴ በ አዎንታዊ መልኩ አየዋለሁ። ሆኖም ግን ጽንፈኛ ፖለቲከኛው ካፍራሽ ሃይሎችህ ጎን እንዳይሰለፍ ወይም እንዳይደመር ተንቃቄ ያስፈልጋል።

በኔ እይታ የጊዜው ችግር የመልካም አስተዳደር፡ ችግር ነው። ቢሮክራሲዉን ልጓም ካስያዙ፤ ሌቦችን በህግ እንዲገዙ ካደረጉ፤ ጉቦኞችን መቆጣጠር ከቻሉ፤ የህግ ተገዥነትን ካረጋገጡ፤ የችግራችን አብዛኛው መሰረት ይስተካከላል የሚል እምነት አለኝ።

ዲሞክራሲ የሚተገበረው ባገሩ ባህልና እድገት መሰረት ነው። የዲሞክራሲ አተገባበሩ እንዳገሩና እንደ ባህሉ ዪለያል። የየአህጉራቱ ዲሞክራሲያዊ የጋራ አካፋዩ ሰብዓዊ መብት ማክበሩ ላይ ነው። አለበለዚያ በዲሞክራሲ ስም ህዝበኝነት ዪነግሳል፤ የጎሳ ፖለቲካ የበላይ ዪሆናል፤ እልቂት ፈጣሪ መንጋኝነት የበላይ ዪሆናል።

ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ እሳት ብሎ መጮህ በወንጀለኝነት ያስከሥሣል ዪላሉ ፈረንጆች።

አመሰግናለሁ

 

 

 

Back to Front Page