Back to Front Page


Share This Article!
Share
ልክቡር ዶ/ር አብይ አህመድየኢትዮጵያ ፈደራላዊት ዲሞክራሲያዊት ረፑብሊክ ጠ/ሚኒስቴር

 

ልክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ

የኢትዮጵያ ፈደራላዊት ዲሞክራሲያዊት ረፑብሊክ ጠ/ሚኒስቴር

 

አዲስ አበባ

 

በቀለ ብርሃኑ 09-25-18

 

ሁለተኛ መልእክት - ስለ መሰረታዊ ጉዳዮች

 

ባለፈው ጊዜ በጻፍኩት መልእክት ስለጠንካራ ድርጅት አስፈላጊነት፡ የብሄረትኘነት አደጋና ከፋሸትነት ጋር ሊኖረው ስለሚቸል ቁርኝት፡ ስለአሁጉራዊ ግንኙነቶችና አካባቢ ሃገሮች ዲፕሎማሲ፤ ስለአጠቃላይ ኢኮኖሚ ሂደቶችህ፤ ወዘተ.. አንዳንድ ሃሳቦችን አቅርቤ ነበር።

 

በዚህኛው መልክቴ በሁለት ተያያዥ ጉዳዮች - ሰከን ያለ አካሄድንና መሰረታዊ ችግሮችን አበጥሮ መለየትን ጠቅሜታ ባጭሩ ለማተት ልሞክር። አስቀድሜ ግን ስልጊዚያዊው ያገር ሁኔታ ስጋቶቼን ልግለጥ;

 

ክቡር ጠ/ሚኒስቴር፡

በፊትም እንዳልኩት እጂግ አስቸጋሪ በሆነ ጊዚ ነው የዚህቺን ድንቅ፤ ታሪካዊትና ተስፈኛ አገር የማስተዳደር ሃላፊነት የወሰዱት። ከገባንበት አዘቅትና ማጥ መውጣት የምንችለው ደግሞ ኣስተዳደርዎ ተገቢዉን አቅጣጫ ማስያዝ ሲችል ነው።

ማለትም በከፊል፤

o   ባገር ሃላፊነት የተቀመጠ ማንኛዉም ሰው አገራዊነት ከ ግልነት በላይ መሆኑን ሲያምን

o   ሁሉም ክልላዊ ችግሮች መፈታት የሚችሉት ሃገርዊ ችግሮች ሲፈቱ መሆኑን መረዳት ሲችል

o   ሃገራዊ ችግሮች የሚፈቱት አገራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት እንዲኖር ሲደረግ

o   ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ አንድ ሃገራዊ እዪታ ያለው መሪ ድርጅት (ፓርቲ) ሲኖር ብቻ ነው።

 

የተቀመጡት ነጥቦች ግልጽ ስለሆኑ ብዙ ማብራራት የሚያስፈልግ አይሆንም።

 

ሃገራዊነት መንደረተኝነት አይደለም። ይህ ወረዳ የኔ ነው ያኛው የኔ ነው እያሉ መቆራቆስ ወይም መኮራረፍ አይደለም። እንድያ አይነት ነገሮች ትልቅነትን ሳይሆን ትንሽነትን፤ አገራዊነትን ሳይሆን የግል ጥቅምንና ዝናን፤ አርቆ አስተዋይነትነ ሳይሆን ጠባብነትንና ስሜተኝነትን የሚያንጸባርቁ አመለካከቶች ናቸው።

 

የቆጡን አወርዳለሁ ብላ የብብቷን ጣለች እንዳይሆን መጠንቀቅ ግድ ይላል። ክልልሎቻችን ያል ኢትዮጵያ ህይወት የሌላቸወ በድን ነገሮች ሊሆኑ እንደሚችሉ መገንዘብ ከባድ ሊሆን አይገባም። 

 

የተለያዩ ማህበራዊ እሴቶቻችን፤ ቋንቋዎቻችን የሁላችንም ሃብቶች አድርገን መውሰድ ይገባናል። ገዳ ስርዓት የሁላችን ነው፤ አማርኛ ቋንቋ የጋራችን ነው። የደቡብ ማህበራዊ እሴትና ትጋት፤ ታታሪነት ኩራታችን ነው። የትግራይ ጥንታዊ ታሪክና የአፋርና የሶማሌ የተፈጥሮ ምንጭነት ኩራታችን ነው። ስር መሰራታችንም ነው።

ይህንን አገራዊነት ወደ መንደረኝነት መቀየር ጸያፍ መሆን አለበት።

 

ባሁኑ ዘመን አገሮች የሚመሩት በግለሰብ ሳይሆን በተደራጀ የፖለቲካ ድርጅት (ፓርቲ) ነው።

 

ባሁኑ ጊዜ ፓርትዎ ኢህአደግ የተጠናከረ ድርጅት መስሎ አዪታይም። በዉስጡ የሚሻኮት መርሁን ያጣ ድርጅት ይመስላል።  ይህ አባባል እውነትነት ካለው በፍጥነትና በጊዜ መታረም አለበት።

 

አንድ ትልቅ ጉዳይ አሁኑኑ በምታደርጉት ጉባኤ መፈታት አለበት።  የክለል ፓርቲዎች ስም መቀያየር ለናንተ ትርጉም ቢኖረዉም በህዝብ ደረጃ ፋይዳው ብዙም ግልጽ አይደለም።

የክልል ፓርትዎች ሃላፊነታቸው ለክልልላቸው ነው። መሆን ያለበት ይህ ነው። እነዚህ ክልል ፓርቲዎች የክልሉ ህዝብ ከፍላጎቱ ጋር አጣጥሞ የሚመርጣቸው ዪሆናሉ። የዚህ አይነት አካሄድ ሌሎች አማራጭ ክልላዊ ፓርቲዎች መቋቋም መንገድ ከመክፈቱም በላይ ልክልል ህዝቦች አማራጮችን ይፈጥራል።

 

ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት አንድ ወጥ የሆነ ፓርቲ ነው። ይህ ፓርቲ ከክልል ፓርቲዎች ነጻ የሆነ፡ የራሱ ፓርቲ ቅርንጫፎች በየክልሉ የሚክትሙ ሆኖ የተዘጋጀ አገራዊ ፓርቲ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ አገሪቱ የምትፈልገው አደረጃጀትነው።

 

ባጭሩ አሁን ኢህአደግ ወደ ፓርቲ የሚሸጋግርበት ጊዜ አሁን ነው።

ኢትዮጵያውያን በማንኛውም የኢትዮጵያ ምድር ያለምንም ስጋት የመኖር ያልተገደበ መብታችው የሚከበረው፤ የሚረጋገጠው አንድ ወጥ የሆነ አገራዊ ራዕይ ያለው ድርጅት ጠንካራ አመራር መስጠት ሲችል ብቻ ነው።

 

መልካም እድል

 

Back to Front Page