Back to Front Page


Share This Article!
Share
ግልፅ ደብዳቤ፥ ለተከበሩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድ

ግልፅ ደብዳቤ፥ ለተከበሩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድ

ከሓጎስ አረጋይ 27/11/2010ዓ/ም

ብሄር ተኮር ጥቃት ይቁም!!!!

በአማራ ክልል ውስጥ በትግራይ ተወላጆች ላይ እየተፈፀ ያለውና ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የዘለቀ ጥቃት ይቁም። በእርግጥ በየተኛውም አካባቢ የሚፈፀም ብሄር ተኮር ጥቃት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ መቆም አለበት ። በተለይ በማራ ክልል ውስጥ በትግራይ ተውላጆች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ግን በተከታይነቱና በመንግስት ከለላ የሌለው ቅጥ ያጣ ጥቃት ነውና አንድ ነገር መባል አለበት ። ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርበዋል።

1.   በ 2007 ዓ/ም በአብርሃ ጅራ፣ ሸዲ ፣ እና በመተማ አካባቢ በሚኖሩ ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች ላይ በንብረትታቸው ላይ ዘረፋና የማቃጣል ግፍ ተፈፅመዋል። እንዲሁም በቅማንት ብሄረሰብ ላይ ጥቃት ተፈፅመዋል። ጉዳዩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሳኔ የተላለፈበት ነው። ነገር ጥቃቱ ቀጥለዋል።

Videos From Around The World

2.   ከ ሰኔ 2008 ----መስከረም 2009 ዓ/ም በሰሜን ጎንደር ዞን ፣ ጎንደር ከተማ፣ በምእራብ ጎጃም እና ደቡብ ጎንደር ላይ በብዙ ሚልዮን የሚገመት ንብረት ተዘረፈዋል/ወድመዋል፣ የሰው ህይወት ጠፍተዋል ። እንዲሁም

       በማህበራዊ ሚድያ እንደተገለፀው ከ80 በላይ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆጅ በዚሁ ጥቃት ህይወታቸው ማለፉ ተነግረዋል ። በቤታቸው ውስጥ እያሉ በድንጋይ ተቅጥቅጠዋል/ተቃጥለዋልም ፣

       እንደ ከብት በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ተሳድደዋል፣

       ጉዳዩ በሰብዓዊ መብት ኮሚሺን ተጣርቶ በህዝብ ተውካዮች ም/ቤት ቀርቦ ፀድቀዋል። በዚህ ሰው በላ የጭካኔ ተገባር የአመራርና የፀጥታ ሃይል የተሳተፉበት ብሄር ተኮር ጥቃት እንደ ተፈፀመ በኢትዮጵያ የህዝብ ተውካዮች ም/ቤት ውሳኔ (resolution) 11/2009 በግልፅ ተቀምጠዋል።

       ከሰላሳ ሺ በላይ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች ወደ ሱዳን ፣ አዲስ አበባ እና ትግራይ ተፈናቅለዋል

3.   በሃምሌ 19, 20, 21 በ2010 ዓ/ም በጎንደር ከተማ በትግራይ ተውላጆች ንብረት ላይ ተቃጥለዋል /ተዘርፈዋል ለዳግመኛ ግዜ ማለት ነው። እንዲሁም በዚሁ ወቅት ሰላም ባዝም ተቃጥላለች

4.   በጥር እና የካቲት 2010 ዓ/ም በወልድያ ፣ ቆቦ፣ መርሳና አካባቢው በትግራይ ተወላጆች ላይ ለሶስት ሳምንታት የዘለቀ ጥቃት ተፈጸመዋል። በዚሁ ጥቃት በብዙ ሚልዮን የሚገመት የትግራይ ተውላጆች ንብረት ወድመዋል/ተዘርፈዋል ቁጥሩ ያልታወቀ የስው ህይወት ጠፍተዋል ፣

5.   ከሰኔ 16 /2010 ዓ/ ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በከምሴ፣ ባቲና አካባቢው በትግራይ ተወላጆች ንብረት ወድመዋል/ተዘርፈዋል፣

6.   ሃምሌ 24/2010ዓ/ም በአዊ ዞን በጣና በለስ ፕሮጀክት በመሃንዲስነት ይሰሩ በነበሩ ሶስት የትግራይ ተውላጆች እጅግ አስቃቂ በሆነ በድንጋይ ተቀጥቅጠው ተገድለዋል። ስርዓተ ቀብራቸው በመቕለተፈፅመዋል

ከላይ ከተገልፀው ቀጥታዊ ጥቃት በተጨማሪ ፣

7.   በጎንደር ዩንቨርሲቲ በሰላሙ ግዜ መምህራን የነበሩ ነገር ግን በ2008ዓ/ም የነበረው ብሄር ተኮር ጥቃት ከ50 መምህራን በላይ ተፈናቅለዋል። ነገር ግን የጎንደር ዩንቨርሲቲ ም/ፕ የሆኑት ዶ/ር አስራት አፀደ ወይን በሚመሩት ዩንቨርሲቲ በተፈናቃዮች ብሄር ተኮር ጥቃት በመፈፀም ላይ ናቸው። በማንነታቸው ምክንያት ለመፈናቀል መዳረጋቸው፣ እንዲሁም የደረሰባቸው የሞራልና የስነ ልቦና ጫና ኣንሶ በነዚህ የተፈናቀሉ የዩንቨርሲቲ መምህራንና የትግራይ ተወላጆች የትምህርት የውል ግዴታ ብቻ (commitment) አለባችሁ በሚል ሰበብ፣ እኔ ከማቃቸው ሰዎች በመነሳት ፣

       ከቤተ ሰባቸው ለመበደር የቻሉ ሁለት መምህራን ያለአግባብ እስከ 400000ሺ (አራት መቶ ሺ ብር) እንዲከፍሉ ተደርገዋል ።

       ከቤተ ሰባቸው መበደር ባልቻሉ ሁለት ሌሎች የትግራይ ተወላጆች የዩንቨርሲቲ መምህራን ደግሞ በእያንዳንዳቸው ከ650000( ከስድስት መቶ አምሳ ሺ) ብር በላይ በሆነ ገንዝብ በጎንድር ፍ/ቤት ክስ መስርተው እያንገላትዋቸው ይገኛሉ። ወደ ጎንደር ለመመላለስ ምን ያህል አስጊ እንደሆነ ሁሉም የሚገነዘበው ይመስለኛል። በመሆኑም ጉዳዩ በፊዴራል ፍ/ቤቶች እንዲታይላቸው ቢጠይቁም መብታቸው ተነፍገዋል ። ነፍሴ ውጪ /ግቢ በሚል በከፍተኛ ስጋት ወደ ጎንደር ፍ/ቤት ለመመላለስ ግድ ሆኖባቸው በመመላለስ ላይ ናቸው ። ችግሩ አሳሳቢ እየሆነ ነው ቢታሰብበትና መፍትሄ ቢገኝ ።

       እኔ በማውቀው ስማቸውም መጥቀስ የሚችል የትምህርት የውል ግዴታቸው ያልፈፀሙ ወደ ባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ና ደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የሄዱ ነገር ግን የአማራ ተወላጆች በመሆናቸው ብቻ በነጻ ለቀዋል አሉ። ስለዚህ የጎንደር ዩንቨርሲቲ አመራር በተለይ ዶ/ር አስራት በብሄር ተኮር ጥቅት ብርቱ ተሳትፎ እንዳለው ያሳያል።

8.   ከጥር 2010ዓ/ም ጀምሮ ወዲህ በቆቦ ወልድያ መስመር ወደ አዲስ አበባ በመኪና በሚያልፉ የትግራይ ተወላጆች ላይ መንገድ ከመዝጋት ጀምሮ በመኪና ውስጥ በመግባት ዛቻና ማስፋራርያ በተለያየ ወቅት እየደረሳቸው እንደሆነ ከተለያዩ ሰዎች መረጃ አለኝ ።

ከላይ የተጠቀሱ ጥቃቶች በአማራ ክልል ውስጥ ከአማራ ህዝቦች ጋር ለ 40 ዓመታትና ከዚያ በላይ አብረው የኖሩትን የትግራይ ተወላጆችን ያካትታል። ለዚህ ጥቃት መነሾ የሆነው ጥላቻ እንጂ በአማራና ትግራይ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በግልፅ የወጣ ለኪሳራ የዳረገ በወሰኑ አከባቢ በሚኖሩ ሰዎች ላይ የተፈጠረ ግጭት/መጠቃቃት የለም። ይህ በመሆኑ ደግሞ

       በኢትዮጵያ ኦሮምያና ሶማልያ ክልል ከተፈጠረው ችግር ለየት ያደርገዋል ። በእርግጥ በዚህ አካባቢ የተካሄደው ጥቃት አሳዛኝ ነው። ነገር ግን በአዋሳኝ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት በምክንያትነት ሊጠቀስ ይችላል። ማለትም በሁለቱም ወገኖች ማጥቃትም ሆነ መከላክል የታየበት ነበር/ነውም።

       በኢትዮጵያ ኦሮምያና ደቡብ ክልል ከተፈጠረው ችግር ለየት ያደርገዋል ። በእርግጥ በዚህ አካባቢ የተካሄደው ጥቃት አሳዛኝ ነው።ነገር ግን በአዋሳኝ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት በምክንያትነት ሊጠቀስ ይችላል። ማለትም በሁለቱም ወገኖች ማጥቃትም ሆነ መከላክል የታየበት ነው።

       በሃውሳ ከተማና አካባቢ ዘር ተኮር ያደረገ ጥቃት አንድ ግዜ ተፈፅመዋል ።መጥፎ ክስተት ነው ለማለት ይቻላል። የክልሉ መንግስት በበኩሉም በችግሩ ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎች ወደ ህግ መቅረባቸው ገልፀዋል።

       በአሶሳ ግጭት ተከስተዋል ። ጥፋተኞች ለህግ ቀርበው ቅጣታቸው አግኝተዋል በማግኘትም ላይ ናቸው። በቅርቡ ለተቀሰቅሰው ችግር እንኳን ከ100 ሰዎች በላይ (የመንግስት አካላትን ጨምሮ ) ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአማራ ክልል ውስጥ ለሶስት አመታት በተከታታይ በትግራይ ተወላጆች ላይ በደረሰው ጉዳት ምንም የተባለ ነገር የለም። በጣና በለስ ለደረሰው ጉዳት እንኳን ተጠርጣሪ ተይዘዋል ከማለት በስተቀር ማንና ብዛት የተገለጸ ነገር የለም ።

በአማራ ክልል በትግራይ ተወላጆች የደረሰውና እየደረሰ ያለው ጥቃት ጥላቻን መሰረት ያደረገና ከወሰን ግጭት ምንም ነገር ተያያዥነት የሌለው ነው። እንዲሁም በእስከ አሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል በትግራይ ተወላጆች የደረሰው ጥቃት ግብረ መልስ በህየወት ያሉ ከመሽሽ፣ ህይወታቸው ካጡ መካከል ጥቂቶቹ ሬሳቸው ወደ ትግራይ ተጉዘዋል። ማለትም የመልሶ ማጥቃት አልታየም ምክንያቱ ትእግስት የተመረጠ ይመስለኛል። በጣም አሳዛኝ ድርጊት ነው እየተካሄደ ያለው ።

ስለዚህ ፣

       በትግራይ ተወላጆች ላይ በአማራ ክልል ውስጥ በሚኖሩና በመንገድ በሚያልፉ ከሚደርስባቸው ጥቃት መንግስት ዋስትና መስጠት አለበት ፣

       በአማራ ክልል በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የፊዴራል መንግስትና የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትኩረት ሊሰጠው የገባል ፣

       በትምህርት ውል ሰበብ / commitment/ ብቻ በጎንደር ዩንቨርሲቲ ከሳሽነት ወደ ጎንደር ፍ/ቤት የሚመላለሱ ወገኖቻችን ጥቃት እንዳይደርስባቸው የዳኝነት ስርዓቱ ይቋረጥ፣ ወይም መካሄድ ካለበትም ዳኝነቱ በፊዴራል ፍ/ቤቶች አዲስ አበባ ላይ ይካሄድ ፣ በዚሁ መልክ ሰው ማሰቃየት ነው ይቁም ፣

       ከሚኖሩበት አከባቢ በግድ መፈናቀላቸው አንሶ በትምህርት የውል ግዴታ ሰበብ ብቻ ተመስርተው ጎንደር ዩንቨርሲቲ ያስከፈላቸው ገንዘብ ይመለስላቸው ። ግፍ ነው በነዚህ ሰዎች ጉዳት ማድረስ

       በብሄር ትኮር ይቃት የተሳተፉ ግለ ሰቦች ግልፅና ገለልተኛ በሆኑ ፍርድ ቤቶች እንዲታይ ይደረግ ።

ይህን ሼር በማድረግ በአጠቃላይ የብሄር ተኮር ጥቃት ተግባር እናውግዝ። በተለይ ደግሞ በማራ ክልል እየተፈፀመ ያለው ተከታታይ የሆነና ሃላፊነት የጎድለው ብሄር ተኮር ጥቃት ነውና አምርረን እናውግዝ።

Back to Front Page