Back to Front Page


Share This Article!
Share
ሴቶችን ወደ ላይኛው የስልጣን እርከን በብዛት በማምጣት ብቻ የሴቶችን ተሳትፎ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አይቻልም

 

ሴቶችን ወደ ላይኛው የስልጣን እርከን በብዛት በማምጣት ብቻ የሴቶችን ተሳትፎ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አይቻልም

ፍስሃ መረሳ  11/06/2018

አገራችን ባለፋት ሁለት አስርት ዓመታት በተከለችው ትክክለኛ የልማት መስመር ሴቶች በተፈለገው መንገድ ባይሆንም በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚነታቸው ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መጥቷል ፡፡ በተለይ ለትምህርት መስፋፋት በተሰጠው ልዩ ትኩረት በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ፡፡ በጤና ረገድም መሰረታዊ የጤና እንክብካቤ ባቅራቢያቸው በማግኘታቸው የእናቶችና የህፃናት ሞት በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ የራሱ አስተዋፅኦ አድርጓል ፡፡ በሌሎች የመሰረተ ልማት የመጡ ውጤቶች ሲታዩም ቅድሚያ ለሴቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዳደረጉ ማንም የሚመሰክረው ሃቅ ነው ፡፡

Videos From Around The World

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከነበረው የብዙ ዓመታት የተከማቸ ችግር ሲታይ ከልማቱ በተፈለገው ደረጃ ተጠቃሚ መሆን ስላልቻሉ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እየሆነ እንደመጣና ለአገራዊ ቀውሱ መፈጠር የራሱ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ይታወቃል ፡፡ ይህ የሴቶች የልማት ተጠቃሚነት መጓደል መነሻውና ምክነያቱ ሲታይ የታያዘው የልማት መንገድ የማያስኬድ በመሆኑ ሳይሆን ችግሩ በየደረጃው የነበረ አመራር የተቀመጠው የልማት አቅጣጫ በመተግበር ረገድ ያሳየው የአፈፃፀም ጉድለት መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡

ይህ ማለት የአገሪቱ ከ 50 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሴቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ መስመር አብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመር መሆኑ በተግባር የተረጋገጠና ከዛ ውጪ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ሴቶች ራሳቸውም ቢሆን በትከከል ለገነዘቡት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ለማስቀመጥ ነው የተፈለገው ፡፡
አሁን በለውጥ ስም በቅርቡ 50 % የሚሆኑ ሴቶች ወደ ከፍተኛ ስልጣን እንዲመጡ በመደረጉ ይህ አካሄድ ለሴቶች ይጠቅማቸዋል ወይስ ለጊዜውም ቢሆን እነሱን ለፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ የመጨረሻ ውጤቱ ግን ሴቶችን ሊጎዳ የሚችል አካሄድ ነው የሚል በትክክል መገንዘብ ያስፈልጋል ፡፡

በመሰረቱ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተሟላና ባስተማማኝ መልኩ ሊረጋገጥ ሚችለው እንደ አገር የያዝነው የልማት የዴሞክራሲ ጉዞ በተገቢው መንገድ ሲፈፀምና እድገታችን በነበረው ፍጥነት መቀጠል ሲቻል ብቻ መሆኑ ግልፅና የማያሻማ ጉዳይ ነው የሚሆነው ፡፡ አሁን ሴቶች ተጠቅመዋል ወይ አልተጠቀሙም ልንል የምንችለው በኣብዛኛው በእርሻ የተመሰረተ ኑሮ የሚገፉ ሴት አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች እንዲሁም በከተማ የሚኖሩ ሴቶች ሂወት በመሰረቱ የመቀየር ጉዳይ እንጂ የ10 ካብኔ ኣባላት ወደ ስልጣን የመምጣት አለመምጣት ጉዳይ አይደለም ፡፡

ሴቶች የሚጠቀሙበት ስርዓት ሊገነባ የሚችለው የአገሪቱ ህገመንግስታዊ ስርዓት ተከብሮ በበለጠ በግጭትና ግርግር ተጠቂ የሆኑትን ሴቶች ሰላማቻው ተጠብቆ እንደፈለጉት መንቀሳቀስና ሰርተው መኖር ሲችሉ ነው ፡፡ የሴቶች ወደ ስልጣን መምጣት ትርጉም ሊኖረው የሚችለውም ይህን የሴቶች ፍላጎት ለማሳካት እስከጠቀመ ብቻ ነው ፡፡
ታድያ አሁን በአገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ሲታይ በመቶ ሺዎች እናቶች ከመኖር ቤታቸው ተፈናቅለው በበረሃ ያለ በቂ ምግብና ሕክምና ብዙ እናቶች በተጠለሉበት በረሃ ያለ በቂ ድጋፍ እየወለዱ ባሉበት አንዳንዶቹ ለሞት በተዳረጉበት ሰኣት የነዚህ ችግር በመሰረቱ መፍታት ያልቻለ መንግሥት ለጊዜያዊ ፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ታስቦ ካልሆነ በስተቀር በየትኛው መመዘኛ ነው ለሴቶች የተለየ ትኩረት ተሰጥቷል ማለት የሚችለው ? ይህ ጉዳይ በተገቢው መንገድ መታየት ያለበት ነገር ይሆናል ፡፡

ስለዚህ አጠቃላይ የተያዘው የልማት የሰላምና የዴሞክራሲ ጉዞ በተቀመጠው አቅጣጫ መተግበር ካልቻለና የሰፊው ድሃው ህዝብ የልማት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የሚመልስ ፈጣን እድገት የማረጋገጥ ጉዳይ በቂ መልስ ሳያገኝና አገራችን ወደ ነበረችበት ሰላምና መረጋጋት መመለስ ካልቻለች ሴቶች ስልጣን ላይ በብዛት መምጣታቸው የሚፈይደው ነገር እንደሌለ በመገንዘብ በስልጣን ላይ ያሉትንም ጭምር በተሟላ መንገድ የሴቶች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ጠንክረው መታገል ይኖርባቸዋል ፡፡

 

Back to Front Page