Back to Front Page


Share This Article!
Share
በመዳከም ላይ ያለው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ትግል የሚቀጣጠልበት ሰዓት አሁን ነው

በመዳከም ላይ ያለው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ትግል የሚቀጣጠልበት ሰዓት አሁን ነው

 

ታጁ ሙሓመድያሲን  03/01/2011ዓ/ም                                                   muhamedyassintaju@gmail.com

 

 

በመዳከም ላይ ያለው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ትግል የሚቀጣጠልበት ሰዓት አሁን ነው።

በዳግም በጥልቀት መታደስ ወቅት የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት ታስቦ የታሰሩት ህገ መንግስታዊ ስርዓት በሚፈቅደው መሰረት እንዲፈቱ፣በውጭ ያሉ ተቃዊሚዎች እንዲገቡ ኢህአዴግ መወሰኑን ይታወሳል።

ይሁን እና ባለፉት 5 ወራት በተግባር የታየው በአገር ክህደትና ሽብርተኝነት ምክንያት የተፈረደባቸውን እሰረኞች ጨምሮ በምህረት እንዲፈቱ፣ቅንጣት ታህል ነፃ መሬት ንሯቸው የማያውቁ "ነፃ አውጪ"ምህረት ተሰጥቷቸው ወደ አገርቤት እንዲገቡ፣በአሜሪካና አውሮፓ ሃገራት በየጎደናውና መንገዱ ሰልፍ በመውጣት፣ፅሑፍ በመፃፍ ተቃውሞ የሚያሰሙ የነበሩ ተቃዋሚዎችና በኢትዮጵያ በተካሄዴው የተራዘመ የትጥቅ ትግል ተሸነፈው ወደ ውጭ አገር የኮበለሉ የደርግን ባለ ስልጣናት ሳይቀሩ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ከመግባቱ በፊት ተጠቃልለው አገር ቤት እንዲገቡ ተደርገዋል።ከእስር ለተፈቱትና ምህረት ተደርጎላቸው ወደአገራቸው ለገቡት ህገ መንግስታዊ ስርዓት በጣሰ መንገድ ጭምር"የጀግና"አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Videos From Around The World

የትምክህተኛው ጎራ ከላይ በተጠቀሰ መንገድ በሚጠናከርበት ወቅት የአብዮታዊ ዲሞክራስያውያን ሐይሎች አደረጃጀት ኩፍኛ የተዳከመትና መበታተን የታየበት፣ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት አገሪቱ መምራት ተስኖት በመንጋ ፖለቲከኞች መመራት በመጀመርዋ 2.8 ሚልዮን ህዝብ የተፋናቀሉበት፣የዜጎች ንብረት በጠራራ ፀሃይ የሚዘረፍበት፣በ100ዎች የሚቀጠሩ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገደሉበት አልፎም ተርፎም ህዝብ በተሰበሰበት አደባባይ በመንጋ ፖለቲከኞች ዜጋ በአድባባይ እንደበግ ተሰቅሎ የተገደለበት፣ በአዲስ አበባ እምብርት በአብዮት አደባባይ እንጅነር ስመኝ በቀለ የተገደለበት፣በሰኔ 16/2010ዓ/ም ለድጋፍ ሰልፍ በወጡ ንፁሃን ዜጎች ቦምብ ፈንድቶ የሰው ሂወት የቀጠፈበት 5 ወራት አልፈዋል።

በሌላ በኩል ኢህአዴግ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በማሰብ በመንግስት እጅ የሚገኙ የንግድ ተቋማት በኪፊልና ምሉ ለሙሉ ወደ ግል ለማዛውር መወሰኑን የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው።ይህም ተግባራዊ ለማድረግ የተኬሄደበት አቅጣጫ ችኮላ የበዛበት ከመሆኑም በላይ የውስጥ ዓቅምን በሚፈጥሩ እንደ ግብርናና አምራችኢንዳስተሪ የመሳሰሉ የኢኮኖሚ ዘርፎች መምራት ይቅርና ለስሙ የማይወሱበት ደረጃ ተደርሰዋል።

ኢህአዴግ በአስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የኢትዮጵያና ኤርትራ ወደሰላም ጤረጴዛ እንዲመጡ ሁለቱም መንግስታት በመንግስት ደረጃ ያሳዩት መነሳሳት የሚደነቅ ነው።የዘላቂ ሰላም ባለቤት ህዝቡ ሁኖ ሳለ መንግስት ለመንግስት በሚፈጥሩት ግንኙነት ብቻ ለመጨረስ እየተካሄደ ያለውን አካሄድ ግን የተጀመረው የሰላም ግንኝነት እንዳይቀለበስ የሚል ስጋት እንዲፈጠር አድርገዋል።በተለይ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በአፋጣኝ እንዲጀመር በህዝቦች የተደረገ ትግል እያየለ በመጠበት ወቅት ጭምር ሁለቱን መንግስታት ያሳዩት ዳተኝነት የሰላም ስምምነቱ በህዘቦች ዘነድ ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ ምክንያት ሁነዋል።

ከላይ እንደተጠቀሰው በዚህ 5 ወራት አንድአንድ ቦጎ ጅምሮች ቢኖሩም በአመዛኙ የትምክህተኞችና ፀረ ህዝብ ጎራ(ካምፕ) ተጠናክሮ የታየበት በአንፃሩም የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ትግል የተዳከመበት ወራት ነበሩ ለማለት ያስደፍራል።

ነሓሴና ጳግሜን የተካሄዱ ሁለቱ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባዎች በኋላ በኢህአዴግ ውስጥ አንአንድ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች እየታዩ ናቸው።ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የተሰጡ ሁለቱን መግለጫዎች የአብዮታዊ ዲሞክራስን አስተሳሰብ ወደ ነበረበት ቦታ የመመለስ አዝማምያ እንዳለ አመላከተዋል።አንድአንድ ለማህበራዊ ሚድያ የሚፅፉ(አክቲቪስቶች)ሳይቀሩ ወያናይ/አብዮታዊ ዲሞክራስያውያን ሓይሎች/የበላይነትን ለመቆጣጠር የሚያስችላቸው ትግል እያካሄዱ እንዳሉ የሚያመላክት ፅሑፎች እስከመፃፍ ደርሰዋል።ይህ ተስፋ ሰጪ ምልክት ወደ ኢህኣዴግ ምክርቤትና ኢህአዴግ ጉባኤ ከተዳረሰ እንዲሁም የኢህአዴግ አባል ድርጅት አባላትና መላው የአቤታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመር ባለቤት ብዙኋኑ ህዝብ ከተዳረሰ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስታሰሰብ በተሟላ መንገድ የበላይነቱን ይቆጣጠራል።ስለዚህ የተዳከመው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ትግል የሚቀጣጠልበት ሰዓት አሁን ነው።

የኢትዮጵያ አብዮታዊ ዲሞክራስያውያን ሐይሎች የልማታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ 04/01/2011ዓ/ም በሚካየደው የኢህአዴግ ምክርቤት ስብሰባ የበላይነት እንዲኖሮው ለመፋለም ተዘጋጅታችሁ መግባት ይገባችኋል።ኢህአዴግ ያስቀመጣቸው አቅጣጫወች ለምን ምህዋራቸው እንዲለቁ እንደተደረገ፣ህገ-መንግስትና ህገ መንግስታዊ ስርዓት ለምን እንደተጣሰ፣አገሪትዋ በመንጋ ፖለቲካ ስትመራ ህዝቦች ከቄያቸው ሲፈናቀሉ፣ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣የህዝብ ንብረት ሲወድም ሲዘረፍ፣የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ምን እየሰራ እንደነበረ፣ተጠያቂ በተቋምና በግለሰብ ደረጃም እንዲቀመጥ ያላሰለሰ ትግል ማድረግ ይጠበቅባችኋል።ከዚህ በተጨማሪ የልማታዊ ዲሞክራሲ መስመር የተከተለ እቅድ እንዲታቀድና ተግባረዊ እንዲሆንም መረባረብን ይጠበቅባችኋል።

የኢትዮጵያ አብዮታዊ ዲሞክራስያውያን ሐይሎች በኢህአዴግ ምክሪቤት የምትጎናፀፉትን ድል ለማስጠበቅ በኢህአዴግ ጉባኤ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችል ትግል ማካሄድ አለባችሁ።ከዛም አልፎ ወደ አባላትና ብዙኋኑ ህዝብ ትግሉ መሸጋገር አለበት።ብዙኋኑ ህዝብ አብዮታዊ ዲሞክራስያውያን ሐይሎች የሚመሩት ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል እንደሚደግፍ ጥርጥር የለውም።

ድል ለአብዮታዊ ዲሞክራስያውያን ሐይሎች!

ድል ለሰላም ወዳዱ ህዝብ!

ዘለአለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማእታት!  

 

Back to Front Page