Back to Front Page


Share This Article!
Share
ጥርጣሬን የሚዘሩና ጠብን የሚጭሩ

ጥርጣሬን የሚዘሩና ጠብን የሚጭሩ

ይቤ ከደጃችውቤ 10-20-18

ያለንበት ዘመን ሉላዊነት ማለትም(Globalization) ነው። ዓለም ወደ አንድ መንደርነት እየተንደረደረች ያለበት ዘመን ነው። ዘመኑ የመረጃ ዘመን በመሆኑ በአንድ አካባቢ የሚከወኑ ክስተቶች በቅፅበት ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚዳረሱበት ነው።ለዚህም ዘመኑ የፈጠረው ማLበራዊ ድረ ገ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።ሰሞኑን አንድ አብሮ አደጌ ሳይታመም በድንገት አረፈ።እኔን ጨምሮ አብሮ አደጎቹ ፎቶውን ለጥፈን በየረሳችን ፌዝ ገፅ አንረሳህም የሚል መልዕክት አሠራጨን፣ የተሰማንን ሀዘን ለመግለፅ ሞከርን ።ሆኖም በዐረብ ሀገር ያለችው እህቱ ብዙ ገፆች ላይ ፎቶውን ዐይታ ወንድሜ ምን ሆኖ ነው?ብላ ጠየቀች።በግሌ መሳሳቴን አምኜ ለወደፊት ትምህርት ወሰድኩበት።የተሰማኝን ስሜት እንኩዋ መግለፅ ከፈለግሁ በጣም ዘግይቼ መሆን እንደነበረብኝ ተገነዘብኩ።

Videos From Around The World

በሀገራችን ባህልና ወግ መሠረት አንድ ሰው የቤተሰብ ሀዘን ቢያጋጥመው መኪና እያሽከረከረ"በእግር እየተዘዋወረ"ወይም ሥራ እየሠራ ባለበት የጋጠመው ሀዘን በድንገት ሊነገረው አይችልም።ወደ ቤት እንዲመጣ ተደርጎ አረጋግቶ የደረሰበት ችግር ወይም ሀዘን ወዳጅ ጎረቤት ይነገረዋል።መንገድ ላይ ቢነገረው አደጋ ያጋጥመዋል በሚል ዕሳቤ ነው ወዲያው የማይነገረው።ዘመናዊውን የመረጃ ቴክኖሎጂ የማያውቁት ቤተሰቦቻችን ባልተፃፈ ሕግ ይህንን ሥርዓት ዘርግተውልን ቆይተዋል።ከላይ አንደገለፅኩት እኔና ደኞቼ ግን ለJች አብሮአደግ ወዳጃችን ያለንን ሀዘንን የነበረንን ፍቅር ለመግለፅ በለጠፍነው ምስል ዐረብ ሀገር ያለች እህቱ ወንድሜ ምን ሆነ?ምን ችግር ተፈጠረ?ብላ እስክ መጠየቅ የደረሰችው እኛም የሚመጣውን ተፅዕኖ ሳናስተውል በማወቅም ይሁን ባለ ማወቅ ባህላችንና ወጋችንን የመጣሳችን አንዱ ማሳያ ነው።

ማLበራዊ ድረ ገጽ ከሚያበረክተው አዎንታዊ አስተዋፅዖ ጎን ለጎን በአሉታዊ ጎኑ እያሳደረ ያለው ተፅዕኖ የገነነ ነው።በተለይ face book የፌዝ ገፅ በመሆን እያገለገለ ነው ማለት ይቻላል።የተማሩትም እያወቁ"ያልተማሩትም ሳያውቁ"እንቶ ፈንቶውን እየጫሩና እያሰራጩ የባጥ የቆጡን እየቀባጠሩ ሕዝብን ከሕዝብ"ብሔርን ከብሔር እንዲሁም ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማነሳሳትና ለማጋጨት እየጣሩ ነው። ሠራተኞችም በሥራ ሰዐታቸው ፌስ ቡክን በማየት ሰዐታቸውን እየገደሉ ሠርቶ የሚገባ ሰው ለመሆን ይሞክራሉ።ወጣቶችም በማLበራዊ ሚዲያ ዋዛ ፈዛዛውን እያዩ ጥርጣሬን የሚዘሩ"የሚያሠራጩና ጠብን የሚጭሩ ሆነዋል ።

ስብሰባ በሚደረግባቸው ትልልቅ ቦታዎች ሳይቀር ተሰብሳቢዎች የተሰበሰቡበትን ዓላማ ዘግተውና ዘንግተው የኪስ ስልካቸውን አየከፈቱ እንደ ህፃናት የሚጫወቱ ፣የፌዝ ገፃቸውን በማየት ጊዜውን የሚያሳልፉ ብዙዎች ናቸው።ጠንካራ የቀረፃ ባለሙያዎች እንደዚህ ዓይነት እንከኖችን በቴሌቪዥናቸው እያሳዩ ተሰብሳቢዎችም እንዲነቁ፣ ተመልካቾችም እንዲስቁ ቢያደርጉ መልካም ነበር።መገናኛ ብዙሃንም በማLበራዊ ድረ ገጽ የሚተላለፉ መልዕክተችን በማየት ችግርና ግርግር እንዳይፈጠር መጣር የሚመለከተውን ክፍል በማነጋገር አፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚጠበቅባቸው ሃላፊነት ነው።ለዚህም ንቁ ሆነው ተዘጋጅተው ለፈጠራ ወሬዎች ምላሽ የሚሰጡ ዘገባዎችን ማዘጋጀትና ማሠራጨት ተልዕኮዋቸው መሆኑን ማስተዋል አለባቸው።

ኢትዮያውያን በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሀሳብን የመግለፅ መብት ተረጋግጦላቸዋል።ሀሳብን የመግለፅ መብት ሲረጋገጥ ግን የተወሰነ ገደብ ተጥሎበት ነው። ሕዝብን በሕዝብ ሃይማኖትን በሃይማኖት ላይ የሚያነሳሱ መረጃዎችን ማሰራጨት የተከለከለ ብቻ ሳይሆን በወንጀልም የሚያስቀጣ ነው።አሉታዊ መልዕክቶችን በሚያመነጩና በሚያሠራጩ አካላት ላይ ገደብ ተጥሎ አደብ እንዲገዙ ማድረግ አስፈላጊ ነው።አዎንታዊ መልዕክቶችን ለሚያሠራጩ አካላትም የማበረታቻ ሥርዓቶች ቢዘረጋም መልካም ነው።

የኢህአዴግ አባላት በሀገሪቱ ቀደም ሲል በየቦታው ሲታዩ የነበሩ ቁርሾዎችን ለማስወገድ በወሰዱት እርምጃ የአመራር ለውጥ ተደርል።የአመራር ለውጡን የመራራቸው አንዳንድ አካላት በየቦታው ግጭቶችን ለመለኮስና ለመቀስቀስ ሲፍጨረሩ ይታያል።ከነዚህም የዕኩይ ድርጊቶች ማቀጣጠያ መድረኮች አንዱ የማLበራዊ ድረ ገጽ ተጠቃሽ ነው።የማLበራዊ ድረ ገጽ መረጃዎች በፍጥነት ስለሚደርሱበት የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ሕዝብን ለማጋጨት የሚተጉ ብዙ ዜጎች ተጥድው ይውሉበታል ማለት ይቻላል።

በሌሎች ሰዎች ስም ማLበራዊ ገጽ ከፍተው ሌት ተቀን ጠብ ለመጫር የሚንቀሳቀሱ አካላት ዋነኛ ዓላማቸው መረጃ ማሠራጨት ሳይሆን የተገኘውን ለውጥ መቀልበስ ነው።እንኳን ባለንበት በዚህ ዘመን የጋዜጣ በሌለበት ዘመን ሳይቀር የአሉባልታ ጠንቅ የከፋ መሆኑን ቀደምት ወላጆቻችን በብሂላቸው ሲናገሩ ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ብለዋል።በዚያ የመረጃ ቴክኖሎጂ ባልተስፋፋበት፣ መረጃ ከኤሊ እጅግ ባዘገመ መልኩ በሚዳረስበት ጊዜ ያን ያህል ተፅዕኖ ካመጣ ባለንበት መረጃ በብርሃን ፍጥንት በሚዳረስብት በዚህ ዘመን ደግሞ ጉዳቱ ምን ያህል የከፋ እንደሚሆን ማስተዋል ተገቢ ነው። በተደጋጋሚ ለዕኩይ ድርጊት ማLበራዊ ሚዲያውን የሚጠቀሙ ዜጎችም ላይ ርምጃ መውሰድ፣ ተጠያቂ ማድረግ ወይመ መስመሩ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል።

ባለፈው ወር የጋሞ ሽማግሌዎች ግጭትን ለማስወገድ ተንበርክከው ለምለም ቄጠማ ይዘው የፈጠሩት ሰላም ሀገሩ ሁሉ አወድሷቸዋል።ወጣቶችም ባህላቸውን አክብረው የጎሣ መሪ አባቶችን ተቀብለው ታዘው ከግጭት በመቆጠባቸው ምስጋና ይገባቸዋል።ይህንን በጎ ዓላማ ያለውን ምስል ያሠራጩ ሰዎችንም እናደንቃለን። ነገር ግን ይህን ምስል በቅድሚያ ያሠራጩ ሰዎችም በአካባቢው ባህል መሠረት እንዳስፈላጊነቱ ዕውቅና ልንሰጣቸው ይገባል። የሠሩት ሥራ የሰላም ሥራ ነው።ሌሎች ሰዎች የነሱን በጎ ዓላማና አርአያ ተከትለው እንዲዙ መነሾ ይሆናል።

ማLበራዊ ሚዲያ ጠባሳውን ወይም ተፅዕኖውን በዐረብ ሀገሮች በፈጠሩት ሁከት ማስተዋል ይቻላል።እንደ ግብፅ ያሉ በተፈጠሩ ውዥንብሮች ዜጎች ተጎድተው የሆስኒ ሙባረክ አመራር ከወደቀ በ=ላ እንኩዋ የመሐመድ ሙርሲ አመራር ቢቀጥልም ችግሩ ግን ሊgጭ አልቻለም ነበር።የአብዱል ፈታህ አልሲሲ አመራር ሥልጣኑን ከተረከበ በ=ላ ግን ሀገሪቱ አንፃራዊ ሰላም አግኝታ መረጋጋት ችላለች።‘እነ ቱኒዝያ፣ ሊቢያ እና ሶርያ የመሳሰሉ የዐረብ ሀገራት የዚህ ማዕበል ተጠቂዎች ከነበሩ መካከል ናቸው።

መንግሥትም ማLበራዊ ድረ ገጽ አጠቃቀም ዙሪያ ሊያወጣ ያቀደው ሕግ ለሀገር ደLንነት እና ለውጡ እንዳይቀለበስ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ በአዎንታዊነት የሚቀበሉት ነው።ይህም ማLበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ ዘገባዎች ሕዝብን ከሕዝብ እንዳያጋጩ የሃሰት መረጃዎች እንዳያሰራጩ ለመቆጣጠር የሚቻልበት መንገድ ይሆናል ተብሎ ይገመታል።ሕጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ሰሞኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ማLበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ሥርዓት ያለው አሠራር ለመዘርጋት በሚያስችል መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል።ይህም ሲፈልጉ ብሔራቸውን ሲያሻቸው ፆታቸውንና ስማቸውን አየቀያየሩ ለዕኩይ ዓላማ የመጠቀሙበት ዜጎች ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉበት ሥርዓት ይዘረጋል ማለት ነው።

 

Back to Front Page