Back to Front Page


Share This Article!
Share
መናገሻ ከተማ


መናገሻ ከተማ

 

በላይ ግዛው 09-28-18

 

አንዳንዴ ነጮች እንደሚሉት you have to think outside the Box ፡ ይሄው ከBoxሱ ውጭ እያስብኩኝ ነው ከታች የምተቼው።

በ16/1/11 አቶ በቀለ ገረባ ስለ ፊንፊኔ/ አዲስ አበባ ምንነትና ለቤትነትን ብሎም የኦሮሞ ንብረትነትን መሆንዋን በማያዳግም ለማረጋገጥ መላ  የኦሮሞ ድርጅቶችን ወክለው ተናግረዋል። 

 

Videos From Around The World

የፍክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል እንደሚሉት: ሁለት ቢሔርተኞች አዲስ ኣበባ ነው ስምዋ: የለም ፊንፊንኔ ነው የምትባለው: የትኣባትክና፡ ምን ትባል ምን የኔ ነች: ለም  የኔ እንጂ : ሲባባሊና: ሲወነጃጀሉ፡ ሲደባደቡና፡  ሲደበድቡ፡ ሲገዳደሉ፤ ሲገድሉ፡ ሲፈራሩ ሲያስፈራሩ፡ ቀናት :ወራት: ኣመታት አስቆጥሮ ከተማዋ እየታመስቻ አትበላ አትጠጣ ከሆነች ቆይታለች።

 

ይባስ ብሎም ለዓንድ ብሔር (ኦሮሞ) የተለየ ጥቅም  መጠበቅና ማስከበር (special interest) ግዳጅ እንዳለባት ሲደነገግ፡ ከፌደራል ቁጥጥር ውጭ በቢሔር የተደራጁ ፓሊስ ኃይልና ልዪ ልዪ መንግሥታዊ ኣካላት ሲተገበሩላት፡ ለሁሉ ኢትዮጽያዊ የማያጠራጥር የጋራነት ስሜት ብሎም መብትና እኩልነት የጎደላት ክፍለ መሬት: ሓገራዊና : ሁለገብ መንግሥታዊ መናገሻ ከተማ  ልትሆን በጣም ያስቸግራል።

በድሮ በሬ ያረስ የለም እንደሚባለው፡ እንዴውነቱ አነጋገር ከሆነ የአዲስ አበባ ባለቤት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሕዝብ ነው መወስን ያለብት።  አለበለዚያ ባለቤትነትዋ አሁን ካለው ነዋሪ ሕዝብ ቀድም ብሎ የነበረ ሕዝብ ወሳኝ ከተባለ፡ ቀድመ፡ ቀደም ብሎ የነበረ ሕዝብ ደግሞ የለም አዲስ አበባ የኔው ነበረች ስለዚህ አሁን ለኔ ትገባለች ሊል ነው፡ እና ነገሩ ማለቂያ የለውም፡ ልክ እንደ ቀይ ኢንዲያኖች (.  ) ኣሜርካ የነጭ ሳይሆ የኛ ኢንዲያኖች ነው አሁኑኑ ይውጡ እንደማለት.ም፡ ሲሆን ነጮች ጔዛቸው ጠቅልለው አሜን ብለው ይወጣሉ ብሎ እንደማስብ ይሆንስል።

 

ዳሩ ግን ይህ አጨቃጫቂ አመለካከት ወደጎ እንተውና ሌላው አማራጭ እንከተል፡፡ ዋናው ኣላማችን ኣዲስ አበባ የማን ናት ሳይሆን መናገሻ ከተማ ከማን ተወስዳ ለማን ጥቅም ተውላለች ነው።

 

 

ከዚህ ሁሉ ተሻግሮ ማንም ኢትዮጽያዊ ከዛም ኣልፎ ማንም ስው ከየትም ይሁን ከየት፡ ማን ይሉት ቋንቋ ይናገር/አይናገር፡ ያለ ምንም ስጋት የሚንቀሥቀስባት፡ በንብረቱና በሕይወቱ ስጋት የማያድርበት ከተማ፡ እንደመሆን ቀርቶ: አሬንጔዴ ይሁን ብጫ፡ ቀይ ይሁን ስማያዊ፡ ነጭ ይሁን ጥቁር፡፡ የአዞ ቅርጽ ይለጠፍበት ወይም ዲያብሎስ ጦር ትክሻው ላይ ተሸክሞ የሚንጎራደድበት  ስንደቅ ባንዴራ ያውለብልብ: በማያስቸግር  ሁኔታ በሁሉም ያገር ልጅ  ባይ ነኝ ፍላጎትና ታሪካዊ አመጣጥ የተመረኮስ መናገሻ ከተማ መመስረት እንደምርጫ መውስድ ወቅታዊ መስሎ የሚታይበት ጊዜ ነው።

 

እንድህ አይተቱ ሁለገብ (ሁሉ አቀፍ) ከተማ በወቅቱ ከሌለ (በእርግጥም በአሁኑ ስዓት የኢትዮጽያ ሁኔታ እንደሌለ ነው የሚያመላክተው)። አንድ ከተማ እንደመናገሻ ሲገነባ የከተማው ቅድመ ነዋሪዎች እንደፀጋ ይህ አጋጣሚ ወስደው መኩራትና መደስት ሲኖርባቸው፡ የለም ከተማችን ከኛ ተነጥቆ መናገሻ ስለተደረገ ለኛ ብሔተስቦች፡ ለቌንቌችንና ለባሕላችን ልዩ ጥቅምና  ትኩረት ሊስጥን ይገባል እንደማንኛው መጤ መታየት የለብንም ብሎ ማኩረፍ ወይም ብትር ማንሳት ተገቢ ኣይድለም። 

የከተማው መብቱና ባለቤትነቱን ለፌደራል መንግሥት እንደመልቀቅ፡ ባል ፈልገሽ ጥምም ጠልተሽ እንደሚሉት እንቆቅልሽ፡ የከተማ እድገትን ተፈልጎ የኔ ባይነት ትምክህተኝነትም ተጎናፁፎ ሕግን ያላስከበረ፡ ለማስከበርም ፍቃደኛነት የተጔደለው ከተማ እንደ መናገሻ ከተማ ዘላቂ ኣገልጋይነት የለው።

 

ለዚህ መፍትሔ ረዢምና ኣስቸጋሪ ቢሆንም፡ ብዙ ወጭ የሚጠይቅ ቢሆንም ላንዴ ለመጨረሻም ስላምና ተመንፈስ እረፍት የሚስጥ ኣማራጭ፡ ቢሆን ኑሮ ሁሉንም ቢሔሮችና/ቢሔረስቦች የሚያካትት ደምበር፡ ኣለበለዚያ በዛ ያሉትን ቢሔሮች/ብሔረስቦች የሚያካትት/የሚያዋስን መሬት ከቢሔረስቦቹ ተገምሶ/ ተወስዶ የጋራ መናገሻ ከተማ፡ ከሁሉም የሚያኮራ ሁሉም የሚያጋራ፡ መመስረት አስፈላጊ አማራጭ  መሆኑ ከአሁኑ መታስብ ብሎም መተግበር ያለበት አላማ ይመስለኛል:: ለምሳሌ አንድ ምርጫ፡ አዋሳኝ መሬት ከትግራይ፡ከአማራና ከአፉር፡ ወይም ሌላው ኣማራጭ ከኦሮሞና፡ ሱማልያ፡አፉር፡ ኣዋሽ ኣካባቢ ጨምሮ የሚያጠቃልል መሬት በጋራ ስምምነት ተገጥሎ/ተወስዶ እንደ መናገሻ ቢቆረቆር ላለው መፍትሔ ሊሆን ይችላል። 

መሬት ለስጡት ቢሔሮች ትርፍ ምንድን ነው ቢባል ለቢሔራቸውና  (multiplier effect) የጋራ ሀገራቸው እድገት ተጠቃሚነት በቂ ምላሽ ሊሆን ሲችል፡ መሬቱ የሚያዳብሩት ግለስቦች/ኩባኒያዎች መሬቱ ከመንግሥትም ሆነ ከግለስብ በግዥ መሆኑን መገንዘብ ይኖርንባቸዋል።

 

ከዚህ በተረፈ ሓገርራዊ መናገሻ ከተማ ለማንም ይሁን ለማን ልዪ መብት (special interest) ቌንቌም ይሁን ባሕላዊ አድልዎት መስጠት የለበትም መስጠትም አግባብ አይደለም። 

 

ኣንድ ሐገር ኣለ ከተባለምሐገር የጋራ ነው። መናገሻ ከተማም ኣለ ከተባለ መናገሻው የጋራ ነው። ባንድ መናገሻ ከተማ ባለመብትና መብተአልባ ባይቶዋር መኖር የለበትም:: ሲያሻቸው ግቡ ሲከፉቸው ልቀቁ፡ ውጡ የሚባልበት ከተማ መሆን የለበትም።

 

 

Back to Front Page