Back to Front Page


Share This Article!
Share
ስሜታዊ ድጋፍና እውቅና ወዴት ያደርሰናል?

ስሜታዊ ድጋፍና እውቅና ወዴት ያደርሰናል?

ከኣሉላ የውሃንስ 30 ነሃሰ 2010 ዓ/ም

 

ሰው ስሜቱን መግዛት፣ መግራትና መቆጣጠር ከልቻለ ከወዳጅ ዘመድ ያጣላል፣ ወደኣዘቅት ያስገባል፣እድሜንም ያሳጥራል፡፡ ይህ ብቻ ኣይደለም ራሱ በፈጠረው የዘር ጥላቻ ለታናናሾቹ በሲሪንጅ ወደጭንቅላታቸው ካስገባ ታናናሾቹ ስላለፈው የህዝቦች መስተጋብር ምንም ዓይነትግንዛቤ ስለlማይኖራቸው ከዘለፋ ባሻገር እንደ እሳትራት በመንጋነት እየተወረወረ ጠላት በሚለው ህዝብ ላይ ከማሳደድና ከመጨፍጨፍ እስከ መግደል፣ ኣገዳደሉም የትም ዓለም ተደርጎና ተሰምቶ በማያውቀው ሁነቴ በድንጋይና በበትር ተቀጥቅጦ፣ እንደበግ ተዘቅዝቆ ተሰቅሎና ተጨፍጭፎ፣ በእሳት እንዲቃጠል ተደርጎ በሂወቱ እያየ ጉድጓድ ውስጥ ኣስገብቶ ኣፈር ላይላዩ ተጭኖበት፣ ወዘተ በተግባር ኢትዮጵያ የሲኦል ምድር እስክትመስል ድረስ ግፉ እንዲበረታ ሆነዋል፡፡

ይህንን ኣካሄድና የጥላቻ ፖለቲካ ለስልጣን መወጣጫና ኣንድን ዘር ቢሞትም ኣላምነውም በሚመስል ኣካሄድ ሙሉ በሙሉ ስልጣኑ ቢቀማም ማሳደዱና ጥቀርሻ መቅባቱ፣ ንብረቱና ሃብቱ ማውደምና መዝረፉ በስፋት እየተካሄደ ባለበት ወቅት ያስታወሰኝ ኣንድ ነገር ኣለ ይኸውም ቀዳማዊ ሃይለስላሰ ለሁለተኛ ግዜ ጣልያነ ኢትዮጵያን ለመውረር በመጣበት ግዜ ህዝቡን ጥለው እግሬ ኣውጭኝ ብለው ወደለንደን ሸሽተው በኣራቱም የኢትዮጵያ መኣዝነናት ኣርበኞቻችን ባደረጉት ተጋድሎ በመውደቅያው መጨረሻ ገደማ ከተሸነፈ ተመልሰው መጥተው የኢትዮጵያ ንጉስ መሆን እንደማይችሉ ስለወቁ የእንግሊዝ ጦር እርዳታa ጠይቀውና ይዘው ሲገቡ በየመኣዝኑ የነበረው ኣርበኛ ደስተኛ ኣልነበረም ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ተቃውሞም ደርሶባቸው እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል፡፡

Videos From Around The World

በዚሁም ምክንያት ኣልገዛ ያለ በእንግሊዝ የውግያ ኣውረፕላኖች እየተጨፈጨፈ ኣሜን ብሎ እንዲገዛ ተደረገ፡፡ ከሁሉም የበለጠ ተቃውሞ ደርሶባቸው የነበረም ከትግራይ መሆኑ ይታወቃለ፡፡ ተድያ በዚህ ምክንያት ስንት ውግያ ተካኤደ፣ በእግር የማይበገር ሆኑ ሲያገኙት ከሰማይ በናፓል ቦምብ እንዲደበደብ ተደረገ፡፡ ከብዙ ድብደባና ጦርነት ቀዳማይ ወያነ ተሸነፈ፡፡

ከዛም ይህንን መሰል ተቃውሞ እንዳይነሳ የትግራይ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ኣቅም ለማላሸቅ ሰራዊት በመደበኛ ለኣመታት ከገበሬው ጋር እንዲኖር ታዘዘበት፡፡ ሁሉም የምግብ ነገር ገበሬው እንዲችለው ተደረገግን በዘዚህም ኣላበቀም እያንዳንዱ ገበሬ የሚመደቡት ነፍጠኞች ገበሬው እንዲበሉ ሲያሳጥባቸው ለታጠቡበት ለእያንዳንዳቸው ኣምስት ፍራንክ እንዲከፈሉም ይደረግ ነበር፡፡በዚህ ብቻ ኣላበቃም ትግራይ ሃብታም ነው በሚል የሸት ብሂል ከሌሎች ክልሎች ከፍ ያለ ግብር እንዲከፍል ተደረገ፡፡ በዚሁም ሰበብ በርከት ላሉ ዓመታት በድህነት ካቴነ ታስሮ፣ መሃይም እንዲሆን ተፈርዶበት /በጣልየን ግዜ የተከፈቱት ትምህርት ቤቶች እንከን እንዲዘጉ ተደርገው/፣ በበሽታ ተሰቃይቶ እስከ ደርግ ግዜ መቆየቱ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ሲሆን በስተመጨረሻ ኮለኔል መንግስቱም የክልሉን ጠመኔ መግዣ ያክል ግብር የማይሰበሰብባት ብሎ መሳደቡ ይታወሳል፡፡

ይህን ሁሉ ግፍ ተቋቁሞ እንደኣዲስ ትግሉን በማፋፋምና ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በመሆን ሰው በላውን የደርግ መንግስት ከስሩ መንግሎ ጥሎ በምትኩም ፌደራላዊ ስርዓት በመመስረትና በህገመንግስት የሚመራ ሃገር ፈጥረዋል፡፡ በዚሁም ላለፉት 27 ዓመታት እያንዳንዱ ቤሄርና ብሄረሰብ በኣፍ መፍቻ ቋነቋው እንዲናገር፣ እንዲማር፣ እንዲዳኝና ባህሉን እንዲያሳድግ ተደርገዋል፡፡ በኢኮኖሚ፣ በባህላዊ፣ በጤና፣ በትምህርትና በመሰረተ ልማት እምርታ ያለው ውጤት ኣስመዝግበዋል፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በኢህኣዴግ የሚመራው ስርዓት የተዋጣለት ነበር ማለት እንዳልሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቀል፡፡ የመልካም ኣስተዳደር፣ የፍትህ፣ ፍትሄዊ የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትና የመሳሰሉት መሰረታዊ ችግሮች ነበሩበት፡፡ እነዚህ ድክመቶች ባይኖሩ ንሮ በ27 ዓመታት የተመዘገበውን እድገት እጥፍ ድርብ ይሆን እንደነበር ኣካራካሪ ኣይደለም፡፡ በዚሁም ምክንያት የለውጥ ኣስፈላጊነት ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምእራብ ህዝቡ ማመን ብቻ ሳይሆን ይፈልግና ይታገል ነበር፡፡ በስተመጨረሻም የኢህኣዴግ ኣመራር መቀያየርና መስተካከል፣ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ መንቀሳቀስነና ኣቅምን ያገነዘበ ተጠያቀነት ያለውና ከችሎታ በታች ሆኖ የተገኘ ከሃላፊነቱ ማውረድ፣ ወዘተ የሚሉ ሃሳቦች፣ ይቅር መባባል፣ ጥላቻን ማስወገድና ኣንድ ሆነን ለሃገራችን እድገት መትጋት፣ ወዘተ የሚሉ ዲስኩሮች እምብዛም ከህዝበቡ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይቀር ተቀባይነት ያላቸው መልካም ሃሳቦች ስለነበሩ ሁሉም ደግፈዋል ማለት ይቻላል፡፡

ለጥቆስ በተግባር ምን መጣ የዚህ ፅሁፍ ዋነኛ ማጠንጠኛ ነው፡፡ ከላይ የተገለፁ ማረ የሆኑ ቃላቶች በቃለትነታቸው ኣሁኑም በባለስልጣኖቻችን ተደጋግመው ይነገሩናል፡፡ ሆኖም እየተሰራ ያለውና ውጤቱ የዚሁ ተገላቢጦሽ መሆኑ ኣይደለም ታዛቢ ኣሁነኑ በስልጣነ ላይ ያሉም በሚገባ ተገንዝበውታል፡፡ ሰሞነኞቹ በዚህ ኣገር ኣሁን እየተከተሉት ያለው ስርዓት ምንነት በተገቢ መንገድ ኣልያዙትም፣ ኣልተገነዘቡትም፣ ገና ስም ለማውጣት እስከ ኣሁን እያወጡ እያወረዱ ነው ኣልያም ዓላማቸውንN እስኪያሳኩ ድረስ ለህዝቡ መግለፅ ኣልፈለጉም፡፡ ስርዓተኣልበኝነት ነግሶ በጠራራ ፀሃይ ዝርፍያ እሚካሄድበት፣ በሰው ላይ ከጉዳት እስከ ሞት ክንዋኔዎች እሚካሀድበትና ለዚሁም ሃይ የሚል የለም ብቻ ሳይሆን ማንንም ተጠያቂ እማይደረግበት፡፡ ይህ ማለትም ከበስተጀርባ የነዚህ ነውጠኞች ኣየዞህ ባይና ጉርሻ ሰጪ ዘመነኞቹ መሆናቸወ ቁልጭ ኣድርጎ የሚያሳይ ስረጃ መሆኑ፡፡ ያውም እንዲህ ኛይነት ስርዓተ ኣልበኛ ወጣቶችና እነዚህን የሚያንቀሳቅሱ የኢህአዴግ ካባ የለበሱ የውስጥ ኣርበኞች የሚወደሱበት ሁነዋል፡፡ ኣገርን ወደ ከፍታ ማማ ያደርሳሉ የተባሉት ሜጋ ፕሮጄክተች መቆምና ማዝገም፣ ምንም ዓይነት ኣዲስ የሚባል ፕሮጄክት ኣለመኖርና ኤርትራን ጨምሮ ከተለየዩ ሃገራት የመጡት ባለስልጣናት ባለፉት ዓመታት በኢህኣዴግ መሪነት የተሰሩት ሲሆን ለህዝበ በኢህኣዴግ ያለውን ጥላቻ እንዲያበረታ ሲባል ባለፉት 27 ዓመታት ምንም ነገር ያልተሰራ  ብቻ ሳይሆን የጨለማ ግዜ እንዳለፍንና ኣሁን ብርሃን መፈንጠቅ እንደጀመረ በማለት ምንም ባልሰሩበት ብቻ ሳይሆን ተሰርተው የነበሩትም እንዲወድሙና የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲገታ የደረጉት ሰሙነኞችን ማመኳሸትና የኣርበኝነት ሰበካ በሁሉም ሚድያዎች ሌተቀን በማሰራጨት በህዝቡ ላይ የተሳሳተ ኣመለካከት እንዲይዝ ማድረግ ሰሙነኞቹ ስራየ ብሎው ተያይዘውታል፡፡ ወደ ቻይና ሄደው ለመለመን ያመቻቸው ዘንዳ ግን በመልካም አጋርነት ቻይና ኣገራችን ተጨባጭ ለውጦች ማስመዝገቧን ሲገልፀ መስማቱ ይበልጥ የተለዋዋጭነት ባህሪ ሰሙነኞቹ ማሳያ ነው፡፡

ሃገራችን ባለፉት 27 ዓመታት የራስዋን ሰላም ከማስጠበቅ ኣልፋ የብዙ የኣፍሪካ ሃገሮችን የሰላም ኣጋር በሞን ሰላማቸው እንዲመለስና ከመፈናቀል፣ ስደትና እልቂት እንዲድኑ ዘብ እንዳልቆመች ኣሁን በኣገር ውስጥ ወደ 3 ሚልዮን የሚጠጋ ተፈናቅሎ፣ መጠልያ ኣጥቶ ገሚሱም ወደ ኣጎራባች ሃገራት ተሰዶ ስናይ ልባም ለሆነ ሁሉ እንቅል የሚነሳ ነው፡፡ በእውነት የሃገራችን ውርዴት ነው ምንም እንኳ ሰሙነኞቹ ስልጣናቸው ማደላደል ካልሆነ ይኸኛው ኣያሳፍረቸውም ብቻ ሰይሆን ከቁብም ኣይቆጥሩትም እንጂ፡፡ እንዲያውም ይህ መሰሪ ተግባራቸው እንዳይታወቅባቸው ወደ ሰላም ወዳዱና የፌደራሊዝም ጠበቃ ወደሆነው ሊያላክኩት ይሞክራሉ እንጂ፡፡

ባለፈው ግዜ ሚድያ ወገንተኛ በመንግስት የሚፈለገውን ብቻ የሚዘምር፣ ሌሎችና ወደህዝብ መተላለፍ የሚገባቸው ግና የሚያፍን፣ በፍትህ በኩልም ሰዎች ያለ ኣግባብና ማስረጃ የሚታሰሩበትና የሚንገላቱበት በወቅቱ ፍርድ ማግኘት የማይቻልበት ሲሉ የነበሩ ሰሞነኞቹ በትረስልጣኑ በእጃቸው ሲገባ ያው ይኮኑኑት የነበረውን እያደረጉት ይገኛሉ፡፡ የምርመራ ውጤቶች እነሱ በሚፈልጉት መልኩ ድራማ እስኪሰሩበት ከርችመው ይይዛሉ፡፡ በክልሎች ውስጥ ጣልቃ እየገቡ ያለ ክልልና ወረዳ ፓላማ ይሁንታ በለስልጠናትን ያወርዳሉ፣ ያወጣሉ፡፡

የኦሮማራ መርህ ኣልባ ግንኙነት፣ በየክልሎቹ እጃቸው እያስገቡ መበጥበጥ፣ የፀጥታ መዋቅሩ ለኤፍቢኣይ  ኣሳልፎ መስጠት፣ ግብፅን ጨምሮ የኣረብ ሃገራት በገንዘብ እየተደለሉ ተላላኪና ተንበርካኪ መሆን፣ በ27 ዓመታት በሚገባ የተገነቡ ተቋማት ግዜ ባልጠበቀ መልኩ ለውጭ ሃገራት ክፍት እንዲሆን ማድረግና ይህንንም ከኢህኣዴግ ኣካሄደ ያፈነገጠ ብቻ ሳይሆን ዩሉም ኣባል ድርጅቶች ይሁንታ የሌለውና ከኢህኣዴግ ውጭ የሉ ፓርቲዎችም ያላመከረና ይሁንታ ያላገኘ መሆን፣ ለመስዋእት ብለው ወጥተው በእድል ተርፈው ከበረሃ የገቡና ባሳለፍናቸው 27 ዓመታት ሚናቸውን ሲጫወቱ የነበሩት ኣንጋፋ ታጋዮችን እንደቆሪጥ ማሳደድ፣ ከድርጅታዊ ሃላፊነታቸው ማውረድ ለዚሁም ሲባልና እርምጃው ተቀባይነት እንዲያገኝ በጣም ፈር በለቀቀ መንገድ ጥላሸት መቀባት፣ ለድሎቱ ሲል የከበለለ፣ የሃገሪቱ ሃብት የመዘበረ፣ የቀይ ሽብር ተዋናይና ግፋበለው ሲል የነበረ፣ በወታደራዊ ህግ የሃገር ክህደት የፈፀመና የጦር መሳርያን ለጠላት ኣሳልፎ የሰጠ ኣረ ምን ግዳቹ ሁሉም የሃገር ኣርበኛ ኣቀባበልና ክብር ሲቸረው፣ በመርህ ኣልባ ጉንኝነት የኣንድን ክልል ተቃዋሚ በስመ ፌዴራል ክልሉን ለመውጋት ኮጎኑ እንዲሰለፍና እንዲያ ካደረገ ስልጣን እንደሚሰጠው በኤርትራ በተደረገው ሚስጢራዊ ድርድር መነሰቱን እየተሰማ ነው፡፡ ኣለዝያ ማ የድርድሩ ፍሬሀሳብ ለህዝቡ ኣልተገለፀም፣ ኣምሓራና ኦሮምያ ከፌዴራለ ውጭ ወደ ኣስመረ እየተሸራሸሩ ውጤቱ ለማይታወቅ ተደራድረን መጣን ሲሉ የትግረራይ ሲሆንና የክልሉ መንግስት ጥሪ ኣቅርቦለት ሲያበቃ በፌደራለ ባለስልጣናት የሆኑ የኦሮምያና ኣምሓራ ተወላጆች ያለ ንድ የትግራይ ክልል ባለስልጣን ለድርድር ባልተኬደ ነበር፡፡ የቀድመው ጠ/ሚኒስትር የሃይለማርያም ደሳለኝ በስመ ንግድና ኢንቨስትመንት የኣስመራ ጉዞ የህወሓትና የብኣዴን የቀድሞ ኣመራሮች ኣስቸጋሪነትነና ኣንድ እንዲልላቸው ኣቶ ኢሳያስን መማፀናቸው ተሰምተዋል፡፡

ታድያ እነዚህ ኣሁን የዓመቱ ምርጥ ሰዎች ተብለው የተመረጡት ግማሽ ዓመት እንኳን ሳይመላቸው፣ ጠብ እምትል ተግባራዊ ማሳያ መሬት ላይ ሳያሳዩ፣ በዚች ኣጭር ግዜ በጠራራ ፀሃይ በዋሻ ሳይሆን በመሃለ ከተማ ሰዎችን ዘግናኝ በሆነ መንደግ እንዲገደሉ ያስደረጉ፣  በሚልዮኖች ዜጎች እንዲፈናቀሉ ያስደረጉ፣ በጨለማ ሳይሆን በቀትር ንብረት እንዲወድምና እንዲመዘበር ያደረጉ፣ የሌላትን ገንዘብ ለሽርሽር፣ ለሽልማትና ግብዣ እያዋሉ ያሉ በየተኛው መስፈርት ነው ምርጥ ሰው ተብው የሚሸለመ የኣይጥ ምስክር ድንቢጥ ካልሆነ በስተቀር፡፡  እና መሸላለሙ ቀርቶኣችሁ ያለፈው ይበቃ ብላችሁ በመርህ መመራት ብትጀምሩ እየተንገዳገድን ካለንበት ተመልሰን ኣሁንም ትልቅ የመሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ምኞት እውን ይሆን ነበር፡፡   ኣለዚያ ግን የሃገሪቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ መገመት ኣስቸጋሪ ነው፣ ድሮውም ኣዲስ ኣበባ ያሉ ዓለም ኣቀፍና ኣህጉራዊ ተቋማት ለመውሰድ ይውተረተሩ የነበሩ የኣፍሪካ ሃገራት ሰላም የለም በማለት ከእጃችን እንዲያመልጡ መስራታቸው የማይቀር መሆኑንና ይህንን ታሪካዊ ስህተት እንደፈጠር ማድረግም ጥቁር ጠባሳa ጥሎ የሚያልፍ መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡ ለዚሁም የኢትዮጵያ ህዝብ ሹፌሮቻችን ወዴት እየነዱን እንደሆነ በማስተዋል ኣደብ እንዲገዙ ማድረግ እንጂ በተግባር ባልተፈተኑበት ሁኔታ የምርጥ ሰው ሽልማት መሸላለም ኣወቅሽ ኣወቅሽ ቢልዋት የባልዋን መፅሀፍ ኣጠበች እንደተባለው እንዳይሆን በርጋታ እንንቀሳቀስ እላሎህ

ሰላም ለህዝባችንና ለሃገራችን እግዚኣብሄር ይዘዝልን  ኣሜን

 

Back to Front Page