Back to Front Page


Share This Article!
Share
ጥቂቶች ቆራጦች ዳግም ታሪክ ይሰሩ ይሆን?

ጥቂቶች ቆራጦች

ዳግም

ታሪክ ይሰሩ ይሆን?

 

 

ታጁ ሙሓመድያሲን

muhamedyassintaju@gmail.com

17/01/2011ዓ/ም

17/01/2011ዓ/ም

ጥቂቶች ቆራጦች ዳግም ታሪክ ይሰሩ ይሆን?

ኢህአፓ በተሳሳተ የትግል አቅጣጫ የኢትዮጵያ የተማሩ ወጣቶች እንዲጨፈጨፉ ስታደርግ፣ በኢህአፓ ውስጥ የነበረ ቅራኔ ጫፍ ረግጦ በድርጅቱ ውስጥ የፀረ ዲሞክራሲ አመራር የበላይነቱን ሲቆጣጠር በድርጅቱ ውስጥ የነበሩ ታጋዮች ተስፋ ቆርጠው ትግል ማካሄድ አይቻልም ብለው  ለደርግ ኢጃቸው የሰጡበትና(ሂሳቸው የዋጥበት) ወደ ውጭ አገር የሚኮበልሉ በበዙበት ወቅት ጥቂቶች ቆራጠች ለትግል የተዘጋጀውን ህዝብ መርተው ታግለው ለማታገል ከኢህአፓ ተለይቶው በመውጣት ኢህዴንን(የአሁኑ ብአዴን) በመመስረት ትግላቸው አጠናክረው የቀጠሉበት ወቅት ነበር።

በዛን ግዜ፤-

 ስንቶች ተኮላሽተው ከአሮንቋ ዘቀጡ፣

ስንቶች ተቸንፈው ከጎዳናው ወጡ፣

ጢቂቶች ቆራጦች ያልተምበረከክነው፣

ነገ አእላፍ እንሆናለን ታሪክ ምስክር ነው።የሚል መዝሙር ዘመሩ። ከህዝባቸው ጋር ሁኖው ታገሉ ለድልም በቁ።1983 ዓ/ም በኢትዮጵያ ህዝቦች ትግል ፋሽስታዊ ስርዓት ደርግ ከተደመሰሰ ብኋላ ብአዴን በአማራ ክልል ለሰላም፣ለልማትና ለዲሞክራስያዊ ግንባታ ያላሰለሰ ትግል በማካሄድ በአማራ ክልል  እምርታን ማስመዝገብ ቻለ።  

Videos From Around The World

ብአዴን ከቅርብ ግዜ ወዲህ  ጥቂቶች ቆራጦች የጀመሩት የህዝብ ትግል የሚኒድ ኢህአፓን ለመውደቅ ምክንያት የሆኑትን ትምክህተኝነትና ፀረ ዲሞክራሲ አስተሳሰብና ተግባራት በውስጡ ማቆጥቆጥና መጠናከር ጀመሩ።ብአዴን ህዝባዊ ውግንናው ኩፉኛ እተሽመደመደ መጣ።ይህንን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የከረፉ ትምክህቶኞች የብአዴን ማእከላይ ኮሚቴን ዙፋን ተቆጣጠሩት።የአማራ ብሄር ክልላዊ መንግስትም በበላይነት ያዙት።ሁሉን የድርጅትና የመንግስት መዋቅር እነሱን በሚታዘዙ አመራሮች ተተኩ።የትምክህተኛ አስተሳሰባቸው ማራመድ በሚችሉበት ደረጃ ሲደርሱ ዘር መሰረት ያደረገ ጥቃትን አጧጠፉ።

የአማራ የበላይነት እናስመልሳለን በሚል በተሳሳተ ፈሊጥ ተጋሩና ቅማንቶች ከቤት ንብረታቸው አፈናቀሉ ንብራታቸውም ዘረፉ አለፍ ሲሊም ግፍ በተሞላበት ገደልዋቸው።የአገው ህዝቦች ለማጠናከር ይንቀሳቀሳሉ ለሚባሉት የብአዴን ማእከላይ ኮሚቴም ሳይቀሩ ለማዳከም ተንቀሰቀሱ።ከዚህ አልፎ ትግራይ ክልል ለማተራመስ የትግራይ ክልል ወረዳ ለሆነችው ወልቃይት ወደ አማራ ክልል እናመጣታለን በሚል አስመላሽ ኮሚቴ በጎንደር ከተማ በማዋቀር ትምክህተኛው ድራማቸውን አጠናክረው ቀጠሉ።ይህ ያምረኛል ያም ያምረኛል የሚል አባዛያቸው ወደ ትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚያስተዳራቸው ራያ ኣላማጣ፣ራያ ዓዘቦና ኦፍላ ወረዳዎች ለማሸጋገር ደፋ ቀና አሉ።ከሱዳንም ሃገራችን ወደ ሰጣ ገባ ለማስገባት ተንቀሳቀሱ።

ይህ አማራ ክልል ውስጥ የመሸገው የትምክህት ጎራ የአማራ የበላይነት እናስመልሳለን በሚል መፎክር የአማራ ክልል በማተራመስ አለበቃም።ጎንደር የጀመረው የትርምስ ስትራተጂ መላው ሃገሪትዋ አተራማሳት።የአማራ ህዝብ የማይፈልገውና ሊሳካም የማይችለውን የበላይነት ይቅርና አካባቢውን በማልማት በየደራጃው ተጠቃሚ የሚሆንበት አመራር አጣ።የአማራ ህዝብ ከቦታ ቦታ በሳላም መንቀሰቀስ፣ያመረተው ምርት በፈለገው ቦታ ወስዶ የመሸጥ መብቱ ተነፈገ።ትምክህተኛው ባደረጃቸው "ፋኖዎች" የአማራ ህዝብ ሃብት የሆኑቱን እህልና በጎች በጠራራ ፀሐይ በአደባባይ ተዘረፉ።የአማራ ህዝብ ያመረተውን ምርት ወደፈለገው ቦታ ወስዶ እንዳይሸጥ "በፋኖዎች" መንገዶች ተዘጉ።የአማራ ህዝብ በሰላምና ዲሞክራሲ እጦት እየተሰቃየ ነው።የአማራ ህዝብ ሰላም ወዳድ ሁኖ ሳለ ሰላም እንደማይፈልግ፣ዲሞክራሲ ፈላጊ ሁኖ ሳለ ዲሞክራሲ እንደማይፈልግ፣ልማት ፈላጊ ሁኖ ሳለ ልማት እንደማይፈልግ ሁኖ በሌሎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንዲሳል አድርጎታል።ከአማራ ክልል ውስጥ የተካለሉ የራሳቸው ማንነት ያላቸው ህዝቦች ሳይቀሩ በክልሉ መንግስት የሚሰጠው የትምክህተኛ አመራር ተስፋ ቆርጠው ለምብታቸው መከበርና የራሳቸው ክልል ለመመስረት ጥያቄ የሚያቀርቡበት ሁኔታን ተፈጥረዋል።በአማራ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ ክልሎች ከአማራ ብሄረዊ ክልላዊ መንግስት ዛሬ ነገ ትንኮሳ ይደርስብን ይሆን የሚል ስጋት የሚወድቁበት ሁኔታም ተፈጥረዋል።

በማጠቃለል የብአዴን የአመራርነት ቍንጮ የተቆጣጠረው ትምክህተኛው ሓይል ለአማራ ክልል ህዝብ የመልማት መብቱ በመንፈግ ዲሞክራሲ መብቱ በመከልከል ሰላም እንዲያጣ በማድረግ ወደማይወጣው አዘቅት እየዘፈቀው ይገኛል።

የአማራ ክልል ህዝብ  የብአዴን የስልጣን ቁንጮ በተቆጣጠሩት ትምክህተኛ አመራሮች ከፈጠሩት አዘቅጥ በፍጥነት መርተው የሚያወጡት ጥቂጦች ቆራጦች አብዮታዊ ዲሞክራስያውያን ሐይሎች  ይፈልጋል።ክልሉ ትምክህተኛው  ከፈጠረው ጨለምተኝነት በማውጣት ታግለው የሚያስታግሉት አመራሮች ይፈልጋል።ይህ ከትምክህተኝነት አስተሳሰብና ተግባር በማስጣል የአብዮታዊ ዲሞክራስያዊ አስተሳሰብ ልዕልና ያለበት ድርጅትና መንግስት ለማድረግ ትግሉ መጀመር ያለበት በ12ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤ ነው።ከዚህ ጉባኤ በኋላም ፀረ ትምክህተኛ አስተሳሰብና ተግባር ትግል ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።ጥቂቶች ቀራጦች ክልሉ ዳግም ወደ ብጥብጥ  የማይገበት ሁኔታ ለመፍጠር ቆርጦው ይተጋላሉ የሚል እምነት በአማራ ህዝብ ዘንድ አለ።

በዚህ ጉባኤ ጥቂቶች ቆራጦ ያልተምበረከክነው በቆራጦች የአማራ ህዝብ ታጋይ ልጆች ዳግም ይዘመራል ዳግም ለድል ይበቃሉ በሚል እምነት በብዙ የኢትዮጵያ አብዮታዊ ዲሞክራስያውያን ሐይሎችና  ህዝቦች እየተጠበቁ ናቸው።ጥቂቶች ቆራጦች ዳግም ታሪክ ይሰሩ ይሆን?የሚል ጥያቄ በ12ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤ መልስ ያገኛል።

ድል ለአማራ ክልል አብዮታዊ ዲሞክራስያውያን ሐይሎች!

ድል ለአማራ ክልል ሰላም ወዳዱ ህዝብ!

ሽንፈት ለከረፉ ትምክህተኞች!

ምንጭ:-

*ከብአዴን የተሰጡ መግለጫዎች

*መንግስት ከሚቆጣጠራቸው ሚድያዎች

*ከማህበራዊ ሚድያዎች

Back to Front Page