Back to Front Page


Share This Article!
Share
ሶስተኛው መልእክት

ሶስተኛው መልእክት

 

በቀለ በርሃኑ 10-04-18

 

ለአራቱም የፖለቶካ ድርጅቶች መሪዎች

ለኢሀአደግ ከፍተኛ አመራሮች

ለኢትዮጵያ ምሁራን (ኤሊትስ)

 

ድርጅታዊ ጉባኤዎቻችሁን አገባዳችሁ ወደ ዋናው ወሳኝ የጋራ ስብሰባዎቻችሁ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ። በመጠኑም ቢሆን ስብሰባዎችሁን ለመከታተል ሞክሪያለሁ። ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች ተመልክቻለሁ። ምንም ላጀንዳ የማይገቡ ትናንሽ ነገሮች አጽኖት ተሰጥቶባችው ሰዎችህ ሲከራከሩም ሰምቻለሁ።

 

አሁን ጉዳዩ አገር የማነጽና የማዳን ጉዳይ ነው። ዶ/ር አቢይ እንዳሉት አንዱ ባንዱ ላይ እየተደመረ አገሪቱ ወደ ተፈላጊው የእድገት ጎዳና እንዴት እንጓዝ የሚለው ሃሳብ መሪ ሃሳብ መሆን አለበት። የቀድሞው ሰው እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ የመደማመር ታሪክ ነው። የኢትዮጵያ ገባር ወንዞች አባይን እንደፈጠሩ ሁሉ ኢትዮጵያም የመላው ህዝቧ ድምር ፈጠራ ናት። የህችን የተደማመረች አገር ማጎልበትና ማጠናከር የሁሉም የቤት ስራ መሆን አለበት።

Videos From Around The World

በዚህ አጋጣሚ ዶ/ር አቢይ ትጉ ተማሪ መሆናቸዉንም ሳልገነዘብ አላለፍኩም።

 

ዋናው ችግራችን ችግራችንን ለይተን አለማወቃችን ነው። በጥቅሉ ሲቀርብ ችግራችን የመንግስት ባለስልጣኖች የማስፈጸም ደካማነት፤ የሙስና ቅጥ ማጣት፡ የባለስልጣኖች በተወሰነ ደረጃ ያለአግባብ መበልጸግና የመንግስት በሰላም ማስከበር ላይ የሚታየው ደካማነት ነው።

 

ኢሃአደግ እንዚህን ችግሮች መፍታት ላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ዪገባል።

ክልል ማካለል፤ ህዝቦችን በስሜት እየተንኮሱ ማጣላት፤ አንዱን በበሌላው እንዲነሣሳ መገፋፋት፤ የደካሞች ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ችግርና እሮሮ መገንዘብ ከማዪችሉ አመራሮችህ የሚፈልቁ ችግሮች ናቸው።

 

እናም ጉባኤያችሁ የሚተገበሩ እቅዶች ላይ ትኩረት መስጠት ዪገባዋል። የአመራሮቻችሁ ትልቅ ችግሩ ይህ ነው።

ማንም ኢትዮጵያዊ በየትም ቦታ የመኖር ፍጹማዊ መብት (አብሶሉት ራይት)። የማንም ክልል መሪ ፈቃድ አያስፈልገዉም።

የትግራይ መሬት የሚባል ነገር የለም፡

የአማራ መሬት የሚባል የለም

የኦሮሞ መሬት የሚባል ነገር የለም

የደቡብ፤ የሶማሊ የጋምበላ፤ የአፋር መሬት የሚባል ነገር የለም

መሬቷም፤ ንብረቷም፤ እድገቷም ውድቀቷም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው።

 

ስለዚህ ነው ማዓከላዊው መንግስት የዚህን መሰረታዊ ሃሳብ የማስረጽ፤ ተግባራዊ የማድረግ፤ በእጅጉ መወጣት ያለበት።

እጅግ የሚደንቀው ደግሞ ለኦሮሞው የኦሮሞ መንግስት፤ ለአማራው የአማራ መግስትወዘተ.. ተጠሪና ተቆርቋሪ አድርጎ የመውሰድ እምነታቸው ነው።

 

ትግራይ ውስጥ ያለ አማራ ወይም ኦሮሞ ወይም ጉራጌ (ወዘት..) ሃላፊው ተቆርቋሪው፤ አለኝታው እዚያው ያለው የትግራይ ክልል መንግስት እንጂ የኦሮሞ ክልላዊ መንግስት ወይም፣ የደቡቡ ወይም የሃረሪው አይደለም። በሌላው ክልል የሚኖሩ የተለየ ቋንቋ የሚናገሩ ህዝቦችም እንደዚሁ።

 

ይህንን የማይገነዘቡ ፖለቲከኞች ሳያስቡት የዘረኝነት ጥንሥሥ፤ አስተሳሰብና አደገኛ አገር በታኝ አካሄድ እያራመዱ እንደሆነ ሊገነዘቡት ዪገባል። ብሄረትኝነት የ ፋሺዝም አደጋ መንደርደሪያ ሊሆን ዪችላል የሚለው አባባልም ከዚህ የሚመነጭ ነው።

 

የአማራ ክልላዊ መንግስት ስብሰባ ላይ ባመራሩ ሲነገሩ የነበሩት ነገሮች ትንሽ አሳስቦኛል። እንደምያርሙትም ተስፋ አደርጋለሁ;

 

ክልል አስተዳደራዊ አደረጃጀት ነው። የህዝቦችን ባህል፡ ቋንቋና መሳይ እሴቶችን ለማጎልበት፤ ለማስከበር፡ ለማበልጸግ የታለመ አስተዳደራዊ ተቋም ነው። በክልሉ ነዋሪ የሆኑ ህዝቦችና እዝያ መኖር የሚሹ ህዝቦችን የኤኮኖሚ ፍላጎቶችን የሚመልስ፤ መብቶችን የሚስከብር መንግስታዊ ተቋም ነው ሁነታው ብዙም ያልገባቸው ወይም ለግላዊና ቡድናዊ ጥቅሞች ሊጠቀሙበት የሚሹ ሃይሎች ግን ጠባብ ትርጉም ይሰጡታል። ቦታ ሊሰጣቸው አይገባም።

 

በሌላው ገጹ የቋንቋ ክልልላዊነት ጸረ-ኢትዮጵያነት አድርገው ባለማወቅ የሚጮሁ፤ አውቀው ደግሞ ሌላዉን የመጫን አባዜ ያላቸው ቡድኖች ነገሩን እያውገረገሩ የሚዳክሩ እንዳሉም ልብ ማለት ያስፈልጋል።

 

ምህራኖቻችን፤ ሊሂቆቻችን፤ አርቲስቶቻችን

 

ከጊዜ አንጻር ያለሃተታ የሚከተሉትን ነጥቦች ላስቀምጥ።

ጛዜጠኛውም፤ ምሁሩም፤ ፖለቲከኛውም የመገንጠልን ጥያቄ (ሰልፍ ደተርሚነሽን) የኮሚኒስቶች ጥያቄ አድርገው የሚወስዱት አተረጓጎም ነው። በርግጥ ኮሚኒስቶች ተጠመዉበታል። ነገር ግን በተባበሩት መንግስታት መብትን የሚዘረዝሩ አንቀጾች ዉስጥ ተካቶ ዪገኛል። በ መረጃ ደረጃ ህዝብን ማወናበድ አያስፈልግም። በርግጥ በዚህ መገንጠልን በምያበረታታ አንቀጽ ላይ ምንም አስፈላጊነቱ አይታየኝም። ነገር ግን የም እራቡን አለም ደሞክራሲያዊ ፍልስፍና ወደ አገራችን እንዳለ ለማምጣት ለሚጥሩት ልሂቆቻችን መካከል ትንሽ የሃሳብ መተርረማመስ እንዳለ ያሳያል።

 

ሃቁ ግልጽ ነው። ለትግራይ ህዝብ መገንጥል ጸያፉ ነው። ለአፋሩም፤ ኦሮሞዉም፤ ደቡቡም፤ ሶማሊም፤ በኒሻንጉሉም፤ አማራዉም - ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች። ይህን ማመን የግድ ነው።

 

የኛ ሙሁሮች ካንዳንድ እጂግ አስተዋይ ሰዎችህ በስተቀር የዲሞክራሲ ስርዓት አለመኖር፤ ውዘተ.. እያሉ የምእራቡን አለም አስተሳሰብ በሰፊው ሲተነትኑ እሰማለሁ። ከ አፊካዊነት፤ ከኢትዮጲያዊነት ጋራ የማስተሳሰር ነገር አይታዪም።

 

አፍሪካ፤ ኢትዮጵያ የራሷ እሴት፤ ባህል፤ አስተዳደራዊ ታሪክ ያሉበት ህብረተሰቦችን ሲስተዳድሩ የነበሩ አገሮች ናቸው። የአፍሪካ/ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ በ ሰው ልጆች መብት መከበር፡ ሌላዉን መርዳት፤ ሽምግልና፤ ምክክር ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲ ነው። በተጨማሪም ዘመኑ ባመጣው እድገት መጠን እነዚህንና መሰል የዲሞክራሲ እሰቶችን ማዘመን፤ ህጎችህ ማውጣትን፤ እነዚህን ህጎች እንደ ገዳው ስርዓት ያለ አድሎ የማይፈጸሙበት መዋቅሮችን (ኢንስቲቱሺንስ) መፍጠር፡የግድ ይላል።

 

የኛ ምሁራን ግን ከፈረንጆቹ ክብረ -ነገስት ማለትም ማኛ-ካርታ (Magna Carta) እንዳሉ ሃረጎቹን በመምዘዝ ዲሞክራሲ እንዲህ ነው ይሉናል። በርግጥ ከምእራቡ አለም ብዙ የምንማረው ነገር አለ። ነገር ግን ፈረንጅ ስለሆነ አሠስ-ገሰሱን ሁሉ ለማግበስበስ መቻኮል ግን ትልቅ ስህተት ዪሆናል።

 

ሙሁራኖቻችን ከጠባብ አስተሳሰብ ወጥተው ስትራተጊች የሆነ አገራዊ መመሪያዎችን ለ ማውጣት ታላቅ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ዪገባል።

አርቲስቶቻችንም እንደዚሁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አርቲስቶቻችን የዝቡን አንድነት፤ ትስስር ወንድማማችነትን እንጂ አሁን እንዳለው የሆያ-ሆየ መዝሙር አላስፈላጊና ምክንያታዊነት የጎደልው የስሜት ፈረስ መጋለብ ጎጂ ነው።

 

መልካም ብሩህ ጊዜ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዉያን ሁሉ

 

Back to Front Page