Back to Front Page


Share This Article!
Share
በሶስቱ ወራት የመደመር ውጤቶች

 

በሶስቱ ወራት የመደመር ውጤቶች

ከኣሉላ የወሃንስ መቐለ 07-29-18

 

መደመር በሳይንስም ሆነ ወላጆቻችን እንዳስተላለፉልን የሚቻለው ሊወሃድ የሚችል፣ በሙሉ ሁኔታ የሚስማማ እንዲሁም ኣንድ የሚሆን ማለት ነው፡፡ ይህ በሌላ መንገድ ሲመነዘር ደግሞ የሚደመረው ሁሉንም ነገር ሳይሆን ሊደመር የሚችለው ብቻ እንጂ እንዲሁ በዘፈቀደ ያለውን ነገር መደመርና ማደባለቅ ከቶውን የሚቻል ኣይደለም፡፡ ለምሳሌ ዘይትና ውሃ ኣይደመርም፣ ወተትና ጓያ ኣይደመርም፣ ከኣንድ እናት በተገኙ ልጆች መካከል ያለውን ሃሳብ እንኳን ምንግዜም የሚደመር ሊሆን ኣይችልም፡፡

 

በመደመሩ የማወናበጃ ስብከት ግን ስንቱን እንዳወናበደው ሳይ በጣም ገረመኝ፡፡ ህዝብ ወሳኝ ነው የሚባለውን መርህ በሚገባ ያፈረሰ ሆኖ ኣግኝቸውኣሎህ፡፡ ኣገር በሆይሆይ ሊመራ እንደማይችል በኣዲሱ ንጉስ የሶስቱ ወራት ኣገዛዝ ከጅምሩ ፍሬው እያጎመራ ነው፡፡

 

ደማሪው ለመደመር እየሞከረ ያለው የተለያየ ፖለቲካዊ ኣመለካከት ያላቸው ብዱኖችን ብቻ ኣይደለም፡፡ እየደመረ የሚገኘው ኣሸናፊና ተሸናፊ፣ ድል ኣድራጊና ድል ተደራጊ፣ ውጣቶችን በኣደባባይ የረሸነና ያስረሸነና ኣረመኔውን ስርዓት ከስሩ መንግሎ መቃብር ውስጥ ከትቶኣቸው ከነበረው ሃይሎች፣ ይብዛም ይነስም ነፍጡ ኣንግቦ ስርዓቱን ለማፍረስ በውጭ ጠላቶቻችን ተላላኪነት ሲያገለግል የነበረው ለሽብር የሚገለገልበት ታጣቂውን ይዞ የሚመጣና በሰላማዊ መንገድ ያለምንም ዓይነት ነፍጥ ሳያስፈልገው ከሚታገለው ጋር፣ ኣረ ስንቱ፡፡

 

Videos From Around The World

በተለያዩ የመልካም ኣስተዳደርና ፍትህ የተማረረውን ህዝብ ልብ በመገንዘብ ለግል ፍላጎት ማሟያ እየተጠቀመበት የሚገኘው ደማሪው በሃገራችን በ27 ዓመታት ታይቶ የማያውቀውን የሰላም እጦት፣ ንብረት መውደም፣ ዘረፋ፣ መፈናቀልና ግድያ በሺዎእ ሳይሆን በሚልዮኖች እየሆነ ያለው በደማሪው ንጉስ ዘመን ነው፡፡ በዘመነ ኢህኣዴግ ከየመልካም ኣስተዳደርና ፍትህ እጦት ባሻገር የዚህ ኣይነት ስፋትና ጥልቀት ያለው ሁኔታ ኣልተከሰተም፡፡

 

ከዛም ኣልፎ በሰላምዋ ትታወቅ የነበረችውን ሃገር፣ ከራሷ ኣልፋ ለሌሎች የኣፍሪካሃገራት ሰለም መስፈንም ጭምር ትልቅ ኣበርክቶ የነበራትና በኣለም እውቅና የተቸራትን ሃገር በግብፅና መሰል የኢትዮጵያ እድገት የማይመኙ ሃይሎች ቅጥረኝነት የሚሰሩና እስከነ ታጣቂ ብዱኖቻቸው በደማሪው መልካም ፍቃድ ወደሃገርቤት በገቡ ሃይላት በጠራራ ፀሃይ ሲያራምዱት የነበረውን የሽብርተኝነት ተግባራቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ መደመር ማለት ይህ ነው፡፡ ወንጀለኛ ሁላ በስመ ይቅርታ እንዲወጡና የወጠኑትን ስራ ዳር እንዲያደርሱ ሲፈቀድላቸው በተቀራኒውና ኣገርን እያገለገሉ የነበሩት ያውም የኣንድ ብሄር ተወላጆችን ማሰር ምን እሚሉት መደመር ነው?

ወደ ኬንያ፣ ኤርትራ ና ኣሜሪካ የክልል ባለስልጣናት እየለዩ የፈለጉትን ዘር መውሰድ የዘንድሮ መደመር የትየለሌ ሁኖብኛል፡፡ በዚህ ኣካሄድ ጠንካራና የተደመረች ሃገር ትኖራናለች ማለት እንዲህ ነው፡፡ የኣሁኑ ይባስ ሆነና የዳንጎቴ ስራስክያጅ እስከነ ባለደረቦቻቸው በኣረመኔኣዊ ሁኔታ

የተደረገው ግድያ በኣስቸኳይ እናስታውቃለን ሲበል እስከኣሁን ደብዛውን የለም፣ የሰነ 16ቱ የመስቀልኣዳባባዩ የቦንብ ፍንዳታ ደማሪው መደምደምያ ደርሶ መግለጫ ለመስጠት ደቂቃዎች ያልወሰደው ሸጊቱ መሆንዋን ሲታወቅ እስከኣሁን ምርመራው ውሃ እንደበላው ነው፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ ለራሱ ሳይሆን ለሃገሩ እድገትና ብልፅግና ይኖር የነበረው ኢንጅነር ስመኘው በጠራራ ፀሃይ፣ በከተማዋ እምብርት በሆነው በመስቀል ኣደባባይ፣ በደህንነት ካሜራ በሚጠበቀው የመስቀለ ኣደባባየ፣ መኪናው ሞተሩ ሳየጠፋ በተቀነባበረ ሴራ ሲገደሉ በጣሚ የሚገርመው ሞተው ተገኙ የሚል ዜናና የፖሊስ ኮሚሽነር ሳቅ በሳቅ የተሞላው መግለጫ መስጠትና ኣውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት ኣይሰማ እንደሚባለው እስከኣሁን ደብዛው ኣልተገኘም፡፡ ግን ይህ ሰው ሽልማቱ እንዲህ እንዲሆን የሚያደርግ የደማሪው መንግስት እችሄገር ሃገር እንዳትሆን የሚያደርግ እርምጃ በመውሰድ ለይ እንደሚገኝ ግልጭ ተግባር ነው፡፡ በእንጅነሩ ግድያ የተቀነባበረው ሴራ ደግሞ በጣም ግልጭና ኣዲስ የደህንነት ስራ ጀማሪ ኣካሄድም ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚከተሉትን ልጥቀስ፡

 

 

ደማሪው ኣሰቀድሞ ግድቡ የዛሬ 10 ዓመት እንደማያልቅ መናገሩ፣

እንጅነሩ የደማሪው ኣባባል እንደማይቀበሉትና በኣጭር ግዜ እንደሚያልቅ መናገራቸው

ከሁለት ቀን በላይ ከግድቡ ተለይቶ መኖር የማይፈልገውን እንጂነር ስመኘው ለኣንድ ሳምንት ያክል ኣዲስ ኣበባ እንዲቆይ መታዘዙ፣

ጠባቂውና ሹፌሩ በሌላ ይተካልሃል ሰበብ ከሳምንት በፊት በማባረር ብቻውን እንዲነዳ መደረጉና እስከተሰዋበት ግዜ ድረስ ሌላ ጠባቂም ሆነ ሹፌር ያለመመደቡ፣

በሰኔው 16 እና እንጂነሩ ከመገደላቸው ሁለት ቀናት ኣስቀድሞ የነበረና በዚሁ እለት እንዲነሳ በማድረግ ለግድያ ማመቻቸቱ

ደሮ ሲያታልሉዋት እንደሚባለው ራሱን የገደለ ለማስመሰል ገድለው ሸጉጥ ማስያዙ የተለማማጆች ቅንብር

 

ከዛም ኣልፎ ነገሩን ለማድበስበስ ሲባል የሃገር ብርቅየ ባለውለታ የሆነው ስመኘው እንደ ኣንድ ተራ ሰው ለነገታው ለመቅበር መቻኮልና ይህ ነገር የበለጠ ያጋልጠናል በሚል ለሳልስት እንዲዘገይና የስርዓተ ቀብር ኣስተባባሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም መደረጉ የቁርጥ ቀን እንጅነር በማን እንደተገደሉ ግልፅ ያደረጉ ዋቢዎች ናቸው፡፡

 

ከዚህ ኣልፎ እርስ በራሱ ተቃርኖ ያለው የደማሪው ኣገላለፅ በኢቶ ኤርትራ ጉዳይ ላይ የማእከላዊ መንግስት ጉዳይ ስለሆነ በድንበሩ ኣካባቢ ያሉና እለት ተእለት የሚገናኙ የትግራይና የኣፋር ህዝቦች ኣያገባቸው ብሎ በተቻኮለ ሁኔታ እየተዝናናበት በሚገኘው በኣሜሪካ ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡ ባለማወቅም ሆነ የትምክህት ሃይሎችን ለማስደሰት እንዲህ ቢልም ለዘላቂ ሰላም በጎረቤታሞች ብቻ ሳይሆን በተዋለደው የኣዋሳኝ ሃገራት ህዝቦች የግድ ይላል፡፡ ለዚህም የደማሪው መልካም ፈቃድ የሚጠየቅበትም ኣይሆንም፡፡

Back to Front Page