Back to Front Page


Share This Article!
Share
ድንቄም የውጥ ሐወሪያ?

ድንቄም የውጥ ሐወሪያ?

በሃይላይ አበራ                                                                2018/10/04

 

የማፊያ ፖለቲካ ቁማርተኞች፣ የግሪሳ መንጋ  ፖለቲካ፣ የህግ-አልበኝነትና ግጭት ስርዓት ፈጣሪዎች (anarchism and  conflict entrepreuneurs)፣ ደቀ መዛሙርትና አውራዎቻች፣ እንትና የሚባል ድርጅት ልፒስቲክ ስለተቀባ፣ ተለውጧል (Reformist or change champion) ነው፣ እንትና ግን ተመሳሳይ ልፒስቲክ ስላልተቀባ ፀረ-ለውጥ ነው፡፡ አርጧል፡፡ መወገድ አለበት፡፡ መቆረጥ አለበት ወዘተ ሲሉ ይታያል፡፡  የነዚህ ነውረኞችና አራዊቶች ስትራተጂ፣ ከነሱ ጋ በየአደባባዩ ያልደነሰ፣ ቡድን፣ ከዚህ ቡድን ጋ ትስስር ያላቸው (በቋንቋ፣ በባህል፣ በታሪክ፣ በብሔር፣ ወዘተ) በማፈን ህዝብ እንደ  መያዣ (hostage)  በመጠቀም፣ ለነሱ ያለተምበረከከ አካል (ቡድን) ያንን  ህዝብ፣ መደራደሪያ ማደረግ ነው፡፡ ይሄንን እውነታ፣ ከሚያዝያ በፊት፣ በሀገራችን በነበረው ዓመፅ፣ ህወሀትን ለማንበርከክ፣ ሰርተው የዕለት ጉርሳቸው፣ ለማግኘት፣ የሚታትሩ ንፁህ የትራይ ተወላጆች፣ የዩኒቭስቲ ተማሪዎች ወዘተ፣ እጅግ አስቅኝና ፣ የወረድ ድራማ በመስራት፣ እንደ መያዣት ታፍነው፣ ከ50 በላይ ሂወታቸው አጥቷል፣ ተገርፈዋል፣ ታስረዋል፣ ብዙ አሰቃቂ ድርጊቶች ተፈፅመባቿል፡፡ እነዚህ  ህሊናቸው፣ ሽጠው፣ የሐሰት ፕሮፖጓንዳ፣ በማሰራጨት፣ ወጣቶች በማደራጀት፣ የነገ ተስፋ የሆኑ ሀገር ተራካቢ ወጣቶች፣ በማያውቁት፣ ሴራ ውስጥ ገብተው እንደ ተናካሽ አራዊት (a trained muling beast) ለርካሽና ነውረኛ ዓላማ በመጠቀም፣ የፈለገው መስዋእት ተከፍሎ ፍላጎታቸው ማሟላት ነው፡፡

 

 

Videos From Around The World

በሀዋሳው የግርግር ጉባኤም፣  በዚህ ጉባኤ ፋላጎታቸው ካልተሟላ እና ነገሮች በሚፈሉጉት መንገድ ካለሄዱ፣ ተመሳሳይ  ሠይጣናዊ ድርጊት ለመፈፀም ያቆበቆቡ በርካታ ድርጅቶች፣ ቡድኖች እና ግለሰዎች እንዳሉ ፣ እጅግ ታማኝ መረጃዎች ያመለክታሉ ፡፡ ስለዚህ ተጨባጭና ከፍተኛ ስጋት ስላን ከወደሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪያችን እናቀርባል፡፡ ስጋቱ ተገቢ ነው ወይ? መለሱ አወ በደንብ ነው፡፡ ለምን ቢባል የኃ/ለማሪም የኢህአዴግ፣ የመሪነት (የአመራር) ስበት ስላል ነበረው፣ በቀላሉ፣ ለመሰንጠቅ የሚዳርግ አዳጋ  ተደግኖበት፣ በትልቅ ገደል፣ አፋፍ ላይ ደረሰ፡፡  የሀገራችን ህልውና እና የህዝባችን ድህንነት ተናጋ፡፡ የሀገራችን ልማት፣ ሰላም ድምጥማጡ ጠፋ፡፡ ዜጎች አንድ መንገድ ላይ ተሸግረው፣ የዕለት ጉርሻቸው ለመግዛት የማይችሉበት ደረጃ ደረስን ወዘተ፡፡ ይህንን ለማስተካከል መሲህ ነው፡፡ ሙሴ ነው ወዘተ እተባለ፣ በአሜሪካ CIA እና በዓረቦች ከፍተኛ ድጋፍና አስቻይነት ወደ ስልጣ የመጣው አመራር ወደ ስልጣን የመጣው የመደመር የተስካር ፖለቲካ እና ልፋፌ ታግዞ በተደጋጋሚ የሀገራችን ችግር እነደሚቀረፍ እና ሀገራችን ባጭር ወቅት የኤደን ገነት እንደምትመስል የምኞት (አምሮት) ቃል የገባው እና ከራሳችን ተርፈን ለምስራቅ አፍሪካ እንሆናለን ያለው አመራር፣ ከዚሁ በተቃራኒ ከዕለት ፣ ዕለት የማቾችና፣ ተፈናቃዮች፣ የብሔር ግጭት ወዘተ ከፍተኛ ጣራ ላይ ደርሶ፣ ለአፍሪካ ቀንድ ሸክም ከመሆን አለፈን፣ በዓለም ከፍተኛ የውስጥ መፈናቀል ቀውስ  ተሸብበን ሶሪያና አፍጋንሲታን ቦንሰን፣ የዓለም ቁንጮ ሆነናል፡፡ ከ500 በላይ ንፁህ ኢ/ያን በግጭቱ እና ከዚህ ጋር ግንኙነት ባለው፣ ችግር ሂወታቸው እንዳጡ ሪፖርቶች ያመላክታሉ፡፡

 

ስለዚህ አሁንም ኢህአዴግ የመሰንጠቅ አደጋ፣ እንደ ነሐሴ ደማና ከላዩ ላይ አንዣብቧል፡፡ ኢህአደግ የመለያዩት አደጋ  ተጋርጦበታል፡፡  ይባስ ብሎ የአሁኑ ኢህአደግ ደሞ፣   የርእዮተ-ዓለም፣ የሀገረ መንግስታዊ  አወቃቅር ስርዓት (State formation)፣ የሀገረ መንግስት ስርዓት ግንባታ (State Biulding)፣ ከርእዮተ-ዓለሙ የሚመነጭ የሀገር ግንባታ ስርዓት (statehood)፣ የፍትህና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ወዘተ የማይታረግቁ ልዩነት አሉ፡፡ በሌላ አባባል፣ በህገ-መንስቱ ላይ የተቀመጠው፣ የብሔር ብሔረ-ሰቦች፣ የራሳቸው ዕድል፣ በራሳቸው የመወሰን ሉዓላዊ ስልጣን፣ ብሔር-መሰረት ያደረገ ከህገ-ምንግስቱ የሚመነጩ፣ የፌዴራል ስርዓት፣ በሊበራል ዲሞክራሲ እና ልማታዊ መንግስት ከፍተኛ ልዩነቶች አሉ፡፡  እነዚህ ልዩነቶች በዲምክራሲያ አገባብ አጥጣሞ፣ የመሄድ ዕድሉ ከፍተኛ ቢሆንም፣ ከላይ የተገለፁ የብጥብጥና ግጭት ነጋዴዎች እና ድንክየ የሸር ፖለቲካ ተንታኞች ተብየዎች፣ ጉዳዩ ሌላ መልክ በማስያዝ ወደ ማንወጣው አዘቅት ሊያስገቡን ይችላሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ ሁኔታዎች የሚያሳዩትም ይኸ ነው፡፡

 

አንዱ የሚያሰራጩት የውሸት (ቤረ ወለደ) የሴራ ፖለቲካ፣ ዶ/ር አብይ የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆኖ ላይመረጥ ይችላል፡፡ የለውጥ ቀልባሽ ሓይል ህወሀት ተመልሶ፣ ስልጣን ለመጨበጥ እያ ሴረ ነው ወዘተ በማለት፣ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት ሊሰገቡን ይችላሉ፡፡ ካሁን በፊት እንደተለመደው (እንደታየው)፣ በእህት ድርጅቶች፣ የማ/ኮ ኣባላት እና የድርጅቶች (በተለይ ኦዴፓ እና አዴፖ) ነገረ ፈጅ ነን ባዮች ዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና ከፍተኛ ኃላፊነት ወስደው እንዲንቀሳቀሱ አበክረን እንመክራለን፡፡ ይሄን ጉዳይ ካሁን በፊት ከፍተኛ ኃላፊነት ያለቸው፣ የማ/ኮ አባላትም ጭምር በዚህ ሴጣናዊ ድርጊት ሲዳክሩ እንደነበር፣ ማየት ይቻላል፡፡ በተለይ ለሻምበል አረጋይ የተባለው የትግራይ ተወላጅ (የህወሀት ደጋፊ ሊሆን ይችላል)፣ ከአንድ የኦዴፓ ማ/ኮ አባል (አቶ ሀብታሙ ኢተፋ)የደረሰው የማስመራሪያ መልእክት እጅግ ይሰቀጥጣል፡፡  መልእክቱ ከሞላ ጎደል እንዲህ ይነበባል፡፡ በዚሁ የሀዋሳ ጉባኤ፣ የድርጅቱ ዶ/ር ሊ/ቀ መንበር  ቦታ ለሌላ ለመስጠት/ለመውሰድብትንቀሳቀሱ (ብታሤሩ)፣ በብሔራችሁ (በትግራይ ህዝብ) እስከ ትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ እልቂት፣ እንዳወጃችሁ እንዲታወቅ ይላል፡፡ ተመልከቱ፣ የዲሞክራሲያሲ እድገቻተች፣ የአንድ ኃላፊ የመምረጥና ያለ-መምረጥ መብት፣ በህገ-መንግስቱ ከለላ የተሰጠው፣ ተፈጥራዊ እና ፖለቲካዊ መብት መሆኑ አይገነዘቡም፡፡ እነዚህ ሰዎች እንግዲህ፣ ምን ሊያዘጋጁ እንደሚችሉ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል፡፡ በቬሮኒካ መልአክሱ ስም የተከፈተ፣ የአዴፓ፣ ከፍተኛ አመራሮች (ሥራ አስፈፃሚአባላት ጭምር)  እንደሚጠቀሙበት የሚታወቀው፣ የፌቡ አካውንት በትግራይ ህዝብ ላይ ካሁን በፊት ተመሳሳይ ጥቃት እንዲፈፀም ጥሪ ሲያደርግ ነበር፡፡ በአማራ ክልል ውስጥ፣ ወደ ትግራይ ፣ ተገዝተው የሚሄዱ፣ ሸቀጣ ሸቀጦች፣ ጥርያ ጥሬዎች፣ በጎችና ደሮዎች፣ እንዲቀሙ እና እንዲዘረፉ፣ ትእዛዝ ሲያስተላፉ፣ እንደነበር፣ ተጨባጭ ማስረጃዎች አሉን፡፡ 

“Conspiracy against  Lemma  and Abiy will make you all and your children pay unnecessary price! Your move is against 40 million “ Habtamu Itefa

 

እርስ በርሱ ያልተግባባ ኢህአዴግ ኢ/ውያን ሊያግባባ ይችላል ወይ? የፌዴራል ስርዓቱና የሀገራችን አንድነትስ ጠብቆ ሊያስቀጥለው ይችላል ወይ?

የኛ ፍላጎት ህወሀትን ለመደገፍ አይደለም፡፡ ለሀገራችን  ገፅታ አሳፋሪ ነው እንጅ የድርጅት መሪዎች እና አባላት መየመድረኩና በየ አደባባዩ ቢቧቆሱ ደንታ የለንም፡፡ እጅግ አሳዛኝ ነገር፣ ግን ሁሌ ገፈት ቀማሽ የሚሆነው፣ ውድና ብርቅየ ልጆቹ መስዋእት አድርጎ፣ እዚህ፣ የሀገር ዋልታ፣ የሀገር መከታና ዋርድያ ሆኖ እዚህ ደረጃ ያደረሰው የትግራይ ህዝብ የጦስ ደሮ  በመሆኑ ነው፡፡ 

 

የኢህአዴግ በዘህ ወቅት ሳይፈርስ፣ "እንደተጣመርን ኣለን" ለማለት ያክል  በያለንበት፣ ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው፣ እና በሂዴት ኮሚቴ ተቋቁመው፣ እነዲጠና የመፍትሔ ሐሳብ እንዲቀርብ የሚቀርብ ሆኖ አንድነታችን ተጠብቆ፣ ጥሩ መንፈስ ተፈጥሮ ወዘተ ወጥተናል ሊሉ ይችላሉ፡፡ በዚህ መልኩ ኢህአዴግሊፒስቲክ ተቀብቶ የሚወጣ ከሆነ፡፡ የህወሀት አመራሮች፣ በሁኑ ወቅት ከዶ/ር አብይ የተሸለ መሪ ይፈልጋሉ ብየ ፍፁም አልገምትም፡፡ ከየትስ ይመጣል?ከደኢህዴን እዳይባል፣ ወ/ሮ መፈሪያት ካሚልና አቶ ሚልዮን ማትዮስ፣ አዲስ መጪዎች ሰለሆኑ፣ የልምድ እና የዐቅም ድንክየነት ያጠቃቿል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአመራር ቦታውም(የሚመኙት) የሚፈልጉት አይመስለኝም፡፡ ከ1987 ዓ/ም ጀምሮ በየክልል ድርጅታቸውና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ደመቀና አቶ ገዱም አሁን ከያዙት ቦታ የሚለጠጥ ዓቅም ኖሯቸው ከፍተኛ ኃላፊነት የሚመኙ አይመስለኝም፡፡ ቢመኙም የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ከ20  ዓመት በላይ፣ አእምሮየ አከራይቼ፣ በህወሀት ኃላፊች፣ በጓዳ በኩል ስሽከረከር ነበርኩ  ያሉት አቶ ደመቀ፣ የአጃቢነት ቦታቸው የማሰጠበቅ ዕድልሉ ከፍተኛ ነው፡፡  እዚህ ላይ፣ ያልታሰበ ሁኔታ ተፈጥሮ  ትንሽ ግምት ሊሰጣቸው የሚችል፣  ግማሸ ትውልዳቸው የስልጤ፣ ከፊላቸው የኦሮሞ ተወላጅ እንደሆኑት የሚነገረውወ/ሮ መፈሪያት ከሚል  የምክትሉ ቦታ እንዲይዙ፣ የኦዴፓ ፍላጎት ሊኖር ቢችልም፣ በሁለት ምክንያት ገቢራዊ የመሆን ዕድሉ የጠበበ ነው፡፡ (1) ህወሀት ለማጥቃት የተፈጠረው፣ በኦሮማራ  ታክቲካዊ ቅንጅት፣ ዶ/ር አብይ (ኦዴፓ) ስልጣን እንድይዝ፣ ባለቀ ሰኣት  የማይተካ ሚና  በመጫወታቸው፣ ለአዴፓ ካሳ የመክፈል እና ትስስሩ የማሰቀጠል፣ ሂደት ስለሚያጠናክርአቶ ደመቀ በያዙት ቦታ ቢቀጥሉ የኦዴፓ፣ ከአዴፓ በቀጣይነት ለማግኘት የሚፈልገው የግሊያነት አገልግሎት ለማጠናከር ስለሚያግዝ፡፡ ሌላም፣ ትንሽ ልምድና የዐቅም ውስንነት እንዳላቸው የሚገመቱት ወ/ሮ ከሚል፣ ይህንን ስልጣን (የም/ጠ/ሚ) ቦታ ይሰጣቸው ቢባል፣ በደቡብ ህዝችም ኦዴፓ ቁጥር ሁለት እንደነገሰ ስለሚገመት የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ ይህንን አማራጭ ይደግፋሉ ብየ አልገምትም፡፡  በቬሮኒካ መላኩ ስም ተከፍቶ በንጉሱ ጥላሁን እና ዶ/ር አምባቸው እና ሌሎች ቡድኖች የሚጠቀሙበት፣ አካውንት፣ የም/ጠ/ሚ ቦታ ከአዴፓ ለመውሰድ ሴራ እየተሰራ ነው፣ በሚል የማስጠንቂቃ አይሉት ማስፈራርያ ፅሑፍ አውጥቷል፡፡ ነገር ግን ይህንን ክስ ብዙ ውሀ የሚቋጥር እና ሚዛን የሚደፋ አልመሰለኝም፡፡

 

 

ስለዚህ በአሁኑ ወቅት፣ከነ ጉድለቶቹ ከኦዴፓ ውጭ፣ የሰው ስሜት ያለው (ሰው ሰው የሚሸት) ማግኘት ስለ ማይችል የሊ/መ ቦታው እንደተጠበቀ እንደሚቀጥል እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡ ያ ማለት የክርክር ዓውድ ሊሆን የሚችለው የርእየተ ዓለም፣ በፖሊሲና ፕሮግራም ወዘተ ነው፡፡ እስኪ የልነቱ አንጓ በየድርጅቱ ከፋፍለን እንየው፡፡

(1)  የህወሀት፡- የዚህ ድርጅት ችግር፣ አቤታዊ ዲሞክራሲ ወይ ሞት! ልማታዊ መንግስት ወይ ሞት የሚል አክራሪ አቋም ነውየሚያራምደው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ ኒዮ-ሊበራሊም እና የሊበራል ዲሞክራሲ እንደ ጭራቅ አድርጎ የማቅረብ ስታሊናዊ እይታ ነው፡፡ በመሰረቱ ሁሉም አመራጮችናቸው፡፡ አማራጮች ስለሆኑም፣ ህዝብ እንደየፍከላጎቱ እንዲመርጥ፣ እኩል መብት ሊሰጠው ይገባል፡፡ለሀገራችን የተኛው ይሻላል የሚል ግን ሊያከራክር ይችላል፡፡ እንደዚህ ዓይነት፣ አክራሪ የህወሀትአቋም ግንለድርድርም አይመችም፡፡ የፖለቲካ ዋና ጥበብ ደሞ ለመደራደር መዘጋጀትና በድርድር ክህሎት የተገነባ ዓቅም ማዳበር ነው፡፡ ህወሀት በባለቤትነት የምታንቀሳቅሰው የአብዮታዊ ዲሞክራሲና የልማታዊ መንግስት ርእዮ-ዓለም፣ ከሀገራችን ድህነት፣ ኋለ ቀርነትና ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ አልቻለም፡፡ አሁንም ኢ/ያ ከዓለም 3ኛ ድሀ ሀገር ነች፡፡ ስለዚ የእይታ ክለሳ ማድረግ ያሰፈልጋል፡፡ ልዩ ትኩረት የሚሻ እግጅ አንገብጋቢ ጉዳይም ነው፡፡ እዚህ ላይ ያለው ውስብስብ ችግር የሀገራችን 80 ፐርሰንት አርሶደር በሆነበት ስርዓት፣ የኒዮ-ሊበራሊዝማ  ዲሞክራሲና የሊበራሊዝም  ዲሞክራሲ ስርዓቶች፣ ፍቱን መድሐኒት ናቸው ብየ አላምንም፡፡ ሊሆኑም አይችሉም፡፡ ከኔ ሐሳብ የሚስማሙ በርካታ አንቱ የተባሉ ሙሁራን እንዳሉ፣ ለማሳየትም፣ በነሐሴ ወር  2010 ዓ/ም በዶ/ር አለማዮህ ገዳ፣ በሪፖርተር አማርኛ ጋዜጣ የወጣው፣ በጥናት የተደገፈ እና በርካታ ተጨባጭ ተመኩሮዎች የዳሰሰ ምርጥ ፅሑፍ ማየት ይቻላል፡፡

በደንብ ሳይገባቸውና ሳያኝቹ አለምጠው የሚውጡ ግብዝ ሰዎች እና የ60ዎቹ ቆሞ ቀሮች የኒዮ-ሊበራሊዝምና፣ የሊበራሊዝም አማራጭ ለሀገራችን ይበጃል ሲሉ፣ ከምር የኢ/ያ ህዝብ ውስብስብ ችግር፣ ይፈታል የሚል እውነተኛ እምነት ኖሯቸው ሳይሆን፣ የሀገራችን አብኛው አርሶ አደር ወደ ከፋ የኢኮሞኒ ማጥ ከተው፣ የአሜሪካ እና አውሮጳ ከበርቶዎችና ትላልቅ ካምፓኒዎች ተሸጠው የሚያገለግሉ፣ ለሆዳቸው ሲሉ ህሊናቸው እና ወገናቸው የሸጡ፣ የ21 ክ/ዘመን ባንዳዎች ናቸው፡፡

 

እዚህ ላይ፣ ህወሀትን ሳያውቁት በደንብ ያወቁት የሚመስላቸው የውሆች የሚፈፅሙት መታረም ያለበቸው ትላልቅ ስህተቶች አሉ፡፡ ህወሀት የርእዮተ-ዐለም አክራሪ ድርጅት ነው እንጂ፣ ከትግል ወቅት ጀምሮ፣ ልቅም ያለ፣ በጥብቅ ዲሲፒሊን የሚፈፀም እና ሁሉም እንደ መጽሓፍ ቅዱስ የሚያነበው፣ የኮሚኒስታዊ የርእዮተ-ዓለም ባለቤት ነው፡፡

ይህን ለማለት የፈለጉበት አንኳር ምክንያት ዶ/ርደረጄገረፋ የተባሉ ኦዴፓ ነገረ ፈጅ፣አሉት የተባለው፣ ከፌቡ መንደር ከ ብሩክ ብርሀኑ ፖስት ያገኘሁትBiruk Birhanuእንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 

የኦዴፓ ነገረ ፈጅ እና የእፍኝ ልጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ዶ/ር ደረጀ ገረፋ ትሉ በመስከረም 22/2011 ዓ/ም ከፎርቹኑ ታምራት ወልደጀመወርጊስ ጋር በፋና ቲቪ አደረጉት ከተባለው ውይይት፣ ዶ/ር ደረጀ የፈፀማቸው ህፀፆች (ስህተት) በትንሹ መቃኘት ፈለኩ፡፡  ብሩክ እነዲህ ሲል ከትቦረታል፡-

“ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የፎርችኑ አቶ  ታምራት " እስካሁን ካለው የኢህአዴግ አመራር ግልፅ መልስ ያላገኘሁባቸዉ" ብሎ ካነሳቸዉ ጥያቄዎች አንዱ እንዲህ በማለት ያስቀምጣል. <<ከዚህ በፊት ኢህኣዴግ ግልፅ organizational እና operational principles እንደነበሩት ኣዉቃለሁ. ኣሁንስ ኣለዉ ወይ?>> ብሎ ጠየቀ: ዶ/ር ደረጀ ቀጠለ (መልስ መሆኑ ነዉ)..<<ኢህኣዴግ ድሮም organizational principle አልነበረዉም ኣቶ መለስ ያመጡት ነዉ ከሳቸዉ ዉጪ የሚያዉቀዉ ኣልነበረም፡፡ ይሄ ዴሞክራሲያዊ ማእከላዊነት የሚባለዉ operational principle ግን በጥርናፈ ማጨናነቅ ነዉ. ኣሁን ለምሳሌ እኛ እንደ ኦሮሞ ማህበረሰብ መጨናነቅ ምናምን ኣይመቸንም...>> እያለ ቀጠለ” ዶ/ር ደረጃ እዚህ ላይ የፈፀሙት ስህተት ትልቅ ቢሆንም፣ሀገር ከመውደድና ድርጅታቸው ከመደገፍ ከቅን ልቦና ተነስተው፣ ከሞያቸው ውጭ የሆነው ዓውድ ገብተው፣ ሐሳባቸው ሲገልፁ ከቅንነትየተነሳ፣ የተፈፀሙ ህፀፆችይሆናል በማለት በጨዋ አገላለፅ የዶ/ር ደረጃ ህፀፆች ባጭሩ ልቃኝ፡፡

(ሀ) ህወሀት/ኢህአዴግ እጅግ ጥርት ያለና እንደ ጧት ውሀ ኩል የመሰለ፣ ርእዮተ ዓለም እንዳለው እና ከ50 ሺ በላይ የከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ እርከን አመራሮች እንዳሰለጠነ እና እስካሁን ስለጠናው የቀጠለ እንደሆነ፡፡

(ሁ) በኔ አረዳድ  የኢህአዴግ ርእዮተ ዓለም የሚባለው፣ የአብዮታዊ ዲሞክራሲና ልማታዊ መንግስት የገቢያ መር እንጅ፣ የዚህ ማስፈፀሚያ ስልት የሆነው ዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት አይደለም፡፡ ስለዚህ ዶ/ር ደረጀ ርእዮተ-ዐለም፣ ፖሊሲ፣ ስትራተጂና እና ማስፈፀሚ ስልት ለይተው መረዳት አለባቸው፡፡

(ሂ) ከሷቸው በላይ ስለኦሮሞ ህዝብ ማውራት ድፍረት ቢሆንም፣ ሳስበው ግን፣ ቤት ውስጥ የምትናገረው ነገር ግን ወደ ውጭ የማይወጣ መዓት የቤተ-ሰብ ነገሮች (ሚስጥሮች) ሊኖሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ የዲሞ0ክራሲያዊ ማዕከላውነት፣ ልዩነት ካለህ በመድረክ ውስጥ ትገልፃለህ እንጂ ልዩነትህን ወደ ውጭ ይዘህ የመውጣትና የመናገር ነፃነት የለህም የሚል ነው፡፡ አፋኝ አሰራር መሆኑ ግን ሁሉም የሚያግባባ ነጥብ ይመስለኛል፡፡

 

 

(2)  አዴፓ፡- አቶ ደመቀ ለመገናኛ ብዙኃን (ለአማራ ቲቪ) በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ የድርጅታቸው ምርጫ፣ በግለ ሰብ መብት ላይ የተንጠለጠለው፣ ሊበራል ዲሞክራሲ እንደሆነ በማያሻማ አቅጣቻ አስቀምጧል፡፡ እንደዚህ በግልፅ፣ እንደ አማራጭ መቅረቡ መብትም፣ የሚጠበቅም ነው፡፡ ነገር ግን በግለ ሰብ መብት ላይ የተንጠለጠለ፣ የሊበራሊዝም ስርዓት የአማራ ህዝብ ተግዳሮቶች፣ ድህነትና ኋላ ቀርነት እዴት ሊፈታው እደሚችል አላብራሩም፡፡ ለወደፊቱም፣ የሚያውቁትና የሚያብራሩት አይመስለንም፡፡ በግለ-ሰብ ላይ የተገነባ የሊበራል ዲሞክራሲ ስርዓት፣ የቡድኖች መብት እንደማያከብር፣ የተገነዘቡት አልመሰለኝም፡፡ ግለ-ሰብ ላይ የተገነባ ሊባራል ስርዓት አዴፓ የሚገነባ ከሆነስ፣ ከአግ7 በምን ይላያል ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች፣ አሁንም አልተመለሱም ወደፊትም ይሄንን የሚመልስ ዓቅም ያለው አመራር በአዴፓ ያለ አልመሰለኝም፡፡ ባጭሩ ግን የአብዮታዊ ድሞክራሲ ርእዮተ-ዐለምና የሀገራችን የፌዴራል ስርዓት እንዲከለስ አዴፓ/እንዲቀየር አበክሮ ይሰራል በሚል መነፈስ፣ በባህርዳር የተካሄደው 12 ኛው የድርጅቱ ጉባኤ ድምዳሜ ተይዘዋል፡፡

(3)  ኦዴፓ፡-የመደመር ዝባዝንኬ የጠራ ቆመና ሳይነሮውና የተደላደለ ቅርፅ ሳይዝ፣ የሚቀርብልህ አማራጭ zero-sum game (dummy politics) የታጀበ ወይ መደመር ወይ ሞት ነው፣ ወይ ከነሱ ጋር ወይ ከኛ ጋር ወዘተ  የሚሉ ናቸው፡፡ተከታይ መንጋዎችም እነዚህ እንደ መፅሃፍ ቅዱስ ይዳጋግሙታል፡፡ እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ፣ለውጥየሚጠላ አካል የለም፡፡ ተፈጥራዊምም ነው፡፡ ስለዚህ ለመኖር መለወጥ ኣለብህ፡፡   ማ/ሰባዊ ለውጥ (social transformation)  እውን የሚያደርግ ለውጥ፣ አካታችና ሁሉም ተጠቃሚ የሚያደረግ ለውጥ፣ መደገፍ እና ማበራታት ያለበት ነው፡፡ ነገር ግን ከ80 ከመቶአርሶ አደር ባለበት ሀገር፣በመሰረቱ ተለውጧል  የተባሉ ድርጅቶች ምናቸው እንደተለወጠ፣ ርዮተ-ዓላማችው፣ ምን እንደሆነ፣ ፖሊሲው፣ ስትራተጂው፣ ፕሮግራሙ፣ ስልቱ መገልጥ የማይችሉ ከእውቀት ነፃ የሆኑ  ፍልጦች፣የለውጥ ምንነት ሳይገባቸው፣ በደፈናው፣  እንትና መለወጥ የማይችል የሽማግሌዎች፣  ስብስብ ነው፡፡ እንትና ማህፀን አርጧል፡፡  በተለይ የመደመር ደቀ መዛሙርት፣ ያልተደመረው እንትና ፀረ አብዮት ወዘተ እያለ፣  እነሱ በፈጠሩና ምልክት በሰጡት ( labeled) ባደረጉት፣ ሳጥን (box)፣ ምልክት ያደረጉበት ባዶሳጥንና በምናባቸው፣ አምሮቸው፣ እና  ተአምር መስራት እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡

 

አንድ ወጥ የሆነ፣ መሀከለኛ አቋም ይዘው፣ ከግራ እና ከቀኝ ያለውን ኃይል ለማቀፍ ከመሞኮር ይልቅ፣ የጭብጨባው ርዝመት እና የጭሆቱ ድምቀት ተከትለው ወደ ግራና ወደ ቀኝ ወደ ነፈው የሚነፍስ ግራ የተጋባ ኃይል ነው፡፡ ነገር ግን ከፍ ሲል የፎርችኑ አቶ ተአምራት እንዳለው፣ የርእዮተ ዓለም፣ የፖሊሲ፣ የስትራተጂ ወዘተ የጠራ ማዕቀፍ የላቸውም፡፡ ለዚህም ነው፣ አንዴ እዚህ፣ አንዴ እዚያ ሲረግጡ የሚታዩት፡፡

 

የኦዴፓ ግራ መጋባት ቁልጭ ብሎ የሚታየው፣ ዛሬ (መስከረም 23/2011 ዓ/ም) ባደረጉት የሀዋሳ የመክፈቻንግግር እንመልከት

‹‹ክልላዊ አስተዳደርን ከብሄር ማንነት ጋር ሳናምታታ ማስተናገድ ከቻልን፣ እንደኛ አገር ላለ ነባራዊ ሁኔታ ፌደራሊዝም ተመራጭ የአስታዳደር ስርዓት መሆኑ አያጠያይቅም።›› የሚለው አገላለፅ፣አሁን ያለው፣ ብሔር (ቋንቋ) መሰረት አድርጎ የተዋቀረው፣ የፌዴራል ስርዓት የሀገረ መንግስት አወቃቀር ስርዓት መከለስ አለበት ማለት ነው፡፡ እነዲህ ዓይነት ግራ የሚያጋቡ እና አሻሚ ትርጉም ያለቸው ንግግሮች በየመድረኩ ያደርጉና በቂ ትንተና ሳይሰጡ፣ ርእዩተ-ዓለማቸው፣ ፖሊሲያቸው፣ ራኢያቸው ወዘተ ሳያስቀምጡ ይቀራሉ፡፡

ይሄንን ንግግር አድቅቆና በታትኖ ላነበበው አካል የሕብረ-ብሔራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት የሚፃረርና፣ ቋንቋ መሰረት ካደረገ ፌዴራላዊ ስርዓት ይልቅ፣ ሌሎች ተፈጥራዊና መልከዐ-ምድራዊ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ያስገባ የፌዴራል ስርዓት ግንባታ እንደሚያሰፈልግ አቅጣጫ ተቋሚ ነው፡፡ እንደዚህ ያለ አሻሚ መልእክት ያዘሉ ንግግሮች ከጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የተመዱ ናቸው፡፡

‹‹እንቁላል ከውስጥ ሲሰበርሀ ብሎህይወት ይጀምራል፣  ከውጭ ሲሰበር ግን ሞት ነው፡፡ ኢህአዴግም ከውጭ ተሰብሮ ከሚሞት ከውስጥ ሰብረን ህይወት እንዘራበታለን ፡፡››  ይሄም በተመሳሳይ አሻሚ እና፣ የኢህአዴግ ርእዮተ ዐለም መቀየር አለበት የሚል እንድምታ ያለበት ነው፡፡ እንደ ሀገራችን ጠ/ሚ እና እንደ ኢህአዴግ መሪ፣ የፈለጉት ርእዮተ-ዐለም፣ ፖሊሲ፣ ስትራተጂ፣ ራኢ ወዘተ የመቀየር(ለመቀየር የመነሻ ሐሳብ ማቅረብ)መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ ምንም ችግር የለውም፡፡ ችግሩ ግን ምንም አማራጨች ሳያስቀምጡ ማለፋቸው ላይ ነው፡፡ ይሄ ደሞ አሁን ያለው ግራ መጋባት ያጠናክረዋል፡፡

እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ግን፣ በኦሮሞ ሊሂቃን የኦሮሞ ህዝብ ብሔራዊ ድርጅቶች፣ ዋና የየብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ትክክለኛ ፌዴራላዊ ስርዓት ደጋፊዎች እንደሆኑ ሳል ጠቕስ አላልፍም፡፡

(4)  የደኢህዴን፣ የፌዴራል ስርዓቱ የዚህ ክልል ውስብስብ ችግር ለመፍታት በሚያስችል ሆኖ አልተቀመጠም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ የዚህ ክልልና ድርጅት ችግር እጅግ የተወሳሰበ እና በጥሞና ተጥንቶ የመፈፍትሔ አማራጮች ሊቀመጡለት የሚገባ ነው፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ ድሮም ደካማ እና ተከታይ ከመሆኑ ጋ ተያይዞ፣ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ዐቅምና፣ ችሎታ እና ልምድ ያላቸው ጉምቱ፣ የድርጅቱ መስራቾች ጠራርጎ አባርሮ፣ የተራ ሰዎች መፈንጫ ሆነዋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ድርጅት የሚጠበቅ ርእዮ ዐለም፣ ፖሊሲ፣ ስትራተጂ  ወዘተ ብዙ አይኖርም፡፡ የኦዴፓ አጫፋሪ ሆኖ የመቀጠል ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡

በእጅ የያዙት ወርቅ እንደ ጨርቅ ይቆጠራል !እንደሚባለው፣ የያዙት ርእዮተ-ዐለምና የልማታዊ መንግስት መስመርና ትግበራ በቅጡ ሳይረዱ እና በተግባር ተፈትሽው ስኬቱ እና ውድቀቱ ሳያረጋግጡ በየመድረኩ፣ በየዕለቱ፣ እንደየ እየለቱ የዐየር ፀባይ፣ ርእዮ-ዓለማቸው እና የመንግሰት ፖሊሳቸው የሚቀያይሩ መሪዎች ይሰውረን!

 

ምን እንጠብቅ?

ከሞላ ጎደል የድርጅቶች አሠላለፍ፣ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ነጥብ ለማየት፣ በኢህአዴግ ጉባኤ  በመድረኩ የተላለፉ መልእክቶች እና ከጉባኤው በፊት፣ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃንና በሶሻል ሚድያ የሚተላለፉ መልእክቶች መቃኘት ያሰፈልጋል፡፡ ከአዴፓ ብንጀምር፣ በአማራ ክልል የተደረጉ ሠልፎች፣ በተላያዩ መድረኮች፣ በክክልሉ መገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉ መልእክቶች፣ በአዴፓ 12ኛው የድርጅቱ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች፣ ወደ ክልሉ የተንቀሳቀሱ ኃይሎችና ግለ ሰቦች ወዘተ ያሰተላለፉት መልእክት አንድ እና ተመሳሳይ ነው፡፡ የፌዴራል ስርዓቱ አማራ አልተሳተፈበትም፣ የአማራ ጥቅም አላከበረም፣ በኢ/ያ የሚታዩ ሁሉም ችግሮች፣ ግጭቶችና እልቂቶች የሐብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ግድፈቶች ውጤት ናቸው ፣ የሕብረ-ብሔራዊ የፌዴራል ስርዓቱ ሠይጣናዊ እና እርኩስ ስለሆነ፣ መጣል አለበት ወዘተ የሚሉ አዝግ ንግግርሮችና ዲስኩሮች ማየትበቂ ነው፡፡

 

ይህንን ጉዳይ በተለያዩ ሚድያዎች ለ25 ዓመት ሲሰብኩበት የነበረው፣ ነገር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በተለይ ወደ ክልሉ የተንቀሳቀሱ፣ ጅርጅቶች፣ ቡድኖችና ግለሰዎች፣ ሕብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም፣ ለማጥፋት፣ ለ25 ዓመት ሲዳክሩ ነው የኖሩት፣ የጠቅላይ አግላዮች፣ የግዛት ተስፋፊዎች፣ የሙታን መንፈስ፣ ወራሾች፣ የምናባዊ ማሕረብ ተወካዮች፣ በሙታን መንጋጋ የሚያመነዥጉ ድኩሞች፣ የአሀዳዊ ስርዓት አራማጆች ናቸው፡፡ የህብረ-ብሔራዊ ፌዳራላዊ  ስርዓት የሁሉም ችግሮች ምክንያት አለመሆኑን ስለማይቁት ሆኖ አይደለም፡፡  ዓላማቸው አሀዳዊ ስርዓት መመለስ ስለሆነ፣ የህብረ-ብሔራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ጥላሽት ለመቀባት ኢ/ያ ውስጥ ለተዩ ችግሮች፣ እምደ ምክንያት መውሰዳቸው ሊገርመን አይገባም፡፡ ‹‹አንድ ህዝብ አንድ ኢ/ያ!›› ብሎ የሚያምነው ኃይል፣ መሬት ላይ ያሉ እውነታዎች መገንዘብ ያልቻለ፣ በ60 እውቀት የቆመ፣ በውስጡ በአሀዳዊ ስርዓት ልዩ ተጠቃሚ ነበርኩ ብሎ የሚያምን  የውሸት  ኢ/ያነት መንነት ጭምብል ለብሶ የሚንቀሳቀስ፣ ባብዛኛው ካንድ አከባቢ የተሰባሰበ ኃይል ነው፡፡  የተለየ (ከፍ ያለ) እውቀት፣ የኢኮኖሚ ዓቅም፣ ችሎታ ያለው ይመስለዋል፡፡ ነገሮች እንደተለዋወጡ አለማወቅና፣ በአሁኑ ወቅት ይህን ኃይል እዚህ ግባ የሚባል ዓቅም እንደሌለው ግን ሊሰመርበት ይገባል፡፡

 

በዲሞክራሲያዊ አሰራር፣ አንደ ሰው ኢ/ያ መንነት ለኖረኝ እፈልጋለሁ ካለ፣ ሊከበርለት ይገባል፡፡ በህግም-ከለላ ለደረግለት ይገባል፡፡ ዲሞክራሲ ልዩነቶች አቻችሎ መሄድ ነውና፡፡ ችግሩ ግን እነዚህ ሰዎች ኢ/ያ መንነት ካላቸው ለምን ሁሉም የኢ/ያ ክልሎች አይጎበኙም? ለምን ስለሁሉም የኢ/ያ ክፍሎች ድርሰት አይደርሱም? ለምን ስለሁሉም የኢ/ያ ክፍሎች ፊልም አይሰሩም? ለምን ስለሁሉም የኢ/ያ ቦታዎች አይዘፍኑም? ለምን ስለሁሉም የኢ/ያ ነገስታት ታሪክ አይደጉሱም? ለምን ስለሁሉም የኢ/ያ ነገስታት አይዘፍኑም? ስለጎንደርና ጎጃም ብቻ እየዘፈኑ ኢ/ያዊ መንነት ነው ያለኝ ማለት  አይናችሁ ጨፍኑ ለሞኛችሁ ማለት አይደለምን? የነዚህ ቁንጮ የሆነው፣ ድምፃዊ፣ቴድሮስ ካሳሁንን እንመልክት፣ ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ዘነፎቹ፣ ስለ ምኒሊክ፣ ስለ ኃይለስላሴ፣ ስለ ቴዎድሮስ፣ ስለ ጎንደር፣ ስለ ጎጃም ወዘተዘፍኗል፡፡ ስለ ካዎ ጦና፣ ስለ አባጅፋር፣ ስለ አዳል ሱልጣን፣ ስለ አፄ  ዮሀንስ፣ አልያም  ሰለ ጅግኖቹ ስለ አሉላ አባ ነጋ፣ ስለ ባሮ ቱምሳ፣ ስለ ታደሰ ብሩ፣ ወዘተ ወይም በአለም ልዩ ክብር የሚሰጠው ስለ ጋዳ ስርዓት ለምን አይዘፍንም? ነገር ግን ኢ/ያዊ መንነት ያለን ቅብርጥሴ እያለ አንድ አዝማሪ መሆኑ ቀርቶ ትልቅ ፈላስፋ መስሎ፣ በትቢት ይናገራል፡፡ ሌሎችም ተመሳሳይ ናቸው፡፡

 

እነዚህ ናቸው እንግዲህ ሐሳዊ የኢ/ዊነት መንነት ጭምብል ለብሰው፣ ስለ ግለ ሰብ ላይ ተመስርቶ የሚገነባ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚሰብኩት፡፡ እነዚህ ኃይሎች መሬት ላይ ለው እውነታ ማየት ያቃታቸው፣ በ60 ላይ የቆሙ ቁሞ ቀር እና እርባና ቢሳ ኃይሎች ቢሆንም፣ በነበራቸው ልምድ ተጠቅመው ሚድያው ተቆታጥረው፣ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ጭምር ተጠቅመው ሌት ተቀን ስለሚሰብኩ፣ ቢያን  በአማራ ክልል፣ በአዲስ አባባ እና ሌሎች አንድንድ አከባቢዎች፣ ተከታይ ማፍራታቸው አለ የማይባል ሐቅ ነው፡፡

እነዚህ ኃይሎች ለቡድን መብት እውቅና የማየሰጡና የግለ ሰብ መብት ከተከበረ፣ የግለ ሰዎች ስብስብ የሆነው ቡድን ይከበራል የሚል አስቂኝ አመክንዮ የሚሰጡ ድንክየዎች ናቸው፡፡ እውነታው ግን የግለ ሰብ መብት ስለተከበረ፣ የቡድን መብት ተከበረ ማለት አይደለም፡፡ እንዳው በተቃራኒው፣ በግለ ሰብ መብት ስም፣ የቡድን መብት ሊጨፈለቅና ሊዋጥ ይችላል፡፡ እጅግ የበለፀጉ ሀገሮች፣ አመሪካም ጭምር በትክክል ያለፈቱት (ያለከበሩት) መብት የቡድን መብት አካል የሆነው ንኡስ ቡድን (minority group right) መብት ነው፡፡

 

በሀገረ አመሪካ እስካሁን ያልከሰመውና ለግጭት መንስኤ የሚሆነው፣ የንኡስ ቡድን መብት (minority group right) አካል የሆነው፣ የጥቁሮች መብት ባለመከበሩ ነው፡፡ የግለ ሰብ መብት ተከብሮ እንዴት የቡድን መብት ሊከበር እንደማይችል፣ አንድ ምሳሌ እንስጥ፡፡ የአካውንቲግና ፋይናነስ የማስተርስ ዲግሪ ያለው አቶ ቶላ በሪሶ በሙያው፣ በኢ/ያ ንግድ ባንክ ዋናው መስራቤት ተቀጥሮ ይሰራል፡፡ እንደ ግለ ሰብ ውሉ ከባንኩ ጋ አስረዋል፡፡ ባንኩ የእድገት መብቱ፣ የት/ት መብቱ፣ የዋስትና መብቱ ወዘተ  ቢጥስ የትም ቦታ ሂዶ ቅሬታ አልያም ክስ አቅርቦ መብቱ ሊያስከብር ችላል፡፡ ነገር ግን አቶ ቶላ የሚወክሉት (የመጡበት/የተወለዱበት) ማ/ሰብ ቋንቋ፣ ባህል፣ ወግ፣ ታሪክ፣ እሴት ወዘተ ክብር የሚነካ ወንጀል ሲፈፀም አልያም ሲጨቆኑ ወይም እኩል እንዳልተሰናገዱ ቢመለከት እና የመጣበት ማ/ሰብ መብት አልተከበረም ብሎ የቡድን መብት ጥያቄ ቢያነሳ፣ የሚያሰተነናግደው አካል የለም፡፡ በነዚህ ኃይሎች የተቋቋመው ሕግ-አውጪው አካል በግለ ሰብ  ደረጃ የተገናበ መብት ነው የሚያውቀው፡፡ ስለዚ የግለ ሰብ መብት የሚመለከት እንጅ የቡድን መብት ጉዳዩ አይደለም፡፡ 

 

ስለዚህ ይህንን የቡድ መበት ጥያቄ ለማስተናገድ የወጣ አዋጅ የለም፡፡ (ለምሳሌ፣ ለደርግ ኢሰፓ-አኮ 10ኛው የልደት በዓል ሲከበር፣ ከተላያዩ አከባቢዎች የባህል ቡድኖች፣ ስራቸው እንዲያቀርቡ፣ ጥሪ ተደርጎላቸው ነበር፡፡ ከትግራይ 13፣ ከወሎ 12፣ ከወለጋ 15፣ ከጎጃም 17፣ ከጎንደር 15 ወዘተ የተለያዩ ዘፈኖች፣ ለዝግጅቱ አስተባባሪዎች ያቀርባሉ፡፡ ኢሰፓ-አኮ ወክላ፣ የዚህ ቡድን ኃላፊ የነበረችው፣ አለምፀሀይ ወዳጆ፣ ከወሎ 8፣ ከጎጃም 13፣ ከጎንድር 15 ስታስተላልፍ፣ ከወለጋ ግን ከትግራይ (ሎሚ ፅባሕ፤-ሶፍያ አፅበሃ) ግን አንድ ዘፈን ብቻ መረጠች፡፡ ምነው ተብላ ስትጠየቅ፣ የናንተ ቋንቋ  ግርድፍ ነው፡፡ ለጀሮ ይከብዳልና የኢሰፓ-አኮ ኃላፊዎችና ጓድ ሊቀመንበር፣ ላያስደስታቸው ይችላል አልች ይባላል)፡፡  እዚህ ላይ በግልፅ የቡድን መብት እንደተረገጠ ማየት ይቻላል፡፡ በሰው በላው የደርግ መንግስት፣ የተኛው መብት ተከበረ ነውና ትሉ ይሆን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች እስካሁን ያለቸው እይታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከ20ና 30 ዓመት በላይ በአሜሪካና አውሮጳ ተቀምጠው፣ የዲሞክራሲ ምንነት ግን አለገባቸውም፡፡ ለ20 እና ለ30 ዓመት ውሀ ላይ እነደተቀመጠ ጋራናይት ዲንጋይ ናቸው፡፡

 

አቶ ቶላ ለፍርድ ቤት አቤት የማለትወይም(ክስ) የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን የቡድን መብት የሚመለከት የወጣ አዋጅ ስለሌለ፣ ፍርድ ቤት ጥያቄው ሊያስተናግድ አይችልም፡፡ አቶ ቶላ ያለው ዕድል የቡድን መብት ሲደፈጠጥ አልያም አሜን ብሎ ተቀብሎ ጭንቅላቱ ደፍቶ መኖርል አልያም ይህንን ኢፍትሓዊና ጮቋን ስርዓት ለመገርሰስ ሁለንታናዊ ትግል መጀመር ነው፡፡ አብዛኛው ከባድ እልቂት ያስከተሉ የእርስ በርስ  ጦርነቶች መንስኤያቸው፣ ከዚህ ከቡድ መብት አለመከበር ጋ ተያይዞ ነው፡፡ የ60ዎቹ የተማሪዎች ዓመፅና፣የኦነግ፣ ሸዓቢያ፣ ህወሀት፣ ወዘተ የትጥቅ ትግልም መንስኤ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው፡፡  ሲጠቃለል አዴፓ የነዚህ ኃይሎች ተላላኪና የኋላ ቀር አስተሳሰብ አራማጅ ሆኖ አርፏል፡፡ ካሁን በኋላ በቀላሉ ታክሞ ይድናል ተብሎም አይጠበቅም፡፡ አዴፓ እንዴት ተብሎ ኃላፊነት ይዞ እደሚቀትል ራሱ እንቁቁልሽ ነው፡፡ በማያምንበት (በማይቀበለው) ርእዮተ-ዐለም፣ በማያምንበት (በማይቀበለው) ሕገ-መንግስት፣ በማያምንበት ከህገ-መንግስቱ በታች ያሉ ሁሉም ህጎች እና የሀገሩቱ አወቃቀር፣ ወዘተ ይዞ ሀገር መምራት ያዳግታል፡፡ ጉዳዩ ባስኳይ ካልተፈታም፣ ክልሉ ወደባስ እልቂጥና ጦርነት ሊያስገባው ይችላል፡፡ አዴፓ መሰረቱ አጥቷል የምንለውም ለዚህ ነው፡፡ ርእዮ-ዓለም የሌለው ፓርቲ፣ በህገ-መንግስቱ የማይገዛ (ሕገ-መንግስቱ) የማያከብር የመነግስት መዋቅር ወዘተ ይዞ ሀገርም ሆነ ክልል መምራት አይቻልም፡፡

 

ኦዴፓ በግለ ሰብና በቡድን መብት መከበር ላይ ያለው አቋም ነጥሮ የወጣና ግልፅ ሆኖ የሚታወቅ አይደለም፡፡ እንደ የኢህአዴግ ሊ/መ ዶ/ር አብይ ንግግር ግን ወደ ግለ ሰብ መብት መከበር የሚያደላ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ይህንን አቋማቻ በኦሮሞ ኤሊቶች፣ በኦሮሞ ተፈካካሪ ድርጅቶችና በታላቁ በኦሮሞ ህዝብ ተቀባይት የሌለው ስለሆነ ከፍተኛ ዋጋ ሊያሰከፍላቸው ይችላልና ይገፉበታል በተግባር ተብሎ አይገመትም፡፡

 

የደኢህዴን በብዙ የስልጣን ይገባኛል ጥያቄ (የአሁኑ ጉባኤ ወላይታ፣ በደኢህዴን ማ/ኮ ምርጫ በሚገባ አልተወከለም የሚል ከፍተኛ ቅሬታ አለ)፣ በጎጠኞች  ሤራ የሚናጥና ራሱን ችሎ ያልቆመበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ራስ ሳይጠና ጉተና እደሚባለው፣ ድርጅቱ በሁለት እግሩ ሳይቆም፣ ስለ ርእተ-ዓለምና ፖለቲካዊ አቋም መተንተን ይከብዳል፡፡ለጊዜው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ርእዮተ-ዐለምና የሕብረ-ብሔራዊ ፌዴራዊ ስርዓት እናጠናክራለን የሚል ለዘበብተኛ አቋም እንዳለው ቢገመትም፣ ቢሂደት ከካበለ ጊዜው ድርጅቶች፣ በተለይ ከኦዴፓ የሚዘው አቋም ሊያራምድ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ 

 

ህወሀት በግለሰብና በቡድን መብት አልተነጣጣይነት ያለው አቋ ም ግልፅ ቢሆን በተባር ግን የግለ ሰብ መብት እኩል ሲከበር አይታይም፡፡ እንዳው የግለሰብ መብት እደተጨቆ ነው ማለት ይቻላል፡፡በተለይ ህወሀትን ተቃውሞ፣ ሐሳቡ በነፃነት የሚገልፅ፣ ግለ ሰብ፣ ሐሳቡ በነፃነት ስለገለፅ ብቻ፣ ለህወሀት ካልወገና እና የህወሀት ደካማ ጎን በማጋለጥ እና እውነታውን በማሳወቅ ከህዝብ ይነጥለናል ብለው የሚያስቡት ሰው ላይ የሚደርሰው በደል፣ ተነግሮና ተፅፎ የማያልቅ ነው፡፡ የመድፍ፣ የሚሰይልና፣ ሌላ ዘመናዊ መሳሪዎች ባሩድ የማያርደው ህወሀት፣ አንድ መስመር በብዕር የተከተበች፣ እንሱን የምትነቅፍ ሐሳብ ግን፣ በፁናሚ እንደተመታ አከባቢ፣ ሲያርዳቸው፣ ብርድብርድ ሲላቸው እና እንቅልፍ ሲነሳቸው ይሰነብታል፡፡ ይገርማል፣ በሚሰይልና መድፍ ያለተንበረከከው ህወሀት፣ በብዕር ሲንበረከክ!

 

ወደ ግለ ሰብ ላይ የተመሰረተ፣ የመብት ግንባታ አራማጆች፣ጭንብል የኢ/ነት መንነት ድብቁ ምኞት (አምሮት) ልመለስና፣ በግለ ሰብ መብት ምክያንያት ንኡሳን መብት (minority right) መደፍጠጥ የሚፈልጉ ኃይሎች ድብቅ ፍላጎት  በነዚህ እንስሳት አማካኝት ሊወከል ይችላል፡፡

 

በአንድ ወቅት ነው አሉ ድሮ፣ የሕብሰተ መና ከመሰማይ እየወረደ በሚገመጥበት ደህና ግዜ፣ 35 ቀበሮ እና 27 ተኩላዎች ሆነው ሲጓዙ 13  በጎች ያገኛሉ፡፡ ከዛ በጎቹ ደንግጠው እግሬ እውጭን ሩጫ ይጀምራሉ፡፡ አንድ ተንኮለኛ ቀበሮ ድምፁ ከፍ አድርጎ፣ አረ ተረጋጉ እኛ እናንተን ለመብላት ሳይሆን ከናንተ ጋር ወዳጅነት ለመመስረት ነው የመጣነው ይላቿል፡፡ በጎቹም በግርምት ቆም ብለው፣ ‹‹ቀበሮና ተኩላዎች›› ከኛ ከበጎችና ወዳጅነት እንዴት ብሎ፣ ብለው በመገረም ይጠይቃሉ፡፡ ቀበረው ቀብረር ብሎ፣‹‹ይሆናል›› ‹‹ለምን አይሆንም ግጥም አድርጎ ነው የሚሆነው ›› ወደ በጎቹ ጠጋ እያለ ማብራራቱ ቀጠለ፣ አያችሁ እኛ በድሮ ታሪካችን አትዩን፡፡ እውነት ነው ድሮ እኛም፣ ስናሳድዳችሁ፣ እናንተም ከመበላት ለመዳን ስትሮጡ ኑሯቿል፡፡ ነገር ግን አሁን ጊዜው ሌላ ነው፡፡ እኛ ለውጥ ፈላጊ ትውልድ ነን፡፡ ስለዚ ተለውጠናልና ኑ ቁጭ ብለን እንነጋገር ይላቿል፡፡ በጎቹም፣ በጥሞና ማድመጣቸው ቀጠሉ፡፡ ቀበሮው ቀጠለ፣ እንግዲህ እንዳልኩችሁ እኛ ተለውጠናል፣ መለወጣችን መተማመኛ ይሆን ዘንድ ቃል ኪዳን እናስራለን፡፡ በቃል ኪዳኑ መሰረት፣ ከሁን በኃላ ሁሉም ነገር በስምምነት ብቻ ይወሰናል፡፡ ያለናንተ ስምምነት የሚፈፀም ነገር የለም ማለት ነው ብሎ፣ ነገራቸው፡፡ በጎቹም ይህን በሰሙ ግዜ ድስ አላቸው፡፡ በስምምነት የሚወሰን ከሆናማ፣ መቸስ እና ብሉን ብለን አንወስን፣ በቃ እንቀበለው ብለው፣ እርስ በራሳቸው፣ ድምፃቸቀው ዝቅ አድርገው፣ ለአፍታ ታክል ተወያዩ፡፡ በጎቹ ሲንሾካሸኩ፣ ንግግሩ ጋብ አድርጎ የነበረው ቀበሮ ቀጠለ እና ነገር ግን ከናንተ አንድ ወሎታ እንፈልጋለን፡፡ እሱ ምንድ ነው፣ ኖሯቹ ከኛ ጋር እዚሁ፣ ጫካ ላይ ይሆናል፡፡ እንደፈለጋችሁ ሳር መጋጥ ትችላላችሁ፡፡ ነፃ ሁናችሁ ትኖራላችሁ፡፡ ነገር ግን የቤት በግ መስላችሁ፣ ወደ ሌሎች የቤት በጎች ትቀላቀሉና እኛ ወዳለንበት አቅጣጫ፣ እንዲመጡ ታደርጋላችሁ፡፡ እኛም ቀላሉ፣ ሌሎች  በጎች እየበላን ምግባችን እናገኛለን፡፡ በቃ ውለታው ይሄ ነው፣ በናንተ የሚያመጣው ጉዳት የለም አላቸው፡፡ በጎችም፣ ይሄንን የመሰለ ሳር፣ እየጋጡ በነፃነት ከኖርን፣ የተጠየቀው ውለታ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸው አረጋገጡ፡፡ በስምምነቱ መሰረት ለ5 ወር በደህና ኖሩ፡፡ ነገር ግን እነዛ ጫካ ላይ የሚኖሩ በጎች፣ እያሰበላቸው እንደሆነ የገባቸው፣ የቤት በጎች፣ እንደተለመደው፣ የጫካ በጎች ከቤት በጎች ለመቀላል ወደ የቤት በጎች ሲሄዱ፣ የቤት በጎች ካሁን በኋላ አንሸወድም ብለው ሩጫውን አቀለጡት፡፡ በዚህ ምክንያት ቀበሮዎችና  ተኩላዎች ምግብ ሳያገኙ ቀሩ፡፡ በነጋታውም ተመሳሳይ ሆነ፡፡ እንደዋዛ 5 ቀን ያለ ምንም ምግብ ሳያገኙ፣ ቀበሮዎች እና ተኩላዎች በራሀብ ሊያልቁ ሆነ፡፡

 

ከዛ ያ ትልቁ ቀበሮ በጎቹ ጠርቶ ኑ እንመካከር አላቸው፡፡ በጎቹ በፍርሀት ተሸብበው፣ ምነው እኛም እኮ እናንተ ምግብ ሳታገኙ ስትቀሩ በጣም አዝነን እኛም፣የችግራችሁ ተካፋይ ሆነን፣ጦም ነው የሰነበትነው፡፡ አሁን የተቀየረ ነገር አለንዴ አሉ በፍርሀት፡፡ የተራበው ቀበሮ፣ በሰለለ ድምፅ የተቀየረ ነገር የለም አሁም ያው በስምምነት ነው ሁሉም ነገር የሚፈፀመው፣ አሁን የጠራኋችሁም ለዚህ ጉዳይ ነው፡፡ እናንተም ምግብ እንዳልቀመሳችሁ ተገንዝበናል፡፡ ይህ አገብጋቢ ጉዳይ ደሞ ተሎ መፍትሄ ያሰፈልጓል፣ ስዚህ ይሄንን ጉዳይ ምክክር ያስፈልገዋል ያልነው ለዚህ ነው፡፡ ወደ ዕለቱ አጀንዳ ልለፍና ለዛሬ ውሳኔ የሚስፈልገው ጉዳይ፣  ለዛሬ ዕራታችን ምን ይሁን የሚል ሐሳብ በነፃ ምርጫ፣ ለመወሰንና ዕልባት ለመስጠት ነው አላቸው፡፡

 

ይሄንን የሰሙ በጎች በየአቅጣጫው እግሬ አውጭን ብለው ፈረጠጡ፡፡ ያመለጡ ተረፉ፣ ገሚሰቹ ደሞ፣ የቀበሮዎችና ተኩላዎች ራት ሆኑ፡፡ ከዛን ግዜ ጀምሮ ነው፡፡ ደጉ እንስሳ በግ፣ ማንም አራዊት ባየ ቁጥር፣ የሚደነህጠውና የሚፈረጥጠው፡፡

"Democracy must be something more than two wolves and a sheep voting on what to have for dinner." James Bovard

ከኢህአዴግ 11 ጉባኤ ምን እንጠብቅ?

አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል እንዳለው ዘፋኙ፣ አህአዴግ ለይስሙላ አንድ ላይ ቢሆንም(ቢሰበሰብም)ተለያይተዋል፡፡ በተለይ አዴፓ የኢህአዴግ እንጥፋጣፌ ሽታ የለውም፡፡ በተለይ በዚህ ጉባኤ በለስ ቀንቷቸው እና ኦዴፓን አሳምነው፣ ቢያንስ በርእዮተ-ዐለም ደረጃ የተወሰነ ለውጥ ካልተደረገ፣ አዴፓ ርእዮተ-ዐለም አይነሮውም (አብዮታዊ ዲሞክራሲና ልማታዊ መንግሰት አለቀበልም ብሏል)፣ ህገ-መንግስቱ አልቀበልም ብለዋል፣ በዚህ ህገ-መንግስት የተዋቀሩ የመግስት አካላትና ክልሎች እውቅና አይሰጥም ማለት ነው ወዘተ፡፡ ስለዚህ ክልሉ ወደ እልቂትና ጦርነት ሊከተው ይችላል፡፡

 

ኦዴፓ ካልተባበረው፣ የዘመኑ የከሰረ የፖለቲካ ፓርቲ አዴፓ ይሆናል፡፡ አቶ ደመቀ በጉባኤያቸው ሆይሆይታና ስሜት ተውጠው የወሰኑት ውሳኔ ምቾት የሰጣቸው አይመስልም፡፡ ፍዝዝ ድንግዝ ብለው ይታያሉ፡፡  የማይናወጥ አቋም ይዞ የገባው ህወሀትም የሚተባበረው ካላገኘ፣ አደጋ ውስጥ ነው፡፡ ወይም አቋሙ ይቀይርና በጉባኤው  ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ይከልሳል፡፡ ይሄ ደሞ ለህወሀት የተፋሀውን ተመልሰህ እንደማልመጥ ነው፡፡ አልያም፣ የርእየተ-ዐለም ልዩነት ይዘው "እንደተጣመርን ኣለን" ለማለት በየለንበት፣ ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው፣ እና በሂዴት ኮሚቴ ተቋቁመው፣ እነዲጠና የመፍትሔ ሐሳብ እንዲቀርብ  እናደርጋለን በሚል የቃላት ጋጋታ፣ የፈረሰው ኢህአዴግ፣ ህለው አስመስለው ያቀርቡታል፡፡ ለማጠቃለል

(1)  ኢህአዴግ እንደ ድርጅት በውል ሊፈርስ ይችላል፡፡ይኸ ወደ ስልጣን ከመጡ 6 ወራቸው ያልመሉ፣ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የሽንፈት ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ ስለሚችል፣ የመሆኑ ዕድል ዝቅተኛ ነው፡፡

(2)  ህወሀት ረግጦ ሊወጣ ይችላል፡፡ አልያም ህወሀት ከኢህአዴግ እንዲወጣ አዴፓ ውስጥ ለውስጥ ሊያሴር ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር ያክል ትዕግስት ያለው በሰከነ መንፈስ የሚንቀሳቀሰው ፣ በዶ/ር ድብረፅዮን የሚመራው ህወሀት ረግጦ ለመውጣት ይመኩራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ነገር ግን በሽማግሎዎቹ ጫና ስር የወደቀው የነ አለም ቡድን፣ የሚወስነው ውሳኔ አይታወቅም፡፡ ለዚህም ነው ህወሀት ረግጦ ሊወጣ ይችላል የሚል እንደ አንድ አማራጭ የተወሰደው፡፡ አዴፓ ውስጥ ለውስጥ አሲሮ ህወሀት ከኢህአዴግ እንዲባረር እንደሚፈልግና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እንደጀመረ በርካታ ማስረጃዎች  አሉ፡፡ ነገር ግን በድርጅት ደረጃ ጠንክሮ ሳይሆን፣ ምንነቱን አጥቶ የመጣው ግራ የተጋባው የአቶ ደመቀ ብዱን ይህንን እውን ለማድረግ በቀላሉ ላይሳካላቸው ይችላል፡፡ አንድ የኢህአዴግ እህት ድርጅት፣ ሊኖረው የሚገባ አነስተኛ ቆመና እና ቅርፅ አጥቷልና፡፡ ባንድ በኩል አሁን የድርጅቱ ሞተርና ባለቤት ነኝ የሚለው፣ ኦዴፓ የኢህአዴግ ‹‹አንድነቱን›› አጠናክሮ መቀጠል እንጂ መበታተን እንደ ሽንፈት ሊወስደው ስለሚችል፡፡ ሰለ ሆነም የአዴፓ ሼር  ላይተባበር ይችላል፡፡ ለአጋር ድርጅቶች የሚሰጠው መልእክትም በጣም መጥፎ ስለሆነ፣ የሀገሪትዋ አንድት የሚናጋ ውሳኔ ለመወሰን አይደፍሩም ተብሎ አይገመትም፡፡ ነገር ግን የአዴፓ ሤራ ለማምከን ህወሀት ከፍተኛ፣ ስራ ያሰፈልጓል፡፡ እዚህ ላይ ከተሸዱ፣ ደርግ ተመልሶ ወደ ስልጣን እንደመጣ ይታሰባል፡፡ ስለዚህ ህወሀት ጥንቃቄ እንዳይለየው እንመክራል፡፡

(3)  አዴፓ፡- ማንነቱን ያጣው ድርጅት አሁን ለህልውናው ሲል የኃይል ሚዛኑ ወደዳለበት ከመከተል ያለፈ፣ ራሱን ችሎ ወጥ አቋም ይወስዳል ተብሎ አይገመትም፡፡ ስለዚህ እንደ የንብ ንግስት ተከታዮች፣ በነገሱ ከኃላ ከመከተል ያለፈ ስራ አይሰራም፡፡ ከሚያሴሩ፣ ማጅራች መችዎች መቀላቀል ወዘተ አልፎ ሌላ ትርም ያለው ስራ አይሰራም፣ ከኦዴፓ ይሁንታ ካላገኘ በስተቀር፡፡በድርጊቶች አኩርፎ አዴፓ፣ ጉባኤው ረግጦ ሊወጣ ይችላል የሚለው፣ ሐሳብ ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ሲጀምር ለዚህ የሚሆን ብቃትና ወኔ የለውም፡፡ ርእተ-ዓለም፣ ሕብረ-ብሔራዊ የፌዴራል ስርዓት፣ ፖሊሲዎች፣ ክልሎች ወዘተ እውቅና ያልሰጠ ድርጅት  በየተኛውም ማዕቀፍ ሊደራደር ስለማይችል፣ ወደዚህ ውሳኔ ይገባል ተብሎ፣ አይታሰብም፡፡ ከባህር እንደ ወጣ ዓሳ ደርቆ እንደሚቀር ያውቃልና! ሲቀጥል፣ አሁም የዚህ ጉባኤ ባለቤት ሆኖ የሚታየው ኦዴፓ ድግሱ የሚያበለሽለት አካል ማየት ስለማይፈቅድ በግድም ሆነ በውድ፣ አዴፓ አርፎ እንዲቀመጥ ያደርገዋል፡፡ ሌላ አማራጭ እንደሌለውና በሀሉም እንደተተፋ ያውቃልና!

(4)  የተሰነጣጠቀው ኢህአዴግ ግንባር፣ በፕላስተር ለጣጥፎ፣ ለፖለቲካ ፍጆታ አንድ መስሎ ሊቀትል ይችላል፡፡ ይሄ የመሆኑ ዕድል ከፍተኛ ነው፡፡ የውጤት እና የውድቀት ዕድሎች በኦዴፓ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው፡፡ ኦዴፓ በጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በግልፅ ስላለቀረበ (እኔ ስላላነበብኩ፣ ስላሰማሁ)፣ ምን ዓይነት አቋም ያራምዳል የሚል ለመገመት ያዳግታል፡፡ የፈለገው አቋም ቢያራምድ ግን፣ ተከታይ አያጣም፡፡ አዴፓም ደኢህዴንም የመከተሉ ሚና በሚገባ ይዋጡል፡፡ ኦዴፓ፣  የአዴፓ አቋም ካራመደ  (ከተባበረ) ግን ለህወህትም ለትግራይ ህዝብ የማንቅያ ደወል ነው የሚሆነው፡፡ ለማይቀረው ጦርነት ለመዘጋጀት፡፡  የሀገራችን ህልውናም ያበቃለታል፡፡ ልትሰነጣጠቅና ልትበተን ትችላለችና!

 

Back to Front Page