Back to Front Page


Share This Article!
Share
Reportage on the Terrorist Act of June 16(EC) In Addis Ababa, Ethiopia

ሸጊቱ ኣዋሽ ማን ነች ?

ታምራት የማነ -ከመቐለ

Bereket66@gmail.com

07-07-18


ሰሞኑን በማህበራዊ ሚድያ በኣቶ ካሌብ ዮና የተባሉ ግለሰብ ሰለ ባለፈው ሳምንት 16 ሰኔ በኣዲስ ኣበባ በተካሄደው ለጠቅላይ ሚኒስትሩን ምስጋና ለማቅረብ ኣራት ሚሊዮን ገደማ ከተለያዩ ክልሎች በሰልፉ በሚሳተፉት ሰልፈኞች ላይ በኣሸባሪዎች በተወረወረ ቦምብ በበርካቶች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡ በዕለቱ በሰልፈኞቹ ላይ በደረሰው ጉዳት ኣስመልክቶ ፅሁፎች በተለያዩ ድረ ገፆችና ማህበራዊ ሚድያዎች የወጣ የጅምላ ፈረጃ ኣለ ፡፡በዚህ ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ መከረኛው የትግራይ ሀዝብና ሕወሓት ላይ ትኩረት ያደረጉ የጥላቻና ውንጀላ ወሬዎቸ ሲዛመቱ መሰበንታቸው ይታወቃል ፡፡

በወቅቱ ኣሸባሪዎች በተወረወረ ቦምብ ኣደጋ መፈፀሙ የሚታወቅ ነው በዚህም በሰውና በህይወት ላይ ቁጥሩ የማይናቅ ኣደጋ ደርሰዋል ፡፡ ለዚህ ለተጎዱት ቤተሰቦች መፅናናትን እየተመኘሁ ወደ ጉዳዬ ልግባ ፤ለዚህ ጉዳይ ኣዲስ ኣበባ ተጉዤ ያገኘሁት መረጃ ነው ፡፡ መስቀል ኣደባባይ በሚገኘው ስኴር ጋርደን ካፌ ንጋት ሩብ ጉዳይ ለኣንድ ሰዓት የታየችው ወጣት ማን ነች ? ፡፡እንደ የፅሑፌ ምንጭ ገለፃ በወቅቱ ኣዲስ ኣበባ ላይ የሚገኙ የፀጥታ ኣካላት እንደ የኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ ፣የኣዲስ ኣበባ የፖሊስና የወንጀል ምርመራ የፌደራል ፖሊስ እና የተለያዩ ኣካላት ጋር በመሆን የመስቀል ኣደባባይን መውጫ መግቢያ ቦታዎች እንዲፈተሸና እንዲያፀዱ ተደረገ ፡፡ እንግዲህ ንጋት ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ኣቢይ ድጋፉን የሚገልፀው ህዝብ በሁሉም ኣቅጣጫ ወደ መስቀል ኣደባባይ መትመም ጀመረ ፡፡ በሰልፉ የነበረው ህዝብ ብዛት ከተለያዩ ምንጮች እንደተረዳሁት ኣንዶንዶች ሶስት ሚሊዮን ሲሉ ሌሎች ደግሞ ኣራት ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ እንደነበር ነው የሚገልፁት ፡፡በዚህ ወቅት ዶ/ር ኣቢይ ንግግራቸውን ከቋጩ በኋላ መድረክ መሪው ግሩም ጫላ " ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከተለያዩ ኣካላት የተዘጋጀ ሽልማት ኣለን" ብሎ ንግግሩን ከመናገሩ ወዲያውኑ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰማ !ሁካታና ግርግር ተጀመረ ሰው በሰው ላይ ተረጋጋጠ ብዙ ወጣቶች ለሰልፍ ብለው ከወጡት ለኣካል ጉዳትና በኋላ በዜና እንደተነገረው ከፍንዳታው ውጭ በርካቶች ለህልፈት የተዳረጉ እንደነበሩ ሲገለፅ ነበር ፡፡

Videos From Around The World

በዚህ ወቅት ከህዝቡ ብዛት ኣኴያ ፀጥታውን ለማስከበር ተጎጂዎችን ለማንሳትና ሌሎችን ለማዳን የኣዲስ ኣበባና በኦሮሚያ ፖሊስ የዓቅማቸውን ያህል ሰርተዋል ፡፡በዚህ ፍንዳታ እንደ ኣሸባሪዎቹ ሃሳብ ከሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩን በህዘብ ዘንድ ያላቸውን ተደማጭነትና ተወዳጅነት ስጋት የሆናቸው የውጭ ሃይሎች ብጥብጣችን እንጂ መተሳሰባችንና መደጋገፋቸን የማይፈልጉት ያፈነዱት ቦምብ ቢፈነዳና ጉዳት ቢደርስባቸው ሃገሪቱ ጉዞዋ ወዴት ይሆን እንደነበር ስታስበው ያሰቅቃል ፡፡

ወደ ድርጊቱ ሰንመጣ ኣፈንጂዋ ሴት እንደነበረችና ቦርሳ ይዛ እንደነበር ንጋት ላይ 12:45 ብትታይም በህዝቡ መጨናነቅ ከፀጥታ እይታ ተሰውራለች ፡፡በሰልፉ የነበረው የህዝብ ብዛት ኣኴያ ሲታይ ጠጠር ብትወረውር መሬት ላይ ኣትወድቅም ሲባል ነበር ፡፡ በሰልፉ ሰንጥቀህ ለጠቅላይ ሚኒሰትሩ ኣደጋ ለማድረስ ሁኔታው ኣዳጋች ቢሆንም ከሰልፉ መጨናቅ ብዛት ጥቃት ኣድራሿ ልጅቱ ቦምቡን ያፈነዳችወ በ40 ሜትር ርቀት ላይ ነው ፡፡ሸጊቱ ቦንቡን የወረወረችው በዚህ ጉዳይ በቂ ስልጠና ኣለመውሰዷ ያሳብቅባታል ፡፡ቦንቡን ማንም ጀማሪ ኣፈንጂ የሚወረውረው ኣይደለም ፡ወጣቷ ፈንጂውን ከወረወረች

በኋላ በፍንጣሪው ተጎድታ ስትወድቅ በዘያ ከድንጋጤ የዳነው ወጣት ሁሉ በወጣቷ ላይ በድንጋይ በእጁ ባገኘው ሁሉ የማርያም ጠላት ኣደረጋት በዚህ መሃል በኦሮሚኛ በማውራት ከኦሮሚያ የወለጋ ልጅ እንደሆነችና እንዲተዋት ተማጸነቻቸው ፡፡

እንደ ምንጮቼ ኣገላለፅ ሌላ በወንጀሉ ተሳፊና ኣቀናባሪ ስኴድ የተላለፈ ትእዛዝ ሚስጠር ሳታወጣ ግደሏትላ (ጨርሷት )የሚል ቀጭን ትእዛዝ መጣ ፡፡ በዚያው ፍጥነት ከኣዲስ ኣበባ ፖሊስ ሃይል ልጅቷን በተቻለ መጠን ከነህይወቷ ተይዛ እንድትመጣ ርብርብ ተደርጎ ኮሚሽነር ግርማ ካሳ እጅ እንድትገባ ተደረገ ፡፡በዚህ ወቅት በሚገርም ሁኔታ እሰከ አሁንም ባለቤትነቱ ያልታወቀ ኣሜሪካ ሰራሽ የድንገተኛ እርዳታ መሳርያዎች ያሟላ ኣምቡላንስ ደርሶ ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ቃልዋል እየተቀበሏት ህክምና እገዛ እየተደረገላት ወደ ጤና ተቋም ተወሰደች ፡፡ ሸጊቱ ኣዋሽ ዓላማዋ ዶ/ር አቢይን ለመግደል ነበር ስትንደረደር የነበረው ይሁንና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዙርያ ኣጥር ሆኖ ያደረው የቄሮ ወጣት ስለነበረ ሊድኑ ችለዋል ፡፡

በሌላ በኩል የፖሊስ መኪና ፈንጂ ይዛለች ኣሸባሪዋን ይዛ የመጣችው ተብላ መኪናዋ ላይ የነበረው የትግራይ ተወላጅ የራያ ልጅ መደብደበ ተጀመረ በዚያው ሹፌሩን እንዳይሞት እንዳይሽር ተደርጎ ድብደባ ተፈፀመበት ፡፡ የመኪናው ሾፌር የራያ ዓዘቦ ተወላጅና ኣንጋፋ ታጋይ ሲሆን ሲደበድቡት " እረ ተውኝ እኔ የፖሊስ ህጋዊ ሰራተኛ ነኝ ፈንጂ ኣልጫንኩም " ቢል ማን ይስማው በከፍተኛ ሁኔታ ተቀጥቅጦ በሞትና በሂወት ኣፋፍ ነው ያለው ፡፡በዚህ ይህ ኣልበቃ ብሎኣቸው የልጁን በድብደባና በቅጥቀጣ የተዳከመ በሞት ኣፋፋ የደረሰውን አስከሬኑን በወሳንሳ እንደ ቅርጫ ስጋ ኣንጠልጠለው ምንም ኣስቸኳይ እርዳታ ሳይደረግለት ደሙ እየተንጠባጠበ ይዘው ወደ ቤተ መንግስት !! ለምን ቢባል "የተፈፀመው ሽብር ተባባሪ ነው ስለዚህ በፖሊስ ጣቢያ ከታሰረ ፖሊሶች ይፈቱታልወደ ዶ/ር ኣቢይ መውሰድ ኣለብን " በሚል ሃሳብ ዶ/ር አቢይ ጋር ቤተ መንግስት ነው መታሰር ኣለበት ብለው ይዘውት ሲሄዱ በስንት እግዚኦታና የፀታታ ሃይል ድጋፍ ወደ ሆስፒታል ተወሰደ ፡፡ ሹፌሩ በኣሁኑ ጊዜ የሃገር ውስጥ ህክምና ለማከም ኣዳጋች በመሆኑ ወደ ውጭ ህክምና ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው ፡፡በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጎጂው ሹፌርና ኣፈንጂዋን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደጎበኙና ኣንዳልጎበኙ የተለያየ ዜናዎች ይሰማል ቢሆንም ለጊዜው በዚህ ትተነው ኣልፈንዋል ፡፡

በዚህ ኣጋጣሚ በወቅቱ ይህ ድርጊት ሲፈፀም በሰልፉ ውስጥ ተገኝተው በጥርጣሬ የተያዙት ሶሰት ወጣት የወለጋ ልጆችም ይህንን ሃሳብ ደግመውታል ፡፤ሲያዙ ቤተ መንግስት ነው መታሰር ያለብን በማለት ከፀጥታ ሃይል ጋር ኣተካራ ገጥመው እንደነበር በማለት ምንጮቼ ኣውግተውኛል ፡፡ ፈንጂ የያዘችው እና ሽብርተኞችን ይዛ የመጣች የተባለችው ቶዮታ መኪና የፖሊስ የህዝብ ግኑኝነት ጋዜጠኞችንና እና የጋዜጠኛ ትጥቆችን ነው የያዘቸው ፡፡በመጀመሪያ ነገር እዚያው ሰልፍ መገኘት ኣልበረባትም ይህ ኣንድ ትልቁ ስህተት ሆኖ ሳለ ሹፌሩን እንደዚያ ኢሰብኣዊ በሆነ ድብደባ መፈፀም ለኣሁነ በሞት ኣፋፍ እንዲገኝ ምክንያት የሆነው ማነው ?በኣጠቃላይ ምንም በማያውቁት ሁኔታ የተጎዱት ንፁሃን ሁኔታ ተጠያቂው ማን ይሆን ? የዚህ ጥቃት ፈፃሚው ማን ይሁን ማን እንደ ሃሳቡ ቢሆንለትማ ዶ/ር ኣቢይ ላይ ጥቃት ማድረስና ሃገሪቱን ወደ ውድመት መምራትና ሃገራችን በተለይ የፌደራል መቀመጫዋን ኣዲስ ኣበባ ባግዳድና ሶርያ ማድረግ ነበር ግና ኣልተሳካም ፡፡

በነገራችን ላይ ሸጊቱ ኣዋሽ ኣለባበሷ ረጅም ቀሚስ ሆኖ ሁለት ቲ ሸርት ደራርባ ለብሳለች ፡፡የውስጠኛው ቲሸርት "መሪን ገድለህ ጀግና መሪ ትፈጥራለህ " ይላል በዚህ ላይ ደርባ የለበሰቸው ደግሞ "ዶ/ር ኣቢይ የመደመር ውጤት " በሚል እንደሆነ ምንጮቼ ገልፀውልኛል ፡፡በኣንዳንድ በማሕበራዊ ሚድያ

የሚታየው ትክክለኛው የሸጊቱ ምስል ላይ ቲሸርቱን ኣውልቃ በእጇ ይዛው ይታያል መኪናዋም ከቃጠሎ በኋላ ስትፈተሸ ይዛ የተገኘቸው ለሁሉም ኣሳዛኝ ነበር ፡፡ የሳምሶናይቱ ሚስጥር ፈንጂ ሳይሆን የካሜራ እቃዎች ነበረ ፡፡ መኪናዋ ተቃጥላ የሚታየው ሳምሶናይቶች የካሜራ እቃዎቻና ትራይፖዶች ናቸው ፡፡ግና ዋናው በተቃዋሚ ነኝ ባዩና በትግራይ ህዝብ መዝመት ያላቆመው ሃይል ኣይኑን የጣለው ትግራይና ሕወሓት ላይ ነበር ፡፡በዚህ ኣጋጣሚ በተለያዩ ድረ ገፆችና ማሕበራዊ ሚድያዎች ፕሮግራም ኣዘጋጆች በፈረደበት መከረኛው የትግራይ ህዝብና ወያነ በረባው ባልረባው ሲበጠልጠል ሲንጓጠጥ መስማት ያማል ፡፡ መሪዎች ቢቀያየሩም ዝም ብሎ ስራውን በሰራና በለፋ ፌደራል ሰርዓቱን በጠበቀ የተለያየ ስም እየወጣለት ይኸው የሃገሪቱን ህልውና እዚህ ደርሷል ፡፡

በዚህ ወቅት በኣዲስ ኣበባ ፖሊስ ምርመራ ጀርባ በቦታው ልጅቱን ውጤታማቷንና ድከመቷን ለበለጠ ሽብር በመዘጋጀት ሂደቱን ሲከታሉ የነበሩት ሶስት ወጣቶች እጅ ከፍንጅ ተያዙ ፡፡ኣራቱም ወጣቶች እያንዳንዳቸው ሶስት ሶስት ከተለያዩ ቦታዎች /ክልሎች / እንደመጡ የሚገልፅ በፎርጅድ የተሰራ መታወቂያ ካርድ ይዘው እንደነበር ነው መረጃ ምንጮቼ የገለፁልኝ ፡፡ይህ ሁሉ ሃቅ እያለ ፈንጁን ያፈነዳው ወያኔ ነው የትግራይ ተወላጆች ናቸው በሚል በመላው ሃገሪቱ ሲናፈስ የቆየው ኣሉባልታ ምንጩ ሌላ ነው ፡፡ይህን ካርድ መዘህ ሌላ ዘመቻ ለማካሄድ ነበር ፡፡አሁንም ወጣቶቹ ከኦሮሚያ ወለጋ እንዲሁም ሸጊቱ ከወለጋ መሆናቸው ታውቆ እያለ " በታቀደ በእውቀት የታገዘ " እየተባለ ሲወራ የሰነበተው በዚህም የተነሳ እሰኪጣራ በጥርጣሬ ተብሎ ታፍሰው የታሰሩ የፀጥታ ኣካላት ኣሉ ፡፡ ዶ/ር አቢይ የይቅርታና ምህረት ዘመን እያካሄድኩ ነው ሲሉ እነኝህ የፀጥታ ኣካላት የታሰሩበት ሁኔታ ለጠያቂና ቤተሰብ ግራ የሚያጋባ ትእዛዝ ነው ፡፡ ታሰሩ ከተባሉበት ቀናት ጀምሮ እስረኛ ጠያቂ ታሳሪውን ሲጠይቅ ታሳሪውም ጠያቂውም በኣንድ ዓይንህ ብቻ አጮልቀሀ ነው ማውራት የሚቻለው ? በቅርቡ ደግሞ ከቤተሰብና ህግ ባለሙያዎቻቸው ጋር እንዳይገናኙ በሩ ዝግ ነው -መገናኘት ክልክል ነው-ተብሎ ከላይ በተወሰነ (በመጣ ) መመሪያ ተጠርጣሪዎች እየተሰቃዩ ይገኛሉ ፡፡

ይህ ተግባር ደግሞ ዶ/ር ኣቢይ ሃገሪቱን በሚመሩበት የይቅርታና ምህረት ዘመን ይህ ነው እንዴ መጨረሻው ጠቅላይ ሚኒስትር የይቅርታና የምህረት ስራ ሲሰራ በሌለ በኩል በቁጥጥር የዋሉ ዜጎች ለቤተሰብ ጥየቃ ኣስቀያሚና ኣሳፋሪ ኣያያዝ ታዲያ ምኑ ነው ምህረቱና ይቅርታው የተሰራው ፡፡ ወዴት ወዴት ነው ጉዞኣችን ወንጀለኛ ወይ ጥፋት ያጠፋ ኣይያዝ ኣይደለም የምለው ወንጀል የሰራ ተገቢውን ፍርድ ያግኝ ግና የፍርድ ሂደቱ ግልፅና ፈጣን ይሁን ፡፡

ወንጀለኞቹ ተይዘው እያለ የምርመራ ስራው በኣጭር ጊዜ ተገባዶ በቁጥጥር ስር ያሉ እስረኞቹም የሞራልና የኣካል ጉዳት ደርሶባቸው መፍታት ማለት የሃገርህን ዜጋ ወደ ስራ ሳይሆን የምትመልሰው ወደ ጥፋትና ሌላ ውድመት ነው ፡፡ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ነገር ግና በሃገራችን እንዲዚህ ዓይነቶች የሽብር ስራዎች ሲፈፀሙ በጠንካራ ብስለቱና ፈጣን እንቅስቃሴው የሚታወቀው የኢትዮጵያ ደህንነት ተቋም ምን ሆኖ ነው ኤፍ ቢ ኣይ የመጣው ? ምላሹን ከመንግሰት ! በተጨማሪም ሸጊቱ ከሽብር ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት ታስራ በይቅርታ ዘመኑ እንደተፈታች ነው ከምንጮቼ የተሰጠኝ መረጃ ፡፡ስለዚህ በሽብር ተግባር ስትያዝና ስትታሰር የኣሁኑ የመጀመሪያዋ እንዳልሆነ ነው ማወቅ የቻልነው ፡፡

አመሰግናለሁ !!

 

Back to Front Page