Back to Front Page


Share This Article!
Share
ወልቃይት እንደ ባድመ የልብ ለልብ መራራቅ፤ድንበር/ወሰን እንደ ምክንያት፤ ጦርነት፤ የድንበር/ወሰን የኮሚሽን

ወልቃይት እንደ ባድመ

የልብ ለልብ መራራቅ፤ድንበር/ወሰን እንደ ምክንያት፤ ጦርነት፤ የድንበር/ወሰን የኮሚሽን

 

አ/ገ

ታህሳስ 21/ 2018 ዓ.ም

 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ አንድ አዋጅ አጽድቋል፡፡ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ ይጽደቅ እንጂ ህገ መንግሰቱን የሚቃረን አዋጅ ነው በሚል ከትግራይ ክልል ተወካዪች ጠንካራ ትችት ሲሰነዘርበት ተደምጧል፡፡ በጽሁፌ ላይ ትኩረት የማድረገው አዋጁ ኢ-ህገ መንግስታዊነት ላይ ሳይሆን ከቅንነቱ፣ ከጦርነት ቀስቃሽነቱ እና ከችግሩን አባባሽነቱ ላይ ይሆናል፡፡ መቼም ይህን አዋጅ እንዲዘጋጅ ምክንያት ከሆኑት ጉዳዮች ዋነኛው የ ወልቃይት የአማራ ነው የሚለው ቅስቀሳ መሆኑ አያከራክርም፡፡ አሁን ላይ በርከት ያሉ የወሰን፣ የማንነነትና የአስተዳደር ጥያቄዎች የተፈጠሩ መሆኑ ባይካድም ይህንን አዋጅ በዋነኝነት የአማራ ክልል መሪዎችና ጽንፈኛ አክቲቪስቶች የሚገፉት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን አዋጅ ወልቃይትን ወደ አማራ ክልል የማስመለስ አዋጅ ብለን ብንጠራው ብዙም የተሳሳትን አንሆንም፡፡ በዚህ አካባቢ ግጭቶች መነሳት ከጀመሩ ጥቂት አመታት ያስቆጠሩ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ጥያቄው ይበልጥ እየተጠናከረና ግጭቶችም እየተካረሩ የመጡት ግን ኢ.ህ.አ.ዲ.ግ እየተፈረካከሰ በመጣበት ወቅት ነው፡፡ ስለሆነም የወልቃይትን ችግር የ ብ.አ.ዴ.ን ና የ ህ.ወ.ሃ.ት የልብ ልዩነት ወደ ከፋ ደረጃ እየወሰደው እንዳለ በግልጥ የሚታይ ነው፡፡ ልክ ኤርትራና ኢትዪጵያ ባበድመ ጉዳይ እንዳልተዋጉ ይልቁንም የኢኮኖሚ መስመርን ተከትሎ የተፈጠረው የግንኙነት መሻከር ባድመን እንደምክንያት አድርጎ ጦርነት ውስጥ እንደተጋባ እንዲሁ በወልቃይት ጉዳይ የህ.ወ.ሃ.ት እና የ ብ.አ.ዴ.ን አመራሮች የልብ ለልብ መሻከር የወለደው የ ሰበብ ጦርነት ይመስለኛል፡፡ ይህ ማለት ልክ እንደ ባድመ ምንም አይነት የድንበር ጉዳይ አልነበረም ሳይሆን ወደ አዋጅና ወደ ንትርክ ብሎም ወደ ጦርነት ሊወስድ የሚችል በቂ ምክንያት ባበድመ ጉዳይ እንዳልነበረ ሁሉ አሁንም በወልቃይት ጉዳይ በሁለቱ ክልል አመራሮችና በፌደራል መንግስት ብሎም በወልቃይትና በሌሎችም የወሰን አስተዳደር ጥያቄ ባላቸው ህዝቦች ዘንድ በሚፈጠር የጋራ መግባባት እንጂ በአዋጅና በሃይል ለመፍታት የሚደረገው ጥረት ውጤቱ አስከፊ ነው፡፡

Videos From Around The World

ወልቃይትን እንደ ሰበብ

ኢትዪጵያና ኤርትራ ከ1983-89 ድረስ ባድመን እንደ ምክንያት ሳያነሱ በሰላም ሲኖሮ ቆይተው በ1989 አጋማሽ ላይ የኢትዪጵያ መንግስት የኤርትራን መንግስት ጥገኛ አስተሳሰብ የሚያስቆም አዲስ የኢኮኖሚ ስርዐት መከተል በጀመረ ማግስቱ ባድመን እንደ ሰበብ በመጠቀም ጦርነት ተጀመረ፡፡ ልክ እንደዛው አዲሱ የብአዴን አመራር በህግ መንግስቱና በፌደራል ስርዓቱ ምንም አይነት እምነት ያለነበረው ስለነበረ ግዜ ጠብቆ በስርዓቱ ላይ የነበረውን ተቃውሞ መግለጫ መንገድ አደርጎ ወልቃይት ይመለስልኝ የሚል ጥያቄ ይዞ ብቅ አለ፡፡ ይህም ጥያቄ የፌደራል ስርዓቱ በተዳከመበት ወቅት እንጂ ባለፉት 20 አመታት በዚህ ደረጃ ሲቀርብ አልታየም፡፡ ስለሆነም ወልቃይት ልክ እንደ ባድመ የሰበብ ቦታ እንጂ ዋና የግጭት ምክንያት አይደለም፡፡

ውይይትና ምክክር ሳይደረግ በአዋጅ ለመፍታት መሞከር

በኢትዪጵያና ኤርትራ መሃል በባድመ ምክንያት የተፈጠረውን ውዝግብ በሰላም ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች ሁሉ አልተሳኩም፡፡ ምክንያቱም ችግሩ ያለው ባድመ ላይ ሳይሆን የኢኮኖሚ ጥገኝነት ላይ ስለነበር ነው፡፡ እንዲሁ በወልቃይት ጉዳይ ምንም አይነት ክልላዊና ህዝባዊ ምክክር ማድረግ ያልተፈለገበት ምክንያት ችግሩ ወልቃይት ጉዳይ ላይ ሳይሆን ወያኔ እና ፌደራል ስርዓቱ ካልጠፋ የሚል እሳቤ ስላለ ነው፡፡ እንበልና ወልቃይት ለአማራ ቢሰጥ እንኳን ቅራኔው አያቆምም በሌሎች መውጫ ቀዳዳዎችም ይቀጥላል፡፡ ወያኔን፣ ህግ መንግስቱን እና ፌደራል ስርዓቱን ከመጥላት የሚመነጭ ቅራኔ በወልቃይት ብቻ አያቆምም፡፡ ሚስትህን ፈልጎ የመጣ ሰው ሴት ልጅህን ብትሰጠውም አይመለስም አንደሚባለው ማለት ነው፡፡

የኢትዪ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን ያሰለፈው ውሳኔ በአካባቢው ያሉ ህዝቦች ከሚያቀርቡት መፍትሄ ያልተሻለ በመሆኑ ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ እንደማይችል ሁሉ፤ የወሰን ኮሚሽን አሁን በተያዘው ህዝብን ባገለለ መንገድ ተሰርቶ ሲመጣ እንዲሁ ለሌላ ግጭት መንስኤ ለመሆን ካልሆነ መፍትሄ መሆን አይችልም፡፡ ልክ ኤርትራና ኢትዪጵያ ሰላም አወረዱ ከተባለ በኋላ የኤርትራው መሪ ህዝባቸው ድንበራችንን አስምርልን ብለው ሲጠይቁት ድንበሩ አያስቸኩለንም፤ የጦርነቱም ምክንያት ድንበሩ አልነበረም ቀስ ብለን እንደርስበታለን ብሎ አንዳለው ሁሉ እርቅና ሰላም ቅንነት ባለበት ሆኔታ ሲታይ አንኳን በአንድ ሃገር ባሉ ክልሎች ይቅርና በሁለት ሃገሮች ባሉ ህዝቦች መካከል ያለ የድንበር/ወሰን ጉዳይ የግጭትና የጦርነት መንስኤ መሆን አንደማይችል፤ አዋጅም እንደማያስፈልገው መረዳት ይቻላል፡፡

እኔ ወልቃይትን በተመለከተ የማውቀው አብዛኛው ነዋሪ ( 90 በመቶ) ትግርኛ ተናጋሪ መሆኑንና በቀድሞ የደርግ የክፍለ ሃገርና የአጼ ሃይለስላሴ የጠቅላይ ግዛት አስተዳደር አካባባቢው ጎንደር/በጌምድር ለሚባል የአማርኛ ተናጋሪዎች ወሰን ስር እንደነበር ነው፡፡ አሁን እየቀረበ ያለው ከታሪካዊ ዳራ አንጻር ይታይልን የሚል ነው፡፡ ይህ ደግሞ የአማራ ክልል መንግስትና አክቲቪስቶች በይፋ እንደሚናገሩት በዚህ ህገ መንግስት አያምኑም፤ ይህን ህገ መንገስት አይቀበሉትም፡፡ ስለሆነም ጥያቄው ቀድሞ ጠቅላይ ግዛት/ ክፍለ ሃገር ይዘውት የነበረው ቦታ ተመላሽ ይደረግ የሚል ያው ዞሮ ዞሮ ህዝባዊ ሳይሆን መልክዐ-ምደራዊ የአንድነት ትርክት ሌላው መገለጫ ነው፡፡ ይህ ከተባለ ትግራይም ወደ አፋር የሄደባትን ዳሎል ዲፕሬሽን፣ ወደ አማራ የተካለለውን ከፊል አገው ልተጠይቅ ነው፡፡ አማራም የከሚሴና የባቲን ኦሮሞዎች ላስተዳደር ብሎ ሊቀጥል ነው፡፡

ማጠቃለያ!

የወሰን አስተዳደርና የማንነት ጉዳይ ኮሚሽን ህገ መንግሰቱን በራሱ ተቋማት የማፍረስ የመጀመርያው ጉልህና ግልጽ እርምጃ ነው፡፡ ጠ/ሚ አብይ አህመድም ህ.ወ.ሃ.ት ስልጣኔን ይነጥቀኝ ይሆናል የሚል ስጋትና ስር የሰደደ የትግራይ ፎብያ ውቅረ ስብዕናቸው ተደምረው ትግራይንና ህ.ወ.ሃ.ትን የሚያዳክም ይሆን አንጂ ከሰይጣንም ጋር አብሮ የመኖር ቃል ኪዳን ከማድረግ አንደማይመለሱ በተደጋጋሚ ንግግርና ስረቻው አረጋግጠውልናል፡፡ የወሰን ኮሚሽኑ ተጠሪ ለሆነለት ጠ/ሚ ክቡርነተዎ 90 በመቶ ትግርኛ ተናጋሪ የሆነውን ወልቃይትን ወደ አማራ ክልል አንዲጠቃለል ይወስኑልን ብሎ ሲሰጣቸው እርሳቸውም ጎሽ ጥሬ ስራ ተሰርቶአል፤ ለውጡን እናጠናክር ጸረ-ለውጥ ሃይሎችን ማዳከም እንቀጥል ብለው ያጸድቁላቸዋል፡፡ ያን ግዜ የአማራ መስተዳደር ትግርኛ ተናጋሪ ወልቃይቴዎችን ያስተዳደር ይሆን ወይስ መሬቱን አንጂ አናንተን አንፈልግም በሚለው የግዛት አንድነት ውቅረ ስብዕና ህዝቡን ወደ ትግራይ ያባርር ይሆን? እንግዲህ የሚሆነውን ማየት ነው!

 

Back to Front Page