Back to Front Page

27 ዓመት እንዴት ነው ጨለማ የሆነው? የጨለመውስ ለማን ነው?

27 ዓመት እንዴት ነው ጨለማ የሆነው? የጨለመውስ ለማን ነው?

ፋኑኤል ዘ አዳማ May 16, 2019

 

ታሪክ ወደ ሃላ መለስ ብለን  የምናየው ተመሳሳይ ስህተት ላለመድገም ነው፡፡one size fits all policy አይሰራም.

ርዕሱ የመረጥኩት በቅርቡ ይህ ርዕስ ተጥቅሞ አንድ ፅሁፍ ቀርቦ ስለነበር እኔም ታሪክ አጣቅሼ ለመፃፍ ታሪክ ወደ ሃላ መለስ ብለን የምናው ተመሳሳይ ስህተት ላለመድገም የሚለው አባባል ለእኔም ልጠቀምበት ወስንኩ፡፡

ርዕሱ የመረጥኩት በቅርቡ በዚህ ርዕስ አንድ ፅሁፍ ቀርቦ ስለነበር እኔም ታሪክ አጣቅሼ ለመፃፍ ይህ አባበል ተጠቀምኩ ፡፡ 27 ዓመት ጨለማ ነበር ማለት በዘመናዊ መንግሰት አስተዳደር ከ27 አመት በፊት የነበረ መቶ አመት ብርሃን ነበረ እያሉን ነው ፡፡ የአትያጵያ ያለፈው መቶ አመት ታሪክ በስሱ መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡ የአፄ ሚኒሊክ ስርአት ትተን ቀረብ ብለን ከንጉስ ሀይለስላሴ እንካን ብንጀምር እአአ ከ1916-1974 ገዝተዋል ሞጉዚት የሆንበተን ጨምሮ፡፡ እአአ በ1931 ንጉሱ ለኢ/ያ ህዘብአበረከትኩት ያሉት ህገ-መንግሰት ስለ ልአላዊነት ምን ይላል ? ስለ ኢ/ያ ህዝብ ምን ይላል? ስለ ሃይማኖት ምን ይላል ?ስለ ቋንቋ ምን ይላል ?ስለ እ ኩልነት ምን ይላል? ማየቱ አስፈላጊ ነው፡፡

Videos From Around The World

በአጭሩ ሁሉም ነገር የሚመነጨው በወቅቱ ገዥ ከነበረው አስተሳስብ ወጥነት/አንድአይነትነ የሚለው ፍልስፍና ነው፡፡ከዚህ የሚመነጭ ፖሊሲ የፈለገ ልይነት ይኑር ሁሉም ነገር በማንኛውም መንገድ አንድ ማደርግ የሚል ሆኖ መለያውም በጉልበት ነው፡፡ምክንያቱም ብዝሃነት መፍቀድ አገር ያፈርሳል ነው ፍልስፍናው ፡፡ ፍልስፍናው በራሱ ችግር አለው በየ አላምንም ዋናው ነገር የትኛው ፍልስፍና የት ይሰራል ነው፡፡ከዚህ በመነሳትም የእአአ 1931 ህገ መንግስት አንድ ንጉስ፤ አንድ ሃይማኖት ፤እንድ ቋንቋ፤ እንድ ባህል፤ እንድ አስተሳስብ (የንጉሱ ስልጣን መለኮታዊ መሆኑ ማመን) ወዘተ አክቶ ነበር፡፡ይህ ማለ ት ፈረንጆች እንደ ሚሉት ለሁሉም እግር ልክ የሆነ ጫማ ወይም ለሁሉም ስው ልክ የሆነ ልብስ (one-size-fits-all ) አይነት አካሄድ ነው፡፡ይህ ማለት ለተለያየ ቁጥር ያለው እግር አንድ ላንተ የሚመችህ ጫማ ቁጥር መርጠህ ለሁላቹህም ይህ ጫማ ልካቹህ ስለሆነ ተጫሙት ብሎ መወሰን ነው እንግዲህ ኢትዮጵያ እንዲህ ነው የነበረችው ይህ መስማት የማይፈልግ ሃይል አለ ግን የትናት ስህተት እየደገምን እንዳንኖር ማንሳቱ ጠቃሚ ነው ፡፡

ይህ የንጉሱ ሁሉም የመዋጥ /assimilation /ፖሊሲ እንደተመኘው ሁሉም ልይነት እንደ ብረት አቅልጦ ስርኣቱ ወደፈለገው ወጥነት /ሞዴል/uniformity / ለማምጣት ይቅርና ትንሽ እንካን ፈቀቅ አላደረገውም በተወሰኑ ከተሞች ካልሆነ በሰተቀር፡፡ የዚህ ዋና ምክንያቱም በጉልበት ብቻ መጫን አንጂ በትምህርት፤ በማህበራዊ (ባህል፤ቋንቋ፤ሃይማኖት) ኢኮኖሚያዊና ፖሊታካዊ አብዮ ት አልተደገፈም ወይም መሬት ላይ አልወረደም፡፡

ለምሰሌ አማርኛ የአገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ ሆኖ አማርኛ (የአማርኛ የአፍ መፈቻ ቋንቋ የሆኑትን ሳይጭምር) መናገር የሚቻለው ትምህርትቤት ስትሄድ ነው ያውም ከክፍል ከወጣህ በሃላ በአፍመፈቻ ቋንቋህ ነው የምትናገረው ምክንያቱም ወላጆችህ እንካን አማርኛ አይናገሩም ሳይፈልጉ ቀርተው ግን አይደሉም፡፡ አማርኛ F ያመጣ ዩኒቨርሰቲ አይገባም ነበር እሰከ ደርግ በሃላ ተቀይረዋል ይህ ሁሉ ተደርጎም ግን ወጥነት አልመጣም፡፡ በንጉሱ የኢ/ያ ትምህርት ሰርጭቱ ለቢሮክራሲው የሚያገለግሉና በንጉሱ የሚምሉ ሊህቃን ከማፍራት ወጪ እዚህ ግባ የሚባል ስርጭት አልነበረውም ይህ ሃቅ ነው፡፡ስለሆነም ሁሉም የመዋጥ /assimilation/ ፖሊሲ የባህል፤ ቋንቋ፤ አስተሳሰብ ፤ሃይማኖት መውራረስ ወጤት አላመጣም፡፡

እዚህ ላይ ግልፅ መሆን ያለበት ሁሉም የመዋጥ /assimilation/ ፖሊሲ ተሳክቶ በዋነኝነት ሁሉም ተዋህደው/ ተውጠው/ ተቀይጠው/ አዲስ ነገር ተፈጥሮ ቢሆንኑሮ የብዝሃነት ጥያቄ አይኖረም፡፡ ምክንያቱም በሂወት የሌለ ነገር መጠየቅ የእበደት ነው የሚሆነው፡፡ለምሳሌ ጋፋት አንዱ የኢ/ቋንቋ ነበር በሂደት ተውጦ ተናጋሪ የለውም አሁን ስለ ጋፋት የሚጠይቅ የለም፡፡ በሂወት ያሉት ግን እስከ አሁን የተለያዩ ጥቄዎች እየጠየቁ ነው መልስም ያሻቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ቋንቋው፤ ባህሉ፤ ሃይማኖቱ፤ ስነልቦና ወዘተ ብዝሃነት ቀጭጨው ሳይሆን ተጠናክረው ይገኛሉ፡፡ የእነዚሀ ማበብ ዘረኝነት/ጎሰኝነት ተንሰራፋ ይባላል፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ተሞክሮ የከሸፈው የወጥነት ፖሊሲ አስተሳሰብ መሬት ላይ ካለው ሀቅ በላይ ምክንያት እየተፈለገ ፀረ ፈደራል ስርአቱ ከተጀመረ ጀምሮ በእጅጉ ሲጮህበት የነበረ አጀንዳ ነው፡፡ ለውጡን አስታኮ ደግሞ ሁሉም የመዋጥ /assimilation/ ፖሊሲ አቀንቃኞች ኢትዮጵያዊነት በሚል ሽፋን የበላይነት ለማግኘት ይፍጨረጨራሉ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ያለቸው ብዱኖችም የመጣው ለውጥ ፈዳራሊዝምና ህገመግስቱ ካላፈረስ ምኑ ለውጥ ሆነ ይላሉ፡፡ ህገመንግሰት ለማፍረስም በግላጭ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ይህ ሃቅ አንድ ምሳሌ በቻ በማቅረብ ማየት ይቻላል፡፡

ፈዳራሊዝም እና ህገመግስቱ በተመለከተ እንድ ቃል እንካን በማንም አካል እንዲነሳ አይፈልጉም/ አይፈቅዱም፡፡ስለዚህ የዴሞክራሲ ሽታ የሌላቸው ሲበዛ ፅንፈኛና በጥላቻ ፖለቲካ የታወሩ ናቸው፡፡ የለውጥ አካ

ነን ከሚሉት ውሰጥ በርካታ ወራት ስለ ፈዴራሊ ምንም ያሉት ነግር አልነበረም በአንድ ወቅት በሁኔታ ተገደው በፈዳራሊዝም አንደራደርም ብለው መግለጫ በመስጠታቸው የመዋጥ ፖሊሲ (assimilation) የሚያራመዱ ቡዱኖች እና ይህ ለማቀንቀን ከተፈጠሩት እንደ አሽን የፈሉት የሚድያ አካለ ት በመጣመር ያለማቀረጥ ዘመቻ ከፈትባቸው፡፡የአንድ አመቱ ጉዞ ደማቅ ብርሁን ሲሉ ቆይተው በአንድ ጊዜ ጨለማ አደረጉት፤ ለውጡ ተደናቅፈዋል፤ ለውጥ የለም አሉ፤ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው እያሉ ሸወዱን ወይም ሻሻ ሰሩን ብለው ኡኡ አሉ፡፡ ልብ ብሎ ለተመለከተው ሰው ይህ ምን ማለት ነው ?

አሁን ወደ ዋናው ጥያቄ ስንመጣ ለማን ነው የጨለመው የሚለው መልስ የምናገኝ ይመስለኛል፡፡ (ስለ ለውጡ መዘርዘር የአሁን አላማየ አይደለም )እነዚህ ናችው እንግዲህ በፈዳራሊዝም አንደራደርም ማለት ሲጀመር የአንድ አመት ለውጡን ጨለማ ብለው ሰዎችን እየሰደቡና እያጣጣሉ ብዙ እያስተጋቡ ያሉት፡፡ ልይነቱ ያጠለቁት መነፀር ሁሉም የመዋጥ ፖሊሲ(assimilation )ስለሆነ ሁሉም አንድ ሆኖ ነው የሚታያቸው ይህ ደግሞ ብዘህነትን የመካድ (Divesity blindness) ችግር ነው፡፡ ስለሆነም የድሮ መነፀር አሁን ያለው ሁኔታ ስለማያሳይ one size fit all policy መቀየር ያስፈልጋል እንደ አገር አብሮለ መኖር፡፡

እነዚህ ከላይ ያየናቸው ፅንፈኞች /ጭፍን ጥላቻ ያላቸው/ ስልጣን ቢይዙ አገሪቱ ምን ትሆናለች? አሁን ፈደራሊስት ስርአት አራማጅ መስለው የመዋጥ ፖሊሲ(assimilation) የሚራመድና የሚተገብሩ አካላት ስልጣን ላይ አሉ (ሁሉም አይደሉም) ለዚህም ነው ከችግርና ከግጭት መውጣት እያቃተን ያለው ምክንያቱም በተግባር ህገመንግሰቱና ፈድራል ስርአቱ ከህገመንግሰት ማሻሻል በፊት እየናዱ ስለሆነ ነው በተግባርም እያፈረሱት ነው እንዲፈጥንላቸው ድግሞ ኮሚሽን አቋቁማ፡፡የት አንደሚያደርስ ማየት ነው

ሁለተኛው ደግሞ 27 አመት ጨለማ ነበር ያሉት ሌላ ምክንያት የላቸውም ምክንያቱ ተመሳሳይነው፡፡ አዲሱ ፈደራል ስርአት እውን የሆነበትና ተግባራዊ መሆን የጀመረበት አመታት ስለሆነና ሌሎችን የመዋጥ ፖሊሲ (assimilation ) ያመከነ ስርአት ስለሆነ ነው፡፡ ለእነዚህ ፅንፈኛች ሌሎችን የመዋጥ ፖሊሲ (assimilation) ውጪ ሁሉም ጨለማ ነው፡፡ ለነሱ ኢትዮጵያ ማለት በተጨባጭ አሁን በእውነተኛው አለም ያለችው ብዙሁነት የተላበሰች ኢትዮጵያ ሳትሆን ምናባዊ ኢትዮጵያና ሊፈጠርዋት ሞክረውም ያልተሳካላቸው ኢትዮጵያ ናት፡፡

የሚገርመው ግን ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ማለት የተፈቀደለት ለካ ሌሎችን የመዋጥ ፖሊሲ /assimilation/ ለሚያራምድ ፅንፈኛ ሀይል ብቻ ነው፡፡ በፈደራል ስርአትና በህገመንግስቱ ለሚያምን ሰው ኢትዮጵያዊነት የሚል ቃል አይመለከትውም፡፡ በእነሱ የምናብ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ለመባል የሚከተሉት ፈፅሞ ማንሳት የለብትም፡-ብሄር፤ ብሄረሰብ፤ ፈደራሊዝም፤ ህገመንግሰት ፤ቋንቋ፤ ክልል፤ ፌደሬሽንም/ቤት ወዘተ፡፡ የሚገርመው ነገር የጠ/ሚነስተሩ የድህንነት አማካሪም በቅርቡ በምን ጥናት እንዳገኙት ወይም ምን አይነት ጊዛዊ ፖሊቲካ ለማብረድ እንደሆነም አይታወቅም የኢትዮጵያ ፖሊቲካ በብሄር የመደራጀት ችግር ነው አሉ ተከታትሎም የብሄር ፖሊቲካ ይታገድ የሚል ዘመቻ ተጀመረ ዘመቻው መሪ ሻለቃ ተመስገን መሆኑ ነው ደንቄ የድህንነትአማካሪና አክሰቲቪት መሬ ፡፡ በእውነት አሁን የኢ/ያ ችግር ይህ ነው? በበኩሌ ዋናው ቸግሩ እሱ አይመስለኝም ፡፡ ፕ/ር መራራ በቅርቡ የተናገሩት ሃሰብ ልጋራ አሁን ባለውሁ ኔታ የማንነት መሰረት ያደረገ ፖለተካ ማሰቀረት አይቻልም ምናልባት ቀጣይከ10 አስከ 30 አመት ማየት ነው ብለዋል ትክክል ናቸው፡፡ በህ/ሰባዊ እድገት የሚመጣ እንጂ እንደ አሁኑ በሚዲያ ጫጫታ፤ በሸር ፖሊቲካና አስፈፃሚ ዘረኛ /መርዘኛ/ toxic/ ፓርቲ በመፍጠር በፍፁም አይቻልም፤አይቻልም ፤ አይቻልም፡፡

ለምሳሌ በአማራ ክልል እጅግ አብዛኛዎቹ በራሱ ክልል ውሰጥ የተፈናቀሉ ናቸው:: የትኛው ብሄር ሄዶ አፈናቀላቸው? ለምንስ ክልሉ መፍታት አቃተው? አማራ ክልል ብቻ ለማተኮር ፈልጌ አይደለም ግን በራሱ ክልል ወስጥ ይህን ያህል ህዘብ ካፈናቀለ ሌሎችን መውቀስ አይከብድም ወይ? በክልሉ ወሰጥም የሌሎች ብሄርተ ወላጆች በመሆናቸው ብቻ የተፈናቀሉት ቁጥር ብዙ ናቸው እሰከ አሁን ፡፡ በቅርብ ከምሴ አከባቢ የነበሩት መፈናቀሎችና ግጭቶች የክልሉ ታጣቂ ሃይል ተሳታፊ እንደነበረ የፈደራል የፀጥታ አካለት በግላጭ ገልፀዋል፡፡ ታደያ ይህ ችግር የብሄር ፖሊቲካ ያመጣው ችገር ነው ? ስለዚህ ችግሩ ሰበብ አስባብ ፈጥሮ ፌደራል ስርአቱ አልሰራም ለማለት የሚደረግ ዜዴ ነው፡፡ ይህ ለማራመድ የተፈጠረ እጅግ ፅንፈኛ/መርዘኛ /toxic/ አብን የሚባል ሃይልም ተፈጥረዋል፡፡

ለምሳሌ በቅርቡ ከምሴ አከባቢ በተፈጥሮወ ችግር ደሴ ስቴድዮም ሰብስቦ በመንግሰት ሚድያ በግላጭ ጦርነት የሚያወጅ፤ ተነስ የሚል ነው፡፡ ዘረኝነቱ፤ ተንካሽነቱና ተስፋፊነቱ በዘህ አለም ተወዳዳሪ የለውም ፡፡ ልብ በሉ እንደ ፈከሮው አቅም ቢኖሮው ምን ሊያደርግ እንደሚችል የቤንሻንጉል ማየት ነው፡፡ ሆኖም ለእያንዳንደዋ ትንኮሳ አፀፋው ከእጥፍ በላይ ስለሆነበት እንጂ የወታደራዊ የብላይነት ቢኖረው ይህቺ አገር ወደ ርዋንዳ አይነት ይቀየራት ነበር ፡፡እንደ ፈኮሩት /ሸለሉት /ቢሆንማ ኑሮ ትግራይ እንጨብጣት አለን ባሉበት ጊዜ እስከ አሁን ራያ አይደለም መቀሌ ገብተው ነበር ሀኖም ግን ወያኔ ቀድማ በቆረጣ ባህርዳር እንደምትደርስ ስለሚያወቁ በአከባቢው በሩቁ ውር ውር ከማለት ወጪ ወፍ የለም ፡፡ አምላኬ ለትዕቢተኛም ሃይለኛ አውርድለት ብየ እፀልያሎህ ወያኔ አንድ ቀን ቢያቀምስልን ሰላም አናገኝ ነበር፡፡

በቅርቡ በፅነፈኛ/ፍፁም ጥላቻ/ ፖለቲካ አራማጆች ሰለባ የሆኑ አማራ ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች በቤንሻንጉል ተወላጆች የበቀል እርመጃ ወስደዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ውሰጥ ያለቁት ዜጎች ቁጥር ስናስብ ምልክቱ አደገኛ ነው፡፡ ስለሆነም ፅነፈኛውና ዘረኛው ሃይል እድል ካገኘ በጅምላ ህዘብ እንደሚጨርስ በቤንሻንጉል ክልል የተፈፀመው ድርጊት ማየት ይቻላል ፡፡ ስለሆነም ይህ ሃይል ወላጅ አባቱን ጨምሮ አንድ ሊባሉ ይገባል ፡፡ ቤንሻንጉል ክልል ም/አስተዳዳሪ አለም ቀአፍ አጣሪ ቡዱን ያጣራልን ሲሉ ለአለም አቀፍ ሚድያ ለሉበርምበግ ገልፀዋል ምን ያህል መተማመን እንደጠፋ መገንዘብ ይቻላል ፡፡ ጉድ እኮ ነው ዘንድሮ ሞኩሮው አቅም ሲያጡ ለመከላከያ ልክ እንደ እሳት አደጋ በለኮሱት እሳት ሁሉ አሳት ያጥፋልን እያሉ እረ ማለት አቅድመ ደካማ( ሴቶች፤ህፃናትና አረጋውያን ) ሲገኙ ህዘብ እየጨረሱ ሊኖሩ ነው የተፈቀደላቸው፡፡ አቅም ካለህ ወያኔ አትሞክረውም ህፃናት ላይ ከምትለማመድ ፡፡ አሁን ይህ ምን ይባላል?

ሌሉችን የመዋጥ ፖሊሲ ያነገቡ ሃይሎች ሌላው ዘረኛ ብለው ይፈርጁታል ፡፡እንዲያውም አሁን ልክ እንደ ካርታ ጭዋታ ጆኬር /ባጣቆየኝ/ ሆነዋል፡፡በብሄር ለተደራጀ ዘረኛ ሲሉ ቆይተው እንሱም ይደራጁበታል ሲፈልጉ ድግሞ ብሄራዊ/ዜግነት ይላሉ የሚገርመው ለነሱ ሲሆን ዘረኝነት አይሆንም፡፡ እንደ አሽን ለውሽት የተደራጀው ሚድያቸው ድግሞ የብሄር ስም እያነሱ የብሄር ፖሊቲካ እያለ ያንቃሽሻሉ ሌሎችን የመዋጥ ፖሊሲ/ assimilation/ና የብሄር ፖለቲካ እያጣቀሱ የሚዘበርቁት ይወደሳሉ ምክንያቱም በቦሌም በባልም ብሎ ስልጣን መያዝ ነው፡፡ ሁኔታው ለጫማው በሃላ ይታሰብለታል አይነት አካሄድ ነው ሆኖም ሁሉም ነገር የሚኖሮው አገር ሲኖር ነውና ብታስበት፡፡

በመግብያየ እንደገለፅኩት ታሪክ ወደ ሃላ መለስ ብሎ በማየት ተመሳሳይ ስህተት ላለመድገም ያግዛል፡፡የደርግ ከንጉሱ በምንይለያል ? በመሰረቱ ስርአቱ ከፍፁም ንጉሳዊአ ገዛዝ ወደ ፍፁም ወታደራዊ አገዛዝ ከመቀየር ውጪ የነበረው የወጥነት /አንድ አይነትነት/ ፖሊስ አጠናክሮ ቀጠለበት፡፡ብዘሃነትን/diversity / በጉልበት ለማጥፋት ልክ ከአሁኑ የመዋጥ ፖሊሲ/ assimilation/ አራማጆች አንድ እና አንድ ናቸው፡፡ምክንያቱም የአስተሳስብ ጉዳይ ነው፡፡ማንም ይሁን ማንም ከአፄዎቹ ዘመን እሰከ ደርጉ ዘመን ሲሰራበት የነበረ ፖሊሲ ስለሆነ የዚህ አስተሳሰብ ሰለባ የሆነ ሁሉ ያራምደዋል፡፡ ይህ ፖሊሲ መጨረሻው ኤርትራን አስረክቦ ግብአተ መሬት ግባ አሁን ደግሞ የቀረወ አለ መሰለኝ ተመልሶ መጣ፡፡

የአሁኑ ልይነቱ ግርግር ለሌባ ይመቻል እንደ ሚባለው ለውጡን አስታኮ የፖሊሲ ለውጥ፤ የህገመንግሰት ለውጥ፤የግዛት ማሰፋፋት፤ በጉልበት መጨፍለቅ፤ ዘራፍ ያዙኝ ልቀቁኝ፤ ፉፁም ጥላቻ መስበክ፤ ግጭት መፍጠር ወዘተ ታክቲከ ተጥቅሞ የፈደራል ስርአቱ አልሰራም ህጋዊም ህገወጥም እየቀላቀሉ ህገመንግሰቱ ይወገድ ለማለት ነው አጀንዳው፡፡

ለዚህ በርካታ በጀት ተመድ ቦበማህበራዊ ሚድያ፤ ቴለቨዥን ፤ሬድዮ፤ጋዜጣ፤ በስብሰባ፤ በግጥም ምሽት ወዘተ ማሰተገባት ነው፡፡ የትም ኮሽ ሲ

የዘር ፖለቲካ ይላሉ የሚገርመው አብዛኛው ራሰቸው የፈጠሩት መሆኑ ነው፡፡ አሁን ያሉ የመንግሰት እና የግል ሚድ የፈደራል ስርአቱን መናድ፤ የአ/ያ ችግር የብሄር ፖለቲካ ነው የሚል መግለጫ ሁሉ ይሰጣል፡፡ የአሁን ግርግር ፤ ወዥንብርና ግጭት ለነዚህ ሃይሎች ሰርግና መልስ ነው፡፡ ሰሜን ጫፍ ሆኖ ምእራብ ጫፍ ኮሽ ሲል የዘር ፖለቲካ ብለው ይንጨረጨራሉ፤ ማሀል አገር ላይ እንቅፋት መትቶት ከወደቀም ብሄር ተኮር ጥቃት ይላሉ፤ እነሱ በፈጠሩት ግጭት በርካታ ሰዎች ሲፈናቀሉ ፤ ሲገደሉ ሚድያዎቻቸው ግን ትንፍሽ አይሉም ታድያ ይህ ኢትዮጵያዊነት ወይስ ፍፁም ዘረኝነት፡፡ እርዳታ ለማግኘት ብቻ ተፋናቃያቸው ይገልፃሉ ራሳቸው አፈናቅለው መልሰው የብሄር ፖለቲካ አውግዝ ብለው ሰልፍ ያወጡታል ፡፡ የሚገርመው እነሱ ከማንም በላይ በህጋዊነት ልባስና በህገወጥ መንገድ አገር እያመሱ ሁሉም ችግር ለኦነግና ቄሮ ሰጥተው ያለማቃረጥ እነሱ ላይ መዝመታቸው ነው፡፡ይህ ምን የሚሉት የፖለቲካ ፈሊጥ ነው? እስከ መቼስ ?

አሁን ያለው ፖለቲካ ሁኔታ ሲጠቃለል፡-

ብአዴን ማሃል ሜዳ ላይ ሆኖ ከጭዋታ ህግ ውጪ እያተራመሰ ሁሌ በአጥቂ ግራ መስመር በኦፍሳይድ ውስጥ የሚጫወተው አብን ካስ እያቀበለ የዘረኝነት፤ ጥላቻ ና ግጭት ጎል ያገባል፡፡ ዳኛ(ኢሳትና ተመሳሰይ ሚድያ)እና የመስመር ዳኛች (ፋና ፤ዋልታ፤ዕንፋኛ ሚድያ) ግቡን ያፅድቁታል ፡፡

ብአዴን ከማሀል ስልጣን ላይ ሆኖ ወቅታዊ አጅንዳ ለአብን እያቀብለ ያቀጣጥላል፡፡ ታክቲኩን እንመልከት ጠ/ሚስትሩ ሚነሰተሮች በሽሙበት ጊዜ ትውልድ ቦታ እንጂ ብሄር አልገለፁም ቢሆንም ስልጣን በትውልድ ቦታ ሳይሆን በብሄር መሆኑ ግልፅ ነበር ፡፡ ወ/ሮ ሙፍርያት ጅማ በመወለድዋ አይደለም ሚኒሰተር የሆነችው ስልጤ በመሆንዋ ነው ሌላውም ተመሳሳይ ፡፡ በሹመት ጊዜ የተሻሚ ብሄር ባለመጠራቱ ፅንፈኞቹ አጨበጨቡ መስማት የማይፈልጉት ቃል ለይስሙላ ስለቀረ ብቻ፡፡ በነጌታው ዘር መቁጠር ጀመሩ ድርሻችን አነሰን አሉ ከማሀል ሜዳና ከአጥቂ መስመር በኦፍ ሳይድ ወስጥ ሆነው ፡፡ ኦህዴድ በይሉኝታ (ሼም ይዞት) መሰለኝ ፕሬዚዳንትነት ለብአዴን ለቀቀ ሆኖም ኡኡታው ቀጠለ ፤ አሁንም ጩሁቱ ስላሰጋው ኦህዴድ የውጪ ጉዳይ ሚኒሰተር ሰጣቸው ፤ አሁንም ጩሁትና ዘረኝነት ቅስቀሳ ቀጠለ የገቢዎች ሚ/ር በአንድ ብሄር ተያዘ ብለው በሁሉም ሚድያ ተቀባበሉት እውነታው ግን በሁሉም መ/ቤት ሲታይ በግልባጩ ነው ፡፡

ገቢዎች ሚ/ር በስነ ምግባርጉ ጉድለት በዘረኝነት ቅስቀሳ የታገደ ሰራተኛ የብሄር ጥቃት ደረሰበት ብለው በሁሉም ሚድያም ተቀባበሉት፡፡ ለዚህ ነው ከሰሜን ጫፍ ሆኖው ማሀል አገር እንቅፋት ስለ መታው ሰው ከልክ በላይ ይጮሆሉ ጉያቸው ውስጥ ያለው ልቅሶ ትተው ከላይ የገለፅትኩት ለዚህ ነው ፡፡ ስለሆነም ጤነኛ የስልጣን ጥያቄ አይደለም ፡፡ ቀጥሎ ደገግሞ የተመሩጡ መ/ቤቶች እየመረጡ የጥላቻ ፖለቲካ በመፍጠር ስራ እንዳይሰራ በማድረግ በአንድ ብሄር ተያዘ እያሉ ማወናበድ ነው የፈለጉትን አላማ እስኪያገኙ ማደናበር ነው፡፡ በላፈው ለትም//ር ሲጮሁ ነበር ፤ ፍ/ቤት ላይ በአንድ ብሄር ተያዘ እያሉ ነበር ወዘተ አይቆሙም ፡፡ እንደኔ ግን በፈደራል መ/ቤቶች ያለው የብሄር ተሳትፎ የሚጣራ ኮሚሽን ያሰፈልገናል ውጤቱም ለህዘብ የሚያሳወቅ የአዞ እንባ ባያቆሙም በውጤቱ መሰረት ደግሞ ማሰተካክያ ማድረግ ይህ ከተደረገ ለውጥ አለ ማለት ነው ፡፡ ሌላው የተቋቋመው ኮሚሽንማ ችግር ለመፈጠር እንጂ ችግር ለመፍታት አይደለም ፡፡

የሚገርመው ደግሞ ወጤታማ መ/ቤት ነው የሚመረጡት፡፡ መጨርሻ መቼ ነው ይህ የተደራጀ የዘረኝነት ቅስቀሳ የሚያቆሙት? ቀጥሎ መንግሰት አዳክሞ /አልቻለም ብሎ በመጮህና በማሰጮህ ቀዳዳ ከተገኘ ቦታ መያዝ ነው፡፡ በመጨረሻ ይህ ሃይል/ አስተሳስብ/ ስልጣን ከያዘ / አሁንም አለ ግን../ መጮህ ቀርቶ መተንፈስ አይፈቅድልህም ስለሆነም ሁሉም ነገር በጥንቃቄ ማየትና ትርጉም መስጠት ያስፈልጋል፡፡ የቀድሞ ኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንእል አራሀሞይ የተናገሩት ልጥቀስ አይናቹሀ ጨፍናቹህ ፀልዩ አሉን ፀለየን አይናችን ስንገልጥ ሁሉም ነገር ወሰዱትምን ለማለት ፈልገው ነው? ለኛስ ምን ማለት ነው?

ለማጠቃለል የኢ/ ያ አንደነትን ልይነትንት በመጨፍለቅ ይመጣል ብለው ሞኩሮው ያልተሳካላቸው የፖለቲካ ፅንፈኞች ከያሉበት ሁሉ በባትሪ ድንጋይ እየተፈላለጉ መሰባሰብ ከጀመሩ ስንበትበትብለዋል፡፡ታድያ የኢ/ያአንድነት ለማምጣት ነው ወይስ የኢ/ያ እንድነት ለማፍረስ ? በሀዝቡ ዘረኝነት በማስፋፋት ህዘቡን ማለያየት ወይሰ ህዘቡን ወደ አንድ ለማምጣት ? የዜጎችን መብት መጠብቅ ነው ወይስ እድል ሲያገኙ ህዘብን መጨፍጨፍ ? የኔን ምልከታ አቀርቤሎሀ ድምዳሜው ለአንባቢ ትቻሎህ ፡፡

 

 

 

 


Back to Front Page