ግብጽዬ
የድሮው መሪሽ እስርቤት
ያሉት
ሽርቡን ተንኮሉን ያቀነባበሩት
በግልጽ በቴሌቭዥን እንደተናገሩት
ፍርክርክ አልን ብትንትን
ሙሽሽ አለን ምንምን
ጥንካሬን ጠልተን
ባንቺ ተረግመን
ስኳርሽን ቀምሰን
ዝቅ ብለን ወርደን
ልዑላዊነትን ንቀን
ልመናን መርጠን
ወጥመድሽ ውስጥ ገባን
ይሄው...
ኢንጅነር ስመኝን
በአደባባይ ደፍተን
ያመጣሽልንን ነውጥ
ተቀብለን እንደለውጥ
አመት አከበርን
ዘፈንን ጨፈርን
አመስግነን ፈጣሪን
ለዚህ ያደረሰን
ሶስት ሚሊየን ተፈናቃይ
እንደሌለ ክደን
ሸፋፍነን ደብቀን
እንደምንፋቀር
ቀን ከለሊት ሰብከን
ይኸው ግብጽዬ
ፍርክርክ ካልን
አንድ አመት ሞላን
ኢዮብ ከጮማ እምኒ
4-3-19