Back to Front Page

መቐለ አደራ አለች

መቐለ አደራ አለች

መብታችሁ ሲረገጥ ... ሲታፈን ድምጻችሁ
መቐለ ... መሮጥነው ... ሁሌም አመላችሁ
መቐለ ... ሆደሰፊ ...
ሁሉን አስተናጋጅ
መቐለ ... መጠለያ ...
ለሁሉም ብሄር ... ተወላጅ

መቐለ ... ቻለች
መቐለ ... ደገፈች
መቐለ ... አስጠነቀቀች

አዳማ የሄደ ... የሚወደስበት
ባህርዳር የተገኘ ... የሚጨበጨብለት
መቐለ የተሰበሰበ ... የሚኮነንበት
በገሀድ በግልጽ ... የሚገለልበት
ይሄነው ... የነውጡ ውጤት
የመሪው ... ክህደት
የ "አጋሮች" ቅጥፈት

መቐለ ... ለፌደራሊዝም ብላ ...
የገበረች ... የቆሰለች
የደማች ... ያሸነፈች
ያልተመቀኘች ... ያላጎበደደች
የተዋበች ... የተሸለመች
ሰሜናዊት ኮከብ ... መቐለ ...
እንዲህ መከረች ....

ሳትጨፈለቁ ... ሳትኮሰምኑ
በብልጽግና መንግስት ...
የእሳት ራት ሳትሆኑ
ታገሉ አጥብቃችሁ ... ሁሉንም ከአሁኑ

ባህልና ቋንቋችሁ ...
ታሪክና ነጻነታችሁ ... ገብቶ ሳለ በእጃችሁ
ለሰኳር፣ለግል ጥቅም ... ካጎበደዳችሁ
ፌደራሊዝምን ...
በፈቃደኝነት ካከሰማችሁ
መቐለ ሳይሆን ... ተወቃሽ ራሳችሁ

መቐለ ... መክራለች
መቐለ ... መርጣለች
መቖለ ... ታሸንፋለች !!!

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

12-12-19

Videos From Around The World

Back to Front Page