መጥረጊያው አይጠርግም
ይቀየር መጥረጊያው
ምንም የማይጠርገው
ቆሻሻን ከንጹህ
ለይቶ የማያውቀው
አይጠርግም አይጠርግም
መጥረጊያው አይጠርግም
ቱባ ቱባን ቆሻሻ
በፍጹም አይነካም
ስብዕናን ያራከሰ
የጨከነ የገደለን
በተሰበረ ካልኩሌተር
የሸወደ ያታለለን
ያጋጨን ያተራመሰን
የአፍ አርበኛችን
የህዝብ ሸክሞችን
ወንጀለኛ ዘረኞችን
መጥረጊያው አልጠረገም
አዎ አልጠረገም
ዶክተሮቹም አስተማሪዎቹም
በአንድ ድምጽ
ብለዋል
መጥረጊያው አይጠርግም
መጥረጊያው አይሰራም
ኢትዮጽያውነትን
አልተላበሰም
መጥረግም አይፈልግም
መጥረገም አይችልም
መጥረጊያው አይጠርግም
ኢዮብ ከጮማ እምኒ
5-20-19