ሰባተኛው ንጉስ! አዲሱ ተሿሚ ፤ሰባተኛው ንጉስ፤ ጥርጊያውን ሰርቶልህ፤ ኢህአዲግ ወመለስ በቀናው ጎዳና፤ ስትችል መመላለስ ምነዋ ተመኘህ፤ የሰሩትን ማፍረስ? ኧረ ቀስ፣ ኧረ ቀስ! ሰባተኛው ንጉስ! አለህ ጥሩ ምላስ፤ አትናደፍበት፤ትግሬ ነፍሱ አይላስ። አንደበትክን አድስ፤ በቃልህ አትርከስ። ሰባተኛው ንጉስ! አምናለሁ እያልከን ፤በኢየሱስ ክርስቶስ ተው አትመላለስ ፤በይሁዳ መንፈስ። Ahadu Selamu 1-19-19
|