Back to Front Page

ከአማራ ክልል ባለስልጣናት እና ጀነራሎች ግድያ በስተጀርባ ማን ይኖራል?ክፍል ሁለት

ከአማራ ክልል ባለስልጣናት እና ጀነራሎች ግድያ በስተጀርባ ማን ይኖራል?

ክፍል ሁለት

ሱሌማን ከድር;- ከአዲስ አበባ 7-16-19

በመጀርያው ፅሁፌ ዶ/ር ዓብይ ከውስጥም ከውጭም ህገ መንግሰቱ አክብረው የ2012 .ም ምርጫ እንድያካሄዱ ጫና እየደረሰባቸው እንደሆነና:: እሳቸውም ውስጥ ለውስጥ በዚህ የተስማሙ ስለሆነ ቅድመ ዝግጅት የጀመሩ ይመስላል:: ይህንን ምርጫ ለማካሄድ ግን ቀንደኛ ተቃዋሚዎችን የሚልዋቸውም ከኦሮሞ የበላይነት ከአዲስ አባባ አስተዳድር ስጋት የሆኑትን እና በጠዋላይ ለፌደራል ስልጣን የሚቃወሙ ማወገድ እና ያለ ተቀናቃኝ ልክ እንድድሮው ኢህዴግ ማሸነፍ ይፈልጋሉ::ለዚም በግብፅ እና ኤርትራ አማካሪነት እና በኢትዮጵያ ደህነት ሃይሎች እውቅናና ድጋፍ ተቀናቃኝ የሚሉዋቸውን ማስወድ አለባቸው:: ለዚህም ሁለት ቡድኖች ከቤተመንግስት ተሰየሚዋል 1. ድብቁ ቡድን ጥቂት የኦዴፓ ብቻ የሚዋያቀወቁት 2ኛው ደግሞ ጥቂት ኦዴፒ እና አዴፓ የሚያወቁት በተለይ ከአዴፓ ደመቀ; ገዱ; ንጉሱ እና የሃንስ ባያለው ይታማሉ::


Videos From Around The World

የመጀመርያ ቡድን ግምገማ:- ከኦሮሞ የበላይነት እና ለአዲስ አባባ አስተዳድር ስጋት የሚሆኑት መለየት


ጁሃር ስለ ኦሮማራ ስትራተጂ ሲገልፅ በግልፅ እንደተናገረው ህወሓትና ትግሬዎችን በማዳከምና ከፌደራል መንግስትና በጠቅላላው በኢትዮጵያ ፖለቲካ የነበራቸውን ሚና ዝቅ እንዲል ልካቸውን እንዲያቁ ካደረግን በኃላ ትላልቆቹ ክልሎች ኦሮሚያና አማራ ብዙ ህዝብ ያላቸው ወሳኙን ሚና ይጫወታሉ ብለን የተሳካ ስራና ውጤት አስመዝግበናል ብሎ ይገልፅና ያጋጠመውን ችግር ደግሞ ሳይደብቅ ያብራራል ከነመፍትሄው። ይህ ካሳካን በኃላ አማራዎቹ ግን ሌላ የብቻቸው ዕቅድ እንዳላቸው ደረስንበት። ህወሓትንና ትግሬዎችን በጋራ አንድ ላይ ሁነን ካዳከምን በኃላ ኦሮሞዎቹን በቀላሉ ከስልጣን አውርደን የቀድሞ ስልጣናችን እናስመልሳለን ብለው እያሰቡ እንደሆነ አወቀናል። መፍትሄም አበጅተናል። ሚዛን መጠበቅ አለብን። ሁለቱ አማራና ትግራይ በቀጣይ እንዲናቆሩ ማድረግ ነው ብሎ ነበር (source OMN & FB)


ሆኖም የብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ ዝግጅት ትግራይ ብቻ አይደልም የሚመለከተው ጠቅላላ ኢትዮጵያ ከቻለም እስከ ቀይባህር መንግስ ይፈልጋል:: ለዚህም ዝግጅት ኤርትራ የነበሩት ታጣቂ ቡድኖች ጨምሮ በአማራ ክልል እሰከ መቶ ሺ ሚልሸያ አሰልጥኖ አስመርቀዋል :: ፈዴራል እና የአማራ ክልል መንግስት በሚያውቁት በቂ በጀት ተመድቦለታል::
በቂ መሳሪያም ገዝተዋል:: ይህንን ዝግጅት ግን ለትግራይ ብቻ አይደልም ብሎ ቀድሞ የነቃው ጃዋር ሳይሆን አይቀርም ይባላል. ስለዚህ ከቲም ለማ ሳይመክርበት አይቀርም:: /ር ዓብይም ደሴ ስብሳባ ጥያቄ ሲመልሱ በጀቱ ለመሰሪያ ግዝ አና ሰራዊት ስልጠና ከዋላ ልማት ከየት ይመጣል በማለት በአማራ ክልል ያለው ዝግጅቱ በግልፅ መቃወም ጀመሩ :: እሱም ቢሆን ጠላቶቻን እንደ ግራኝ መሃመድ ያሉ እና እነዚህም ለመውጋት እና ልክ እንደ አቡነ ጵጥሮስ ሁሉም ሰው ለመስዋእት ዝግጁ እንድሆን በየስበሳበው ሲናገር ነበር::


የሁለተኛው ቡድን ግምገማ:- ከአዴፓ ስልጣን ማስጠቅ እና ተቀናቃኙን በተለይ አብን መዳከም


ደመቀ እና ቡዱን ሁሌም የራሰ ምታት የሆነው አንድ ነገር አለ:: በአማራ ክልል በሰፊው የሚታማ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች በወሎ ሰዎች ተያዙ እየተባለ ይታማል (ደመቀ: ገዱ እና ፀጥታ እና ደህንንቱ አመራሮች ከወሎ ናቸው) አሁን ደግሞ አዴፓ አመራሮች በዚህ የቀጠሉ ይመስላሉ:: በዚህም ዶ/ር አምባቸው ወደ ክልሉ ስልጣም መምጣት በተለይ ፕሬዝዳንት መሆን ለነዚህ ሰዎች አልተዋጠላቸም በተለይ ለደመቀ; ዮሃንስ ባያለው እና ጀነራል አሳምነው ፍራቻ አደራባችው:: ጀነራል አሳምነው ከዶ/ር አምባቸው ይልቅ የሚተማመኑት በደመቀ እና በዶ/ር ዓብይ ነበር:: የጎጃም እና ጎንደር አመራሮች ደግሞ ዶ/ር አምባቸው የአደፓ መሪ እና የክልሉ ፕሬዝዳንት መሆን ይፈልጋሉ :: በደመቀ መኮንን ሁሌም ተጎታች ደስተኛች አይደሉም:: ሰለዚህ ይህንን ሰው ዶ/ር አምባቸው በደመቀ ቡዱን ጀነራል አሳመነው ደግሞ በፌዴራል ቡድን እንድወገዱ ስምምነት ላይ ተደረሰ ይባላል:: (አቶ ገዱ ተቃውመዋል ይባላል) (source: ze-habesha & 360 የቀድሞ ኢሳት አባላት)


ጀነራል ሰአረ ለማስወገድ ቀደሞ የተወሰ ቢሆን ግዜ እና ሁነታዋች እየተጠበቁ ነበር:: ለዚህ ነበር ለስም እንጂ ጦሩ የሚመሩት ሌሎች ጀነራሎች ነበሩ::
በተለይ ጀነራል ሰዓረ ከጠቅላይ ሚነስቴሩ ከቦታ ቦታ መዞር እንጂ ጠለቅ ያለ ስራ እና ተሳትፎ በሰራዊቱ እየቀነሰ የመጣው ግን ህወሃት ለማዳካም እና ሞራል ለመስበር ቀድሞ በሻዕቢያ የተጠነሰሰ ሴራ ሰለነበር:: (ከጀነራል ብርሃኑ ጁላ ውጭ) የተወሰኑ የደህንንት እና ከመከለከያው የደህንት ሰዎች አሉበት ይባላል:: ለዚህም ይመስላል አሁን ሻዕቢያ የተወሰነ ዝግጅት በተለይ ተኩስ እና ልምምድ ጀምረዋል ይባላል::


አፈፃፀሙ


ይህንን ዝግጅት ከተደረገ በሃላ በላፈው እነደገለፅኩት ሁለት ቲም ተቋቋመ:: አቶ ደመቀ የሚመራው ቡዱን በዶ/ር አምባቸው ትእዛዝ በደብዳቤ ወይ በሌላ መንገድ ጀነራል አሳምነው ፅጌን ከስልጣን እንድወገድ ሌለው ድብቅ ቡዱን (ዮሃንስ ባያለው ነው ይባላል ሌሎች ደግሞ ከድህንት ሰዎች ይላሉ) አንተን ሰለሚያምንህ የጎንደሬው ቡደን ወሎን ይጠላል በተለይ ደመቀን እና አንተን:: ለዚህም ከስልጣን ልያስግዱህ ተዘጋጅተዋል:: ውሳኔን ተሰንዋል:: ሰለዘህ ቅደማቸው ከዚያም ከፌደራል ድጋፍት ታገኛለህ በተለይ ከአዴፓ የሚል መልክእት ጀነራሉ አደረሳቸው:: ለዚህም ውለታ ይመስላል ጎንደሬዎች ብቻ እየለየ የገደለቻው የሃንስ ባያለው ህድ ውጣ በሎ ነበር የተወው (ውስጡን ሳያውቅ) ወደ ፌደራል እና መከለከያ ሪፖሪት ያደረገ እሱ እንደሆነ ይነገራል:: ጀነራል አሳምነውም ያሰቡት ሳይሆን ያላሰቡት ክህደት ገጠማቸው ::ይህ ሁሉ ሲደረግ አቶ ደመቀ እና አቶ ገዱ ሆን ተብሎ ወደ ውጭ እንድሄዱ ተደረገ የለንበትም ለማለት ይሆን? በዚህም የጎንደሬው ቡዱን ሳይዘጋጀበት እና በማያውቀው ጉዳይ ለመስዋእት ተዘጋጁ ተገደሉም::


በነ ዶ/ር አምበቸው (ጎንደሬዎቹ) ግድያው እንደተፈፀመ ጀነራል አሳምነው እስከ ሶስት ሰአት ገደማ ማለትም መፈንቅለ መንግስት ተደረገ ተብሎ እስከታወጅ አልሞቱም ነበር:: በተወሰነ አከባቢ ከለላ አግኝተው ነበሩ:: በሃላ ለሳቸውም ዱብ እዳ የሆነባቸው የመፈንቅለ መንግስት ዜና ከሱሙ እና በመከላከያ ከተከበቡ በሃለ ነው :: ለዚህም እንደ ማስርጃ የሚሆነው 2;30 አካባቢ የሰጠት ቃለምልልስ እንመልከት


"/ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ


ምን አሉ?


ባህር ዳር ከተማ ላይ አንድ አንድ ግጭቶች እንዳሉ እና ጉዳቶችም እንደደረሱ ነገሩኝ። 'ስፔሲፊክ' እንዲሆኑልኝ ስለፈለኩኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የፕሬስ ሴክሬቴሪያት ኃላፊው አቶ ንጉሡ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነው ብለው መግለጫ ሰጥተዋል እና እርስዎ ግን ግጭት ነው ያሉኝ ስላቸው መፈንቅለ መንግሥት ብሎ ነገር የለም። መፈንቅለ መንግሥት በየመንደሩ አይደረግም። መፈንቅለ መንግሥት ሊደረግ የሚችለው ማዕከላዊ መንግሥት ላይ ነው፤ እና ይህ ከእውነት የራቀ ነው። ምናልባት የምጠረጥረው የፌዴራል መንግሥት ወደ ክልሉ ለመግባት ፈልጎ የሰጠው ምክንያት ይሆናል ብዬ ነው የምገምተው አሉኝ። ከዚያ መፈንቅለ መንግሥት ካልሆነ [ታዲያ] ምንድነው 'ስፔሲፊካሊ' ያለው ነገር ስላቸው እሱን አሁን መናገር አንችልም፤ ምክንያቱም እኛ ምርመራ ላይ ያለነው፤ እያጣራን ነው። እሱን እንደጨረስን እናሳውቃችኋለን አሉን።


መቼ ነው የምታሳውቁን ስላቸው [ደግሞ] ነገ ጠዋት በተወሰነ መልኩ ምርመራውን ስለምንጨርስ መግለጫ እንሰጣለን አሉኝ ከዚያ ተሰነባብተን። ከዚያ በፊት ግን የመጨረሻ ጥያቄ ብዬ ተኩስ አለ ይባላል፤ አሁንም ድረስ አልተረጋጋም ወይ? ስላቸው እኔም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማኛል አሉኝ። መከላከያ ገብቷል ስለሚባለውስ ነገር? ስላቸው እሱ ላይ ኮሜንት ማድረግ አልችልም፤ የማውቀው ነገር የለም አሉኝ፤ ከዚያ በኋላ ብዙም ጥያቄ ለመመለስ ፍላጎት አልነበራቸውም። የሚሉኝ የነበረው ምርመራ ላይ ነን፤ እያጣራን ነው፤ አልጨረስንም፤ እሱን እንደጨረስን ነገ ጠዋት መግለጫ እንሰጣለን የሚል ምላሽ ነበር የሰጡኝ። ይላል ቃለ ምልልሱ


ከዚህ ቃለ ምልልስ በሃላ ጀነራል አሳምነው ፅጌ እንደተገዱ ይነገራል:: መንግስት ግን ሌላ ገዜ ማለትም ከሁለት ቀን በሃላ በሌላ ቦታ ልያመልጡ ሲሉ እንደተገደሉ ይገልፃል:: ግን ትክክል አይደልም ይባላል ብዙ ልምድ ያላቸው ጀነራል እስክ ሁለት ቀን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እና ሞባይላቸው እንዴት ከአንድ ማስ ሚድያ ግንኝነት አያደርጉም በተለይም ከሚያመናቸው ሰዎች ጋር በተለይ ከክልሉ ማስ ሚድያበሞባይል ወዘተ ሰለዚህ ግድያው የተፈፀመው 3 ሰአት አካባቢ ነው ይህንን ከተረጋጋጠ በሃለ ነው የነ ጀነራል ሰዓረ ግድያ የተፈፀመው ይባላል::


ሌላው ደግሞ ጀነራሉ መፈንቅለ መንግስት ቢየሰቡ ኖረው ከተራ አባላት አብን ወይ ባልደራስ አይደልም:: ከፌደራሉ እና ክልሉ ፀጥታ እና ደህንንት የተወሰኑ አባላት እንጂ ከተራ ሰዎች አይደልም ልሆንም አይችልም:: ስለዚህ የአማራ ክልል በለስልጣናት እና ጀነራሉ ግድያ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ እና የተሰወነ ቡዱን እና ፓርቲ ለማዳከም የተወሰደ እርምጃ ይመስላል:: ግቡም


  1. ኦዴፓ እንደሰብው ተሰክቶለታል:: ከጠቅላይ ሚነስተሩ ጀመሮ መከለከያ (አቶ ለማ) ምክትል እታማጆር ሸም እና ኦሬሽን አዛዥ (ጀነራል ብርሃኑ ጁላ) አየር ሃይል አዛዥ (ጀነራል ይልማ መርዳሳ) የደህንት ሃለፊ (አቶ ደምመላሽ) እስከ የኢንሳ ሃለፍነት ቦታዎች ሙሉበሙሉ ተቆጠጥረዋል:: ቀጥሎም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ቦታዎች የሚባሉት የአገር ውስጥ ገቢ ጉምርክ ጨምረው; ግብርና; ዉሃ መስኖ እና መብራት ሃይል; ኢንዱስትሩ ፓርኮች; ኢዲሰ አባባ አስተዳድር ወዘተ ተቆጠጥረዋል:: ስለዚህ የምን ምርጫ ነው!! ያለተቀናቃኝ ማለት እንደዚህ ነው!! (በግሌ የመከለከያ ምክትል እታማጆር ሽሙ እና ኦፕሬሽን ሓለፊው ከዚህ ደም ንፁህ እና በቅንንት የሚገለግሉ ይመስለኛል ለደነቁም ይገባል)

የጦር ሃይሎች መከለከያ አታማጆር ሸም መሆን በአሁነ ሰአት ፕሬዝዳነሻል ወይ ሲምቦለ መሁን ነው ምክንያቱ ዋናው የደህንት ሓላፊ አቶ ደምመላሽ መከላከያ ሚነስተሩ አቶ ለማ ምክትል እታማጆር ሽሙ እና ኦፕሬሽን ሓለፊው ከአንድ የአየር ሃይል አዛዥ ምርጫ ቦርድ ሰብሰቢ ጠቅላይ ሚንስተሩ ወዘተ ቁልፈ ቁልፍ ቦታዋች የአንድ ፓርቲ ወይ ብሄር አባላት ሰለሆኑ የመወሰን አቅም የለውም::

  1. ሁተኛው ድል ለአቶ ደመቀ እና ጥቂት የወሎ ቡድኖች ነው ::የአዴፓ ተቀናቃኝ አብን እና የአዲስ አባባ ተቀናቃኝ ባልደራስ በማስወገድ ወይ በማዳከም አዴፓ በአብን የተወሰደበት የህዝብ ድጋፍ ለማስመለስ ወይ ልክ እንደ አብን የአማራ ህዝብ ቁስል በመቀስቀስ (መግልጫው ድሮ አብን ሲለው የነበረ ነውና) መልሶ ከአብን ለመንጠቅ ነው የተደረገ ውሳኔ ነው ለዚህም ለግዜው የተሳካ ይመስላል ምክንያቱ በአሁኑ ሰአት አዴፓ እና አብን በመርህ ደረጃ ምንም ልዩነት የላቸውም (ድሮም ወስጥ ለስጥ የነበረ ቢሆን) ለዘህም የበቁት ዶር አምባቸውን እና ጀነራል አሳምነው የመስዋእት በግ በማድረግ ነው:: ይህንንም ከቲም ለማ የተሰጠ ስጦታ ነው እነ ደመቀ በስልጣን እንድቆዩ::

አብን እና ባልደራስ በማዳከም እና በመበታተን ለሚቀጥለው ምርጫ መንግድ ለመጥረግ ሲሆን እግረ መንገዱም ህወሃት; ኦነግ; አፌኮ አባላት በማሰር በተወሰነ ደረጃ ለማዳክ የተዘየደ ሴራ ይመስለኛል:: በሁሉም መስክ ግቡ ግን በሚቀጥለው ምርጫ እንደ ደሮ እህአደግ ማሸነፍ እና ኦዴፓ የበላይነት ማረጋገጥ ነው::

  1. በላ ተራው ደግሞ ኢዜማ ይመስለኛል በተለይ ምርጫ ሲቃርብ

ሰላም ለሁሉም

 


Back to Front Page