Back to Front Page

ትዋጣታለህ !!!

ትዋጣታለህ !!!

በቁምህ የሚወጡህ ... አውሬዎች መጥተዋል
ሊያከስሙህ .. ያንሰፈሰፉ ...
ሊያፍኑህ ... ሌትተቀን የሚለፉ
መብትህን ... የሚገፉ
ሸጠውህ ... ሊያተርፉ
በልጽገው ... ሊያደኸዩህ
የኔ ያልካቸው ... ሊሸጡህ
የመረጥካቸው ... ሊክዱህ
ሊዋሹህ ... ሊንቁህ
ከጀዘብክ ... ካንቀላፋህ
የቤት ስራህን ... ካልሰራህ ...
የመቐለ ብቻ... ስብሰባ
ወሬና ፉከራ ... ድጋፍና ጭብጨባ
ካልተደገፈ ... በስራ ...
አረፋነው ... አይያዝም
አቧራነው ... ቧየሚል

ይልቅስ ...
በደላላዎች ... ሳትቀደም
በከሀዲዎች ...
ጮሌና... ጩልሌዎች
ሳትወድም ... ሳትከስም
ሳትሟሽሽ ... ሳትጠፋም
ቀድመህ ... በላቸው አይሆንም
ሩጥ ... ሳትቀደም

ቀርበዋል ... ፊትህ ቆመዋል
ስታንኳኳ ... ልጅህን ቀብረህ
ሰታነባ ... ደምህን ጠርገህ
ሲያባርሩህ ... ሲያዋርዱህ
ስትማጸን ... ሰላም አጣሁ ብለህ
የሳቁብህ ... ያፌዙብህ
የሰላም ሚንስተር ... የሾሙልህ

በስብእናህ ሳይሆን ...
በውሻ ... የመሰሉህ
አጥንት... ወርውረውልህ
ድሀነውና ...
ይጣላል ... ሲልሊበላ
... ብለውየናቁህ
ከኋላህመጥተው ...
አዘናግተው ... ሊቀራመቱህ
ሊያደቁህ ... ሊፈጩህ
ሊሰባብሩህ ... ሊያጠፉህ
ወደህ ሳይሆን ... በግድህ
ጠይቀውህ ሳይሆን ... ያለምርጫህ
አንድህ ሳትቀር .... እያንዳንድህ
አውሬው ሀይል ... መጥቷሀል
ሊቀብርህ ... በርህን ያንኳኳል።

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

12-4-19

 

Videos From Around The World


Back to Front Page