የጉሙዝ እናት
ኧረ ለመሆኑ ማን
ደረሰልሽ
ማንስ ከለላ ማንስ
ጠበቃ
አዛኝ ተቆርቋሪ
አሳቢ ተቋዳሺ
አጋር ማን ሆነልሽ?
አገኘሽ ወይ አልቃሽ
እጅሽን የያዘሽ
አይዞሽ እናትዬ
አይዞሽ እህትዬ
ብሎ ያላቀሰሽ
ኧረ ለመሆኑ በወጉስ
አለቀሽ?
አይተሽው በማታቂው
በዘመናዊዉ መሳሪያ
እነ ፈኖ ጎበዜ
ልቅም ሲያረጉሽ
ልጅሽን እቅፍሽን
እናትሽን ወንድምሽን
አባት ዘመድሽን
ጎጆሽን ባልሽን
ቅንጥስ ሲያረጉልሽ
ኧረ ለመሆኑ ማን
ደረሰልሽ?
በአንድ ደቂቃ
በፍጥነት በቅስበት
በእነ ጎበዜ አለቃ
በእነ ፋኖ ሰራዊት
በ ክልል መሪዎች
ድጋፍና ትብብር
በጥይት እሩምታ
ሲለቃቅሙሽ
ሲቀባበሉሽ
ጭርስ ሲያረጉሽ
ኧር ለመሆኑ ማን
ደረሰልሽ?
ኧረ ጭሆትሽን
ከሩቅ ይሁን ካጠገብ
ኧረ ለመሆኑ ማን
ደረሰልሽ?
ኧረ ይኖር ይሆን
ወይ
ይህንን ጭካኔ
ይሄን አረመኔነት
ይህንን ግድያ
የዘገበልሽ?
ትንሿን ሩዋንዳን
በቀይሽ በደጅሽ
በክልል በቦታሽ
ሲያከናውኑብሽ
Human Rights
Wrong Rright
ወዘተርፈ ወዘተርፈ
ብለው ራሳቸውን
የሚጠረትስ?
አገር በቀል ሚዲያ
ቴሌቭዥን ራዲዮ
ጋዜጣ መጽሄት
የተባሉትስ?
ዘገቡ ጻፉ ወይ
ይሄንን ጭካኔ
ይሄንን ጭፍጨፋ
ይሄን አረመኔነት
?
ዶ/ርዬ መሪዬ
ፎቶውን በከናቴራ
አንግበሽ የያዥውስ
?
መሞት መኖርሽን
ብሎም መፈጠርሽን
ያውቅስ ይመስልሽ
ኧረ ለመሆኑ ማን
ደረሰልሽ ?
ኢዮብ ከጮማ እምኒ
5-6-19