አንምበረከክም
!!!
መንገዱን ሲዘጉት ... አላጎበደድንም
እነሱ እንዳሰቡት ... በረሀብ
አልሞትንም
ክብሪት ሲለኩሱ .... አልተቀጣጠልንም
ሲጎናንጡን ... አልተነቃነቅንም
ሲያፈናቅሉን ... መልስ አልሰጠንም
በ ድንጋይ ሲወግሩን ... አልተበቀልንም
ሬሳ ሲልኩልን ... ሬሳ አልሸኘንም
በወንጀል ሲፈርጁን ... አውቀን
እንደ ካዱን
ስም ሲለጥፉብን .... አንገት
ያልሰበርን
ያልተሰናከልን ... ያልተሰባበርን
ሲቀናንሱን ... የ በረካከትን
ሴራ ሲሸርቡ ... ጠንቅቀን
ያወቅን
ባንዳን ሲቀልቡ ... አምርረን
ያዘንን
ሲሸነጋግሉን ... ተንኮሉ
የገባን
ሲፎክሩ ፣ ሲያቅራሩ ... ለነሱ
ያፈርን
ድግስ ሲደግሱ ... ያልተቋደስን
በእስክሪብቶ ሲጽፉ ... በ
ደም ያስረገጥን
ማንበብ ሳይጀምሩ ... አንበብበን
የጨርስን
ሲሞካካሹ ... ሚስጥሩ የገባን
ጄኔራሎቻችንን ሲያስገድሉ
... ላኪውን ያወቅን
እኛ...
የማንበረከክ ... የማናጎበድድ
እኛ ...
የትግራይ ህዝብ ነን ... ጠንቅቀው
ይወቁን ።
ኢዮብ ከ ጮማ እምኒ
10-21-19