Back to Front Page

የለማ እና የአብይ ፍቅር እስከ መቃብር ጉዞ!

የለማ እና የአብይ ፍቅር እስከ መቃብር ጉዞ!

 

አልማዝ በዳኔ 10-06-19

ከፍንፍኔ

 

መግብያ

አገራችን ኢትዮጵያ ለወጥ በተባለው የነውጥ ጎደና ከነጎደች ሁለት አመት ሊሞላት ነው፡፡ የለውጡ የመጨረሻ ዋዜማም የተደረሰ ይመስላል፡፡ የለውጡ ቲም ላይመለስ ተፈረካክሳል፡፡ ተደማሪውም በቡዱንም በግልም ተቀንሶ ተቀንሶ አልΜል፡፡ ዛሬ ግን ስለ አመራሩ ብቻ ማትኮር ፈለኩኝ፡፡ ነገሩ ሁላችንም የምናቀው ነው፡፡ በለማና በአብይ መራራቅ ከተፈጠረ ቆይቷል። የአገራችን ሁኔታ በግለሰቦች ይወሰን ይመስል አሁን አሁን ሁሉም ሰው በግለሰቦቹ ላይ ተንተርሶ ትንታኔ ሲሰጥ እያየን ነው። በሁለቱም መካካል አባዱላ ሊያስታርቁ መከራቸውን አይተዋል። የፈረንጆች ደላላዎቹ እነጁሃር መላምት በመስራት ተወጥረዋል።

 

ለምን? ለሚለው የሚከተሉት ስድስት ነጠቦች እንያቸውና ሁኔታውን እንረዳለን፡

አንደኛ፡ - ቲም ለማ በሚለው እንቅስቃሴ ውስጥ በነበሩት አባላት መካከል ስድስት ኪሎ በሚገኘው በኦህዴድ ፅ/ቤት የተዋዋሉት ውል ኮ/ል አብይን ስልጣን ላይ አወጣው። በአገር ውስጥም በውጭም ምክንቱ ያልታወቀ ቡዙ ፈንጠዝ ታየ፡፡ የተሰፋ መናዋች ተሰበኩ፡፡ ነገር ግን የጫጉላ ሽርሽሩ እየተገባደደ ከህልም ዓለሙ (ከቢሆን ዓለም) ወደ ውጣ ውረድ ወደ በዛበት እውነተኛዋ ዓለም ሲገባ ከብዙ የአገራችን ችግሮች ጋር መፋጠጥ መጣ። ይህን ሲያይ በዙ የተባለለት ቲም መንጠባጠብ ጀመረ፡፡

Videos From Around The World

 

ቲም ለማ የተባሉት አሁን የት አሉ?  ሁለቱን (ለማንና አብይን) ሰው አደረኩዋቸው የሚለው ወርቅነህ (ገበየሁ?) አሁን የት አለ? አይታወቅም። ተጣለ። አብይ በመጀመርያ ላይ ሲያሞካሸው የነበረውን ደመቀ መኮነን አሁን ‘ዝፍዝፉ ነው፡፡ ምንም ሊያግዘኝ አይችልም’፣ ‘ሰው አይደለም፣ ሰው ቆጥራቸሁት ነው’ እያለ ያመዋል። ይቦጭቀዋል። በተመሳሳይ ገዱን በተመስገን ጥሩነህ ተክቶ አሁን አሁን እምብዛም የቲም ለማ አባል መሆኑም ከተረሳና ከተተወ ቆይቷል። መጨረሻ በለማና በአብይ ልዩነት ተፈጥሯል ሲባል ቆይቶ አሁን ገሀድ እየሆነ ነው።

 

ሁለተኛ፡- በቅርብ ከተካሄደው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ በኃላ ኮ/ል አብይ ለማን ለማቅረብ ቢሞክርም አልተሳካላትም። ለማ ወደ አሩሲ ተከትሎት መሄዱ በቲቪ ብናያቸውም ከሚድያ ፍጆታ ውጭ ፍቅራቸው ተመልሶ ሊመጣ አልቻለም። ሱዳን አብረው ቢሄዱም እንደተባለው ፍቅር እስከ መቃብር ሊሆን አልቻለም።

 

ሦስተኛ፡- ለማ በተለያዩ የድርጅቱ የስልጣን ደረጃዎች ሰብሰባዎች እንዲካሄዱ ቢጎተግትም አልተሳካም፡፡ ለምሳሌ የኦህዴድ ማ/ኮሚቴ እንዲሰበሰብ አብይ አይፈለግም። ለማ ደግሞ ይፈልጋል። ለማ የኦህዴድ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ጥራና ሰብስበን  ልዩነታችንም እንነጋገር ቢለውም ጥያቄው በይዋል ይደር አብይ ፍቃደኛ ሊሆን አልቻለም። በዚህ የተናደደው የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበሩ ለማ መገርሳ ጥያቄውን የሚመልስ ሲያጣ ማ/ኮሚቴውን ሰብስቦ የእሱና የአብይ ልዩነታቸው  ዘረገፎ በዝርዝር አስረዳ። የሱን (የአብይን ማለቱ ነው) ሃሳብ ደግሞ ጠርታቹህ ስሙና የፈለጋቹሁትን ትክክል ያላቹሁትን ሃሳብ መወሰን ትችላላቹህ በማለት ገለፀላቸው። ይህ የለማ ግልፅ ውይይት ኦዴፓዎችን አማልሏቸዋል። እንዲነሳሱም አድርጋቸዋል። ተፈጥሮ የቆየውን የፍርሓት ዳመና በኖ እንዲጠፋ አድርጋል። በዚህም ኦዴፓ የለማ ወይስ የአብይ? አስብላል፡፡

 

አራተኛ፡- ባለፈው ግዜ የኦሮሚያ የተለያዩ ድርጅቶች አዳማ ላይ ባካሄዱት ስብሰባ ኦዴፓን ቢጠሩ ኦዴፓ ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ብቻቸውን ተሰብስቡ፡፡ አገሪቱ ላይ ያንዣበበው አደጋና የኦሮሚያ ህዝብ በአብይ መንግስት እየደረሰበት ያለው ግፍ መፍትሔ እንዲበጅበት ተማፅነውም መግለጫ ሰጡ። በቅርቡ በተካሄደው ስብሰባና የስምምነት ፊሪማ ደግሞ እነዚህ የኦሮሚያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሊቀመበናብርቶቻቸው አማካኝነት ሲፈራረሙ ኦዴፓ ግን በምክትል ሊቀመንበር ለማ መገርሳ ተወክሎ ሲፈራረም አየን። አብይ አህመድ ከውጭ በኃላ የገቡ እና ሁኔታው ደስ ያላላቸው በሚመስል ሁኔታ በስፍራው ተገኝተዋል። አብይ መደመር ብለው ኢህአዴግን ወደ ውህድ ፓርቲ ሊቀይሩ እየተሯሯጡ በሚገኙበት ወቅት ፈርሶ የሚወሃደውን ኦዴፓ ከሌሎች የኦሮሚያ ድርጅቶች እንዴት እየተዋሃደ እንዳለ ግራ ተጋብቶ እያየ የነበረ ይመስላል። ታድያ ከነዚህ የኦሮምያ ድርጅቶች ጋር ህብረት የፈጠረው ለማ ወይስ አብይ?

 

አምስተኛ፡- የመከላከያ ሰራዊታችን ከ’ለውጡ’ በኃላ የይሆናል ጠላት ማን እንደሆነ፣ ለምን ዓይነት ጦርነት እንደሚዘጋጅ፣ በምን ዶክትሪን፣ ህገ መንግስቱንና ፌደራል ስርዓቱን በመጠበቅ የህዝቦችና የአገራችን ላዕላዊነት እንዴት እውን ማድረግ እንዳለበት፣ የአገር ውስጥ ችግሮች ለመቅረፍ እንዴትና በየትኛው ህግ መሳተፍ እንዳለበት የተለያዩ መመርያዎች እየተሰጠው፣ ከህዝቦች ጋር እንዲጋጭና ውስጣዊ አንድነቱ እንዲፈርስ ጥረት ቢደረግበትም እስካሁን እንደምንም ብሎ ሲΜΜም ቆይቷል።

 

ኮ/ል አብይ ‘ህገመንግስት የመጠበቅ ስራ እናንተን አይመለከትም የመንግስት ስራ ነው፣ የናንተ ስራ ዳር ደምበር መጠበቅ ብቻ ነው’’ ብሏቸዋል። በዚህም ጀነራል ሰዓረ መኮንን (ነብሳቸው ይማርን) እና ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ቅሬታ አሳድረው ነበር። በሚሊንዮም አደራሽ የጀነራል ሰዓረና የጀነራል ገዛኢ አበራ የስንብት ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ‘ህገ መንግስቱን መጠበቅ ግዴታችን ነው’ ሲሉ የሰራዊቱን የተከፋ ስሜት እንዴት እንደቀሰቀሱት መረዳት ይቻላል።

 

በተመሳሳይም ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ከሰዓት የመከላከያ ሰራዊት ዓመታዊ ግምገማና ዕቅድ ለማየት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ተሰብስበው ነበር፡፡ አቶ ለማም በስብሰባው ባደረገው የማጠቃለያ ንግግር የአፍሪቃ ቀንድ ሁኔታና የአገራችን አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር። አቶ ለማ ለተሰብሳቢዎቹ እናንተ ህገ መንግስትና ፌደራል ስርዓቱን በመጠበቅ ነው የኢትዮጵያን ህዝቦች ላዕላዊነት ማስጠበቅ ያለባቹሁ አሉ። እስካሁን በተለይም ያለፉት ሁለት ዓመታት ይህቺ አገራችን ከመፈራረስ አድናቹህ ያቆያችሀት እናንተ በከፈላቹሁት መስዋዕትነት ነው። የውጭ ጥቃት ከኤርትራ ሊገጥመን ይችላል ዝግታቹሁን አጠናክሩ ሲሉ ሰራዊቱ በስሜት አጨበጨበ። ይህ ንግግር በሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ መነቃቃት መፍጠሩን ግልፅ ነበር። መሪ አለን ለካ! የሚል ስሜት በአዛዦችም በሰራዊቱም ላይ ተንፀባርΜል።

 

የሚገርመው ደግሞ እነዚያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሌላ ስብሰባ በዚያው ቀን ማታ በኮ/ል አብይ መጣራታቸው ነው። ከሐሙስ ጀምረው ጠበቁ። ሰኞ ጥዋት ሁለት ተኩል ላይ ሂልተን ሆቴል አደራሽ ተቀጠሩ። ሁሉም ተሰብሳቢዎች በሰዓቱ በቦታው ቢገኙም ኮ/ል አብይ የመጡት አራት ተኩል ነበር። ስብሰባው ተጀመረ። አብይ ስለ መደመር ዶሰኮረ። ማንም ያዳመጠው አልነበረም። ሰለቱሪዝም፣ ስለ በብሊዮን ዶላር የሚገመት ማግኘቱ . . . ወዘተ ቀባጠረ። ማንም አልሰማውም፡፡

 

ቀጠለና ’ከዚህ በፊት ህገ መንግስቱ የመጠበቅ ግዳጅ የላቹሁም ያልኩኝ አድርጋቹህ የገባቹህ አለ እንደዛ ከገባቹህ ይቅርታ እጠይቃለሁ’ አለ ማንም ሳይጠይቀው። በሰብሰባው መሃልም አንደ ነገር ተከሰተ፡፡ ለማ መገርሳ ዘግይቶ በስብሰባው ቦታ ደርሶ ወደ አዳራሹ ሲገባ የአብይ አህመድ ፊት ሲቀየር ሁሉ ታዘበ። ለማ ከገባ በኃላ ኮ/ሉ ያደረገው ንግግር ለዛው የጠፋበትና ራሱም ምን እንደተናገረ መልሶ የሚያውቀው አይመስልም ነበር። ስብሰባው እንደጨረሰ ደግሞ ከመድረኩ ወርዶ ለሁሉም  እየጨበጠ እያለ ለማ መገርሳ አደራሹን ጥሎ ሄደዋል። ተሰብሳቢዎችም ምሳ በሂልተን ሆቴል በአብይ አህመድ ተጋበዙ። ታድያ መከላከያስ የለማ መገርሳ ወይስ የአብይ አህመድ?

 

ስድስተኛና የመጨረሻ፡- ‘አብይ ይውረድ!’፣ ‘አብይ መውረድ አለበት እና የመሳሰሉ አገላለፆች በብዛት እየተሰሙ ናቸው። የአብዛኛው የኦሮሞ ህዝብና ሊሂቃን መፈክሮችም ሁኗል። ሌሎች ህዝቦችም አብይን ከጠሉ ቆይተዋል። በተመሳሳይም ‘አብይ ይውረድ!’ እያሉ ናቸው በተለያዩ ሚዲያዎች፡፡ ከኢሣት በስተቀር። እኔም በአብይ አህመድ ተስፋ ከቆረጥኩ ቆይቻለሁ። ሰለሆነም አብይ ከስልጣኑ ኢሣትም ከአየር አብረው ይወረዱ። አገራችን ከመበታታንዋና ህዝባችን ወደከፋ ሁኔታ ከመግባቱ በፊት አብይ አሁኑኑ ይውረድ!

 

አቶ  ለማ የአብይና የመሰሎቹ ሁኔታ ከተረዳ ምን ያድርግ? መልእክቴ ግልፅና የማያሻማ ነው፡፡ ኦዴፓ ሆይ ሙክታርን እንዳደረጋቹሁት አብይንም ጥግ አስይዙትና ኢህአዴግም እናንተን ተከትሎ ጥጉን ያስይዘው። ኦሮሚያ መች መሃን ሆነችና? ነገር ግን የውጭ እጅ እንዳይኖር እንድትጠነቀቁ በፁኑ አሳስባለሁኝ። ሃይልና ብራቸውን ይዘው ገደል ይግቡ! እነሱ የመረጡልንማ አየንው‘ኮ?

ቸር ሰንብቱ


Back to Front Page