|
ዶ/ር ደብረፅዩን ገ/ሚካኤል ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ያደረጉት ቃለ ምልልስ ክፍል ሁለት በየአካባቢው የሚፈጠረው ግጭትና የሰላም ዕጦት መንስኤው ምን ይመስልዎታል? ህዝቡ እራሱ የሚበላሸው መሪ ስላጣ ነው፡፡ ህዝቡ የሚመራው ነው የሚፈልገው፡፡ የአመራር ጉድለት የዶ/ር ዐቢይ የግሉ ነው ብዬ አልወስደውም። የጋራ ጉድለት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ወደ እራሳችን የምንቀስር ባይሆንም የዶ/ር ዐቢይም ሆነ የሌላው ችግር፣ የእኛም ችግር አድርገን ነው የምንወስደው፤ ምክንያቱም እኛም ኢህአዴጐች ነን፡፡ ድርጅቱ መብሠል አለበት፤ በሚከሰቱ ችግሮች ላይ እኛም ድርሻ አለን፡፡ የግሉ ችግር ግን የግል ነው፡፡ እኔም የራሴ ድርሻ አለኝ፤ እንደዚህ አበላሽቻለሁ እላለሁ። በክልልም እኛም አበላሽተናል ብለናል፡፡ ሌላውም የድርሻውን ጥፋት አምኖ ወስዶ፣ ችግሩን በጋራ መፍታት ያስፈልጋል፡፡ በየአካባቢያችን የሚፈታ ከሆነ ደግሞ በአካባቢያችን መፍታት ነው፡፡ ህወሓት የራሱን የአካባቢውን እየፈታ ነው፡፡ ለዚህ ነው ሠላም የሰፈነው፡፡
እርስዎ በቅርቡ “ህገ-መንግስቱ ሲጣስ ዝም ብለን አናይም፤ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡ ምን ዓይነት እርምጃ? ህገ-መንግስቱ ከተጣሰ፣ አንድ ላይ ድምፃችንን ማሠማት አለብን፡፡ ከዛ አልፈን ደግሞ የተለያዩ መድረኮች አሉ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ማለት ነው። በመድረኮቹ ይሄንን ሃሳባችንን እናራምድበታለን። ምክንያቱም የፖለቲካ ችግር ስለሆነ በፖለቲካ መከላከል አለብን፡፡ ለምሳሌ ከትግራይ ተወክለው ፓርላማ ያሉ በአደባባይ ነው እየተቃወሙ ያሉት። እርምጃ እንወስዳለን ስንል በመተኮስ አይደለም። አቋማችንን እንገልፃለን፤ መድረኮች በስፋት እንፈጥራለን ማለታችን ነው፡፡ ዝም ብሎ በድርጅት ብቻ የታጠረ አይሆንም፤ መውጣት አለበት፤ ታፍኖ መቅረት የለበትም፡፡ የህግ ጥሰት አለ ብለን ዝም ብለን ልንቀመጥ አንችልም፤ በአደባባይ፣ በሚዲያ፣ በተወካዮች ም/ቤት፣ በፌዴሬሽን ም/ቤት መድረኮች፣ መፍጠርና ያለማቋረጥ መናገር፣ ህዝቡንም ማሳተፍ፣ ጉዳዩ ግልጽ እንዲሆንለት ማድረግ ማለት ነው፡፡ አንዱ ጉዳይ የድንበር ኮሚሽን ነው፤ ህገመንግስቱን የጣሰ ነው ብለናል፡፡ ፖለቲካዊ ትግል ነው የምናደርገው፡፡ የተቃዋሚ ድርጅቶችን እያመጣን አቋም እንዲወስዱ፣ እነሱም እንዲቃወሙ እያደረግን ነው፤ የእኛ ብቻ አይደለም፤ የትግራይ ብቻ የሚባል ህገመንግስት የለም፡፡ የአገሪቱ ነው፡፡ አንዳንዱ ድፍረት ስላጣ ነው እንጂ ህገመንግስቱ መጣሱን ያውቀዋል፡፡ መድፈር አለበት ነው የምንለው፤ እኛ የተለየ ነገር የለንም፤ አቋማችን ጠንካራ ሊሆን ይችላል፡፡ የትግራይ ህገመንግስት በትግራይ ነው ያለው፡፡ የፌደራል የሁሉም ገዢ ስለሆነ፣ ሲጣስ ዝም አንልም ያልነው፡፡ የድንበር ኮሚሽኑን ለምንድን ነው የተቃዋማችሁት? አንዳንዱ የራያ እና የወልቃይት ጉዳይ ስለተነሳ፣ የድንበር ኮሚሽኑ፤ እኛን የሚጐዳ ይመስለዋል። እዛ ላይ ችግር የለብንም፤ በህዝቡ ውሳኔ መገመት እንችላለን፤ ህዝቡ ምን እንደሚወስን ብዙ የምንጠራጠረው ነገር የለም፡፡ እኛ ህገመንግስቱ ተጣሰ ያልነው፣ ስለ ራያ እና ወልቃይት ለመከላከል አይደለም፡፡ ድሮም በደርግ ጊዜ ትግሬ የሚባል ነበር፤ አፋር የሚባል ግን አልነበረም፤ ቤንሻንጉል የሚባል አልነበረም፣ ጋምቤላ አልነበረም፣ ኦሮሞም፣ አማራም አልነበረም፤ ወሎ፣ ጐጃም እየተባለ ተበታትኖ የነበረ ነው፡፡ ይሄ አንድ አስተሳሰብ፣ ቋንቋ ያለው ህብረተሰብ በአንድ የመደራጀት ውጤት ነው፡፡ እና ይሄ ወሰን የሚባለው ሁሉንም ነው የሚያፈራርሰው፤ የፌደራል ስርአቱን ያፈርሰዋል፡፡ የድንበር ኮሚሽኑ በዚህ ጉዳይ እጁን ማስገባት የለበትም፡፡ ማፍረስ ካለበት ህዝቡ ነው ማፍረስ ያለበት፡፡ ማንም አዋቂ ነኝ የሚል፣ ማንም መሪ ነኝ የሚል መጥቶ፣ ተደራጅቶ ሊወስን አይችልም፡፡ “አንተ ማንነትህ ይሄ ነው” የሚል ሌላ ወገን መግባት የለበትም፡፡ ራሱ ህዝቡ ነው መወሰን ያለበት፤ ያንን ነው ከህገመንግስት ስርአት የወጣ ነው ያልነው፡፡
በሚዲያ ከመወቃቀስና ቃላት ከመወራወር፣ ችግሮችን በውይይት መፍታት አይሻልም? በንግግር እናምናለን፤ የእኛም ፍላጐት ነው፤ ግን ከአንድ ወገን ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ ሁሉም አምኖበት እስኪስተካከል ድረስ አሁን ባለንበት መንገድ እንቀጥላለን፡፡ ከሁሉም በፊት መተማመን ያስፈልጋል፤ ወደ መተማመን መመለስ የግድ ነው። ችግሮች የጋራ ናቸው፤ መፍትሔውም በጋራ ነው የሚመጣው የሚል አስተሳሰብ መኖር አለበት፡፡ ይሄ አስተሳሰብ ካልተቀየረ ችግሮች ይቀጥላሉ፡፡ አንድ ቦታ ላይ ወይ ይፈታሉ ወይ የባሰ ነገር መምጣቱ አይቀርም፡፡ ተገናኝተን ስንወያይ እኮ እንጠይቃለን፤ ለምን ይሄ ይባላል ብለን እንጠይቃለን፡፡ ግለሰቦች እንኳን ትላንት እንደዚህ ተባብለን፣ ዛሬ ካድከኝ ይባባላሉ፡፡ ትዝብት ላይ ይጥላል፣ ትላንት የተግባባንበትን አፍርሶ ሌላ ሲባል፣ እንደ ፖለቲከኛ በጣም ጥፋት ነው፤እንደ ሰው አሳፋሪ ነው፡፡ አቋም መያዝ አለበት፡፡
የናንተ እሠጣ ገባ ህዝብ ላይ ተፅዕኖ አያሳድርም? በፖለቲካ መብሰል፣ መመካከር ይጠይቃል፡፡ ማንም ሰው የሚናገረውን ነገር መጠንቀቅ አለበት፡፡ ህዝብን የሚነካ ይቅርና ግለሰብን መንካት የለበትም። የጠፋ ነገር ካለ ይሄ ጠፍቷል ተብሎ መመካከር ነው የሚያስፈልገው፤ መካሰስ ከሆነ ሌላ ጉዳይ ነው። መመካከር ከሆነ ግን በመጐዳዳት አይደለም፡፡ “የቀን ጅብ” የተባለው ደቡብ ላይ ነበር፤ በመጀመሪያ ተነጋግረንበታል፤ በመጨረሻ ግን ለትግይ ህዝብ ነው የሆነው፡፡ “ፀጉረ ልውጥ” የሚለውም ፖለቲካዊ ጉዳት አለው፤ እኔን በግል ብትጠይቂኝ ግን ምንም አይሠማኝም፡፡ ይሄ በአጠቃላይ የአመራር ብቃት ችግር እንዳለ የሚያሳይ ነው፤ ችግር ካለ መድረኮች አሉ፤ እኛ ያንን ተከትሎ ሌላ ነገር ብንናገር ህዝቡን ነው የምናርቀው፡፡ አመራር ከህዝቡ ጋር አብሮ ተመካክሮ መሄድ ሲገባው፣ በራሱ ብቻ ሲሄድ ይሳሳታል፡፡ ሰው አይሳሳትም አይደለም፡፡ ግን ሲደጋገም ደግሞ፣ በተለያዩ መልኮች ሲገለፅ፣ ወደ አንድ አቅጣጫ መሄዱ መቆም አለበት፡፡ ችግሩ ይቀጥላል ብለን አናምንም፡፡ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፤ ክልሉ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለም ብሏል፡፡ ፍቃደኛ ያልሆናችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? እኛ ፍቃደኞች ነን፡፡ ጄኔራል ክንፈ እኮ ከእኛ ክልል ነው የሄደው - ተጠርጣሪ ነው፡፡ አስረክቡን አሉን አስረከብን፡፡ ሌሎችም ተጠርጣሪዎች አሉ፤ ስማቸው የተላከ፡፡ ግን በእሱ ነው የተጀመረው፡፡ ከተያዘ በኋላ በሚዲያ ሌላ ነገር እንደሆነ ነው የገባን፤ እኛ ነን በሠላም ያስረክብነው፡፡ በካቴና ማሠር፣ በአደባባይ በቴሌቪዥን ማሳየት፣ ዶክመንተሪ ማቅረብ ሲመጣ የተዘጋጀ ነገር እንዳለ ያሳያል፡፡ ይሄ ደግሞ በራሳቸው መፍረድ ጀመሩ ማለት ነው፡፡ ህግን ጠብቆ መስራት ሳይሆን የፖለቲካ አካሄድ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ተጠርጣሪማ ተይዞ ፍ/ቤት ነው መቅረብ ያለበት፡፡ የሆነው ግን ወደ ፍ/ቤት ሳይሆን ወደ ሚዲያ ነው፡፡ እንደዚህ ከሆነ ደግሞ ፍትህ የለም ማለት ነው፡፡ ተጠርጣሪ በፌደራል ብቻ ሳይሆን በእኛም ክልል ቢፈለግ፣ አንለቅም፤ ግን ይሄኛው ፖለቲካዊ አካሄድ ነው፡፡ ዶክመንተሪውን አይተሽው ይሆናል፤ ሄዶ ሄዶ “ትግሬ እንዲህ አደረገ” እየተባለ፣ ጠቅላላ ትግሬ ነው የተጠላው፡፡ ይሄ ሙሉ በሙሉ ፖለቲካ ነው፡፡ “ትግሪኛ ተናጋሪ” እየተባለ ነው ሲነገር የነበረው፡፡ ይሄ ፖለቲካ ነው፡፡ ፖለቲካ ከሆነ ደግሞ መታገል ያለብን በፖለቲካ ነው፡፡ እኛም ዝም ብሎ እገሌ ተጠርጣሪ ነው ስለተባለ ብቻ የምናስረክብበት ሁኔታ የለም፡፡ ቀድሞም ጥርጣሬ አልነበረንም ማለት አይደለም፤ ለምን ከዚህ ክልል ብቻ ብለን ጠይቀን ነበር፡፡
አቃቤ ህግ የሚፈልጋቸው አቶ ጌታቸው አሠፋ፤ በክልሉ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል ይባላል … በክልሉ ምንም ስልጣን የለውም፡፡ የት እንዳለ አናውቅም፤ ተደብቋል፡፡ አቶ ጌታቸው ከቅርበታችሁ አንፃር ምን አይነት ሰው ናቸው? በስራ
ተናዳጅ፣ ተናጋሪ
ሊሆን ይችላል፤ ግን
ስርአት ጠብቆ የሚሄድ
ሰው ነው፡፡ እንደ
ግለሰብ ሊጠየቅ
ይችላል፤ 27 አመት
እንደዚህ ነበር ተብሎ
የቀረበው ግን ፈጽሞ
ውሸት ነው፡፡
የፌደራል ፖሊስንም
ሆነ፤ ማዕከላዊን
አውቀዋለሁ፡፡ ግን
የትግራይ ምርመራ
የሚባል የለም፤ ሁሉም
ብሔር ነው እዛ
ያለው፡፡ በቅርቡ በትግራይ ክልልና በአማራ ክልል መካከል የተካሄደው ሽምግልና ውጤታማ ነው ይላሉ? ችግሩ የፖለቲካ ነው፤ ተገዳችሁ ነው የገባችሁበት ነው ያልኳቸው - ሽማግሌዎቹን፡፡ እኛ እራሳችን ችግራችንን ባለመፍታታችን ህብረተሰቡም እየተጐዳ ስለሆነ፣ በሀይማኖትም በሌሎች ሽምግልና መሪዎችም፣ በቃ ሠላም ማስፈን አለባችሁ በሚል ነው የተደረገው፡፡
Back to Front Page |