Back to Front Page


Share This Article!
Share
እብሪተኛው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን)

 

እብሪተኛው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን)

 

ስማቸው አኑሎ 01-06-19

 

የዋልታ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ስሜነህ ባይፈርስ ከአቶ ክርሲቲያን ታደሰ እና በለጠ ሞላ ከተባሉ አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ በሚል መመሪያ ከዛሬ ስድስት ወራት በፊት ከተመሠረተው ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) መሪዎች ጋር ያደረገውን የመጀመሪያ ክፍል ቃለ መጠይቅ በአጋጣሚ ለመየት እድል አግኝቼ ነበረ፡፡ በቃለ መጠይቁ ወቅት ሁለቱ የንቅናቄው መሪዎች ያነሱዋቸው ነጥቦች አስተያየት መስጠት ተገቢ በመሆኑ እኔ የትኛውንም ቡድን በህጋዊ መንገድ ባልወክልም የተፈጥሮ መብቴን መጠቀም የቡድኑ አመራሮች የሚከተሉት አካሄድ ፈፅሞ አደጋኛ እንደሆነ እንዲገነዙቡ ወይም ሌሎች ህዝቦችን የሚወክሉ ቡድኖች የአብንን አደጋኛ አካሄድ በውል ተገንዝበው ተገቢውን ጥንቃቄ ከወዲሁ ማድረግ እንዲችሉ ያግዝ ይሆናል በሚል በቃለ መጠይቁ ላይ የራሴን ሀሳብ ለማንፀባረቅ ወሰንኩ፡፡

Videos From Around The World

ቅድምያ ግልፅ መሆን የሚገባው ጉዳይ አብን ሆነ ሌሎች ቡድኖች በአማራ ብሄርተኛነትን ተደረጅተው ትግል ማድረጋቸው በራሱ ምንም ጉዳት ያለውም፣ ስህተትም አይደለም፡፡ እንዲያው ብዙ ጥቅም ይኖራዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ባለፉት 27 ዓመታት አማራው በአግባቡ በብሄር ማደረጃት ባለመቻሉ ወይም የአማራነት መሠረት ያላቸው ኤልቶች አማራ በብሄራ ማደረጃት ተገቢ እንደልሆነ በመውሰዳቸው፣ ከህዝባቸው ታሪክ እና ጥቅም አንፃር በብሄር የተደረጁትን ቡድኖች አዘብተው እንደ አገር አፍራሽ፣ የኢትዮጵያ ጠለት አድረገው በመሳላቸው ቡድኖቹ የተደረጁበትን ቅዱስ ዓላማ ስኬታማ ማድረግ እንዳይችሉ አደጋች ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ አንፃር የአማራው ዴሞክራቲክ ብሄርተኘነት ለሌሎች ህዝቦች እድል እንጂ እርግማን አይደለም፡፡ ነገር ግን ችግር ወይም ጨርሶ ሲጋት ሊሆን የሚችለው የአማራውም ሆነ የሌሎች ብሄርተኝነት በሂደቱ ሆነ በተገባበሩ የሌሎችን ማንነት፣ ጥቅም፣ ታሪክ የሚጎዳ አካሄድ የሚከተል ከሆነ ብቻ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በአብን በኩል እየታዬ ያለው አዝማሚያ ለአገራችን አንድነት ብቻ ሳይሆን ለህዝቦች ሰላማዊ ግንኙነትም ጭምር እንቅፋት ሊሆን የሚችል አካሄድ ያለው በመሆኑ ችላ ሊባል የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሆኖም አሁኑ ወቅት አቢን እንቅልፍ ሊነሳን የሚችል ኃይል አይደለም፡፡

ለመሆኑ በአቢን አመራሮች በኩል በቃለ መጠየቁ ወቅት ከተነሱ ነጥቦች ውስጥ ማስተካከል ያለባቸው ወይም በመሠረቱ ስህተት የሆኑ ጉዳዮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

የመጀመሪያው አመራሮቹ በቃለ መጠይቁ ወቅት ከነሱዋቸው ጉዳዮች አንዱ ባላፉት 27 ዓመታት የነበረው ፕሮጄክት ፀራ-ኢትዮጵያ ነው፣ በኢትዮጵያ ታሪክ አይኬን በምንላቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ጣፍቷ፣የኢትዮጵያን አንድነት ከመሠረቱ ጀምሮ አናግቷዷል፣ብዙ ነገር አፍርሷል የሚል ሀሳብ የሰነዘሩ ሲሆን እንደማሳያ ያቀረቡዋቸው ነጥቦች በአድዋ ድል ስምምነት የለም፣ አፄ ምንልክ ላይ ያበረከቱዋቸው ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸው ከፍተኛ አስተዋፅዎች ላይ ስምምነት አለመኖር ብቻ ሳይሆን በሌላ ታተርጉሞ አይታናል፣ በስንዳቃ ዓለም ላይ ያሉ ንባቦች አንድ አይደሉም የሚሉ ናቸው፡፡ አንድ ነገር ማካድ የማይቻለው በላፉት 27 ዓመታት ሆነ ከዚያ በፊት አገራዊ አንድነታችን ቸግር ውስጥ ገብቶ ነበረ፡፡ አሁንም ዋስትና የለውም፣ ፀራ-ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሁኔታ አገራዊ አንድነት ጠንካራ ይሆናል ማለት ግብዝነት አልያም ድቁርና ወይም ራስን ማታለል ነው የሚሆነው፡፡ አዎን ልክ ነው ፀራ- ዴሞክራሲ ነበረ፡፡ ግን ፀራ ዴሞክራሲ በኢትዮዮጵያ ውስጥ የጀመረው ከዛሬ 27 ዓመታት በኃለ አይደለም፣ በደርግ ዘመን የከፋ ፀራ-ዴሞክራሲ ነበረ፣ በአፄዎቹ ዘመን ጫፍ የወጣ ፀራ-ዴሞክራሲ ነበረ፡፡ ለዚያውም የመደብ ጭቆና ነበረ፣ የብሄር ጭቆና ነበረ፣ የህዝቦች ማንነት፣ ባህል፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ ተጨፍልቆ ነበረ፡፡ ይህ ሁሉ ግፍ እና በደል በነበረበት ሁኔታ ባለፉት 27 ዓመታት የነበረው ፕሮጄክት አገራዊ አንድነቱን አፍርሷታል የሚል ሀሳብ ማቅረብ በራሱ ስህተት ነው፣ ሊታርም የሚገባ ነው፡፡ ማውገዝ የምገባን መርጠን ሳይሆን በመሪህ ነው ማውገዝ የሚገባን፣ የእኛ አባቶች የሰሩትን ስህተት እንዘክራለን፣ የሌሎች አባቶች የሰሩት ስህታት እንቃወማለን የሚለው አካሄድ አብሮ የሚያኖር አይደለም፣ ተገቢ የሚሆነው በታሪክ አጋጣሚ የተሰሩት ስህተቶች ተቀብሎ በማያደግም ሁኔታ የእርማት እርምጃ ወደ ፊት መሄድ የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ነው፡፡ ሌላው በአድዋ ጦርነት፣ በአፃ በምንልክ ጉዳይ እንዲሁም በባንድራ ጉዳይ አንድ አይነት አስተሳሳብ አለመኖር የአገርን አንድነት ከማፍረስ ጋር ምንም የሚያገኘው ጉዳይ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ሊቆም የሚችለው የባንድራችን ቀለም፣ ቅርፅ፣ አርማ ምን መሆን አለበት በሚለው አይደለም፣ አፄ ምንልክ፣ አፄ ኃይለስላሴ፣ ኮሎኔል መንግሥቱ ባደረጉት አስተዋፅዎች ዙሪያ ስምምት በመፍጠር ሳይሆን ፍትሃዊ አሰራር እና ተጠቃሚነት በማስፋን፣ እውነተኛ ዴሞክራሲ ስርዓት በመገንባት እና ፈጣን ልማት በማረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ በአፄ ምንልክ፣ በአድዋ ድል ባንድራ ጉዳይ ሙሉ ስምምነት ሊኖር አይችልም አይኖሩም፣ አብን በአጀንዳዎቹ ዙሪያ ስምምነት እንዲኖር ማድረግም አይችልም፣ በእነዚህ ጉዳዮች ተመሳሳይ አቋም ሊኖር ይገባል ማለት በራሱ ፀራ- ዴሞክራሲ ነው፡፡

 

ሌላው የአብን አመራሮች ሸውራራ እይታ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አነሰ ብሄሮችን በሚመለከት ያላቸው አቋም ነው፡፡ አመራሮቹ ስለአነሳ ብሄሮች ያላቸውን ንቃት ውሁዳን የሚል ስያሜ በመስጠት ገልፀዋል፡፡ ለሌሎች ህዝቦች አዋራጅ እና ክብረ-ነክ ስም መስጠት በአብን አባቶችም ዘንድ እርግጥም የተለመደ ነው፣ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ አብኖች በአግባቡ ያልገባቸው ነገር ቢኖር ምን አልባት በታሪክ አጋጣሚ በአንዳንድ ክልሎች ያሉ የተወሰኑ አነሳ ብሄረሰቦች የማወጥ አደጋ ተደቅኖባቸው ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አነሳ ብሄረሶቦች ከአንድ መቶ ዓመታት በላይ የተጨናባቸውን ሁሉንአቀፍ ጭቆና ተቋቋመው ማንነታቸውን፣ ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን ጠብቀው ለቴክኖሎጂ ዘመን አድርሰዋል፡፡ ስለዘህ አነሳዎች እንጂ ውሁዳን አይደሉም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አብን አመራሮች ያለአንዳች ፍራቻ ውሁዳን መብታቸው እና ጥቅማቸው ተከብሮላቸው ይኖራሉ የሚል በንቃት የተሞላ ሀሳም ሰጥተዋል፡፡ የአብን አመራሮች ምንም አልገባቸውም፣ ተምታቶባቸዋል የተባለው በጣም ትክክል የሆነ እይታ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ እና የነበሩ አነሳ ብሄረሰቦች መብታቸውን እና ጥቅማቸውን ተጠብቆላቸው ወይም ተከብሮላቸው ሳይሆን የራሳቸውን መብት እና ጥቅም በራሳቸው አስከብረው ነው ያኖሩት፣ ለማስከበር ሲታገሉ ነው ያኖሩት፣ ከብዙሃን ያገኙት አንዳችም ጥቅም የለም፣ ጉዳት እንጂ፣ ሌላው ቀርቶ ኮንሶ ማህበረሰብ መብቱን ያሰከበረው በትግል እንጂ በስጦታ አልነበረም፡፡ ሲጀመር አንድን ብሄር ጥቅም ማስከበርን መመሪያው አድረጎ የተመሰረተ ቡድን ስለሌሎች ጉዳይ አያገባውም፣ አይመለከተውም፡፡ የራሱን ብሄር ጥቅም የተሟላ ጥቅም ሊያረጋግጥ የሚችለው በሌሎች ብሄሮች ኪሰራ እና ጉዳት ብቻ ነው፣ አብሮ ማልማት፣ አብሮ ማደግ ፣ የጋራ ጥቅም የሚል መመሪያ ያለውም፡፡ በነገራችን ላይ ይህች 60% እና 70% ድስኩር ለመኖሪያ ቤት ፕሮግራም እንጂ ለአገር ግንባታ አትሆንም፡፡ እኛ ብዙሃን ኦሮሞና አማራ እጣ-ፋንታችሁን እንወስናለን የሚለው ስህተት ነው፣ በፖለቲካ አመለካከት ወይም አይዶሎጂ ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ፓርቲዎች ግንባር ፍጥረው ወይም አገር አቀፍ ፓርቲ በምርጫ ተወዳድረው/ተወዳድሮ አብላጫው ድምፅ ያገኙ /ያገኘ ፓርቲ መንግሥት ይሆናል፡፡ የብዙሃን አገዛዝ የአነሳዎች መብት የሚባለው ይህ ነው እንጂ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ብሄር ሁሌ መንግሥት ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ቀላል ምሳሌ፡ ጥቁር አሜሪካዊው ባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን ችለው የነበረው ጥቁሮች በአሜሪካ ብዙሃን ስለሆኑ አይደለም፡፡

ሌላው የአብን አመራሮች ከቁማታቸው በላይ የተንጠራሩበት ነጥብ ማንኛውም የኢትዮጵያ አንድነት እንዲቀጥል የሚፈልግ ኃይል እኛ(አብን) appreciate ማድረግ አለበት የሚል ቅዥት ነው፡፡ ሰዎቹ ጤናማ መሆናቸውን እግርጠኛ ቢሆኑም አንድ ከተመሰረተ ስድስት ወር ብቻ የሆነው በምርጫ ቦርድ በወጉ ያልተመዘገባ ገና እዚህ ገባ የሚባል ፕሮግራም የሌላው ቡድን ይህን ዓይነት ሀሳብ ሲቀያቀርብ ምን ማለት እንደሚቻል ፈፅሞ ግራ የሚያገባ ነው የሚሆነው፡፡ የጤንነታቸውም ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው፡፡ ስንት ማስዋእትነት የከፈሉ፣ አንቱ የተባሉ ፖለቲካኞች በሚገኙበት አገር አንድ ተግዳሮት እንኳ ያለለፈ ቡድን በዚህ ዓይነት መልኩ ሲቀርብ ተረጋጉ ከማለት ውጪ ምን ማለት ይቻላል?

የአብን አመራሮች የተወጠላቸው አምባገነን መሆናቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ በግልፅ ያሳዩበት ሌላው አቢይ ጉዳይ ህወሓት በሚመለከት የሰጡት አስተያየት ነው፡፡ ለግልፀኝነት ያህል እኔ በግሌ ህወሓትን የሚከለከልበት የተለያ ምክንያት የለኝም፣ ህወሓት ከሌሎች የኢህዴግ አባል ድርጅቶች የተለየ ጥፋት ፈፅሟል የሚል እምነትም አይኖረኝም፡፡ ከህወሓት ጋር በተያየዘ የአብን አመራሮች ሲናገሩ የሕወሓት ስም ቀርቶ ምልክቱን መጠቀም ወንጀል የሚሆንበትን ሥርዓት እንዘረጋለን የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ በአጭሩ አብን ይህን ማድረግ አይችልም፣ የአማራ ህዝብ እወክላለሁ የሚል ቡድን የትግራይን ህዝብ የሚወክለውን ቡድን ስያሜ እና መልክት እኔ እወስንልሃለሁ ማለት እብደት ነው፣ ህወሓት የትግራይ ህዝብ የሚፈልገው ፓርቲ ከሆነ እንኳን አቅመ ቢሱ አብን ቀርቶ የአሜሪካ መንግሥትም ህወሓትን ሊያጠፈው አይችልም፡፡ ይህ ምን ግዜም እውነት ነው፡፡

የአብን በኢትዮጵያ ታሪክ አፃዎቹ በሌሎች ህዝቦች ላይ የፈፀሙትን ጥፋት እንደ ቅድስና አድርጎ የሚቆጥር ቡድን በመሆኑ ብቻ ከሌሎች ኃይሎች ጋር አብሮ መሥራት የሚችልበት እድል ዝግ ነው፣ ይህ ብቻ አይደለም፣ እጅግ ሲበዛ እብሪተኛ ስለሆነ በቀላሉ ከሌሎች ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ትምክተኛነት የአንደኛ እና የሁለተኛ ዓለም ጦርነቶች በዓለም ላይ እንዲከሰቱ ምክንያት ነበረ፡፡ ትምክተኛው አብን ወደ ጦርነት እንደያስገባን ከወዲሁ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ይህን ኒው -ምንልክ ቡድን እንደህና መጣህ ብለን የምንቀበለው ሳይሆን ገና ከጅመሩ አካሄዱን እያጋለጥን የሚስተካከልበትን እድል መፍጠር አልያም ሌሎች በድኖች ይህን አደገኛ ኃይል በንቃት እንዲካተተሉ ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

Back to Front Page