Back to Front Page

አርማጌዶን ዘኢትዮጵያ፡፡

አርማጌዶን ዘኢትዮጵያ፡፡

 

ይህ ፅሁፍ በነፃ ጉተማ ፌስቡክ እየተፃፈ የሚገኝ ነው፡፡ አላለቀም፡፡ ነገር ግን አገራችን የሚትገኝብትና ተጨባጭ አደጋና ለወደፊት የተደገሰላት የጥፋት ድግስ የሚሳይ በመሆኑ በሐሳብ ልእልነት በሚያመነው በአይጋ ድረ ገፅ ቢወጣ ቡዙ ኢትጵያዊ ተገንዝበው አገራቸውን ለመታደግ ይተጋሉ ብየ አስባለሁ፡፡ የአርትኦት ስራ ብቻ ነው የተጨመረው እንጂ ፅሁፍ የነፃ ጉተማ ነው፡፡

መኮነን ነብይ፣ ከአዲስ አበባ 10-2-19

አርማጌዶ የግሪክ ቃል ነው። የተጠቀሰውም በዮሀንስ ራእይ 1616 ላይ ነው። ትርጉሙም ከፍርድ ቀን በፊት የሚደረገው የመጨረሻው ጦርነት ስፍራ ነው። ሀይማኖትን ልሰብካችሁ አይደለም። ነገር ግን የቁጣ(ቂያማ) ቀን ከመድረሱ በፊት፣ ህዝብ በህዝብ ላይ መንግስትም በመንግስት ላይ ከመዝመቱና ከመተላለቁ በፊት የጦርነቱ አባትና ባለቤት አውሬው ከተሰጡት

ነገሮች ውስጥ አንዱ የስድብ_አንደበት ምናልባት እኔ እንደሚገባኝ የስድብ_ሚድያ ነው ይለናል ባለ ራእዩ። እናም አውሬው መልካም ነገር ለመናገር፣ እውነትን ለማውራትም ሆነ ቀናን ነገር ለማድረግ ስብእናው አይፈቅድምና ይሳደባል፣ ይወርፋል፣ ያበሻቅጣል።

 

Videos From Around The World

በምድራችን የተከሰቱ የህዝብ ፍጅትንና በርካታ የአርማጌዶን_መንትዮች ብንመለከት ህዝብ ሳንጃ መዝዞ በባሩድ ከመታጠኑ በፊት የፕሮፖጋንዳ ማሽኖቹ ሚድያዎች በዙ ነገር ብለው ነበር። ለምሳሌ የናዚ ፍጅት፣ የናፖሊዮን ፍጅት፣ የአርመኖች ፍጅት፣ የስታሊን ፍጅት፣ የኤዲ አሚን ፍጅት፣ የደርግ ፍጅት፣ የሩዋንዳ ፍጅት፣ የሶሪያ ፍጅት ወዘተ ከመፈጸማቸው በፊት ሚዲያዎች እልቂቱን በጣም በሚያማልሉና ልብ በሚያቀልጡ ንግግሮች ሲያሽሞኖሙኗቸው ነበር። እነዚያ ሚዲያዎች በወቅቱ ያደረጉትን ባያደርጉ ፍጅቱ ተረት እልቂቱም ነበር በሆነ ነበር። ግን አለማችን አልታደለችም። ስልጣንን በአቋራጭ ለሚሰቀሉባት፣ መንበርን በቆረጣ ለሚጋልቡባት ህሊና ቢስ የሀይል ሚዛን አምላኪዎች ስትል ብቻ ይህች አለማችን ሚሊዮኖችን ዶግ አመድ አድርጋ ለሌላ እልቂት ትዘጋጃለች።

 

እኛ ጋርስ? እኛ ጋርስ ምን አለ? እኛ ጋርም ልክ እንዲሁ ነው። ዳቦ ተነጥቆ ቆሎ የተሰጥው፣ ጠጅ ተቀምቶ ድፍርስ ውሀ የተሰጠው ግፍና በደሉ በመቶ እጥፍ ተሰብኮለት በፍጅት ዳክሯል። በዚያው ልክ ደግሞ አሻሮ ተነጥቆ ዳቦ የታደለው፣ ድፍርስ ውሀ ተቀምቶ ወተት የተሰጠውም መጥፎውን ቀምተው ጥሩውን የሰጡህ ለአሻጥር ነው፣ ሸውደውህ ነው፣ ዘርፈውህ ነው ወዘተ ተብሎ፣ ታሪክ ተገልብጦ በፍጅት ውስጥ ተንከባሏል። በአሁኑ ሰአት በገዛ አይናችን ፊት የምናየው ይህንን ነው።

 

ሚዲያዎቻችን ምን ምን እንዳደረጉ፣ ያስተላለፏቸው ስርጭቶች አገራችንን እንዴት እንዳመሳቀለው፣ ለማይቀረው አርማጌዶን በምን ልክ እያዘጋጁን እንደሆነ በሚገባ እንመለከታለን።

 

የሊበራል አስተሳሰብ ማስረጫ ከሆኑት መንገዶች አንዱ አድሀሪነት ነው። አድሀሪነት አለምን ካጎሳቆለበት አንዱና ምናልባትም አንደኛው ሀይማቲካ ነው ሀይማኖት+ፖለቲካ ማለቴ ነው። ምእራባውያኑ አገራችንን ለማመሳቀልም የከፈቱት ትልቁ ዘመቻ የሀይማቲካ ልሳን ወይንም ሀይማኖት+ፖለቲካ+ሚድያ ነበር። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ላንሳ ድምጻችን ይሰማ፣ ኦኤምኤን፣ ኤሻዳይ ቲቪ፣ ቃና፣ መለከት አሁን እልም ያለ የፖለቲካና የሀይማኖት መሰልቀጫ የሆነው የነ_ቤቲ_ኤልቲቪ።

 

የባለስልጣኖቻችን የነፍስ አባት የሆኑት የምወዳቸው ዶክተር ቄስ ገመችስ ከሀይማቲካ ልሳኖች ውስጥ አንዱ ነበሩ። በወቅቱ የነበረው የምስጢር ፈልፋዩ ደህንነታችን የዚህን ሚድያ ተልእኮና ድብቅ አጀንዳ ደርሶበት መንግስት እንዳይከፈት አገደውና ቄሱ በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ጆሀንስበርግ ይኮበልሉና እዚያ ተገናኘን። ብዙ አወራን፣ ማንነታቸው ገባኝ። አሁን የእውቅ ፖለቲከኛ፣ ሀይማኖተኛና ሀይማቲከኛ ግለሰቦች የሀሳብ መዋኛ ገንዳ እነ_ቤቲን የመሰሉ የጋዜጠኝነት ስነልቦናና ስነ ምግባር የሌላቸው ጋዜጠኞችን በማግበስበስ ሀይማቲካ ይሰበክበታል። ጥላቻ እንደ ጉድ ይፈጭበታል። አርማጌዶን እንደጉድ ይቦካበታል። ሊበራል እንደጉድ ይደወርበታል። እስኪ ከሰሞኑን የባይቶናና የቤቲ ቆይታ የዚህችን እውቀት የለሽ ሴት ስንክሳር እንመልከት።

 

1- ራሷን እየወከለችና እያንቀሳቀሰች ያለችው እንደ ሀርድ ቶክ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ አንድ ትልቅ የጉዳይ መርማሪ (Investigator journalist) ነው። በምታንቀሳቅሳቸው ነገሮች ላይ ግን ምንም ጥልቅ እውቀትም መረጃም የላትም። አንድም ማስረጃ አታቀርብም። እከሌ አለ፣ እከሌ ነገረኝ፣ እንደዚህ ሊሆን ይችላል የሚል ተረት ብቻ ነው ትርክቷ። አብዛኛው ነጥቧም

እሷም ልክ እንደኛው ከሌላ ሚድያ የተከታተለችው ነው።

 

2- መጠየቅ የምትፈልገው መልሱን ተናግራ ያንኑ እንዲነግሯትና ጀብድ እንዲጨመርላት እንጅ ህዝብ እውነቱን አውቆ መረጃ እንዲያገኝ በማሰብ አይደለም።ይህንንም ለማሳካት አንድን ጥያቄ በተለያዩ መንገዶች በመጠየቅና ተጠያቂውን ፋታ በመንሳት ወደምትፈልገው መልስ ለማስጠጋት መከራዋን ታያለች። እንደ ክብሮም አይነት ወደ ሀሳቧ በቀላሉ የማይገባላት እንግዳ ሲያጋጥማት ያው ትግላለች።

 

3- ገለልተኛ ሆና ከእውነት ጋር መወገን አልቻለም። በዚህም የቀድሞውን የኢህአዴግ አመራር እንደ ሰውበላ የእአውሬዎች መንጋ፣ ነፍሰገዳይና የሚያሰቃይ አድርጋ መስበክና ማስተጋባት ልማዷ ነው። እናም እውነት ገደል ትግባ ብላ ይኸው ለወራት በቆየው ሾውዋ እያደረቀችን ትገኛለች።

 

4- ግብረገብነትን አታውቀውም። አቶ ክብሮም ከዱርዬ በላይ በህዝባችንና በዚህች አገር ታሪክ ላይ የወንበዴ ስራ ሲስሰሩ የነበሩትን ኦሮማራ እንዴት ዱርዬ ትላለህ ህጻናት ይሰሙናል፣ ብላ ስትንጨረጨር የነበረችው ሴት በሰከንዶች ልዩነት "ግብረሰዶም፣ ወንድልጅ ተደፈረ፣ ብልት ወዘተ እያለች ጸያፍ ቃላትን ካለምንም መሸማቀቅ ስትተፋ ነበር። ስንት ህጻናት ይህንን አይተውና ሰምተው የጥላቻ ክትባት ተወግተው ይሆን? አንድን ህጻን ዱርዬ ከማለትና ግብረሰዶም ከማለት የቱ ያሸማቅቀዋል? የትኛውስ ስነልቦናን ይጎዳል? ትውልዳችንን ወዴት እየወሰዱብን ነው?

 

አንድ ወዳጄ እንደነገረኝ መንግስት ያሰራጨውን የዶክመንተሪ ፊልም ከተመለከቱ በኋላ ጠርሙስ ይዘው በዚያ ሲሳለቁ እንደነበር ነው። ይህ ያማል። ምን እየሆንን ነው? ተደፈሩ ተደፈርን እያሉ ማላዘን የሀኪም ማስረጃ አቅርቦ እውነቱን ከማሳየት እንዴት ቀደመ? ተኮላሽተናል ያሉት እነ ሀብታሙ አያሌው ዛሬ ወንድ ልጅ ዱብ አድርገዋል። ይህንንም ዱካውን ብንከተል ብዙ ነገር የምናገኝ ይመስለኛል።

 

ታላቁ መጽሀፍ ሲናገር እንዲህ ይላል "አንደበት የትውልድን ሩጫ ያቃጥላል" ይልና በሌላ ስፍራ ደግሞ " ከልብ የተረፈውን አንደበት ይናገራል" ይላል። በአጭሩ እንዲህ ነው በልብ የነበረውና በአንደበት የተነገረው የትውልድን እሳት ያቃጥላል። እንደማለት ነው። ጠማሞች፣ አምባገነኖች፣ ህዝብ ፈጆች አንደበትን ወይም ልሳንን ትውልድ ለመፍጀትና ትውልድን ለማስለቀስ ተጠቅመውበታል። አገር ያቀኑ ድንቅ መሪዎች፣ ፓርቲዎችና አብዮተኞችም አንደበታቸውን ወይም ልሳንን ትውልድን ለማቅናትና ለማቆም ተጠቅመውበታል። እዚህ እኛ ጋር እንኳን ኢህአዴግ አገር ሲገነባና ትውልድ ሲያቀና አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚባል ልሳን ነበረው። ደካማው የሀይለማርያም አስተዳደር ልሳኑ መዘጋት ሲጀመር የሀገሪቱም የኢህአዴግም ጠላቶች ልሳናቸው ይበረታ ጀመር። ኢሳት፣ ሰንደቅ፣ ፍትህ፣ ኦኤምኤን፣ ድምጻችን ይሰማ ወዘተ በፍለጠው ቁረጠው፣ በልብወለድ ፍረጃ ባለስልጣንን እና ብሄሮችን እየነጣጠሉ ማጠልሸትና ማሳደድ አሁን ላለንበት መያዣ መጨበጫ ለሌለው ውድቀታችን መሰረት ነበር።

         ጀግንነትን ከናዚ መማር

         5 ሚሊዮንን በ100 ሚሊዮን ማጥፋት

         ወባን ለማጥፋት ኩሬውን ማድረቅ

         በማስራብና በማስጠማት ማንበርከክ

         መጨበጥ

         የመለስን ሬሳ ሜዳ ላይ መወርወር

         ልክ እናስገባለን አሉ

የተለያዩ ስያሜዎች።

 

በትውልድ ሩጫ ላይ የተለቀቁ ከሆድ ሞልተው የፈሰሱ የአርማጌዶን ማቀጣጠያ ትርኩስ፣ የማንደጃ ማገዶዎች ነበሩ። የሽንቁራችን ክፋቱ፣ የጨለማችን ጽልመቱ በአንድም ይሁን በሌላ ሊያሻግረን ተስፋ የሰጠንና አምነን ይሁንታችንን የሰጠነው መንግስት በነዚህ የአርማጌዶን መጫሪያዎች ተተብትቦ መያዙ ነው። ከሲሳይ እስከ መሳይ፣ ከእስክንድር እስከ ጃዋር፣ ከደበበ እስከ አሳምነው፣ ከብርሀኑ እስከ ያሲን፣ ከቤቲ እስከ ርእዮት፣ ከሀብታሙ እስከ ነአምን የለውጡ ዘዋሪ ሆነው፣ አርበኛ ሸላይ ተደርገው ሀሳባቸው ሰርቶ፣ ተጽእኗቸው እውን ሆኖ የመሪዎች እልፍኝ አስከልካይ የመደመሩ አለሁ ባይ መሆናቸውን ያየ አርማጌዶን በደጃችን መሆኑን ለአፍታ ታክል አይጠረጥርም።

ቦ ለኩሉ አሉ መምሬ ዲበ ኩሉ።

ጊዜ እድል ከሰጠን ብዙ እናያለን።

 

ይቀጥላል

 

 

 

 


Back to Front Page